Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all 15006 articles
Browse latest View live

Breaking News: ቴዲ አፍሮ ታሰሮ በ30ሺ ብር ተፈታ

$
0
0

teddy afrio
አሁን በደረሰን መረጃ የ30000 ሺ ብር ዋስ ድምፃዊው በማቅረቡ ከእስር ተለቁዋል::

ድምፃዊ ቴዲ አፍሮ በፌደራል ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በቀረበበት ክስ ምክንያት ዛሬ ታስሮ ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡ ድምፃዊው የቀረበበት ክስ ከስምንት ዓመት በፊት ከቀረጥ ነፃ ወደ ሃገር ውስጥ የገባችን ቢኤምደብሊው መኪና ገዝቶ ተገቢውን የቀረጥ ክፍያ ሳያጠናቅቅ ወደ ስሙ አዛውሯል የሚል መሆኑን የኢትዮጲካሊንክ ምንጮች ጠቁመዋል፡፡
ድምፃዊው በዚሁ ክስ መሰረት ዛሬ ረፋድ በአራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ ክሱ ከታየ በኋላ ቀርቦ የዕለቱ ዳኛ 30 ሺህ ብር በማስያዝ በዋስ እንዲፈታ ትዕዛዝ ሰጥተዋል፡፡


ጥላሁን ገሠሠን ስንት ጊዜ እንቅበረው?

$
0
0

ይህ የቁም ነገር መፅሔት 13ኛ ዓመት ቅፅ 13 ቁጥር 188 የሽፋን ርዕሰ ነው፡፡

በታምራት ኋይሉ/
መነሻ

ድፍን የሀገራችን ህዝቦች አዲሱን የኢትዮጵያ ሚሊኒየም ሁለት ሺህን ለመቀበልና በድምቀት ለማክበር ሽር ጉድ በሚሉበት ዋዜማ ታላቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉስ የሆነው ክቡር ዶክተር ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠ ባዶ ቤት ብቻውን ሆኖ ነበር አዲሱን ሚሊኒየም የተቀበለው፡፡ በአዲስ አበባ ሚሊኒየም አዳራሽ የጎረቤት ሀገራት መሪዎችና ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣት በታደሙበት ዝግጅት ላይ የሀገር ውስጥና የውጪ ሀገር ታዋቂ አቀንቃኞች ተጋብዘው መድረክ ላይ ሲወጡ ታላቁን ድምፃዊ ጥላሁን ገሠሠን ያስታወሰው ሰው አልነበረም፡ ፡ አንጋፋው ሱዳናዊ ድምፃዊ መሀመድ ወርዲ ራሱን ችሎ መቆም በማይችልበት ህመም ላይ ቢሆንም ኢትዮጵያ ሚሊኒየሟን ስትቀበል ‹እንኳን አደረሰሽ!› እንዲላት በመንግስትና ያንን መድረክ ባዘጋጁ ወገኖች ተጋብዞ መድረክ ላይ ወጥቶ ነበር፡፡
tilahun
ልክ በአስራ ሰባተኛው ቀን የሚከረበውን የጥላሁን ገሠሠን 68ኛ ዓመት የልደት በዓል በመኖሪያ ቤቱ በመገኘት ለማክበር ቁም ነገር መፅሔት ስትደርስ አንጋፋውና ተወዳጁ ድምፃዊ ሳሎን ቤት ብቻውን ዊልቸር ላይ ተቀምጦ፤ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንን እየተመለከተ ሲተክዝ ነበር የደረስነው፡፡ ከሃምሳ ዓመታት በላይ ያገለገላት ሀገሩ በዚህ ባዕዳን ሳይቀሩ በተጋበዙበት መድረክ ላይ ባለመጋበዙ ስሜቱ መጎዳቱ በግልፅ በስታውቅ ነበር፡፡ አስፈላጊውን ሁሉ በማድረግ የተለያዩ አርቲስቶችን በመጥራት በመኖሪያ ቤቱ የዳመራ ችቦ በማብራት ካከበርነው የልደት በዓሉ ማግስት ለቃለ መጠይቅ ስንቀመጥ ‹እንዴት እናንተ ወጣቶቹ አስታወሳችሁኝ› ነበር ያለው እንባ ባቀረሩ ዓይኖቹ፡፡ ይህ የልደት በዓሉ በሀገር ውስጥ ሳለ የተከበረ የመጨረሻው ልደቱ ነበር፡ ፡በዛው ዓመት ለህክምና ወደ አሜሪካ ያቀናው ጥላሁን 69ኛ ዓመት ልደቱን በ2001 ዓ.ም እዛው አሜሪካ ጥቂት ወዳጆቹ ባሉበት አክብሮ በዛው ዓመት የፋሲካ ዕለት ወደ ሀገሩ የገባ ዕለት ህይወቱ ማለፉ ይታወሳል፡፡

ከጥላሁን በኋላ

የጥላሁን ገሠሠ ዜና እረፍት እንደተሰማ ህዝብና መንግስት አንድ ላይ ሆነው ሀዘን መቀመጣቸውና የቀብር ሥነ በደመቀ መልኩ ማድረጋቸው ይታወቃል፡፡ ይህም መንግስት ለአንድ ግለሰብ /በእርግጥ ጥላሁን ከአንድ ግለሰብ በላይ ነው/ አድርጎት በማያውቀው ሁኔታ ህዝባዊ ሽኝት ማድረጉ ለሀገራችን ሙያተኞች አዲስ ምዕራፍ የከፈተ መሆኑን ጠቅሰን ፅፈናል፡፡ ይህንኑ ተከትሎም ከጥላሁን ዜና እረፍት በኋላ የተለያዩ ነገሮች መደረግ እንዳለባቸውና ለመጪው ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል ሥራ መሰራት እንዳለበት በልዩ ልዩ መድረኮች ላይ ተነገረ፤ በመገናኛ ብዙሃንም ላይ ተስተጋባ፡፡ ዘፈኖቹ በሙሉ በአንድ ሲዲ ተሰብስበው ይታተማሉ ተባለ፤ የህይወት ታሪኩን የሚያሳይ ቪዲዮም ይወጣል ተባለ፤ የተጀመረው የህይወት ታሪኩ መፅሀፍ ይታተማል ተባለ፤ በስሙ አደባባይ ይሰየማል ተባለ፤ በህይወት እያለ የመሰረተው የስኳር ህሙማን ማህበር ህንፃ ግንባታ ይጀመራል ተባለ፤የልደት በዓሉም በየዓመቱ በደመቀ ሁኔታ ይከበራል ተባለ ፤ወዘተ ወዘተ ወዘተ…

ይህ በተባለ በዓመቱ የጥላሁን ገሠሠ 1ኛ የሙት ዓመት ሲታሰብ በህይወት እያለ የተጀመረውና በኢትዮጵያ ደራስያን ማህበር የተዘጋጀው መፅሐፍ ከነጉድለቱም ቢሆን ተመረቀ፡፡ አራተኛ ክፍለ ጦር አካባቢ ያለውና እየተገነባ ያለውን መንገድ መንግስት የጥላሁን ገሠሠ አደባባይ እንዲሆን መፍቀዱ ይፋ ሆነ፡፡ በቃ፡፡ ከዚህ ውጪ ትርጉም ያለው ነገር አልተሰራም፡፡ ከዚሁ የ1ኛ ሙት ዓመት ዝክር ጋር በተያያዘ በሚሊኒየም አዳራሽ በተዘጋጀው የሙዚቃ ፕሮግራም ላይ እንዲገኙ ከተጋበዙት የሙያ አጋሮቹ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት አርቲስቶች ሳይገኙ መቅረታቸው የወቅቱ አነጋጋሪ ጉዳይ ነበር፡፡ይህን ጉዳይ በተመለከተ በወቅቱ የታዲያስ አዲስ ፕሮግራም አዘጋጅ የነበረው ተወልደ በየነ/ተቦርነ/ በሸገር ሬዲዮ ላይ በጥላሁን ገሠሠ የሙያ ጓደኞች ዙሪያ ያዘጋጀው አስቂኝ የሙዚቃ ግብዣ በገዛ ዘፈናቸው የተተቹበት ነበር፡፡ ከአንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ጀምሮ እስከ ወጣቷ ድምፃዊት ዘሪቱ ከበደ ድረስ ‹በጥላሁን ገሠሠ የሙት ዓመት መታሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ ለምን አልተገኛችሁም?› ሲባሉ ሁሉም በየዘፈኖቻቸው ‹የእናቴ መቀነት አደናቀፈኝ› ነበር መልሳቸው፡፡ የጥቂቶቹ እነሆ!
አርቲስት ማህሙድ አህመድ ለጥያቄው ‹መቼ ነው ዛሬ ነው፤ ነገ ነው…› የሚለውን ዘፈን ሲያንጎራጉር፤
ኩኩ ሰብስቤ በበኩሏ ‹ከሰው የተለየ እኔ ምን አውቃለሁ፤ እኔ ምን አውቃለሁ›
ዘሪቱ ከበደ በዘፈኗ ‹አላውቀውም ምን እንደምል እኔ› ብላለች፡፡

ከዓመት በኋላ
Bizunesh and Tilahun Gessese
የጥላሁን ገሠሠ የሙት ዓመት በታሰበው ደረጃ እንዳልታሰበና ዜና እረፍቱ በተሰማበት ወቅት እንዳለው አይነት የትብብር መንፈስ መጥፋቱን የተረዱት የጥላሁን ገሠሠ ቤተሰቦችና ጥቂት አድናቂዎቹ በ2003 ዓ.ም የጥላሁን ሁለተኛ የሙት ዓመት ሲመጣ የአቋም ለውጥ ማድረጋቸውን አስታወቁ፡፡ ይህም ‹የጥላሁን ገሠሠን ሙት ዓመት ከመዘከር ይልቅ የተወለደበትን ብናከብር ይሻላል› ወደሚል ተቀይሮ ሙት ዓመቱ በዝምታ ታለፈ፡፡ ይህንኑ ተከትሎም ሚያዝያ 2 ቀን 2003 ዓ.ም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በተጠራ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ሁኔታው ተነገረ፡፡ ‹የጥላሁን ገሠሠ ህያው የኪነ ጥበብ አደራጅ ኮሚቴ› የተሰኘ ‹ኮሚቴም› መቋቋሙን የሚገልፅ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጠ፡፡ የልደት በዓሉንም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር በየዓመቱ በጀት መድቦ በድምቀት ለማክበር መወሰኑም ይፋ ሆነ፡፡ ውሳኔው በቀድሞው የቴአትር ቤቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አዳፍሬ ተሻገር አማካይነት የተወሰነ መሆኑን መነሻ በማድረግ ‹ይህ ውሳኔ ምን ያህል ተፈፃሚነት ይኖረዋል?› በሚል በወቅቱ በተጠባባቂ ሥራ አስኪያጅነት ለተመደቡትና በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ ለነበሩት አቶ ደስታ ተስፋ ቁም ነገር መፅሄት ጥያቄ አቅርባ ነበር፡፡ ‹ለጥላሁን ብለን የምናዘጋጀው ልዩ ዝግጅት በየዓመቱ አይኖርም፤ የመስቀል በዓል የተለመደ የሙዚቃ ዝግጅት ስላለን ከዛው ጋር አንድ ላይ አድርገን እናከብረዋለን› ነበር ያሉት፡፡ በዚህ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአዲስ መልክ ብቅ ያለው አዲሱ ‹የጥላሁን ገሠሠ ህያው የኪነ ጥበብ አደራጅ ኮሚቴ› እሰራቸዋለሁ ብሎ የዘረዘራቸው ሥራዎች እቅድ የግብር ይውጣ ይመስሉ ነበር፡፡ ጥላሁን በህይወት እያለ ሊያስፈፅማቸው ያልቻላቸውን ነገሮች በሙሉ ሰብስቦ ‹እሰራቸዋለሁ› ብሎ ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠቱ ብዙ ትችት ያስከተለበት ሲሆን እንደተባለውም ከአደረጃጀቱ ጀምሮ በነበረበት የህጋዊነት ጥያቄ እስከ ዛሬ ድረስ ከእቅዱ አንዱንም ማሳካት ያልቻለ ኮሚቴ ሆኖ ቀርቷል፡፡

የብሔራዊ ቴአትር ቃል ኪዳን

የጥላሁን ገሠሠን የልደት በዓል በየዓመቱ በጀት መድቤ አከብረዋለሁ ብሎ ቃል የሰጠው ብሔራዊ ቴአትር ይህንን ባለ ማግስት መስከረም 17 ቀን 2004 ዓ.ም የጥላሁን ገሠሠን 71ኛ ዓመት ልደት ለማክበር ሳይችል ቀርቷል፡፡ ያም ሆኖ በዛው ዓመት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ሲተላለፍ የከረመው የኢትዮጵያ አይዶል የሙዚቃ ውድድር ማጠናቀቂያ ፕሮግራም ስለነበር ከቴአትር ቤቱ በቀጥታ ስርጭት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተላልፏል፡፡በዕለቱ የጥላሁን ገሠሠ መታሰቢያ ተብሎ ተሰይሞ የጥላሁን ፎቶ ተሰቅሎ ውድድሩ ከመካሄዱና ሴት ልጁ የሱን ዘፈን ከማቀንቀኗ በቀር ይህ ነው የሚያሰኝ ጥላሁንን የሚያስታውስና የሚዘክር ዝግጅት አልተደረገም፡፡ በዓመቱ በ2005 ዓ.ም 72ኛ ዓመቱ እና በ2006 ዓ.ም 73ኛ ዓመት የልደት በዓሉም እንደነገሩ ከመከበሩ ውጪ ያንን የኢትዮጵያ ሙዚቃ ንጉስ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ለማክበር አልተቻለም፡፡ ቴአትር ቤቱም የጥላሁንን ልደት በጀት መድቤ አከብርለታልሁ ማለቱን ረስቶ በዕለቱ ቴአትር ቤቱ የሙዚቃ ዝግጅቱን ገንዘብ ከፍለው ለሚገቡ ሰዎች የሚያቀርብ በመሆኑ ቢያንስ የ500 ሰዎችን ወንበር ክፍያ እንዲፈፅሙ በአዲሱ የቴአትር ቤቱ ሥራ አስኪያጅ በኩል ተነግሮአቸው ቤተሰቦቹ በደረሰኝ ለቴአትር ቤቱ ገቢ አድርገው ዝግጅቱ መካሄዱ ይታወሳል፡፡ ቤተሰቦቹ የከፈሉባቸው 500 ትኬቶች ለጥላሁን ገሠሠ ጓደኞች፤ወዳጆችና አድናቂዎች በነፃ ቢበተንም በቴአትር ቤቱ ተገኝቶ ዝግጅቶቹን የታደሙት ሰዎች ቁጥር እዚህ ግባ የሚባል አልነበረም፡፡

የዘንድሮው መስቀል
ብሔራዊ ቴአትር በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ ሶስት የአመራር ለውጥ ያደረገ ቴአትር ቤት ነው፡፡ በዚህ ዓመት ጥላሁን ገሠሠ በህይወት ቢኖር ኖሮ 74ኛ ዓመት የልደት በዓሉን ነበር የሚያከብረው፡፡ነገር ግን የዘንድሮ ልደቱም በተባለው መሠረት በቴአትር ቤቱ አልተከበረም፡፡ እንደውም በአንድ ሳምንት አራዝሞ ለማክበር ማሰቡን ተናግሯል፡፡ በየዓመቱ በመስቀል ዕለት የሚካሄደው የሙዚቃ ዝግጅት ታጥፎ ‹ቶፓዝ› የተሰኘው ቴአትር ነው ለተመልካች የቀረበው፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደምክንያት የተሰጠው ከቀናት በፊት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየውን የረዳት ፕሮፌሰር ሀይማኖት ዓለሙን ሀዘን ለማሰብ ነው፡፡ አንጋፋው አርቲስት ሀይማኖት ዓለሙ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ባልደረባ እንደነበረና ልዩ ልዩ ቴአትሮች ላይ መስራቱ እንዲሁም ማዘጋጀቱ ይታወቃል፡፡ ይህንኑ መነሻ በማድረግም ህይወቱ ካለፈበት መስከረም 9 ቀን 2007 ዓ.ም በኋላ የቀብር ሥነ ሥርኣቱ በሚከናወንበት ዕለት በቴአትር ቤቱ ልዩ የሽኝት ፕሮግራም ተዘጋጅቶ እንደነበር ይታወሳል፡፡ ይህ ሁሉ ከተደረገ ከሳምንት በኋላ‹ የጥላሁን ገሠሠን ልደት ያላከበርነው በሀይማኖት ዓለሙ ሀዘን ነው ›ማለቱ አያስኬድም፡፡

በኢትዮጵያ ቴአትር ቤቶች ውስጥ በሀዘን ሳቢያ ቴአትሮች ወይም የሙዚቃ ዝግጅቶች የተቋረጡበት ጊዜ እንደሌለ ቴአትር ቤቱ ይዘነጋዋል ለማለት አይቻልም፡፡ የታሪክ ድርሳናት እንደውም የሚያወሱት የገዛ ልጆቻቸው ሞት የተነገራቸው አርቲስቶች የመድረክ ስራቸውን ጨርሰው ወደ ለቅሶአቸው እንደሄዱ ነው /የአርቲስት ሙናዬ መንበሩን ታሪክ ልብ ይሏል/ቴአትር ቤቱ ይህንን እያወቀ ወይም ሊያስታውስ እየተገባ የዚህን ታላቅ አርቲስት የልደት ቀን በቸልታ ማለፉና ማራዘሙ ያስተዛዝባል፡፡ በእርግጥም ቴአትር ቤቱ የጥላሁንን ልደት ለማክበር ከልቡ የወሰነ ከሆነ ከዚህ በተሻለና ጥላሁንን በሚመጥን መልኩ ዝግጁቱን ሊያዘጋጅለትና ክብሩን ሊጠብቅለት ይገባል፡፡ ፕሮግራሙ ተካሂዷል ለማለት ብቻ ከመደበኛው ፕሮግራም ጋር ቀላቅሎ ዝግጅቱን ማካሄድ የአፈፃፀም እቅድን ለማሟላትና ለሪፖርት ይጠቅም እንደሆነ ነው እንጂ ኢትዮጵያ ለሙዚቃ ንጉሷ የሚመጥን ዝግጅት ሲካሄድ እስከ ዛሬ ድረስ አልተመለከትንም፡፡

የቴአትር ቤቱ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ተስፋዬ ሽመልስ ግን በዚህ ሀሳብ አይስማሙም፡፡ እሳቸው እንደሚሉት ከዚህ በፊት የነበረው የጥላሁን ገሠሠ የልደት አከባበር ወጣ ገባ እንደነበረውና አልፎ አልፎም ቤተሰቦቹ መጠነኛ ክፍያ ይጠየቁ እንደነበር ገልፀው ‹ከዚህ ዓመት ጀምሮ ግን በተደራጀና በተጠናከረ መልኩ የልደት በዓሉን ቴአትር ቤቱ ሙሉ ወጪውን ሸፍኖ በቴአትር ቤቱ ሙዚቀኞችና ከተጋባዥ አርቲስቶች ጋር የሚያከብርበት ሁኔታ ተመቻቷል › ሲሉ ገልፀዋል፡፡ አቶ ተስፋዬ እንደሚሉት ዝግጅቱ ለአንድ ሳምንት የተራዘመው የአርቲስት ሀይማኖት ዓለሙ የሀዘን መዝገብ ባለመዘጋቱ እንደሆነና ሀዘኑን ለመግለፅ የሚመጣ ሰውን አስቀምጠን የጥላሁንን ልደት ለማክበር ሙዚቃ ከፍቶ መጨፈር ከባህላችን ጋር ስለማይሄድ ነው ብለዋል፡፡ የጥላሁን ገሠሠ የልደት ዝግጅት ከሀይማኖት ዓለሙ የሀዘን መታሰቢያ ዝግጅት ጋርም ምንም ግንኙነት እንደሌለው አረጋግጠዋል፡፡

የዘንድሮስ ልደቱ ?

ጥላሁን ገሠሠ በሥራው ሚሊዮን አድናቂዎችን አፍርቷል፡፡ ከነዚህ ሚሊዮን አድናቂዎች መሀከል ግን የሐረሩን ንጉሴ ታደሰን ያህል አድናቂ አለው ለማለት ያስቸግራል፡፡ መላ ህይወቱን የጥላሁን ገሠሠን ሥራዎችና ፎቶግራፎች ሲሰበስብ የኖረው የሐረሩ መምህር ንጉሴ ታደሰ ጥላሁን በሕይወት እያለም ሆነ ካለፈ በኋላ ለጥላሁን ያለው ፍቅርና አድናቆት ያልተቀየረ ሰው ነው፡፡ /ምናልባት የኪነ ጥብብ ሰዎችን እንወዳለን፤ እናደንቃለን ለምንል አፍአዊ ላልሆንን ሰዎች ንጉሴ ለዚህ ጥሩ መምህር ነው/ንጉሴ ሁሌም እንደሚያደርገው በየዓመቱ ዳመራ በዓልን የሚያከብረው ወደ አዲስ አበባ መጥቶ ነው፡፡ አንድም በዓሉን ለማክበር አንድም የሙዚቃ ንጉሱን ልደት ለማክበር፡፡ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ መስከረም 17 ቀን 2006 ዓ.ም ጠዋት ንጉሴ እንደተለመደው የጥላሁን ገሠሠ መቃብር ያለበት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ተገኝቷል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ያው ግልፅ ነው፡፡ ያ የሚሊዮኖችን የሙዚቃ አፍቃሪያንን ልብ ያሸፈተውና በሚሊዮን የሚቆጠሩ አድናቂዎች ያሉት ጥላሁን ገሠሠ በልደት ቀኑ መቃብሩ ላይ የተገኘው ንጉሴ ብቻ ነበር፡፡ ‹ሁሌም እንደማደርገው መቃብሩ ላይ ሻማ አብርቼ አበባ አስቀምጩ ተመለስኩ› ይላል የንጉሱ ታሪክ ገና በሞተ በአምስት ዓመቱ እንዲህ ችላ መባሉ እያስቆጨው፡፡ ‹ወደ ብሔራዊ ቴአትር ሄጄ የልደት በዓሉ ስለመከበሩ ስጠይቅ፤ ባለቤቱም በሀገር ውስጥ የለችም፡፡ ዝግጅቱም ለአንድ ሳምንት ተራዝሟል አሉኝ› ይላል ለጥላሁን ልደት የሥራ ፈቃድ ጠይቆ መምጣቱንና ቀኑ ማለቁን በሀዘን በማሰብ፡፡›
አበበ ቢቂላ በሮም ከተማ
ጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ የመጀመሪያውን የአፍሪካና የኢትዮጵያ የማራቶን የወርቅ ሜዳሊያ በባዶ እግሩ ያስመዘገበው በጣሊያን ሮም ከተማ ነው፡፡ ጣሊያናውያን ለዚህ ብርቱ ጀግና አትሌት ያላቸው ፍቅር ተነግሮ የሚያልቅ አይደለም፡፡ ማንም ሰው ይፈፅመዋል ብቻ ሳይሆን ሊፈፅመው ለማሰብ ይከብደዋል የሚባለውን የ42 ኪሎ ሜትር ከ195 ሜትር ማራቶን በባዶ እግሩ ሮጦ መጨረስ ለእነዚያ ጣሊያናውያን የሚታመን አይደለም፡፡ አበበ ግን አድርጎታል፡፡ ታዲያ ይህንን በተከታታይ ትውልዶች እንኳ ሊፈፀም ያልቻለና ያልተፈፀመ ጀብዱ ለፈፀመው ጀግና አትሌት በከተማቸው መንገድ ፤አደባባይ ፤ድልድይ ሰይመውለታል፡፡ አሁን በቅርቡ እንኳ አበበ ያንን ጀብዱ ከፈፀመ ከ50 ዓመት በኋላ ድልድይ በስሙ ሰይመው ስሙንና ሥራውን ለጣሊያን ወጣቶች አርአያ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የስፖርት አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሰዒድ ኪያር በቅርቡ ወደ ጣሊያን ሮም ከተማ በተጓዘበት ወቅት ይህንኑ የድልድይ ምረቃ ሥነ ሥርዓት ለህዝብ አሳይቷል፡፡

በየተሰማሩበት የሙያ መስክ ከምንም ተነስተው በሀገር ፍቅር ወኔ ብቻ ለሀገራቸውና ለህዝባቸው ታሪክ ያኖሩ ጀግኖቻችንን የውጪ ሰዎች በዚህ ደረጃ ሲያከብሯቸውና ስማቸውን ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላለፍ ሲያደርጉ እኛ ግን የሲቪል ጀግኖቻችንን ታሪክና ሥራ እንረሳለን፡፡ ካለፉ በኋላም በስራቸው አዲሱን ትውልድ ከማነቃቃትና አርአያነታቸውን እንዲከተል ከማዕደረግ ይልቅ ድጋሚ እንቀብራቸዋለን፡፡ በጥላሁን ገሠሠ ስም ይሰራሉ ከተባሉና ሊሰሩ ከሚገባቸው ነገሮች መሀከል አብዛኛዎቹ አልተሰሩም፡፡ጥላሁንን በቅርብ የሚያውቀውና በመድረክ ላይ ሲጫወትም የተደሰተበት የአሁኑ ትውልድ ለጥላሁን አንዳች ነገር ማድረግ ካልቻለና ካላቆመለት አዲሱና በስም ብቻ የሚያውቀው ትውልድ ምን እንዲያደርግ ይጠበቃል?

ጥላሁን ገሠሠን ስንት ጊዜ እንቅበረው?

ጥላሁን በህይወት በነበረበት ወቅት ያቋቋመውና ለእግሩ መቆረጥ ምክንያት የሆነውን የስኳር ህመም ለመከላከል በስሙ አቋቁሞት የነበረው ‹የጥላሁን ገሠሠ የስኳር ህሙማን መርጃ ማህበር› ከእርሱ ሞት በኋላ ከስሟል፡፡ አስቀድሞም በህይወት እያለ ለማህበሩ ማጠናከሪያ በሚል በሸራተን ሆቴል በጠራው ስብሰባ ላይ ጥቂት ሰዎች ብቻ ተገኝተው ስሜቱን ጎድተውታል፡፡
በመሷለኪያ አካባቢ መንግስት ሰይሞለት የነበረው አደባባይ ላይ ሶኒ ኩባንያ የራሱን አርማ ከፍ አድርጎ መስቀሉና ጥላሁን አንሶ መታየቱ ‹አደባባዩ የማነው?› የሚል ጥያቄ ፈጥሯል፡፡ አደባባዩ በአሁኑ ወቅት ድጋሚ በባቡር ሥራ ምክንያት በመፍረሱ የተነሳ ‹አደባባይ › የሚለውን ስያሜ የማግኘት ዕድሉ ጠቦ ይገኛል፡፡ በስሙ የታተመው የህይውት ታሪኩ መፅሐፍ የመጀመሪያ እትም አሁንም ድረስ በአዟሪዎች እጅ የመገኘቱ ሚስጥር ምን ይሆን? 10 ሺህ ኮፒ ገዝቶ የሚያነብ ትውልድ መጥፋቱ ምን ይባላል?
በስሙ የኪነ ጥበብ ማዕከል ለማቋቋምና ሥራዎቹንም ሰብስቦ ለማስቀመጥ የተያዘው እቅድ የውሃ ሽታ ሆኖ ከመቅረቱም በላይ ዘፈኖቹ በተለያዩ ሰዎች ድጋሚ እየተዘፈኑ/በሴቶችም ጭምር/ የመጀመሪያ ለዛና ወዛቸውን ሲያጡ የሚቆረቆርና ‹ተው› የሚል አካል ጠፍቷል፡፡ በእርግጥ በቤተሰቡ ዘንድ የዚህ አይነት አካሄዶችን ለመከላከልና ለማስቆም ጥረቱ ባይጠፋም ጥላሁን ከቤተሰብ ጉዳይ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ሀብት እንደሆነ የተዘነጋ ይመስላል፡፡ከጥላሁን ስራዎች ከሚገኘው ቤተሰባዊ ውርስ በላይ የኢትዮጵያ ህዝብ ቅርስነቱ ጎልቶ ሊታይ እንደሚገባ ለምን እንደተዘነጋ ግልፅ አይደለም፡፡

ጥላሁን የመጀመሪያ መድረክ ያገኘበትና ለተወሰነ ጊዜም ቢሆን የሰራበት አንጋፋው የሀገር ፍቅር ቴአትር ቤት በዜና እረፍቱ ማግስት የጥላሁን ገሠሠን ሐውልት በጊቢው ውስጥ ‹ከሌሎቹ አርቲስቶች ጎን አቆማለሁ› ብሎ የተናገረ ቢሆንም ቴአትር ቤቱ የሥራ አስኪያጅ ለውጥ ካደረገ በኋላ ስለ እቅዱ አንስቶ ለመነጋገር አልቻለም ወይም ረስቶታል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቴአትር ቤቱ ግቢ ውስጥ የተለያዩ አንጋፋ አርቲስቶች ሐውልቶች ወደ ቴአትር ቤቱ ትርኢቶችን ለመመልከት በሚመጡ ተመልካቾች የሚጎበኙ ሲሆን ጥላሁን ከእነርሱ መሀል የለም፡፡
ገጣሚው እንዲህ ይላል፡-
… እንግዲህ አንች ኢትዮጵያ እኛስ ልጆችሽ ምንድነን?
አመንኩሽ ማለት የማንችል ፍቅራችን የሚያስነውረን
ዕዳችን የሚያስፎክረን
ግፋችን የሚያስከብረን
ቅንነት የሚያሳፍረን፣ ቂማችን የሚያስደስተን
ኧረ ምንድነን? ምንድነን?…
(ፀጋዬ ገብረ መድህን / እሳት ወይ አበባ/)

ደኢህዴን በአጼ ምኒልክ ላይ የሰራው ዶክመንተሪ ኢህአዴግ ውስጥ ቅራኔ ፈጠረ * • በርካታ የብአዴን ካድሬዎች በሰንደቅ አላማ በዓል አልተገኙም

$
0
0

የደኢህዴን 22ኛ ዓመት ክብረ በዓልን ተከትሎ በፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ‹‹ጮራ ፈንጣቂው ጉዟችን›› በሚል የተሰራውና አጼ ምኒልክ የደቡብ ህዝቦች ላይ አሰቃቂ ጭፍጨፋ እንደፈጸሙ የሚሳየው ዶክመንተሪ በዴኢህዴንና በብአዴን መካከል አለመግባባት መፍጠሩን አንድ ከፍተኛ የብአዴን ካድሬ ነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡

Minilik
ዶክመንተሪውን ተከትሎ የብአዴን ፖለቲከኞች ኢህአዴግ በተለይም የዶክመንተሪው አዘጋጅ ደኢህዴን ላይ ተቃውሞ ያስነሱ ሲሆን ‹‹በአንድ በኩል ምኒልክ ይወደሳል፡፡ በአንድ በኩል ደግሞ ይወገዛል፡፡ ፒያሳ ላይ ያለው ሀውልት ምኒልክ መልካም ነገር እንደሰሩ ለማሳየት የተሰራ ነው፡፡ እንዲህ የምታወግዙት ከሆነ ለምን ፒያሳ የሚገኘውን ሀውልቱንስ አታነሱትም?›› በማለት በህዝብ መካከል ግጭት ይፈጥራል ያሉት መቀስቀሻ ዶክመንተሪ ላይ ተቃውሟቸውን ማንሳታቸውን የብአዴን ከፍተኛ ካድሬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

የብአዴን ካድሬዎች ዶክመንተሪውን ባዘጋጀው ደኢህዴንም ሆነ ኢህአዴግ ላይ ባላቸው ቅሬታ የዛሬው የሰንደቅ አላማ በዓል ላይ እንዳልተገኙ ተገልጾአል፡፡ በዶክመንተሪው ምክንያት በኢህአዴግ አንዳንድ ፖሊሲዎች ላይ ጥያቄ ያነሱ ሲሆን ለአብነት ያህልም እስካሁን አንስተውት የማያውቁትንና ሰንደቅ አላማው ላይ ያለው ኮከብ ላይ ጥያቄ ማንሳታቸውን የብአዴኑ ካድሬ ገልጾዋል፡፡

በቅርቡ አጼ ምኒልክን በመኮነን ከተላለፈው ዶክመንተሪ በተጨማሪ ተማሪዎች፣ ለሰራተኞችና ለሌሎች የህብረተሰብ ክፍል በተሰጠው ስልጠና ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ ታሪክ ነክ ወቀሳዎች የአብአዴን ካድሬዎች በደኢህዴንና ኢህአዴግ ላይ ላነሱት ተቃውሞ በተጨማሪ ምክንያትነት ተነስቷል፡፡

ለስድስት ጄነራል መኮንኖች ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ መሰጠቱ ተሰማ

$
0
0

ለስድስት ጄነራል መኮንኖች ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ መሰጠቱ ተሰማ:: መንግስት የሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎች እንደዘገቡት ሶስት ሜጀር ጀነራሎች ወደ ሌተናንት ጀነራልነት ማዕረግ ሲሸጋገሩ ሶስት ብርጋዴር ጀነራሎች ደግሞ ወደ ሜጀር ጀነራልነት ተሸጋግረዋል፡፡
news
የጀነራል መኮንኖች ማዕረጉ የተሰጠው በወታደራዊ ግዳጅ አፈፃፀም፣ በስነ-ስርዓት አክባሪነ፣ በአሰራር ችሎታና ብቃት ብልጫ መሆኑን በሹመት ስነ ስርዓቱ ላይ መገለጹን የዘገቡት የመንግስት ሚድያዎች ከሙላቱ ተሾመ ከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ መቀበላቸውን አትተዋል::

የሌተናንት ጀነራልነት ማዕረግ ያገኙት:-

1ኛ . ሜጄር ጀነራል አብርሃም ወልደ ማሪያም ገንዘቡ
2ኛ. ሜጀር ጀነራል አደም መሐመድ ሞሀመድ
3ኛ. ሜጀር ጀነራል ብርሀኑ ጁላ ገለልቻ ናቸው::

የሜጀር ጄነራል ማዕረግ ያገኙት ደግሞ

1ኛ. ብርጋዴር ጄነራል ዘወዱ እሸቴ ወልዴ
2ኛ. ብርጋዴል ጄነራል ተክለብርሃን ወልደ አረጋይ ገብረስላሴ
3ኛ. ብርጋዴል ጄነራል ክንፈ ዳኘው ገብረስላሴ ናቸው::

ብፁዕ አባታችን ሊበርድዎ ነው መሰል –ከመኳንንት ታዬ(ደ እና ፀ)

$
0
0

ከመኳንንት ታዬ(ደ እና ፀ)

የአንድ ሃገር እድገት የሚመጣው በብዙ ምክንያት ነው ።ለዚህም ብዙ ብዙ ነገሮች ይጠቀሳሉ።በተግባር ውለው ለሚተገብር የሚተላለፍትን እንኳን ትተን በአባባል ደረጃ የሚነገሩትን እንኳን የወሰድን እንደሆነ እነሱ እየታሰቡ ሃገሬው ለአንዳች ነገር መጠቀሙ በሃገራችን ለብልፅግና ሲውሉ ይታያል።ለአብነት ያህል”ቀልደኛ ገበሬ በሰኔ ይሞታል”የምትለውን የወሰድን እንደሆነ፤ ገበሬው ሰኔ ግም ሲል ጨርቄን ማቔን እንዳይል ያግደዋል። በዚህ ምክንያት ለቤቱ ብልፅግና እንዲሆን ተግቶ ይሰራል።ይሁንና ይህን ለመንደርደሪያ ያህል ስል ቤተክርስቲያንስ እንዴታ ለማለት ቃል እንዲሳብልኝ ከመፈለግ አንፃር ነውና ወደዛው ልጓዝ።እርግጥ ነው የዚህችን የሲኦል ደጆች እንኳን አይችሏትም ስለተባለላት እናት እና አንዲት ቤታችን ለመተየብ እኔ ጨዋ ስለሆንኩ ብዙ አይጠበቀብኝም።
abune matias
ግንሳ ሰው ያለውን ከወረወረ ንፉግ አይባልምና በልቤ የሚንቀዋለለውን አንዲት ሃሳብ ለመሰንዘር እንዲህ ልበል ስል ቀለም ከወረቀት ጋር አገናኘሁ።ሰሞኑን ብፁነታቸው(ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘ አትዮጲያ ማለቴ ነው) በመስከረም በዚሁ ባሳለፍነው ወር መስከረም 27-28 ከየ አድባራቱ የመጡትን ካህናትና አስተዳደሪዎች ሰብስበው ሲያወያዩ እንደ ከረሙ በየ ድህረ ገፆች ላይ ስናይ ሰነበትን ።አንዴም እሰየው አባታችን ወደታች ውረደው ማዳመጥ አወቁበት ስንል አንዴም እሳቸውም ሊበርዳቸው ነው መሰል ብርድል ብሳቸውን ያለቅጥ ሞቀ ሲሉ ተስተዋለ ብለን ሲከፋን ሰነበተ።እሲቲ ወደ ነበረው ልጓዝ ።የ ኢትዮጲያ አርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ በአይነቱ እጅግ አስከፊ የሚባሉ ፈተናዎችን አሳልፋለች።ይሁንና በገዛ ልጆቿ ስትፈተን የአለፉት 20 አመታት እንደምሳሌ ለማስተማሪያነት የሚነሳ እንደሚሆን እሙን ነው ።ግን ጠባቂዋ እግዚያሐብሔር ከጎኗ አለና ዘመናትን ሁሉ እንዲሁ ያሻግራታል። እርግጥ ነው ለክፉ ምክንያት የሆነው ባለቦታ አልፎ ሌላ ሲተካ የተሻለ መመኘት ይሆናልም ብሎ መጠርጠር ደግ ነውና። እርሶ ብፁዕ አባታችን አቡነ ማትያስ ሲመጡልን “የጥፋት ምንቸት ውጣ የስራ መንፈስ ግባ”ማለታችን ከስሜታችን በላይ ሆኖብን ከርሞአል።አሁንም ተስፋችን እንዳለ ነው።

እርግጠኝነታችን ደግሞ አሳድጎን እናት ቤ/ክ ስንል እና ልጆቸዎ ከያለንበት ሆነን ተማፅኖአችንን አሰምተናል።ይህም ውጤት አልባ ትረት እንዳልሆነ ይገባናል። ይሁንና አሁን ሰሞኑን ቅር ወዳሰኘን መልክት ልጓዝ።እርሶን የመሰለ አባት ወደታች ወርዶ ሲያዳምጥ ከመስማት ያለፈ ማለፊያ ደስታ ነገር አልነበረም ።የለምም። ነገር ግን ሲያዳምጡ እነማንን ሰብስበው ነው ያዳመጡት ? ስለ ምንስ ተወያያችሁ? በውኑ ሲኖዶሱ ያውቀዋልን ? ገንቢስ ሃሳብ ለቤተክርስቲያን የሚጠቅማት ነበርን? ለማለት ነበር ።ከሆነ ድግ ነው ።ነገር ግን አንድ ቀር ስላሰኘን እና ይህቺን መጣጥፍ እንድፅፍ ካነሳሳኝ ጉዳይ ልግባ።በመጀመሪያ እኔ የማህበረ ቅዱሳን አባል አደለሁም።ማህበሩን ግን ቀንም ለሊትም ከሚያገለግሉት ወገኖች አንዱ ነኝ።ይህን ስለራሴ ካልኩኝ በአንኳርነት ብፁዕነቶዎ ከተሰብሳቢዎቹ ጋር ካነሷቸው ነጥቦች አንዱ ማህበሩ ስለደረሰበት ደረጃ ነው።ይሁንና ከዚህ በፊት መቅደም ያለባቸውን፦

1. በገጠር ያሉ አባያተ ክርስቲያኖች መቀዳሻ ስለማጣታቸው
2.የቤ/ክ ይዞታ እየፈረሰ የሌሎች መደራጃ ስፍራ እንደሆነ
3.በ አክራሪ እስላሞች ወገኖቻችን ስለመታረዳቸውና ከዚህ በሓላ ጥቃት እንዳይደርስባቸው ምን መደረግ ስላለበት
4.ቤ/ክ ዘግተው ከተማ ስለሚመጡ ካህናትና መፍትሄው
5.የ አብነት ት/ቤቶች መዳከማቸውና ብሎም መዘጋታቸው ወደፊት ይህ እንዳይሆን ምን መደረግ እንዳለበት
6.በከተማ ባሉ እና በዘር በጎሳ ደራጅተው ቤ/ክ ስለሚዘርፏት ካህናትና አስተዳደሪዎች
7.በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ አካብተው የገጠር አብያተ ክርስቲያናት
ሀ.በደሳሳ ጎጆ ስለመቀመጣቸው
ለ. መቀደሻ ነዋየ ቅድሳት አጥተው በወር አንዴ ብቻ ስለመቀደሳቸውና ይህ ችግር እንዴት እንደሚወገድ።

ሐ . ጣራቸው አፍስሶ እግዚያብሔር የሚከብርበት ቤት ለመግለፅ በሚያሳዝን ሁኔታ ውስጥ ሲሆን እነኚ ሓብታም ቤተ ክርስቲያንት ካላቸው ላይ አውጥተው የውዴታ ግዴታ እንዴት ችግርዩን ቀርፈው ቤተ ክርስቲያኒቱ እና ካህናቱ ከችግር እንደሚወጡ እና የመሳሰሉትን
8. ከግዜ ርዝመት መጪው ትውልድም ሆነ አሁን ያለው ማህተቡን እንዳይ በጥስ ምን መደረግ እንዳለበት ፤ ብቻ ብዙ ነው እንዲህ ብለነው አያበቃም ።እንኳን ለ እኔ ለደካማው ለእናንተም ለአባቶች እንኳን ብዙ የሆነውን ችግር አወያይተዋቸው በሆነ፤ እኛም እሰየው ባልን።ቅዱስነቶዎ አሁንም እንደትላንቱ በብቸንነት መስራት ከጀመሩ መካሪዎችዎት ሁሉ የንጉስ ሰለሞን ልጅ የሮብዓም ይሆኑና እንደገና ሌላ ደረባ መናድ እንዳይሆን ስለቤተክርስቲያንና በአጠገበዎ ላሉት ቅዱሳን አባቶች እንደገና ጫንቃቸው ላይ ሌላ ሸክም እንዳይሆን በሚል ፍርሃት ውስጥ መሆናችንን ልናሳስቦዎ እንወዳለን።

በመቀጠልም ምን አልባት አንዳንድ ግለሰቦች በማሕበሩ ታቅፈው የሚያሳዩት የግል ባሕሪ አስቆጥዎት ከሆናና እነኛን የክርስቲያን አንደበት የሌላቸውን ሰዎች በተባ ምላሳቸው ያሰማሩአቸው ፤እነርሱ እንደው ነገም እርሶ ዘረፋቸውን፤ጎጠኝነታቸውን ፤ለማስጣል ከሞከሩ ከዚሁ ያልተናነሰ ወቀሳና ከሰሳ ሊያደርስቦዎ እንደሚችል አይዘንጉ።አልያም አፍ ላለው የቀን ጅብ አሳልፈው ሊሰጡአቸው ፈልገው ከሆነም ታሪክ ይቅር የማይለው ስራ ሊሰሩ እንደሆን እንዲታወቆዎ የኢትዮጲያ ክርስቲያንም “ያም መጣ ያም መጣ ለእኔ እናት እንደሆን የበጃት የለም ሁሉም አፈር ጫነባት”ብሎ እንዳይወቅሶዎ ፍርሃቴ ነው።በተረፈው ጥፋት ሊኖር ይችላል ቁጣም የሚሰሙ ልጆቾዎ ስለሆኑ ጠርተው ይሄን በምን እናድርገው ቢሉ የማይፈታ ነገር የለም ።”እርሶ እኮ የቅድስት ሃገር አትዮጲያ ክርስቲያን አባትና ፓትርያርክ ነዎት።ታዲያ እንዴታ አባታችን።
በስተመጨረሻው “ቅዱስ ዳዊት የሰው ልጅ እድሜው ቢበዛ 60 ቢበዛ ሰማኒያ ነው ከዛ ካለፈ ግን ትርፉ ድካም ነው ” እንዳለ ሁሉ እርሶስ በቀረ እድሜዎ ለቤተከርስቲያን የበለጠውን እንዲሰሩላት የዘመናት ባለቤት ሁሉን ቻይ እግዚያብሔር እድሜና ጤና ይስጥልን ዘንድ የህዝበ ክርስቲያኑ ፀሎት ነውና ፊትዎን ከቤተ መንግስት በፊት ወደ ቤተከርስቲያንና ህዝቦቾዎ እንዲያዞሩ የምንግዜም ፀሎቴ ነው።

ቸር እንሰንብት

ጥሪ በጀርመን ፍራንክፈርት ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን፡ የሃገር ፍቅር የሥነ-ጥበብ መድረክ ተዘጋጀ

$
0
0

በፍራንክፈርት አካባቢ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን በሙሉ፤ የሃገር ፍቅር የሥነ-ጥበብ መድረክ የሚከተለውን ጥሪ አስተላልፏል።
flag frankfurt

እስማኤል አሊስሮ 11 ወጣት ምሁሮችን ከስልጣናቸው ሊያነሱ ነው (ሾልኮ የወጣውን የተባራሪዎቹን ስም ይዘናል) –ጸጋዬ በርሄ 12 ሚሊዮን ብር እንደሚያገኙ ተጋለጠ

$
0
0

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው፡

የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ እስማኤል አሊስሮ በመጪው የ2007 ምርጫ የክልሉ ፕሬዝደንት ሆነው ለመቀጠልና በተጨማሪም የአብዴፓ ፓርቲ ሊቀመንበር ለመሆን በከፍተኛ ተስፋ ጥረት እያደረጉ መሆናቸው ታውቋል።

(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)

(አፋር ክልልን ፍልሥሥ ብሎ የሚመራው ኢስማኤል አሊስሮ ይህ ነው)


አቶ እስማኤል አሊስሮ ከምርጫው በፊት ይህን ተግባራዊ ለማድረግ ያሰቡ ሲሆን። ሃሣባቸውንም ለማሳካት በአሰራራቸው የማይስማሙ 11 ምሁር ወጣቶች ከመሀል ኮሚቴ አባልነትና ከየኃለፊነት ቦታዎቻቸው ለማንሳት ተዘጋጅቷል። እነዚህ ወጣቶች በብዛት የህወሓት መንግስት በክልሉ እጁን እንዳያስገባ የሚል አመለካከት ያላቸው ሲሆን አቶ እስማኤል አሊስሮ ደግሞ በዚህ አይስማሙም።

የፓርቲው ሊቀመንበር (የአብዴፓ) የክልሉ የትምሀርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጠሃ አህመድን ጨምሮ አስራ አንድ ወጣቶች ምናልባት ከምርጫው በፊት በተለያየ ምክንያት ከስልጣናቸው ይነሳሉ የሚል ግምት በስፋት እየተነሳ ነው።
1/ አቶ ጠሃ አህመድ
2/ አምባሳደር ሀሳን
3/ አቶ ሱልጣን አህመድ
4/ ወ/ሮ ዛህራ ሁማድ
5/ መ/ድ አሊ ጋርቦኢስ
6/ አቶ ኢሊያስ ሀሳን
7/ አቶ ኡስማን አይኒሳ
8/ አቶ ሀላቶ መሀመድ
9/ አቶ አሊ አብደላ
10/ አቶ ደረሳ አሊ
11/ አቶ ኢብራሂም ሁማድ… ሲሆኑ እነዚህ ወጣቶች ከማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት ሊነሱ መሆናቸው ከአቶ እስሚኤል ቢሮ የተገኘ የውስጥ መረጃ ይጠቁማል።

ከዛ በኋላም በቦታዎቻቸው ለአቶ እስማኤል እና ለህወሀት ተማኝ ሆነው ሊያገልግሉ የሚችሉ ናቸው ተብለው የታሰቡትን ለመተካት ታስቧል። ይሄ ሳይሳከላቸው ቢቀር አቶ እስማኤል አሊስሮ በፈቃዳቸው ስልጣን እለቃለሁ ብለው ህወሃትን መስፋራራት አንድ አማራጫቸው ነው ሲሉም ምንጮቹ ያስረዳሉ።

በተመሳሳይ ዜና በአፋር ወጣቶች ሊመሰረት የታሰበው «ከዳባ አፋር አክሲዮን ባንክ» እንዳይመሰረት ተደረገ። ከሁለት ሳምንታት በፊት በሰመራ ከተማ በአሊ ግደይ ሆቴል በተደረገው ሰብሰባ የቀድሞ የትግራይ ከልል መሪ የነበሩትና አሁን የፈደራል የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ፀጋዬ በርሄ ተገኝተው የነበረ ሲሆን የአፋር አክሲዮን ማህበር አላማው ከአፍዴራ ጨው የሚገኘው ገቢ ለአፋር ክልል እንዲገባና ወጣቶችም በማህበር ተደራጅተው ራሳቸውን ከመለወጥ ባሻገር የአፋር ኢንተርናሽናል ባንክ ለመመስረት ነበር። ግን አቶ ፀጋዬ በርሄ ጣልቃ በመግባት መሆን የለበትም ብለዋል። ምንም እንኳ ከወጣቶች ከፍተኛ ተቃውሞ የገጠማቸው ቢሆንም አሁን ያለው የወሎ አክሲዮን ማህበር የሚባለው ማህበር ያቋቋሙት አቶ እስማኤል አሊስሮ ሲሆኑ የማህበሩ ኃላፊ የሆነው አቶ ሲዒድ ያሲን ለአቶ እስማኢል አሊ ስሮ፣ ወ/ሮ ፈጡማ አብደላ (የእስማኤል ሚስትና) ለአቶ ፀጋዬ በርሄ በየአመት 12 ሚለዮን ብር ይሰጣቸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአፋር ክልል የፀጥታ አካሎች የፍርድ ቤት ዳኞችና የፍትህ ቢሮ ኃላፊዎች በአይሳዒታ ከተማ ስልጠና ላይ ይገኛሉ።

ባለፈው ረቡዕ 28/1/2007 ጀምሮ ለ10 ቀናት ለሚቀጥለው የዚህ ስልጠና አላማ በመጪው ምርጫ ከህዝብ ሊነሳባቸው የሚችለው አመፃን ማዕከል ያደረገ ነው። በአፋር ክልል የሚገኙ 32 ወረዳዎች የተሳተፉበት በዚህ ስልጠና የሚደረገው በአማርኛ ቋንቋ ሲሆን «ለምን በራሳችን (በአፋርኛ) ቋንቋ አታደርጉልንም» የሚሉም አሉ ነገር ግን የአፋር ክልል እሰካሁን በራሳቸው ቋንቋ ሊሰሩ ያልቻሉበት ዋናው ምክንያት በክልሉ ለሚገኙ የወያኔ ድህንነቶች እንዲመች መሆኑን ውስጥ አዋቂዎች ለምንጮቻችን ነግረዋል።

በሌላ ዜና ዛሬ እሁድ2/2 /2007 ጀምሮ ለ10 ቀናት የሚቆይ የጋዜጠኞች፣ የማስታዋቂያ ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም በየወረዳው የሚገኙ ሪፖርተሮች ክልል አቀፍ የሚዲያ ስራተኞች ስልጠና በዛው በአይሳኢታ ከተማ ተጀምሯል።

ከኢቢሲ፣ ከሬዲዮ ፋና እና ከድምፅ ወያነ የአፋርኛ ክፍል ሰራተኞች በስልጠናው የሚካፈሉ ሲሆን ከየጣቢያው ሶስት ጋዜጠኞች በዚህ ስልጠና እንዲካፈሉ ተደርገዋል። ስልጠናው በመጪው ምርጫ ቀስቀሳው በሚዲያ ጉልበት እንዲኖረው ለማድረግ ቢሆንም በአሁን ወቅት በአፋር ክልል እነዚህ የመንግስት ሚዲያዎች የሚከታተል በጣም አነስተኛ ነው።

በአፋር ክልል እስካሁን የሬዲዮ ጣቢያ የሌለ ሲሆን ከመቀሌ በየቀኑ ለ1ሰዓት የሚሰራጨው የአፋርኛ ፕሮግራም ሙሉ በሙሉ የሚቆጣጠረው ራሱ ህወሃት ነው። ሁለቱም ስልጠናዎች እየመሩ ያሉት ከመቀለ የመጡ ባለሥልጣናት እንደሆኑ ታውቋል።

Health: የቁንጭና 101፡ ‹‹የቁንጅናሽ ግዙፍ ኃይል ያለው በውስጥሽ ነው›› –‹‹The power be beautiful lies in you››

$
0
0

ከሊሊ ሞገስ

መዋብን ማን ይጠላል? ማንም! መዋብን እና ቁንጅናስ የሴቶች ብቻ ፍላጎት ያደረገው ማነው? ማንም! ወንዶችም እንደ ሴቶች አምሮና ተውቦ መታየትን ይሻሉ፡፡

ርዕሳችንን እንደግመዋለን፡፡

የቁንጅናሽ ግዙፍ ኃይል ያለው በውስጥሽ ነው፡፡ የውበት ስሜት፣ የቁንጅና ድባብ እንዲሰማው ለውስጥሽ ፍቀጂለት፡፡

‹‹የወጣት ሴቶች ሁሉ የጋራ ፍላጎት ቆንጆ ሆኖ መታየት ነው›› ሉናል ስታሲ አልድራጅ የ‹‹Real women-all you need to look and feel your best›› ዘገባ አቅራቢ፤ በሀሳባቸው እንስማማለን፡፡ በአፍላ የዕድሜ ዘመኗ በርካታ ሰዓታትን መስታወት ፊት የማታጠፋ ሴት የትኛዋ ናት? ቢሆንስ መዋብን መፈለግ ምን ስህተት አለበት? የሚታይ ውበት… በሌሎች ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድር ውበት… ተፈላጊ የሚያደርግ ውበት የበርካታ ሴቶች የጋራ ፍላጎት ነው፡፡

የሆነው ሆነና ውበት አካላዊ ማማር ብቻ ነው? ፈፅሞ! እንዲሁም የሴቶች የቁንጅና ግዙፍ ኃይል ያለው በውስጣቸው ነው፡፡ ይህን አውቀው የሚገነዘቡት ምን ያህሎች ናቸው? ውብ እና ታዋቂ ሴቶች ስለ ቁንጅና በተናገሩት አባባል ወደ ዝርዝር ማብራሪያችን እንግባ፡፡

 

(ኢትዮጵያዊቷ ቆንጆ ሃያት አህመድ)

(ኢትዮጵያዊቷ ቆንጆ ሃያት አህመድ)

ታዋቂ እና ውብ ሴቶች ስለ ቁንጅና ምን አሉ?

‹‹ቁንጅናን በአንፀባራቂ ብርሃን እመስለዋለሁ፡፡ እውነተኛ የሆነው ውበት ያላቸው ሰዎች አይኖቻቸው ብርሃንን ይፈነጥቃሉ፡፡ ቆዳቸውም አንፀባራቂ ነው›› (ካሜሮን ዲያዝ)

‹‹ቁንጅና የቆዳ ማማር ነው፡፡ አስፈላጊውና ዋናው ነገር ግን የሰውነት፣ የአዕምሮና የመንፈስ መመጣጠን ነው፡፡ የሆነ ሰው በአንድ ወቅት ያለኝን አባባል መቼም አልዘነጋውም፡፡ ‹‹ሃያ ዓመት እስኪሞላሽ ስትወለጂ ጀምሮ አብሮ የነበረው ውበት ይንጸባረቅብሻል (ይታይብሻል)፡፡ ከዚያ በኋላ ግን ተንከባክበሽ ያቆየሽው ውበት›› የምወደው አባባል ነው፡፡ ውበታችን በትክክልም ማንነታችንን ይመሰክራል›› (ጄኒፈር ሉፔዝ )

‹‹…የሰውነት፣ የአዕምሮና የመንፈስ መመጣጠን›› የሚለውን የጄኔፈር ሎፔዝ ገለፃ እንዴት ተመለከታችሁት? ትክክል! ውጫዊ ውበት ያለ ውስጣዊ ውበት ምን ሊረባ? ብስለትን፣ በራስ መተማመንን፣ ስለ ሌሎች በጎ ማሰብን፣ ስለ ራስ ጤናማ ስሜት መሰማትንና ተዛማጅ ነጥቦችን በቁንጅና መስፈርቶች መሀል ይመድቧቸዋል፡- የስነ ውበት ባለሞያዎች፡፡ ለነገሩ የቁንጅና ተወዳዳሪዎች ሁነኛ መስፈርት የአዕምሮ ብስለታቸው አይደል? ስለዚህ አባባላችን ያስኬዳል ማለት ነው፡፡ እንደዚህ ከሆነ ደግሞ እያንዳንዱ ነጥብ እያነሳን እናብራራ፡፡

ከዚያ በፊት ግን በዕድሜ የደረጁ የዕድሜ ባለፀጋ (ሲበዛ ቆንጆ እና መስህብ ያላቸው እንደሆኑ ብዙዎች መስክረውላቸዋል) ውብ የሆኑበትን ምስጢር እንዴት እንደገለፁት እንመልከት፡፡ እንዲህ ነበር ያሉት የዕድሜ ባለፀጋዎች፡፡

– ለአንደበቴ እውነትን

– ለድምፄ መልካም ቃልን

– ለጆሮዬ ቅን ንግግርን

– ለእጆቼ እርዳታ አድራጊነትን

– ለልቤ ፍቅርን

አስተማርኩ፡፡ እኔ ማራኪና ውብ ያልተባልኩ ማን ሊባል ኖሯል? ውስጥን ዘልቆ የሚገባ አገላለፅ፡፡ ከእድሜ ባለፀጋው ተሞክሮ የምንማረው ቁም ነገር እንዳለ እንገነዘባለን፡፡ ወደ ነጥባችን እንመለስ፡፡

የምታደርጉትን ነገር ሳይሆን ማንነታችሁን አፍቅሩ

Love your WHO, not your do

እውነታው ይኸውላችሁ፡፡ ሁሉን ነገር ሁል ጊዜ በትክክለኛው መንገድ ላላደርግ እችላለሁ፡፡ ራሳችንም ላናደርገው እንችላለን፡፡ ያ ግን በማንነታችን ላይ ተፅዕኖ መፍጠር የለበትም፡፡ ሰው ነንና ስህተት ልንፈፅም እንችላለን፡፡ ቁም ነገሩ ፈጥኖ ከስህተት መመለስ ነው፡፡ ለማንነታችን የምንሰጠው ግምት ከፍተኛ ከሆነ ከስህታችን ለመመለስ አንዘገይም፡፡ ስለ ራሳችን መልካም ስሜት እየሰማን ስንሄድ የባህርይ ለውጥን፣ ዕድገትንና መሻሻልን እናሳያለን፡፡ ይህ ከውስጣዊ ውበት ይመደባል፡፡

 

በእውነተኛ ጓደኝነት እመኑ

ሰዎች ‹‹ምን አይነት ውብ ልጅ መሰለቻችሁ? ባህሪዋም እንደ ቁንጅናዋ ነው›› የሚል በጎ አመለካከት ባንቺ ላይ እንዲያድርባቸው በእውነተኛ ጓደኝነት እመኚ፡፡ እዚህ ላይ የእውነተኛ ጓደኝነት መስፈርት ምንድን ነው? የሚል ጥያቄ ታነሺ ይሆናል፡፡ እኚውልሽ፡-

እውነተኛ ጓደኛ

– አንቺነትሽን በአንቺነትሽ የሚቀበልና በአንቺ የሚያምን ነው

– በችግርሽ ጊዜ ቀድሞ የሚደርስ ነው

– ስህተትሽን ይቅር ይላል

– ሁሌም ከአንቺ ጋር መሆንን ይፈልጋል

– እውነቱን ይነግርሻል

– ይገነዘብሻል፣ ይረዳሻል

– ውድቀትሽን አይመኝም

አንቺስ ከእነዚህ መስፈርቶች መሀል ምን ያህሉን ታሟያለሽ? ካላሟላሽ አሁኑኑ ለማሟላት አስፈላጊውን እርምጃ ውሰጂ፡፡ በዚህ የእውነተኛ ጓደኝነት ጎዳና ላይ ለመጓዝ ውስጥሽን አሳምነሽ የውስጣዊ ውበት ባለቤትነትሽን እንዳትጠራጠሪ፡፡

 

የመዋቢያ እቃዎች ምርጫሽ ላንቺ የሚስማሙ ይሁኑ

ሰው ላይ ያየሽው ጌጥና ልብስ ደስ ስላለሽ ብቻ አንቺም ማድረግ አለብሽ? የለብሽም! ምክንያቱም ለሌላው የተስማማው ለአንቺ ላይስማማ ይችላልና፡፡ ለእኔ የሚስማሙት መዋቢያዎች የትኞቹ ናቸው? ብለሽ ራስሽን ጠይቂ፡፡ በምርጫ በኩል እናትሽ ወይም ቀሪ ቤተሰብሽ አስተያየት ሊሰጡሽ ይችላሉ፡፡ ‹‹ሰዎች ራሳቸውን ትተው ሌሎችን መሆን ሲፈልጉ ትልቅ ስህተት ይፈፅማሉ፡፡ ራሳቸውንም አያገኙትም፣ ሌሎችንም መሆን አይችሉም›› የሚሉን የማህበራዊ ህይወት ባለሙያው አለን ፓርከር ናቸው፡፡ ይህ ደግሞ በላይ ውበታችንም ሆነ በውስጣዊ ማንነታችን ላይ ትልቅ ተፅዕኖን ይፈጥራል፡፡

ሁሌም የመልካም ጠረን ባለቤት ሁኚ

ጠረን በፍቅርም ላይ ሆነ ቁንጅናን አጉልቶ ለማውጣት ወይም ለማጥፋት የራሱ አስተዋፅኦ አለው፡፡ በውጫዊ ውበቷ እጅግ የምትማርክ እንስት የመጥፎ ጠረን ባለቤት ከሆነች ወንዶች ዘወር ብለው እንደማይመለከቷት ለአንቺ መንገር አያስፈልገን ይሆናል፡፡ ውበትሽን እንዳታደበዝዢ ቅድመ ማስጠንቀቂያ ነውና አታናንቂው፡፡

ውበትሽን አጉልተው የሚያወጡ በርካታ ሻምፖዎች፣ ሽቶዎችና ዶድራንቶች አሉና እነሱን በመጠቀም የበለጠ የምትማርኪ ሁኚ፡፡

ለአብነት እነዚህን ዘርዝረንልሻል

– REVLON

– ESTEE LAUDER

– LOREAL

– MATRIX

– PANTENE

– AVEENO

ቀደም ብለን ለመጥቀስ እንደሞከርነው የቆዳ ማማርና ውጫዊ ውበት ብቻውን የቁንጅናሽ መሰረት መሆን አይችልምና እወቂ፡፡ የፊልም ተዋናይና አቀንቃኝ ጄኒፈር ሎፔዝ እንዳለችው ሰውነትሽን፣ አዕምሮሽንና መንፈስሽን በማመጣጠን ቁንጅናሽን አጉልተሽ ለመውጣት ሞክሪ፡፡ የተመጣጠነ ምግብ፣ የአካል እንቅስቃሴና በቂ እረፍትም በውበትሽ ላይ ያላቸውን ጉልህ አስተዋፅኦ መዘንጋት የለብሽም፡፡

እናሳ? ጊዜው አልረፈደምና ቁንጅናሽን አጉልተሽ በማውጣት የሁሉም ሰው የዓይን ማረፊያ ለመሆን አንድ ብለሽ እርምጃሽን ብትጀምሪስ? መልካም ጉዞ!!

 

ይህን ጽሁፍ ስትወስዱ ከዘ-ሐበሻ ማግኘታችሁን ግለጹ።


ድምጻዊት ጸደንያ ገ/ማርቆስ 2014 Afrima Awards ኢትዮጵያን ወክላ ታጭታለች፤ (ድምጽዎን ይስጧት)

$
0
0

ከዚህ ቀደም የኮራ ሙዚቃ አዋርድ አሸናፊ የነበረችው ድምጻዊት ጸደንያ ገብረማርቆስ አሁን ደግሞ ለ2014 Afrima Awards ታጭታለች። ይህንን ውድድር ለማሸነፍ የኛ ድምጽ ያስፈልጋታል፤ እንዴት መምረጥ እንደሚቻል ፊኖ ደምሴ በቪድዮ አቀናብራዋለች። ድምጽ ይስጧት።

tsedenya

(ሰበር ዜና) ለ1ዓመት ከ6 ወር በላይ በእስር ሲሰቃዩ የቆዩት 12 ተማሪዎች እና 1 መምህር የ6 ወር እስራት ተፈረደባቸው

$
0
0

በእስር የቆዩበት ጊዜ ከተፈረደባቸው በመብለጡ ከእስር እንደሚፈቱ ተወስኗል!
ማክሰኞ ጥቅምት 4/2007

(ድምፃችን ይሰማ እንደዘገበው፡) ከ21 ወራት በፊት ከጅግጅጋ፣ ከሲቪል ሰርቪስ፣ ከባህር ዳር፣ ከጅማ፣ ከደሴ፣ ከሐዋሳና ከደብረብርሃን ዩኒቨርሲቲዎች ታፍነው የታሰሩ 12 ሙስሊም ተማሪዎችና 1 አስተማሪ የስድስት ወር የእስር ቅጣት ተበየነባቸው! በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ወንጀል ሕግ አንቀጽ 32/1/ሀ፣ አንቀጽ 38/1፣ እንዲሁም አንቀጽ 257/ሀ ላይ በሰፈሩት አንቀጾች መሰረትነት የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ሃይማኖታዊ ስነስርአትና አለባበስን በሚመለከት ያወጣውን የስነምግባር ደንብ በመቃወም የተለያዩ አደረጃጀቶችን በመፍጠር ‹‹በመላው አገሪቱ አመጽ በመቀስቀስ በሃይማኖት ሽፋን በአገሪቱ ያለውን ሰላም ማወክ›› እና ‹‹የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቹን በኃይል ለማስፈታት በመጣር›› የሚሉ ክሶች ተመስርተውባቸው ክሳቸው በልደታ ፍርድ ቤት ከ18 ወራት በላይ ሲታይ የዘለቀው ተማሪዎች ዛሬ የመጨረሻ ብይን በፍርድ ቤቱ ተሰጥቶባቸዋል፡፡
(ሰበር ዜና) ለ1ዓመት ከ6 ወር በላይ በእስር ሲሰቃዩ የቆዩት 12 ተማሪዎች እና 1 መምህር የ6 ወር እስራት ተፈረደባቸው
መንግስት የበረታበትን የህብረተሰቡን ተቃውሞ ‹‹አስተነፍሳለሁ›› በሚል ዓላማ ከጥር 2005 ጀምሮ ከሚማሩባቸው የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች አፍሶ ለእስር የዳረጋቸው እነዚሁ ተማሪዎች ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ መስከረም 27/2007 በፍርድ ቤቱ የጥፋተኝት ውሳኔ የተሰጠባቸው ሲሆን የቅጣት ብይን ለመስጠት ለዛሬ ቀጠሮ ያስቀመጠው ፍርድ ቤትም የስድስት ወራት እስርና ምክር እንዲሰጣቸው ወስኗል፡፡ በሃያዎቹ እድሜ መጀመሪያ ላይ የሚገኙት 13ቱ ተማሪዎች በመንግስት ኃይሎች ታፍነው ሲወሰዱ የዩኒቨርሲቲ ትምህርታቸውን ለማጠናቀቅ ጥቂት ጊዜያት ብቻ ይቀራቸው ነበር፡፡

በእነ እስማኤል ኑርሑሴን መዝገብ የተከሰሱትና ብይን የተሰጠባቸው ተማሪዎች እስማኤል ኑር ሁሴን፣ ሰይድ ኢብራሂም፣ ሙሐመድ ሰይድ፣ ፈትሂያ ሙሐመድ፣ ኑርዬ ቃሲም፣ ያሲን ፈያሞ፣ መሃመድ አሚን፣ ዩሱፍ ከድር፣ ጣሂር መሃመድ፣ መሃመድ ሰይድ፣ አብደላ መሃመድ፣ አብዲ ሙሐመድ እና ኢብራሂም ዩሱፍ ናቸው። ከተከሳሾቹ መካከል ብቸኛዋ ሴት የህክምና ተማሪዋ ፈትህያም የክሱ ሰለባ ሆና በቃሊቲ እስር ያሳለፈች ሲሆን ከቤተሰቦቿ ጋር እንዳትገናኝም በወህኒው ሀላፊዎች እቀባ ተጥሎባት ይገኛል፡፡

በግንቦት 2005 ክስ የተመሰረተባቸው እነዚሁ ተማሪዎች በተለያዩ ሰበብ አስባቦች ምክንያት ችሎቱ እየተጓተተ በመቆየቱና የፍትህ ስርአቱ የዜጎችን መብት ማስከበር በማይችልበት ደረጃ በመኮላሸቱ ጥፋተኛ ሆነው ቢገኙ እንኳ ክሳቸው ከሚያስፈርድባቸው በላይ በእስር እየቆዩ መሆኑን የህግ ባለሙያዎች ሲያሳስቡ ቆይተዋል፡፡ በዚህም ምክንያት ፍርድ ቤቱ ዛሬ የስድስት ወር ቅጣት ሲበይን ተማሪዎቹ በእስር ከ21 ወራት በላይ (ከተወሰነባቸው ቅጣት 3 እጥፍ በላይ) በቆዩበት ሁኔታ ላይ ነበር፡፡

እነዚህ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው በእምነታቸው ምክንያት ብቻ ከሌሎች ተማሪዎች ተነጥለው በድብደባ እና በተንዛዛ የፍርድ ቤት አሰራር መንገላታታቸው ሳያንስ የጥፋተኝነት ውሳኔ መተላለፉ አስደንጋጭም አሳዛኝም ነው፡፡ በተለይም ተማሪዎቹ ከትምህርት ገበታቸው ተፈናቅለው ሊመረቁ የሚችሉበት ጊዜ ያለፈ እና የቀሪዎቹም የተራዘመ ሲሆን አሁንም ቀጣይ የትምህርት እድላቸው ምን እንደሚሆን በውል አልታወቀም፡፡ በተማሪዎቹ ላይና በህዝቡ ላይ ለተዘነበለው ፍትህ የህግ ስርአቱ ተዋንያንና አጠቃላይ አስፈጻሚው አካል ተጠያቂ ሊሆኑ እንደሚገባ እሙን ቢሆንም የፍትህ ስርአቱ የመንግስት የፖለቲካ ማስፈጸሚያ ሸንጎ መሆኑ ሁሉንም ዜጋ ሊያሳስበው ይገባል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ እነዚህ ጀግና ተማሪዎች ይህን ሁሉ መስዋእትነት የከፈሉለትን ትግል ከዳር ለማድረስ ያለውን ቁርጠኝነት እየገለጸ ከዚህ ሁሉ ስቃይ በኋላም ቢሆን ተማሪዎቹ እንዲፈቱ ውሳኔ መሰጠቱ ለቤተሰቦቻቸው እና በዱዓና በጭንቀት ከጎናቸው ለቆመው ሁሉ መልካም ዜና መሆኑ አልቀረምና ለተማሪዎቹ እና ለቤተሰቦቻቸው ‹‹እንኳን ደስ አላችሁ!›› እያለ ይገኛል!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በመጨረሻዎቹ ሰዓታት….

$
0
0


ከሳሙኤል ዓሊ

ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ በኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ከ12 አመት በላይ የሰራ ወጣት ጋዜጠኛ “ነበር”፡፡ በነሃሴ ወር ውስጥ በመንግስት ወከባ ህይወቱን ከእስር ለማትረፍ ተሰዶ ወደሀገሩ በሳጥን ለመመለስ እየጠበቀ ያለ ወጣት ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛ…ሚሊዮን፡፡ ተስፋ የነበረው ስደተኛ ጋዜጠኛ የመልካም ባህሪ እና ስብእና ባለቤት የነበረው ሚሊዮን፣ ስለሀገሩ ፍቅር ብዙ መሰናክሎችን ሊጋፈጥ ስደትን መርጦ ባሰበበት ሳይሆን በታሰበለት ሊኖር የተገደደው ሚሊ እንደወጣ በሰው ሀገር ልጄን እህቶቼን ቤተሰቦቼን ሃገሬን እንዳለ በድንገት ታሞ እንደፈራው ላይመለስ አሸለበ፡፡
milion shurube

ከሚሊ ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንት አብረን ኖረናል፡፡ መጀመሪያ ከኢትዮጵያ እንደመጣ ከጓደኛው መላኩ ጋር ከኖረው እና ሆስፒታል እስከገባበት የመጨረሻዎቹ ሶስት ቀናት፤ የተረፉትን ሶስት ሳምንታት አብረን ነበር፡፡ እኔ ባሴ እና ሚሊ በጠባቧ ክፍላችን ያለፉትን ሶስት ሳምንታት ተጋርተን ነበር፡፡ ሚሊ ከሃገሩ ከወጣ በኋላ ወደ ሃገሩ በድጋሚ እንደማይመለስ ሲያውቀው አንድም ቀን ከጭንቀት ወጥቶ አያውቅም ነበር፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ “ከሃገሬ ስወጣ ሰማዩን አይቼ አለቀስኩ ካሁን በኋላ ሃገሬን አላይም” ብሎ ከመጨነቀን እና ከመተከዝ ያረፈበትን ጊዜ አላስታውሰውም፡፡ የህመም ስሜት እየተሰማው እንደሆነ ሲነግረን ስለምትጨነቅ ነው ነገሮችን አምነህ መቀበል አለብህ እያልን እናጽናናው ነበር፤ ቅሉ ሚሊ በድጋሚ እስከመጨረሻው ለሃገሩ እንደማይበቃ ያወቀው ይመስል የሃገሩን ሰማይ እያየ እንዳለቀሰ እያለቀስን በሳጥን ልንሸኝው እየተዘጋጀን ነው ….

ሚሊ ከመስቀል በዓል ጀምሮ የጤንነት ስሜት እየተሰማው አልነበረም፡፡ ራሱን በጣም ያመው ነበር፡፡ ስለ ልጁ ስለእህቶቹ ስለቤተሰቦቹ በጣም ይጨነቅ ስለነበር ሀገሩ አለመግባቱን ናፍቆቱን እያሰበ እንባ ይተናነቀው ስለነበር የህመሙን ምክንያት ጭንቀት ነው ስለዚህ አትጨነቅ እያልን ልናረጋጋው ብዙ ሞክረን ነበር፡፡ በኋላ ላይ በምንኖርበት አቅራቢያ ወደሚገኝ ክሊኒክ ወሰድነው፡፡ ታይፎይድ እንደታመመ እና ምን አልባት ለሃገሩ አዲስ ስለሆነ የምግብ አለመስማማት እንደሚሆን ገልጾልን ግሉኮስ ወስዶ መድሃኒት ተሰጥቶት ወደቤት ተመለሰ፡፡ ሃሙስ ቀን ንጋት11 ሰዓት ተንስቶ በጣም ራሱን እየታመመ እንደሆነ እየገለጸ “ወይኔ በስደት ልሞት” እያለ ሲያለቅስ በድንጋጤ እኔ እና ባሴ ተነስተን መጀመሪያ ወደወስድነው ክሊኒክ ወሰድነው፡፡ ዝግ ነበር፡፡ ከዛ የተሻለ ህክምና ያገኝበታል ብለን ወደአሰብነው ሆስፒታል ወሰድነው፡፡ ሶስት አይነት ምርመራ ካደረጉለት በኋላ መድሃኒት አዘውለት ወደቤት ተመለስን፡፡ ሚሊ የጤናው ሁኔታ እየተሻሻለ ነበር፡፡ ግን የምግብ ፍላጎቱ አነስተኛ ስለነበር አቅም እያነሰው ነበር፡፡ መዳህኒቱን እየወሰደም በቅርባችን ባለ ክሊኒክ ግሉኮስ ይወስድ ነበር፡፡ ቀስ በቀስ አቅሙ እየተዳከመ መጣ፡፡ የመጨረሻዎቹ ሶስት ቀናት ግን ፍጥነቱን ያልገመትነው እና ያልጠበቅነው ነገር ተከሰተ፡፡

ሆስፒታል ከመግባቱ ሁለት ቀን በፊት ጓደኛው መላኩ ቤት ሄዶ ህክምናውን እየተከታተለ ነበር፡፡ ቅዳሜ ጤንነቱ መሻሻሉን አይቼ ደስ ብሎኝ ነበር ወደቤት የገባሁ፡፡ የዛን ቀን ምግብ ስለማይበላ ግሉኮስ ለመውሰድ እንደሚፈልግ ነግሮን ከባሳዝነው ወንድምነህ (ባሴ) ጋር ወደ ክሊኒክ ሄዱ፡፡ ማታ ላይ ሚሊ በጣም ደክሞ ነበር፡፡ ህመሙ በፍጥነት እየተባባሰ መጣ፡፡

የመጨረሻዎቹን ሁለት ቀናት ሚሊ ራሱን አያውቅም ነበር፡፡ ሆስፒታል ተኝቶ መታከም ቢጀምርም ሚሊ ራሱን እንደሳተ ሳይሰናበተን “ሀገሬን አላይም ዳግመኛ እንዳለ” አሸለበ፡፡ ሚሊዬ አንተ ራስህን አታውቅም እንጂ በመጨረሻዎቹ የጭንቅህ ቀናት በምን ያህል ጋዜጠኛ ተከበህ፤ ምን ያህል ሰው አብሮህ እንደነበር ብታየው እንዴት ጥሩ ነበር፡፡

ፍርሃታችን እውን ይሆናል ብለን አልጠበቅንም፡፡ ፈጣሪ በስደት ይጠብቀናል እግዚአብሔር አለን ብለን አስበን ክፉን ከኛ ያርቀዋል ብለን ሁላችንም ተመኝተን ነበር፡፡ ግን አልሆነም፡፡ ሚሊዬ ሃገሬ ናፈቀኝ ልጄ እህቴ ጓደኞቼ…ከእንግዲህ አላያቸውም እኮ እንዳለ ከሃገሩ ከወጣ ከአንድ ወር ከ10 ቀን በኋላ ህይወቱ አለፈ፡፡ መጨረሻ በኦክስጅን በሚተነፍስበት ሰአት እግዚአብሔር እንዲያድነው አልቅሰንለት ነበር፤ ራሴን ያመኛል ምግብ መብላት አልቻኩም ብሎ በተጨነቀበት ሰዓት እግዚአብሄርን ለምነን ነበር…. ሚሊየ “ወይኔ ከሀገሬ እንደወጣሁ ልሞት” ብለህ እንደፈራህ እውን ሆኖ ተለየኸን፡ ምን ማድረግ እና ለማን መደወል እንዳለብን ማወቅ ሳንችል በሰው ሀገር እንደልባችን ማልቀስ ሳንችል ወደየትኛው ቤታችን አስክሬንህን ይዘን መሄድ እንዳለብን ግራ ገብቶን መሃል ሆስፒታል የሰው ያለህ ብለን ብንጮህም ሰሚ አጥተን…ሀገር ማለት ፣..ሰው ማለት ….ስደት ማለት ምን ማለት እንደሆነ አንተን ውድ ጓደኛችን አልፈህ …ምን ማድረግ ለማን መናገር እንዳለብን ግራ ገብቶን ሁላችንም ከአስክሬንህ ጎን አለን ….፡፡ከተሳካልን በክብር ለሀገርህ አፈር እናበቃሃለን፡፡ ሚሊ እስከመጨረሻው ሰዓት ይሄ ይመጣልን ብለን አልበቅንም፡፡ ግን በፈጣሪ ስራ መግባት አንችልም፡፡ ቤተሰቦችህ ምን ይሉ እህት እንዴት ትችዋለች.. ለልጅህ እንዴት ይነግሯት ይሆን…ለጓደኞችህ እንዴት ብለን….

ጋዜጠኛው ስደተኛው ሚሊ ቁመህ ወጥተህ በሳጥን አሽገን እንዴት እንደምንልክህ ዛሬም በሰው ሃገር ሰው በሞላበት የሰው ያለህ እያልን ነው፡፡ ሚሊ ፈጣሪ ነፍስህን በገነት እንደሚያኖራት አምናለሁ፡፡ በሞትህ መጨረሻ ቀናት በድካም 1 ቀን በፊት መድሃኒያም ቤተክርስቲያን ሄደህ ጸበል ተጠምቀህ ንስሃ ገብተህ በብጹህ አባታችን ቅባ ቅዱስ ተደርጎልህ ነበር፤ “ይቅር ላላችኋቸው ይቅር እላቸዋለሁ” ይላልና መጽኀፉ ፤ ፈጣሪ በሰማይ በመልካም ቦታ እንደሚያኖርህ አምናለሁ፡፡ ቤተክርስቲያን ሆነን የጸለይከውን ድህነት በሰማይ እንደሚከፍልህ አመንኩ፡፡ ከቤተ ክርስቲያን ስትወጣ የነበረህን ተስፋ ፈጣሪ በሰማይ ቤት እንደሚሰጥህ አመንኩ፡፡ ከቤተክርስቲያን ከህመም እንዲያሳርፍህ የጸለይከውን ጸሎት በሰማይ በሰላም ያሳርፍ ዘንድ አመንኩ፡፡
እሽ ሌላ ምን ልበል ..ሚሊ የሃገርህ ሰማይ እንደናፈቀህ ሀገሬን እንዳልክ ነገን በተስፋ እንዳየህ ላይሳካ መኖር ሳትጀምር መንገድ አጭር ሆኖ በዚህ ተቋጨ፡፡ የመኖርህን የመጨረሻ ቀናት በስደት ሞት…በስደት ሞት… ከቤተሰብ ርቆ ህመምን አየህ፡፡ በስደት እንኳን ለቅሶ እንኳን ህመም መልካም ነገር መልካም አልነበረም …ሚሊ እውነት ይሆን…እንደ አፈታሪኩ ሞትህን “ለማመን ስትቅበር የማየት” እድሉ ባይኖረንም ፈጣሪ አስክሬንህን ለሃገርህ ለማብቃት ሃይል ይስጠን …

መታመምህን ሰምተው…ስደትህን ሰምተው ጭንቀትህ ሰምተው ሳይጨርሱ ሞትህን የሰሙት ምን ይሉ ይሆን …እኛ ሁሉም ነገር ጨልሞብናል ሚሊየ ድንገተኛ ህመም አፋጥኖ ላፈር አበቃህ፡፡ አሁንም የስደት ጣጣውን ፈጣሪ ሸፍኖ ለሃገርህ አፈር ያብቃህ፤ ሚሊ ሚሊ ሚሊ ስደተኛው ጓዴ ሚሊ ሚሊ……….. ሚሊ

ለሕገ መንግስቱ መቆም ሽብርተኝነት ሲባል (ዞን ዘጠኞችን በተመለከተ) ግርማ ካሳ

$
0
0

የተማሩ ናቸው። አገራቸውን የሚወዱ። በሕዝባቸውና በአገራቸው ዉስጥ የሚደረገዉ ግፍ እንዲቆም በጽሁፋቸው የሚመክሩ። ማንም ላይ ጥላቻ የሌላቸው። ኢፍትሃዊነትን የሚጠሉ ። አምባገነንነትን እንጂ ማንንም የማይጸየፉ።

Haile Mariamበጽሁፋቸው ፍቅርን ሰብከዋል። ነጻነትን አውጀዋል። «ዜጎች እንደ እንስሳ ታስረዉና ታፍነው መኖር የለባቸውም። ነጻነታቸውና ስብእናቸው ሊጠበቅላቸው ይገባል» እያሉ ተከራክረዋል። ለሰብአዊነት ተሟግተዋል።  ሰው ሲከብር እንጂ ሲዋረድ፣ ሲነሳ እንጂ ሲወድቅ፣ ሲድን እንጂ ሲሞት፣ ሲበለጸግ እንጂ ሲደኸይ ማየት አልፈለጉም።

በቢሯቸው፣ በቤታቸው፣ ሴቶቹ በቦርሳቸው፣ ወንዶቹ ደግሞ በኪሳቸው ቦምብ ወይም ፈንጂ አልተገኘባቸው። በድብቅ የዶለቱት ወይንም የሰሩት ነገር የለም። የተወሰኑቱ ካምፓላ ኡጋንዳ ሄዱ እንጂ በድብቅ አስመራ የሄደ ከነርሱ መካከል የለም።  የጻፉትና የተናገሩት ሁሉም በግልጽና በአደባባይ ነው። የተወሰኑቱ አርቲክል ዘጠኝ ከሚባል ድርጅት ጋር ግንኙነት አላቸው።

አርቲል ዘጠኝ እንደ አይሰስ፣ ወይም አልካይዳ ያለ ደርጅት አይደለም። የአርቲክል 19 ድርጅት አመጣጥ እንደዚህ ነው፡

የተባበሩት መንግስታት የሰባአዊ መብት ድንጋጌ (THE UNIVERSAL DECLARATION OF HUMAN RIGHTS የሚባል አለ። የዚህ ድንጋጌ አንቀጽ 19 ( አርቲክል 19) እንዲህ ይላል ፡

«Everyone has the right to freedom of opinion and expression; this right includes freedom to hold opinions without interference and to seek, receive and impart information and ideas through any media and regardless of frontiers.»

በዚህ አንቀጽ ላይ የተጻፈው ነጻነት በአለም ዙሪያ ሁሉ እንዲከበር ለመርዳት (አድቮኬት ለማድረግ)  የተቋቋመ የሲቪክ ማህበር ነው፣  አርቲክል ዘጠኝ። ይህ ማህበር አርቲክል 19 የሚል ስያሜ ይዞ፣ በአሜሪካ፣ በአዉሮፓ ባሉ በርካታ አገሮች፣ በኬንያ፣ በቱኒዚያ ፣ በባንግላዲሽ ሳይቀር እውቅና አግኝቶ የሚንቀሳቀስ ነው። በአገራችን ዉስጥ በኢሕአዴግ መንግስት ተጋብዞ በምርጫ ዙሪያ ስልጠናዎች የሰጠ ድርጅት ነው።

ይህ የተባበሩት መንግስታት አንቀጽ 19 ድንጋጌ  በኢትዮጵያ ፌዴራል ሕገ መንግስት አንቀጽ 29፣ ን ኡስ አንቀጽ 1 እና 2 ላይ በግልጽ ተቀምቷል። «Everyone shall have the right to hold opinions without any interference.Everyone shall have the right to freedom of expression without interference. This right shall include freedom to seek, receive and impart information and ideas of all kinds, regardless of frontiers, either orally, in writing or in print, in the form of art, or through other media of his choice.» ይላል የሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29።

በተባበሩት መንግስታት የሰባአዊ መብት ድንጋጌ አንቀጽ ( አርቲክል 19) ወይንም የኢትዮጵያ መንግስት አንቀጽ 29፣  በኢትዮጵያ ተግባራዊ እንዲሆን የሚጽፉ፣ የተደራጁ ሰላማዊ ዜጎች ናቸው። ለሕገ መንግስቱ ፣ ለሕግ ከበሬታ ያላቸው ናቸው።

ነገር ግን ከዘመናዊት ፍጹም የራቁ፣ በሚድል ኤጅ ይኖሩ ከነበሩ በአስተሳሰብ የማይተናነሱ፣ አዲስ አበባ ያሉ ገዢዎች ግን፣  ራሳቸው ያወጡትን ሕገ መንግስት ረጋግጠው ፣ ሽብርተኞች ናቸው በሚል ክስ ከሰዋቸው ከፍተኛ መከራና እንግልት እየፈጸሙባቸው ነው። ይኸው ነገ ለዘጠነኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ፣  የዞን ዘጠኝ ጦማሪያን !!!

እንግዲህ አገራችን የምንላት ኢትዮጵያ እንዲህ አይነት አሳዛኛ አሳፋሪ ግፎች የሚፈጸምባት አገር ናት። ኢትዮጵያ ለጥቂቶች ገነት፣ በአሥር ሚሊዮን ለሚቆጠሩ ልጆቿ ግን ሲኦል የሆነች አገር ናት።  ይሄ መለወጥ አለበት። ይሄ መቆም አለበት።  ይህን አይነት ግፍ አይቶ ዝም የማለት ሕሊና ሊኖረን አይገባም። ሁላችንም የድርሻችንን በመወጣት፣ የሚሊዮኖች ንቅናቄ አካል በመሆን፣  ለነጻነት፣ ለፍትህ ለእኩልነት መቆም ይኖርብናል። ዞን ዘጠኞችን በማሰሩ አገዛዙ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዞን ዘጠኞች መፈጠራቸውን ልናሳየው ይገባል።

 

በአዲስ አበባ ከተማ መስከረም 24/2007 ዓ.ም የዱቄት ፋብሪካ ለመትከል የመሰረት ድንጋይ በሚቀመጥበት ሰዓት የፋብሪካው ስም በጠቅላይ ሚንስትሩ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋይ ሊሰየም ነው ስለተባለ የከተማው ህዝብ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ምንጮቻችን አስታውቁ፣

$
0
0
addis abeba city and roman tesfay
ምንጮቻችን ከከተማዋ የላኩልን መረጃ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ልዩ ስሙ ለገጣፎ ተብሎ በሚጠራው 60 ሄክታር በሚሆን መሬት ላይ የሚያርፈው የዱቄት ፋብሪካ፤ በጠቅላይ ሚኒስተሩ ባለቤት ወ/ሮ ሮማን ተስፋይ ስም እንዲጠራ በተወሰነበት ጊዜ፤ ይህንን ድርጊት የሰማው ህብረተሰብ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳደረገ ለመወቅ ተችሏል፣
መረጃው ጨምሮም ህብረተሰቡ ፋብሪካው የሚሰራው በህዝብ ገንዘብ ነው ለምን? በግለሰብ ደረጃ እንዲጠራ መንግስት የወሰነው በማለት ተቃውሞውን እያሰማ እንደሆነና፤ በሚካሄደው የህዝብ ተቃውሞም ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎችም ተቃዋሚ ድርጅቶች ከህዝብ ጎን እንደተሰለፉና ሁኔታውንም አጥብቀው በማውገዝ ላይ እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣

Source:: Debirhan

የደብተሮቹ ጥምጣም ሲፈታ….የታየዉ …. ማህበረ ቅዱሳንን ለቀቅ አርጉት እስቲ!

$
0
0

ከበሲሊዮስ ዘዓማኑኤል

mahibere-kidusan“ሚሉሽን በሰማሽ ገበያ በሎጣሽ”…..  ይላል ያሀገር ሰዉ ሲተርት! ህዝብ ምን እንደሚላችሁና እንዴትስ  ምዕመኑ እንደታከታችሁ በወቃችሁና አፈችሁን ሞልታችሁ ማህበረ ቅዱሳንን ለመዝለፍ….. “አሸባሪ“ ምናምን እያላችሁ ስለማታዉቁትና በልግፅ ስላለገባችሁ ነገር ለመዘባረቅ ባልደፈራችሁ! “የራሷ እያረረ የሰዉ ታማስላለች“ እንዲል አሁንም የሃገር ሰዉ … ደብተሮቹ የሚያስተዳደሩትን ደበርና አጥቢያ በአግባቡ መምራት ተስኗቸዉ ከሙስና ማፅዳት አቅቷቸዉ ሳለ  በሚሊዮኖች መንፈሳዊ የትግል ፅናት ለሃያ አራት ዓመታት ሲገነባ የነበረን ማህበር ለማፈረስ ሲዶሉቱና ሲፈርጁ መዋለቸዉ ሲታወቅ አንግት ያስደፋል!

ሲናገሩ ካየኋቸዉ አንዱ ማንነቱን በቅጡ ያለወቀ ደብተራ ቅዱሳን አባቶችን ለማስፈራራት ሲሞከር ማስተወሌ መድረኩ የቱን ያህል የማሰብ ስንኩላን የተሰባሰቡበት እና መነፍሰዊነት በቦታዉ ያልተጋበዘበት የጠምጣሚዎች ስብሰባ እንደነበር ለመረዳት አያደግትም! አንዱ ተናጋሪ ብቻ ትንሽ አመክኖዊነት ያለዉ ይመስላል ነበር … የማህበረ ቅዱሳንን መሪዎች ዘልፎ አብዛኛዉን አባል ለመካከል የሞከረዉ (ገሎ ማዳን ሆነበት እነጂ) … ከሌሎቹ ደናቁርት ደብተራዎች ይሻል ይሆናል! በርግጥ እሱም የተንሸዋረረ አመለካከት አለበት! ንግግሩን ሲያበቃ እንደብዞወቹ በፍርጃና በማስፈራራት ነዉ የዘጋዉ….  ብዙ የኢህዴግ አባልና ደጋፊ የሆኑ የማህበሩ አባላት እንዳሉ ሲታወቅ “በፌደራሊዝም የሚያምኑ” ምናምን እያለ የማያወቀወን በጥራዝ ነጠቅነት ሲቀባጥረና ወጥ ሰረግጥ ነበር! ጠርዝ የመያዝና ፍረጅነት በሽታ የሆነበት ሃገር!

ግን ማህበረ ቅዱሳን ምን አደረጋቸዉ? ምዕመኑን ስላስተማረ? መንፈሳዊ እዉቀት ስለዘራ? ወጣቱን ከዘመናዊ አሰተሳሰብና  ከቤተ ክረሰቲያን ቀኖና ጋር አስማምቶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን እንዲያገለግል ስላስቻለ? ከርሳቸዉን ከመሙላት በቀር ለትዉልዱ ምንም አስበዉለትእና ምንም ሰርተዉለት የማያዉቁ፣ ጥምጣም ከማሳመርና በየመንደሩ እየዞሩ ህዝብን ከመበዝበዝ በቀር በመንፈሳዊነት ትዉልድን ማነፅ… ወንጌል በቅጡ መስበክ የማይችሉ… ዛሬ ተነስተዉ አፋቸዉን ሲያላቅቁ ከዉስጣወቹ የሚወጣዉ የክፋትና የአጥፊነት ክርፋት መሆኑ ታየ! ወየዉ….. እኔ ስለናተ አፍረኩ! አባቶቼ ብዬ መስቀል መሳለሜ … ጉልበት መሳሜ ፀፀተኝ! የተሰራን ማጥፋት… የተሰበሰበን መበተን ለነገሩ የአባይ ደብተራ ወጉ ነዉ!

ቅንጣት ታህል መንፈሳዊነት ያልጎበኛችሁ መሆናችሁን በአንደበታችሁ መሰከራችሁ! እናተ ስታነቀላፉ በተኩላ ልታስበሉት የነበረዉን ወጣት ሰብስቦ፣ አስተምሮ፣ ለሃገርና ለቤተክርስቲያን ልማት የቆመን አካል ቂጣ ባሰፋዉ አፋችሁ እየተነሳችዉ መዘንጠላችዉ…ምራቃችሁን ጢቅ ማለታችሁ ያሳፍራል! ከንቱ መሆናችሁንም በገዛ አንደበታችሁ መስመሰከራችሁ! ይልቅስ እዉቀቱና እዉነቱ ኖራቹሁ ቤተ ክርስትያንን የንግድ ቤት አድርገዉ ኪሳቸዉን ከሚሞሉ ሸቃጭ “አገልጋይ ነኝ” ባዮች ብትገላግሉን ምንኛ ቤተ ክርስትያንን በተጠቀመች እኛም ባከበርናችሁ! በዚያ መድረክ አላማችሁ ባንድም በሌላም ምንግድ ምን እንደሆነ ታይቷል…. ማህበሩን ከመንግስት ጋር በማጋጨት ለማፍረስ እንደሆነ ለሁሉም ምእመን ግልፅ ነበር…. እኛም ነቄ ብለናል! ከነቱ ልፋት! መእመኑ ማንን እንደሚመርጥ ያዉቃል … አክበሮቱንም ክብር ለሚገባዉ ይሰጣል!

የልም አትልፉ ማህበሩ ከመንግስት ጋር በፍጹም አይጋጭም! የሃገሪቱን ህግና ደንብን አክሮ ስራዉን ይሰራል…. ማህበሩና አባላቱም ከቅዱሳን አባቶቹን በቀንነት ያገለግላል! …. አባቶቹን አክበሮ …የቤተ ክርስትያንን ስርአትና ቃለ ዐዋዲ ጠብቆ ቅንጣት ታህል ስርአት ሳያዛንፍ ይሰራልና የሚፈራዉ ነገር የለም! ህግ አዋቂስ ከሆናችሁ የቤተ ክርስትያኗን ደንብ አዉቃችሁ እራሳችሁን ባረማችሁ … የምትዘርፉትን ህዝብንም እፎይታ በሰጣችሁት ነበር! ማወቅ ከለባችሁ ደግሞ ማህበሩንም…ቤተ ክርስትያንንም… ምንግሰትንም…ሃገርንም በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግሉ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ አባላትና … ሚሊዮን ደጋፊዎች አሉት! እረፉት እንጊደህ የተገባ ባይሆንም ሺዎች የማህበሩ አባላት ኢህዴግን ተቀላለቀለዉ አየሰሩ ነዉ! ሌላዉና በጣም ልታዉቁት የሚገባዉ ጉዳይ… እዉነቱን ለመናገር በርካታ የኢህዴግ አበላትና መሪዎች ከናተ ከሆዳም ደብተሮቹ ይልቅ ማህበሩን ቀርበዉ ያወቁታል… ያከብሩታል! በትምህርት ቤት ደጃፍ ያለፉ አባላት የሞሉት የሙህራን መድረክ የሆነ ማህበር ስለሆነ!

ከሁሉ የሚያሳፍረዉ “መናፍቅ” ለሚለዉ ትርጉም ማግኘት ተስኗቹህ የፖለቲካ ተንነታኔ ለመስጠት መመከራቸሁ ነዉ! እስኪ የፖለቲካዉን ትርከት ለፖለቲከኞቹና ለተማሩት ትታችሁ መናፍቅነታችህን ላስመሰከራችሁበት ምንፍቀናችሁ ትርጉም አብጁለት! ቤተ ክርስትንን እና ሃገርን በታማኝነት የሚያገለግልን ማህበርን እነደ ይሁዳ አሳለፎ ለመስጠጥ (ለማፍረስ) ከመዶለት…. አባላቱን እነደ አይሁድ “ይሰቀሉ… ይሰቀሉ!” ከማለት የተሻለ ምንፍቅና ከቶ ከየት ሊመጣ?

ማህበረ ቅዱሳን ህንፃ መስራቱ ይህን ያህል ያንገበገባቸዉ አረ ለምን ይሆን ግን!? ህንፃ ቢሰራ በአባላት መዋጮ ነዉ! ተማሪዉ ሆዱን አስርቦ የቁርሱን ዳቦ ሸጦ፣ ሰራተኛዉ የቤተሰቡን ጉሮሮ ዘግቶ አንጀቱን አስሮ በጠራቀማት ፍራንክ ህንፃዉ እንደተገነባ ለናተም ግልፅ ነዉ! እንደናተ የቤተ ክርስትያን ህንፃ አሰሪ ኮሜቴን አስቸግሮ አልያም ከኮሚቴ ጋር ተመሳጥሮ ከህዝበ ዘርፎ ኪሱን የሞላ አባል አለነበረም ወደፊትም አይኖርም! አንድ ደብተራ ዱንቡሎ ባለወጣበት ሁኔታ ለምን ማህበሩ ህንፃ ሰራ በሎ ይህን ያህል መጨነቁ የድንቁርናችሁንና የክፋታችሁን ልክ ያሳያል! ሌላዉ ህንፃዉ የተሰራዉ እናተ እንደ ምታድሩበት የመቃብር ቤት ከቤተ ክርስትያን መሬት ተቆርሶ ሳይሆን ሚሊዮን ብሮች ፈሶበት ከግለሰብ በተገዛ መሬት ላይ ነዉ! እና ምናችሁ ተነካና ነዉ ይን ያል ግብግብ ያላችሁት? መስራት ያልቻለችሁትን ስረቶ ስላሳያችሁ?

ለነገሩ “ደብተራ …የልማት ደንቃራ” እንደምተባሉ እናተም ታዉቀታለችሁ! ከእሁድ እከ እሁድ… ከወር እሰከ ወር በአል ነዉ፣ ግዝት ነዉ …. ዉግዝ ነዉ እያላችሁ ሀገሬዉን አሳንፋችሁ በድህነትና በረሃብ ስታሳክኩት የኖራችሁ መሆኑን ዛሬ እነዴት ተዘነጋችሁት?! “ሰማይ አይታረስ ንጉስ አይከሰስ” የሚል ቢሂል ፈጥራችሁ ህዝብን ስታስጨቁኑና አብራችሁ ስትበዘብዙ ኖራችሁ ዛሬ በየት በኩል ዞራችሁ ነዉ የዲሞክራሲና የፌደራሊዝም ሃዋርያ የሆናችሁት? መሰራት የሚችሉ ስታዩ አይናችሁ ደም ለበሰ! ህንፃ መስራት ጥምጣም እንደ ማሳመር ቀላል ይመስላችሁ ይሆናል… ተሳሳታችሁ! ፆም መዋልና ማደርን ይጠይቃል…. ከዛም አልፎ ለትዉልድ ሃሳቢ ሞሆንን … በለዕራይ መሆን ይጠይቃል! ዘኬ ቤት ተጎልቶ ከርስ ከመሙለት የተሻለ ሃሰብ ያስፈልጋል…   አጉል ሚሲጢር ልታሶጡኝ ነዉ እንጂ በሚያሳፍር መልኩ ሆደሞች ለመሆናችሁ ምስክሩ በየሰንበቱ ደጀ ሰላም ዳቦ ስትቃሙ… ለፍርፋሪ ብላችሁ በመቛሚያ የምትዣለጡት ምን ያህል ወጣቱን ምእመን እደሚያሸማቅቀዉ ባወቃችሁት! አመታዊ ግብር አለተከፈለም ብላችሁ ስነቱን ደሃ ያለፈትሃት እንዲቀበር… ስንቱንስ ደሃ የመቃበር ስፍራ አሳጣችሁት?! በሚሊዮን የሚቆጠሩ የኦርቶዶክስ አማኞች ሃማኖቱን ትቶ ሌሎች የእምነት ተቛማትን እንደተቀላቀለ እስታቲክስኩን ማን ባስረዳችሁ?!…. ይህ ሁሉ ታዳያ በናት አሳፋሪ ስራ፣ዳተኝናትና ምዝበራ ነዉ!  ለአሳፋሪ ስራችሁ መቼ ጆሮ አላችሁና ትሰሙታላችሁ?! ግመል እየዋጣችሁ ትንኝ ማጥራቱ የተለመደ ግበራቸሁ ሆኖ እነጂ የጭቃ ጅራፋችሁን ለማጮህ ባለደፈራችሁ ነበር! ሆዳችሁ አመላካችሁ እንደሆነ ክርስቲያኑ ብቻ ሳሆን ሌላዉም ወገን ያወቀዉ ጉዳይ ከሆኖ እንዴት እነዳቃችሁ ባወቃችዉ ምንኛ መታደል ነበር!

ለማኝኛቸዉም ህንፃዉ የተሰራዉ ለቤተ ክርስትያን አገልግሎት፣ ለመፍሰዊ ተልኮ እንጂ እናተ እንደምታስቡት ለከነቱ አላማ ወይም ደግሞ ለፖለቲካ ዱለታ አይደለም! ለፖለቲካ ጨዋታዉ መች ሌላዉ መድረክ ገና ተነካና? እናተ ቤተ ክርስትያንን ንቃችሁ እንዳስናቃችኋት … ደፍራችሁም አንደአስደፈራችሃት ማህበሩና አባላቱ ቀለዉ ቤተ ክርስትያንን አያቀሏትም! የቅዱሳን በዐት…. የፀሎት ዋሻ መሆኗን አብዝተዉ ይመሰክራሉ!

ሙሁራን አባላቱ ማታ ማታ መሰብሰባቸዉም ቀን ለስጋቸዉ ሲደክሙ ዉለዉ ለሊቱን ቤተ ክርስቲንን ለማገልጋል እንጂ እናተ በትንሿ መሰቢያችሁ እንደበሰለሰላችሁት ፖለቲካ ለመዶለት አይደልም! ለነገሩ ምን ታረጉ እናተ ካገልግሎት ሰዓታችሁ ሳይቀር እሰረቃችሁ ድራፍት ቤትና ገሮሰሪ ስትጋፉ አይደል ምታመሹት?! እንግዲዉም እወቁት አባለቱ ቀን በተለያዩ ስራዎች ሲደክሙ ይዉሉና በአዳር መርሃ-ግብር ደግሞ እንዲያ ያብከነከናችሁን የመሃብሩን ስራዎች ይሰራሉ! ለነገሩ መጎናጸፍያ አንዠርግጎ ሉካንዳ ቤት መሰለፍ፣ መስቀል ወድሮ ማኪያቶ ማንቃርር፣ ቀሚስ እየጎተቱ ቢራ መጋጨት ሞያዉ ላደረገ የደብር አሰተዳዳሪ፣ ክህነቱን ንቆ በዘማዊነት እራሱን ላዋረደ ካህን የክፋት ህሊናዉ ያቀበለዉን ከማዉራት፣ በየመደረኩ አደርባይነቱን ከማሳየት እና ከማሽቃበጥ በቀር የተለየ ነገር አይጠበቅም! ለሁለት ጌታ መገዛት ሆዳሞች ግበር ነዉና!

በጣም ያሰቀኝ…. ቆይቶ ደግሞ ያሰቀቀኝ ነገር ስለምርምርና ጥናት በምሬት ሲያነሱት የነበረዉ ነገር ነዉ…. ጉድ ነዉ መቼም እቺ ቤተ ክርስትያን ስነቱን ገለቱ ሰብስባ ይዛለች?! ኋላ ቀርንነታችሁ የቱን ያህል እንደሚያንገበግባችሁ በይፋ የተነገራችሁት! ጥናትና ምርምር የሚደረገዉ ቤተ ከርስትንን ለመጥቀም እንደሆነም አታዉቁም! በበጎ ፍቃደኝነት የሚጠናዉ ጥናት በአማካሪ ተቛማት ቢሰሩ ስነት ስነት ሚሊዮን በሮች ሊያሶጡ እንደሚችሉም አታዉቁም! ከዘመኑ ጋር ለማራመድ…. ሰራን በቅድ/በፕላን ለምመራት… በሚሰሩ ስራዎች ላይ ክትትል ለማድረግ… የልማት ስራዎችን ዉጤትና ስኬት ለመገመገም ጥናትና ምርምር ያስፈልጋል ጎበዝ! ይኼን የማታዉቁ ጉዶች ናችሁ ቤተ ክርስትንን እነመራልን ብላችሁ የተኮለኮላችሁት?! በእዉነት ስለናተ አፈረኩኝ!

እሰቲ አይናችሁን ከፍታችሁ ተመልከቱ … ዛሬ አለም ዘምኗል …. ቴክኖሎጂዉ ረቛል…. እንመራሀለን የምትሉት ምእመን በርቀት ጥሏቹሁ ኼዷል!  እናተ ግን ዜሬም ቁራሽ በለመናችሁበት …. የቆሎ ተመሪነት ዘመናችሁ ላይ ቆማችሁ ባረጀና ባፈጀ አስተሰባቸሁ ህዝበን ለመምራት ትፈልጋለችሁ! ሌሎች የእመነት ተቋማትን እስኪ ተመለከቱ የቱን ያህል የዘመኑ መሆናቸዉን! በየ አድባራቱ ህንፃ ገንብቶ ሱቅ እያከራዩ ግበር የማከፈልበት የሃገር ሃበት መመዝበር…. አልያም በየ ንግሱ ጃንጥላ አዘቅዝቆ የምእመናን ኪስ ማራቆት ዘመናዊነት ከመሰላችሁ ተሳሰታችኋል! አለያም ከቤተ ክርስቲን በዘረፋችሁት እና የንስሃ ልጆቻችሁን ቁም ስቅል አሳይታችሁ ሰልቫጅ አዉቶ ሞበል ግዝቶ ልታይ ልታይ ማለቱ አይደልም የቤተ ክርስትያን እደገት! ይልቁንስ የቤተ ክርስትያንን ታሪክ በማጥናትና ለአዲሱ ትዉልድ በማሰተማር ለመጨዉ ዘመን ማሸጋገር፣ ቤተ ክርስትያን እንደ ተቛም ያለባትን ችግርና ፈተናዎወች መርመሮ የመፍትሄ አቅጣጫ በማዉጣት ስርአትና ተዉፊቷን አጽንቶ ለማኖር አሰተዳደራን ማዘመን፣ በዙሩያዋና ቡወስጧ የተሰባሰቡ ምእመናን ከመንፈሰዊዉ ስራ በተጨማሪ ያለቸዉን አቅም ጉለበትና ሃበት በማዋጣት ህዝብ የሚጠቀምበትን አገልገሎት ማስፋትና ማደረስ እንዲቻል ማሰተባበር በተገባ ነበር፡፡ ይሁናና ዶሮ ብታልም ጥሬዋን እነዲል የሃገር ሰዉ…. ጥሬ ነገር ከመቛጠርና እንቶ ፈንቶ ከማዉራት እለፋችሁ ሙሁራንን ተንጠራርታችሁ ለመዝለፍ መነሳታችሁ የጠፋታችሁ ሁሉ ጥፋት ነዉ!

ማህበረ ቅዱሳንና አባለቱን በፖለቲካ ለመክሰስ ከመነሳታችሁ በፊት እራሰችሁን መረምሩ! ወደ ማህበሩ የቀሰራችሁትን ጣት እራሳችሁን ተመልከቱበት! አፄ  ቴድሮስ ለቀደሙት ደብተሮች በማያገባቸዉ እየገቢ ሲያስቸግሩ እንደተናገሩት እናተም በቅንነት ቤተ ከርስትያንን የሚያገለግል ማህበር ከመወነጀላችሁ በፊት በየጥመጣመቸሁ ስር ያለዉን ቆሮቆር የወረረዉን የረጀ አሰተሰበችሁን አፅዱ! ማፍረስ እንጂ መገንባት ዳገት ለሆነባችሁ ደበተሮች ከራሳችሁ ጥቀም አስበልጣችሁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ፍላጎት ለማየት ሞክሩ! አላመችሁ ግልፅ ነዉ! ማህበሩን በማፍረስ ቤተ ክርስትያንን እና ምእመኑን ያለ ሃይ ባይና ለምን ብሎ የሚጠይቅ በለለበት ለመዝረፍ ነዉ! ይህ ደግሞ አይሳካም! የማህበሩ የበላይ ጠባቂ የማያንቀላፋዉ ትጉህ እረኛ ልዑል እጊዚያብሔር ነዉና!

ለሁሉም ማህበሩን ለቀቅ ….አርጋችሁ በትችሉ በትብር ለመስራትና ቤተ ክርስቲያንን ለማገለግል ሞክሩ ከልሆነ ግን እነተከበራችሁ ከነጠመጣማችሁ ሰንበቱ!

እስቲ ለሁሉም ልቦና ይስጣችሁ! አሜን!

 

የህግ የበላይነት፣ የፓለቲካ ምህዳር እና ሰብአዊ መብት –የጸረ ሽብር ህጉ ሲገመገም

$
0
0
“ጋዜጠኝነትን እና የፖለቲካ ድርጅትን ሽፋን በማድረግ የሀገሪቱንና የሕዝቦቿን ሰላም ለማደፍረስ ከሚያስቡና ከሚፈልጉ ‘ሀይላት’ ጋር ግንኙነት በማድረግ የተለያዩ  የሽብር ተግባራትን ለመፈጸም ሲንቀሳቀሱ በቁጥጥር ስር አውለናቸዋል።“ 
zoneeይህ መግለጫ (መልስ) የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ 652/2001 ከወጣበት ከነሀሴ 2001 ዓ.ም. ጀምሮ ጋዜጠኞችና በሰላማዊ መንገድ ተመዝግበው የፖለቲካ ምህዳሩን የተቀላቀሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች አባላት በኢህአዴግ መራሹ የኢትዮጵያ መንግስት ከታሰሩ በኋላ በመንግስት አካላት የሚሰጥ የተለመደ አባባል ነው። የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ እስከ መስከረም 2007 ዓ.ም ባሉት አምስት ዓመታት ውስጥም ከጋዜጠኛ እስከ ፖለቲከኛ (political personalities)፣ ከሀይማኖት መሪዎች እስከ ጦማሪያን፣ ከታጣቂ ወታደሮች እስከ የኮንትሮባንድ ነጋዴዎች… በዚሁ አዋጅ አማካኝነት ‘ሽብርተኝነታቸው ተረጋግጦላቸዋል’ ወይም ‘ይረጋገጥባቸው ዘንድ ፍርዳቸውን እየጠበቁ ይገኛሉ።’ ለመሆኑ ይህ ከ14 ዓመት ህፃን[1]  እስከ 80 ዓመት አዛውንት[2]  በሽብርተኝነት ወንጀል ክስ የሚያስቀጣው፣ ይህ ከጉምቱ ምሁራን እስከ ገበሬዎች ድረስ የሚያስረው… ሕግ በተጨባጭ ስፋትና ጥበቱ ምን ያህል ይሆን? ለታሪካዊ ጥያቄዎች ያለው ምልከታስ?  በሀገሪቱ ስላለው የዲሞክራሲ ሁኔታስ (The state of Democracy) ምን ይነግረናል? ስለ ጨቅላው የኢትዮጵያ ፌደራሊዝምስ ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ተግባራዊነት አንፃር ምን ይታየናል? ወ.ዘ.ተ. የሚሉትን ጥያቄዎች መሰረት በማድረግ በመሬት ላይ ያሉ የሕጉ እውነታዎችን በመመርመር (Fact investigation) ምልከታዎቹን (Implications) በዚህ ፅሁፍ ለማየት ሞክረናል።
የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ
ዓለማቀፉ የፀረ-ሽብር ውጊያ (The Global War on Terror) በቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ቡሽ <We will not tire, we will not falter> ንግግር ከታወጀ ጀምሮ በተለያዩ በተለያዩ የዓለም ክፍሎች የሚገኙ ሀገሮች በሽብርተኝነት ዙሪያ ያላቸውን የሕግ ማዕቀፍ ለማሻሻል ጥረት ማድረግ ጀመሩ። ኢትዮጵያም የዓለማቀፉ የፀረ-ሽብር እንቅስቃሴ አካል መሆን አለብኝ በማለት እንዲሁም ሽብርተኝነት በኢትዮጵያ ላይ ግልፅ እና ድርስ አደጋ (clear and present danger) ደቅኗል በሚል መነሻ የፀረ-ሽብር ሕግ አርቅቃ ለፓርላማ አቀረበች።
ረቂቁ በቀረበበት ወቅት የተለያዩ  አካላት (የፓርላማ አባላት፣ የሰብአዊ መብት ተቋማት፣ ጋዜጠኞችና የጋዜጠኛ ማኅበራት ወ.ዘ.ተ.) ረቂቅ ሕጉ ሰፊ የሽብርተኝነት ድርጊት ትርጉም ይዟል፣ ‘ማወቅ ሲገባው’፣ ‘አድርገው ይረዱታል ተብሎ ሊገመት የሚችል መልዕክት’ የመሳሰሉት የሚሉ ለትርጉም ክፍት የሆኑ የወንጀል አይነቶችን አካቷል፣ ለፖሊስና ለደህንነት አካላት እጅግ የተለጠጠ ስልጣን ይሰጣል፣ እንደ የዋስትና መብት ያሉ የዜጎችን ሕገ-መንግስታዊ መብቶች ይነፍጋል፣ የሥነ ስርዓት እና የማስረጃ ሕጎችን በማቅለል ወንጀለኝነትን የማስረዳት ሸክምን ከዓቃቤ ሕግ ወደ ተጠርጣሪ ግለሰቦች ያሸጋግራል (shifting burden of proof) ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ትችቶችን ቢያቀርቡም፤ ‘እነዚህን የሕጉን ክፍተቶች የተለያዩ  የመንግስት አካላት ላልተገባ ጉዳይ ሊያውሏቸው ይችላሉ’፣ ‘ተቃውሞን እና የመናገር ነፃነትን ወደ ወንጀልነት ያሸጋግራል’ የሚሉ ስጋቶችን በጊዜው ቢያነሱም ሕጉ በፓርላማ ከመፅደቅ ያገደው ነገር አልነበረም።
በሕጉ ዙሪያ የሚቀርቡ ብዙና የተለያዩ  ትችቶች ቢኖሩም ከላይ ለመግለፅ እንደተሞከረው የዚህ ፅሁፍ ዓላማ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ በተጨባጭ የትኞቹን የሕብረተሰብ ክፍሎች እያጠቃ ነው? ስለ አጠቃላይ የሀገሪቱ ሁኔታስ ምን ያመለክተናል? የሚሉትን ጉዳዮችን መዳሰስን ዓላማ ያደረገ ነው።
(ማስታወሻ: – በዚህ ፅሁፍ ውስጥ የሚጠቀሱ ተከሳሾች በአሁኑ ወቅት በጊዜያዊ ቀጠሮ ወይም ክስ ተመስርቶባቸው በመደበኛ ቀጠሮ ላይ ያሉ ናቸው።)
የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አተገባበር
የፀረ- ሽብርተኝነት ሕጉ ከመውጣቱ በፊት እንዲሁም ከወጣ በኋላ የሚቀርቡበትን ትችቶች የመንግስት አካላት ምላሽ ሲሰጡበት: -
“ሕጉን ቃል በቃል የገለበጥነው ከAmerican Patriotic Act እንዲሁም ከእንግሊዙ የTerrorism Act ነው። እኛ ጋር ሲመጣ ለምን ትችት እንደሚቀርብበት ሊገባን አልቻለም።” የሚል ነው።  መንግስት እውን ቃል በቃል ገልብጦታልን? የሚለውን ጥያቄ ለመረዳት እንችል ዘንድ የአንዲት እንግሊዛዊት እና የአንድ አሜሪካዊ ታሪክን በማቅረብና በማነፃፀር ትግበራው ላይ ፍተሻ እናድርግ።
እንግሊዛዊቱ Kate Kaplan በዩኒቨርሲቲ ቆይታዋ Mathematicsን በMajorነት Computer Scienceን ደግሞ Minor በማድረግ ትምህርቷን የጨረሰች ስትሆን፤ በተለያዩ  መስሪያ ቤቶችም ከምረቃዋ በኋላ በስራ ዓለም ያሳለፈች ናት። በስራ ዓለምም በData Expertነት Specialize አድርጋለች። ከስራዋ ጎን ለጎን ደግሞ የተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም እንደርሷ ሁሉ ለሀገራቸው መሻሻል የሚተጉ ጓደኞችን ለማፍራት የቻለች ሲሆን፤ ከእነዚህ ወዳጆቿ ጋር በመሆንም በተለያዩ  ጉዳዮች ዙሪያ የምትጦምር ነች። ንባቧን እና ግንዛቤዋን ለማዳበር ይረዳት ዘንድም በተለያዩ  ርዕሶች ዙሪያ የተፃፉ ፅሁፎችን ከድረ-ገፆች ላይ በመገልበጥ ታነባለች። በIreland Republic ዙሪያ ጥያቄ ያለውን IRA የተባለ ፓርቲ ፕሮግራምም ለማንበብ Laptop ላይ ገልብጣ አስቀምጣለች። በዚህ ሁኔታ ላይ እያለች የእንግሊዝ የፀጥታ አካላት እርሷንና የማኅበራዊ ሚዲያ ጓደኞቿን ሰብስቦ  ያሰራቸው ሲሆን ‘የሽብርተኝነት ተግባራትን ሊፈፅሙ ሲሉ ያዝኳቸው’ በማለት ክስ መስርቶባቸዋል። የክሱ ማስረጃ ሁነው ከቀረቡ ሰነዶችም አንዱ Kate ግንዛቤ ለማግኘት በማሰብ ከድረ-ገፅ የገለበጠችው እና ማንም ሰው በድረ-ገፁ አድራሻ ገብቶ ሊያነበው የሚችለው የIRA የፖለቲካ ፕሮግራም ነው። Kateና ጓደኞቿም ፍርዳቸውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ። የእንግሊዝ Terrorism Act ደግሞ የተወነጀሉበት አዋጅ ነው።
በተመሳሳይ ሁኔታ Andrew Martin በአሜሪካው New York University የእንግሊዘኛ ቋንቋ መምህር ሲሆን ከስራው ጎን ለጎን ደግሞ የDemocratic Party የአመራር ክበብ ውስጥ ተሳትፎ አለው። ከፖለቲቻ ስራው ጋር በተያያዘም የተለያዩ  ሰነዶችን የሚያገላብጥ ሲሆን ከእነዚህ ሰነዶች አንዱ ደግሞ ስለ አሜሪካው Black Panters Party የሚገልፅ ሰነድ ነው። በስልጣን ላይ የነበረው የRepublican Party Andrewን ከሽብርተኛ ድርጅት ከሆነው Black Panters Party ጋር ግንኙነት አለው በማለት አሳስሮ የአምስት ዓመት ፍርድ ፈርዶበት በአሁን ሰዓት እስሩን እየገፋ ይገኛል። የRepublican መንግስት በአቶ Andrew ላይ ፍርድ የበየነበት የAmerican Patriotic Act አንቀፆችን በመጠቀም ነው።
እነዚህን ሁለት ጉዳዮች የጠቀስነው የኢትዮጵያ መንግስት የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉን ቃል በቃል ገለበጥኩባቸው የሚላቸው ሀገሮች አሜሪካና እንግሊዝ የሽብርተኝነት ክሶች እስከምን ድረስ ይደርሳሉ? የሚለውን ጉዳይ ለማየት ሳይሆን ሕጉ ቃል በቃል ተገለበጠ በተባለባቸው ሀገሮች የኢትዮጵያ መንግስት በአሁኑ ሰዓት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን እየተጠቀመበት ባለው አግባብ ቢጠቀሙ ምን ሊፈጠር እንደሚችል  ለማሳየት ሲባል፣ በአሁኑ ወቅት በሽብርተኝነት ወንጀል ተከሳ በቃሊቲ የምትገኘውን ጦማሪ ማህሌት ፋንታሁንን በKate Kaplan፣ እንዲሁም በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ተከሶ አምስት ዓመት ተፈርዶበት እስሩን እየገፋ የሚገኘው መምህር በቀለ ገርባን በAndrew Martin በመተካት ማህሌት እና በቀለ ላይ እየሆነ ያለው ነገር የኢትዮጵያ መንግስት ‘ምዕራባውያንም ተመሳሳይ የህግ ማዕቀፍ ነው ያላቸው’ በማለት እያቀረበው ያለውን ማስተባበያ ምን ያህል በአተገባበሩ የተሳሳተ እንደሆነ በቀላሉ ያሳያል።
 ጦማርያን እና ሰላማዊ ፖለቲከኞችን በመፃፋቸው እና ለሀገራቸው መልካም ነገርን በማሰብ ፖለቲካ ውስጥ የገቡ ግለሰቦችን የሚያስር – የሚከሰው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ በኢትዮጵያ ውስጥ ብቻ እንጂ በሌላ ዓለም ማግኘት ከባድ ነው። Kateና Andrew ‘ሽብርተኛ’ የሚባሉት በኢትዮጵያ እንጂ በአሜሪካ ወይም በእንግሊዝ ተመሳሳይ ሁኔታ ሊፈጠር አይችልም፡፡ ታዲያ ቃል በቃል ከምዕራቡ ዓለም የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጎች ‘የተገለበጠው’ የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዴት ቢሰራ ነው ሁሉንም የሕይወት መስመሮች ‘በሽብርተኝነት’ ሊፈርጅ የቻለው?
“የሽብርተኛ ፍለጋና ምርመራው ሂደት “
የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ በተግባር እንዴት ነው እየሰራ ያለው? የሚለውን ጥያቄ መመለሳችን ከላይ የጠየቅነውን ቀዳሚ ጥያቄ ይመልስልናል። እንዲህ በአጭር ምሳሌ እንመልከት:-
‘ሀሰን፣ ሀያት እና ከድር በፖሊስ (በደህንነት ኃይል) ከሽብርተኝነት ጋር የተገናኘ ወንጀል ሊፈፅሙ ሲሉ ተያዙ’ ተብለው ታሰሩ። አሰራሩ እንዲህ ይቀጥላል:-
  1. በብሔራዊ የመረጃና የደህንነት ኃይል በቁጥጥር ስር ይውላሉ። በተለያዩ  የደህንነት ‘እስር ቤቶች’ ላልተወሰነ ጊዜ (ከ6 ወር በላይ በደህንነት ቢሮ የቆዩ ሰዎች አሉ) ከከፍተኛ ድብደባ እና ስቃይ ጋር ይቆያሉ። በአብዛኛው ፍርድ ቤትም ሆነ ቤተሰብ ያሉበትን ሁኔታ አያውቅም።
  2. በደህንነት ‘እስር ቤቶች’ የነበራቸውን የፈተና (ordeal) ጊዜ ከጨረሱ በኋላ ለፌደራል ፖሊስ ተላልፈው ይሰጣሉ። የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) ‘ማረፊያ ቤት’ በማረፍም ‘የምርመራ’ ጊዜያቸውን ይጀምራሉ። የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ባለው ‘የፀረ-ሽብር ዲቪዚዮን’ አማካኝነት ባሉት ከ20 በላይ መርማሪዎችም ‘ምርመራው’ ይጀመራል። በዚህ የምርመራ ወቅትም እጅግ ኢሰብአዊ የሆኑ ድርጊቶች ይፈፀምባቸዋል። የተጠረጠሩበትን ‘የሽብርተኝነት ድርጊት’ እስኪያምኑ ድረስም መከራና ስቃያቸው ይቀጥላል። በዚህ ሁኔታ እስከ አራት ወራት ለሚቆይ ጊዜ ይቆያሉ (እስከ ስምንት ወራት በማዕከላዊ የቆዩ ሰዎች አሉ)።
  3. በአብዛኛው ‘የሽብርተኝነት ወንጀል ፋይሎች’ ላይ እንደሚታየው በነሀሰን፣ ሀያት እና ከድር ጉዳይ ላይም ፖሊሲ በቂ ማስረጃ ስለማይኖረው ‘ማስረጃ’ እዛው በወንጀል ምርመራ  ዘርፍ መርማሪዎች ይዘጋጃል። እንዴት?
ሀ. ድብደባና ስቃዩን በማጠናከር ከሶስቱ ተከሳሾች አንዱን (ለምሳሌ ከድርን) በጓደኞቹ በሀሰን እና በሀያት ላይ ምስክር እንዲሆን (Accomplice witness) በማስገደድ ፖሊስ የሰው ማስረጃ ይፈጥራል። ከድርም ከክሱ ይወጣል።
ለ. ፖሊስ የፈለገውን ቃል በመፃፉ ሀስን እና ሀያት እንዲፈርሙ ያስገድዳቸዋል። ቃላቸውንም ‘በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕግ አንቀፅ 27(2) መሰረት በነፃ የተሰጠ’ ይለያል።
ሐ. ምናልባትም ሀሰን እና ሀያት ‘ቃላችንን በድብደባ ያለፈቃዳችን ነው የሰጠነው’ በማለት በፍርድ ቤት በክሱ ሒደት ወቅት እንዳያስተባብሉት ፖሊስ ስጋት ካደረበት እዛው በወንጀል ምርመራ  ዘርፍ ማረፊያ ቤት (ማዕከላዊ) እያሉ ወደ ፍርድ ቤት በመውሰድ በወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ስርዓት ሕጉ አንቀፅ 35 መሰረት ‘አሸባሪነታቸውን’ አምነው ቃላቸውን እንዲሰጡ ያስደርጋል። በፍርድ ቤት የካዱ እንደሆነ ወደ ማረፊያ ቤት ሲመለሱ ሌሊቱን ሙሉ ከባድ ስቃይ ይጠብቃቸዋል።
መ. ካስፈለገም ‘የሀሰት ምስክሮችን ያሰለጥናል’፣ የወንጀል የሀሰት ሰነዶችን ያዘጋጃል። ወ.ዘ.ተ.
  1. ፖሊስ ‘ምርመራውን’ በዚህ መንገድ ካጠናቀቀ በኋላ ምርመራውን ለፍትህ ሚኒስትር ይልካል። የፍትህ ሚኒስትርም አስፈላጊውን ‘ፖለቲካዊ ግምገማ’ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ካደረገ በኋላ አራት አቃብያን ሕጎችን (አቶ ብርሃኑ ወንድማገኝ፣ አቶ ቴዎድሮስ ጌታቸው፣ አቶ ዘውዱ በቀለንና አቶ ሰውበሰው አድማሱን) ላቀፈው የፀረ-ሽብርተኝነት case team ያስተላልፋል። አቃብያነ ሕጎቹም የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ላይ ከተደነገጉት አስር (10) ወንጀሎች በአንዱ ወይም ከዛ በላይ ክስ ያቀርባሉ።
  2. በመጨረሻም የሀሰንና የሀያት ጉዳይ ወደ ፍርድ ቤት ይቀርባል። አቃቤ ሕግ ከድርን የሰው ማስረጃ አድርጎ  ያቀርባል። የሀሰንና የሀያትን ለፖሊስ ወይም ለስር ፍርድቤት ተገደው የሰጡትን የተከሳሽነት ቃል በሰነድ ማስረጃነት ያቀርባል። የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 4ኛ እና 19ኛ ወንጀል ችሎቶች ካሏቸው ዳኞች[4] ሶስቱ በጉዳዩ  ላይ ይሰየሙና ፍርድ ይሰጣሉ። ከድር ምስክር በመሆን ነፃ ይወጣል። ሀሰንና ሀያት ደግሞ ‘አሸባሪነታቸው’ ተረጋግጦባቸው ይፈረድባቸዋል። (በነገራችን ላይ አሁን ባለው አሰራር የፍርድ ሂደቱ ከሁለት ዓመት በላይ ጊዜ ሊወስድ ይችላል)
ይህ ‘የሁሉም’ ለማለት በሚያስደፍር መልኩ በፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ መሰረት የተከሰሱ ሰዎች ጉዳይ አካሄድ ነው። በዚህም መንገድ ዜጎች ከማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ ገለል እንዲሉ ይደረጋሉ። ምክንያቱም እነሱ ‘ኢትዮጵያዊ አሸባሪዎች’ ናቸውና። የእነዚህን ኢትዮጵያውያን አሸባሪዎች ማንነት ማወቃችን የሽብርተኝነት ትግሉን ምንነት እና የሀገሪቱን ጉዞ በጉልህ ያሳየናልና እስኪ ፍተሻ እናድርግ።
‘መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ፌደራሊዝም’
 “ደርግ በወደቀበት ሰዓት በሀገሪቱ አስራ ሰባት (17) የሚሆኑ የታጠቁ ሀይላት ነበሩ። ይህም ዜጎች በደርግ ስርዓት የተከፉ ምን ያህል ወገኖች እንደነበሩ አመላካች ነው።” በማለት ኢህአዴግ ስልጣኑን ከደርግ በተረከበበት ወቅት የነበረውን ሁኔታ በተደጋጋሚ ያስረዳል።
ኢህአዴግ አያይዞም የተለያዩ  ቡድኖችን መከፋትና ብሶት ለመቀነስና እስከ መጨረሻውም ለማስወገድ የፌደራል ስርዓት እንዲዘረጋ፤ ይህ የፌደራል ስርዓትም ‘ሀገሪቱን እንደ ዩጎዝላቪያ ከመሆን የታደጋት ፍቱን መድኃኒት’ እንደሆነ ይገልፃል።
ደርግም ከወደቀ ሩብ ምዕተ ዓመት እየሆነው ነው፤ የኢትዮጵያም የፌደራል ስርዓት ሀያኛ ዓመቱን ይዟል። እውን ከላይ የተጠቀሱት እውነታዎች ምን ያህል መሻሻል አሳይተዋል? የፌደራል ስርአቱስ ከቃላት ባለፈ ምን ያህል እውነተኛ ለውጥ አምጥቷል?  የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን እና ሕጉ ተግባራዊ የሆነባቸውን ቡድኖች ማንነት ማየቱ ለጥያቄዎቻችን መልስ ለመስጠት  ይሆናልና እስኪ እንመልከት።
በአሁኑ ወቅት ገዥውን ስርዓት ለመገዳደር በማሰብ ‘ፋኖነትን’ የመረጡ ቡድኖች የደርግ ጨካኝና አምባገነን ስርዓት ሲወድቅ ከነበሩት የታጠቁ ሀይሎች ቢበልጡ እንጂ አያንሱም። የአሁኖቹን ታጣቂዎች ከደርግ ወቅቶቹ የሚለያቸው፣ የአሁኖቹ ‘በአሸባሪነት’ የተፈረጁ መሆናቸውን ነው።
ይህ ፅሁፍ በተፃፈበት ወቅት ክስ ተመስርቶባቸው በቀጠሮ ላይ የሚገኙ አስር የተለያዩ  የክስ መዝገቦችን ብናይ መልሳችን ግልፅ ይሆንልናል።
“የጋምቤላ ክልል አሁን ባለው የፌደራል ስርዓት ምንም ዓይነት ጥቅም እያገኘ አይደለም። ለዚህም መፍትሄው ስርዓቱን በኃይል ማስወገድ ነው።” በሚል መነሻ አምስት (5) የተለያዩ  ቡድኖች መሳሪያ አንስተዋል። ከነዚህም አምስት (5) ፓርቲዎች መካከልም በአቶ ሙድ ጎይባሬ የሚመራው የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) ጋር በተገናኘ 11 ሰዎች ማለትም
  1. ኡቺሚ አፐይ ኡቻላ
  2. ኡማን ኡድሉቻም
  3. ኡቻን ኡድላ ኦፒዮ
  4. ኡመድ ኡጁሉ ኡማን
  5. ኝበዲ ኡባንግ ኡጃቶ
  6. ኦፒዮ ቹር ኡባንግ
  7. ኡመድ ኡቶ ኡማን
  8. ኡፐዶካ ኡቱን ኝግየው
  9. ታደሰ ኡዱጊ ቲፋ
  10. ኡማን ኡካይ ኡኩችና
  11. ኦኬሎ ኡበር ኡቻን
በፌ/ዓ/ህ/መ/ቁ 322/06 በቀን 18/07/06 በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 3 (1, 2 እና 3) መሰረት ክስ ተመስርቶባቸዋል፤ ጋህነንም የሽብርተኛ ድርጅት እንደሆነ በክሱ ተመልክቷል። ከጋምቤላ ሳንወጣ አሁን በቅርቡ ደግሞ በቀድሞው የጋምቤላ ክልል ፕሬዝዳንት በአቶ ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ እንደሚመራ በክሱ ከተመለከተው የጋምቤላ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ጋዴን) አባላት ናችሁ ተብለው የተከሰሱ ሰባት ግለሰቦችን እናገኛለን። እነርሱም
  1. ኦኬሎ አኳይ ኡቻላ
  2. ዴቪድ ኡጅሉ ኡባንግ
  3. ኡቻን ኦፒዮ ኡሞድ
  4. ኡማን ኝክየው ኡድሉ
  5. ኡጅሉ ቻሞ ኡኮይ
  6. ኦታካ ኡዋር ኡጋላና
  7. ኡባንግ ኡመድ አቦላ ናቸው።
በቀን 04/10/2006 ዓ.ም. በፌ/አ/ህ/መ/ቁ 508/06 በቀረበባቸው በዚህ ክስ ጋዴን የሽብርተኛ ድርጅት እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ክሱም በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 4 ላይ የተዘረዘሩትን ተግባራት በመተላለፍ እንደሆነ ተገልጿል።
እስኪ ወደ ሌላ ክልል እንለፍ። በኮለኔል አለበል አማረ እንደሚመራ የሚነገርለትን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሀይሎች ህብረትን (አዴሀህ) እናገኛለን። የፌደራል አቃቢ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 071/06 በቀን 28/12/05 ባቀረበው ክስ ‘ግንቦት ሰባት ከተባለ አሸባሪ ድርጅት ጋር ግንኙነት ፈጥሮ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ኦዴሀህ የተባለ ‘ሽብርተኛ ድርጅት’ ጋር አባል በመሆን ሲንቀሳቀሱ ያዝኳቸው’ ያላቸውን 10 ሰዎች በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 7(1) መሰረት ከሶ እናገኛለን። ግለሰቦቹም
  1. ማስረሻ ታፈረ ወ/ገብርኤል
  2. ሻለቃ አለምነው አየለ ነጋሽ
  3. ብርቁ አዲሱ ውቡ
  4. ታደሰ መንግስቱ በላይ
  5. የፀዳው ካሴ አሉላ
  6. አወቀ ደስታው ምህረቴ
  7. መሀመድ ግዛቸው ፋንታው
  8. ቴዎድሮስ ሀይሌ
  9. ታደሰ በለጠ
  10. ታደሰ ባዩ  ገበየሁ ናቸው።
ወደ ኦሮሚያ ክልል ተጉዘናል። ባለፉት 20 ዓመታት የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) አባላት ናችሁ በሚል እጅግ በጣም ብዙ ኦሮሞዎች ታስረዋል፣ ተሰደዋል ወይም ተገድለዋል። ይህ ሁኔታ አሁንም በሰፊው ቀጥሏል። የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ክሱ ‘ራሱን ኦነግ ብሎ ከሚጠራው ‘ፀረ-ሰላም’ ሀይል ውስጥ አባል በመሆን…’ ከሚለው የተለመደ የክስ ቃል  በተለየ መንገድ ‘ራሱን ኦነግ ብሎ ከሚጠራው ‘አሸባሪ’ ድርጅት ውስጥ አባል በመሆን…’ ወደሚል መቀየሩ ብቻ ነው። ምስጋና ለፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ይሁንና። ለዚህም ጥሩ ማሳያ ይሆኑን ዘንድ ሁለት የአቃቢ ሕግ መዝገቦችን እንጠቅሳለን።
በ22/07/2006 ዓ.ም. በፌ/ዓ/ሕግ/መ/ቁ 376/06 በመሰረተው ክስ
  1. ደልዴሳ ዋቆ ጃርሶ
  2. ገልገሎ ጉዮ ቦሩ
  3. ዋርዮ ጣጤሳ ጉዮ
የተባሉ ግለሰቦች የኦነግ አባል በመሆን ‘የሽብርተኝነት ድርጊቶችን’ ሲፈፅሙ ይዣቸዋለሁ’ በማለት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን አንቀፅ 3(1 እና 2) እንዲሁም አንቀፅ 7(1) በመጥቀስ ክስ መስርቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ የፌደራል ዓቃቢ ሕግ በቀን 11/2006 ባቀረበው ‘የሽብር ወንጀል’ ክስ የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የነበሩት
  1. አብዲ ከማል የሱፍና
  2. ቶፊቅ ረሽድ ዩያ
‘የአሸባሪው’ ድርጅት የኦነግ አባላት በመሆን የሽብር ተግባራትን ልትፈፅሙ ስትሉ ተይዛችኋል’ ተብለው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 7(1) ተጠቅሶባቸው ክሳቸውን በማረፊያ ቤት ሆነው እየተከታተሉ ይገኛሉ። በ2006 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል በነበረው አለመረጋጋት ምክንያት ከተለያዩ  የክልሉ ዩኒቨርስቲዎች (ከሀሮማያ፣ ከጅማ፣ ከወለጋ… ዩኒቨርስቲዎች) የተያዙ ተማሪዎች እንዲሁም ከተለያዩ  የክልሉ አካባቢዎች (ከወለጋ፣ ከሞያሌ ወ.ዘ.ተ.)ተይዘው የታሰሩ ዜጎች በኦነግነት ተጠርጥረው በፌደራል የወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) የሚገኙ ሲሆን ይህ ፅሁፍ እስከተፃፈበት ቀን ድረስም ክስ ሳይመሰረትባቸው ከአራት ወራት ለሚበልጥ ጊዜ በወንጀል ምርመራ ዘርፍ ‘ማረፊያ ቤት’ ውስጥ ይገኛሉ።
በድጋሚ ወደ ሀገሪቱ የምዕራብ ጫፍ እንጓዝ፤ ‘አሸባሪው’ ቤሕነንን እናገኛለን – የቤንሻንጉል ሕዝቦች ነፃነት ንቅናቄ። በአቶ አብዱል ወሀብ መሀዲ  የሚመራው ቤሕነን “የክልሉ ነዋሪዎች ኢህአዴግ ከዘረጋው ስርዓት ተጠቃሚ ሊሆኑ አልቻሉም። መፍትሔውም ስርዓትቱን በሀይል ማስወገድ ነው።” በሚል መነሻ ነፍጥ ያነገበ ፓርቲ ነው። በፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ‘የሽብርተኛ ድርጅት’ ከመባል ግን አልተረፈም። የፌደራል አቃቢ ሕግ በ19/12/2006 ዓ.ም. ባቀረበው ክስ
  1. አብዱልከሪም አብዱሰመድ አብዱልቃድር
  2. ሀዎጃ ሚነሳ አጉር
  3. ኢላቅ ኢብራሒም ዓሊ (ዕድሜ 17)
  4. አዴላ ጃባለ ንምር
  5. አብዲ ሀሚዝ ፈረንሳ
  6. ፋተልሙላ አጣሂር አከሶ
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀፅ 7(1) በመጥቀስ ከላይ የተዘረዘሩትን ስድስት ግለሰቦች ‘የአሸባሪው የቤሕነን አባል ናችሁ በማለት ክስ አቅርቦባቸዋል።
ሰሜን ኢትዮጵያ ጫፉ ላይ ነን። በስልጣን ላይ የሚገኘው ‘ኢህአዴግ’ ትግሉን የጀመረበት የትግራይ ክልል ውስጥ። ‘ገዢው ስርዓት ለትግራይ ሕዝብ አመጣልሃለሁ ያለውን ዴሞክራሲና ፍትህ ማምጣት አልቻለምና ስልጣን በቃው’ በማለት የተነሳው ዴሞክራሲያዊ ሕዝቢ ምንቅሳቀስ ትግራይ (ዴሕምት) ደግሞ ከትግራይ ክልል የተገኘው ‘አሸባሪ’ ድርጅት ነው። የፌደራል ዓቃቢ ሕግ በ
  1. ብሎፅ ገ/ፃድቃን
  2. ነጋሌ ብርሃኑ
  3. ሹማይ ተበጀ
ላይ ባቀረበው ክስ ‘የአሸባሪው’ ዴሕምት አባል በመሆን የተለያዩ  የሽብር ተግባራትን ሊፈፅሙ ሲሉ ይዣቸዋለሁ በማለት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን አንቀፅ 7(1) በመጥቀስ ክስ መስርቶባቸዋል።
በዘጠኙም የፌደራል ክልሎች ‘አሸባሪ’ ድርጅቶችን መፈለጋችንን ቀጥለናል፤ ማረፊያችንም ኦጋዴንያ ሆኗል። የኢትዮጵያ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 25 መሰረት በሽብርተኛ ድርጅትነት ከሰየማቸው 5 ድርጅቶች ውስጥ ላለፉት ሶስት አስርት ዓመታት ኦጋዴንን ነፃ ለማውጣት እየታገለ የሚገኘው የኦጋዴን ብሔራዊ ነፃነት ግንባር (ኦብነግ) አንዱ ሲሆን፤ የፌደራል አቃቢ ሕግም በየጊዜው ‘የአሸባሪው’ የኦብነግ አባላት ናችሁ በማለት እጅግ ብዙ ክሶችን በኦጋዴን ተወላጆች ላይ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን በመጥቀስ ክስ አቅርቦ ‘ፍርዳቸውን’ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉ።
እስኪ በዓላማ ደረጃ ብሄር ተኮር ከሆኑት ‘የሽብርተኛ ድርጅቶች’ ሕብረ ብሔራዊ ኢትዮጵያ ‘የሽብርተኛ ድርጅቶች’ እንለፍ።
የግንቦት ሰባት ንቅናቄ “በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የሰላማዊ መታገያ መንገዶችን በሙሉ  ስላፈናቸው፤ ‘በማንኛውም አይነት’ የመታገያ መንገዶች ትግል እናደርጋለን።” በማለት አቋሙን ካላወቀ በኋላ ‘ይሔማ ዋና አሸባሪ ድርጅት ነው’ በማለት በመንግስት ከተሰየመ ወዲህ ትልልቅ የፖለቲካ ስብዕናዎችን ጨምሮ  ብዙ ግለሰቦች ከዚህ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል ‘የሽብርተኝነት ድርጊቶችን’ ለመፈፀም በማቀድ፣ ማሴር፣ መሰጋጀትና ማነሳሳት ወንጀሎች ተከሰው ወደ እስር ቤት ወርደዋል፤ ወይም በሌሉበት ተፈርዶባቸዋል። ይሔው ጉዳይ ቀጥሎ ይሕ ፅሁፍ በተፃፈበት ወቅት እንኳን በፌደራል ዓቃቢ ሕግ በ13/12/05 በቀረበ ክስ
  1. ዘመኑ ካሴ በእውቄ
  2. አሸናፊ አካሉ አበራ
  3. ደህናሁን ቤዛ ስመኝ
  4. ምንዳዬ ጥላሁን ለማ
  5. አንሙት የኔዋስ አለኸኝ
  6. ደሳለኝ አሰፋ ወንድማገኝ
  7. ም/ኢ/ር ሙልየ ማናየ ረታ
  8. ጠጋው ካሳ እንየው
  9. ይህዓለም አካሉ አበራ
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 4,  5 እና 8 ተጠቅሶባቸው ‘በአሸባሪነት’ ተከሰው ፍርድ እየተጠባበቁ ይገኛሉ።
የኢትዮጵያ ሕዝብ አርበኞች ግንባር (ኢሕአግ) ወደተባለ ‘የሽብርተኛ ድርጅት’ አልፈናል። በክስ ሒደር ላይ የሚገኙ ሁለት መዝገቦችንም እናገኛለን። የመጀመሪያው በፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 033/06 በቀን 28/12/05 በ
  1. ፀጋው አለሙ ተካ
  2. ዋሲሁን ንጉሱ ገብሬ
  3. ጎዳዳው ፈረደ ማሞ
  4. ማማይ ታከለ በየነና
  5. ተገኝ ሲሳይ መንገሻ
ላይ የቀረበ ‘የአሸባሪው’ ኢሕአግ አባል የመሆን ክስ ሲሆን፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የፌደራል ዓቃቢ ሕግ በክስ መዝገብ ቁጥር 174/06 በ02/11/06 ባቀረበው ክስ
  1. አስማማው ደሴ ጣሰው
  2. መብራታይ ይርጋ ተስፋዬ
ላይ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀፅ 7(1) በመጥቀስ ‘በሽብርተኝነት’ ክስ አቅርቧል።
በ1987 ዓ.ም. የፀደቀው የኢትዮጵያ ሕገ-መንግስት የሀገሪቱን የአስተዳደር ስርዓት ከአሀዳዊ (Unitary) ወደ ፌደራል መንግስ ሲቀይር እንደ ምክንያት የጠቀሰው ዋነኛ ነገር ለታሪካዊ ጥያቄዎች መልስ መስጠትን፣ በአለፉ ስርዓቶች የተከፉ የተለያዩ  ወገኖችን የከፊል ራስ ገዝነት (Semi-Autonomous) የሆነ ስልጣን በመስጠት ‘ቁስላቸውን መሻር’ ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ሀሳቦችን ሲሆን ለእነዚህ ሀሳቦች መፈፀምም በዘጠኝ ክልሎች የተዋቀረ እና በዋናነት ዘውግን መሰረት ያደረገ የፌደራል ስርዓትን ዘርግቷል።
ገዥው ፓርቲ “ሕገ-መንግስቱ የፌደራል ስርዓት በመዘርጋት ጭቆናን ታሪክ አድርጓል፤ የብሔሮችን ጥያቄም ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መልሷል።” በማለት በተደጋጋሚ ቢገልፅም ከላይ ባየናቸው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የመሬት እውነታዎች በኢትዮጵያ ውስጥ ካሉት ዘጠኝ ክልሎች በስድስቱ ውስጥ ማለትም፥ በኦሮሚያ፣ በአማራ፣ በሶማሌ፣ በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝና በጋምቤላ ክልሎች በብሔር ደረጃ የተቋቋሙ ‘ነፃ አውጪዎች’ በአሸባሪነት ተሰይመውና ተፈርጀው አይተናል።
በፌደራል ስርዓቱ ከተቋቋሙት ክልሎች 2/3ኛዎቹ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መከፋታቸውን የሚገልፁ  ታጣቂ ሀይሎች ያሏቸው ሲሆን በጣም የሚያሳስበው ደግሞ እነዚህ ሀይሎች ‘በአሸባሪነት’ የተፈረጁ መሆናቸው ነው። ታዲያ የኢትዮጵያ የፌደራል ስርዓት አልከሸፈምን? መሳሪያ አነሳ የተባለን ፓርቲ ሁሉ ‘የሽብርተኛ ድርጅት’ እያሉ መፈረጁስ ተገቢ ነውን? አሁን በስልጣን ላይ ያለው ቡድን ስልጣን የጨበጠው በመሳሪያ ነውና፣ የደርግ ስርዓት አሁን ያለው አይነት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ ኖሮት ቢሆን ኢህአዴግ ‘አሸባሪ ድርጅት’ መባሉ እውን ነበር። በዚህ ሂደት ገዢው ቡድን ከቀጠለ ‘ደርግ በወደቀበት ወቅት 17 የታጠቁ ሀይላት ነበሩ’ እንደሚባለው ኢህአዴግ ከስልጣን በሚወርድበት ወቅትስ ስንት ‘የሽብርተኛ ድርጅቶች’ ይኖሩ ይሆን?
ዞን9 ይህንን ጽሁፍ ለማጠናከር የተጠቀምንበትን ከላይ ያለውን መረጃ አንኳን ብንወስድ ዘጠኝ የተለያዩ ቡድኖች ነፍጥ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ሲሆን በዚህ አጭር ጽሁፍ ውስጥ በሂደት ላይ ያሉ የክስ ሂደቶች ቁጥር እንኳን 58 ተከሳሾችን ማየት ይቻላል፡፡ እነዚህ እኛ ማስረጃውን ማግኘት ያልቻልንባቸውን የክስ ሂደቶች እና ቀድሞ የተቀጡ ያለቁ ፋይሎችን እና ክልል ላይ የተደረጉ “የፍርድ ሂደቶቸን” አይጨምሩም፡፡
(ማስታወሻ:  – በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር የተጠቀምንባቸው 10 የሽብርተኝነት ክሶች በሙሉ ከነሀሴ 2005 እስከ ነሀሴ 2006 ዓ.ም. ድረስ ባለው የአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ብቻ በፌደራል አቃቢ ሕግ የቀረቡ ሲሆኑ፣ ይህ ፅሁፍ በተፃፈበት ወቅትም ሁሉም መዝገቦች በቀጠሮ  ላይ የሚገኙ ናቸው። )
‘It’s IslamoPhobic’?
ዓለማቀፉ የፀረ-ሽብርተኝነት ትግል ትኩረቱን በዋነኛነት የሙስሊሙ ዓለም ላይ ማድረጉ በተችዎች ዘንድ ‘የፀረ-ሽብርተኝነት ትግል ሳይሆን የተያዘው ኢስላምጠልነት (Islamophocia) ነው’ እስከመባል ደርሷል። ኢትዮጵያም የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ስታፀድቅ በገዥው ስርዓት የተሰጠው ምክንያት “የፀረ-ሽብርተኝነት ትግላችንን ለማሳደግ ያስችለን ዘንድ የህግ ማዕቀፋችን ማሳደግ አለብን፤ ይሔም ከዓለማቀፉ እውነታ ጋር ለመራመድ ያስችለናል።” የሚል ነው።
ታዲያ የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ በውጤቱ እንዴት ሆነ? ብለን ተጨባጭ ምሳሌዎችን እያነሳን መመልከቱ ጉዳዩን ግልፅ ሳያደርገው አይቀርምና እስኪ እንመልከት።
የኢትዮጵያ ሙስሊም ኢስላምን (Ummah) ከኢትዮጵያዊነት ጋር አንድ ላይ ይዞ በሀገሩ ለመኖር ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ ትግል አድርጓል፡ ‘የአሞራ ቤቱ ከዋርካ፣ የኢስላም ሀገሩ መካ’ ልባል አይገባኝም’ በማለት ለመብቱ መከበር ብዙ ደክሟል። ኢህአዴግ ስልጣን ላይ በወጣበት ወቅትም በብዙሀን ዘንድ የመብት መከበር ጉዳይ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ይፈታል የሚል ተስፋ ተሰንቆም ነበር። ኢትዮጵያ በሕገ-መንግስቷ የሁሉንም ሀይማኖቶች እኩልነት በማወጅ፣ መንግስት በሀይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ አይገባም ብላ በመደንገግ የተሰነቀውን ተስፋ አለመለመችው። በተግባር ደረጃ ግን ከተለያየ የሀይማኖት ሰዎች ዘንድ መንግስት በሀይማኖታዊ ጉዳዮች ላይ ጣልቃ እየገባ ነው፣ እጁን ከሀይማኖታችን ላይ ያንሳልን። ወ.ዘ.ተ. የሚሉ ጥያቄዎች በየጊዜው እየተነሱና በመንግስት አካላት እየታፈኑ ዘልቀዋል።
የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ሁኔታ በዚህ ጥያቄ በመጠየቅ እና በመንግስት አካላት ጥያቄዎችን በመደፍጠጥ ነገሮች ሲመላለሱ ከቆዩ በኋላ ሙስሊሙ ሕብረተሰብ መሰረታዊ ጥያቄዎቹን በመወከሉት ልጆቹ አማካኝነት በተደራጀ እና ሰላማዊ በሆነ መንገድ ከጥር 2004 ዓ.ም. ጀምሮ  አቀረበ። እነዚህ ወኪሎችም መንግስት ለጥቂት ጊዜም ቢሆን መፍትሄ ለማግኘት ጥያቄያቸውን ይዘው ከመንግሰት አካላት ጋር ሲደራደሩ ቆዩ፡፡
በአጋጣሚ ሆኖ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ጥቅም ላይ በሰፊው መዋል በጀመረበት ወቅት ላይ ነበርና ‘የሙስሊሙ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ’ የሙስሊሙን ጥያቄዎች ለተለያዩ  አካላላት በሰላማዊ መንገድ ያቀረበው። እንግዲህ ከዛን ጊዜ ወዲህ ነው የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ በኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ላይ መበርታት የጀመረው።
ሕጉ ጥቃቱን የጀመረው የፌ/ዓ/ሕግ በክስ መዝገብ ቁጥር 122/05 በ19/02/2005 ዓ.ም.
  1. አቡበከር አህመድ ሙሐመድ
  2. አህመዲን ጀበል
  3. መከተ ሙሄ መኮንን
  4. ካሚል ሸምሱ ሲራጅ
  5. በድሩ ሁሴን ኑርሁሴን
  6. ያሲን ኑሩ ኢሳ
  7. ሳቢር ይርጉ ማንደፍሮ
  8. መሀመድ አባተ ተሰማ
  9. አህመድ ሙስጠፋ ሀቢብ
  10. ሙራድ ሽኩር ጀማል
  11. አቡበከር አለሙ ሙሔ
  12. ኑሩ ቱርኪ ኑሩ
  13. ባህሩ ዑመር ሽኩር
  14. ሙኒር ሁሴን ሀሰን
  15. ሰዒድ አሉ ጀውሀር
  16. ዩሱፍ ጌታቸው
  17. ሙባረክ አደም ጌቱ
  18. ካሊድ ኢብራሒም ባልቻ
  19. አብዱረዛቅ አክመል ሀሰን
  20. አሊ መኪ በድሩና
  21. አብሩራህማን ኡስማን ከሊል
ላይ የፀረ-ሽብር ሕጉን አንቀፅ 3 (1, 2, 4 እና 6) እና አንቀፅ 4 ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ በማለት ክስ ባቀረበበት ወቅት ሲሆን በክሱም ‘የሙስሊሞች የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ’ የተባለ ‘የሽብርተኛ ድርጅት’ በመመስረት’ በማለት ‘ኮሚቴውን’ ‘የሽብርተኛ ድርጅት’ በማለት ሰይሞ ሌሎች ሙስሊም ጋዜጠኖችንና የሀይማኖት ሰዎች ‘የሽብርተኛ ድርጅቱ’ አካላት በማድረግ ክስ አቅርቦ በሒደት ላይ ይገኛል።
በጣም አስደንጋጡ እና አሳዛኙ ጉዳይ ደግሞ ህዝበ ሙስሊሙ በሰፊ ድጋፍ ይወክሉኛል በማለት የመረጣቸውን ሰዎች ‘አሸባሪ’ በማለት የመሰረቱትን ኮሚቴ ደግሞ ‘የሽብር ድርጅት’ ከማለት ባለፈ በአጠቃላይ ሙስሊሙ እያደረገ ያለውን ሰላማዊና በአፍሪካ የሰላማዊ ትግል እንቅስቃሴዎች ትልቅ ስኬት እና አብነት እንደሆነ Rene Lefortን ጨምሮ ታላላቅ ምሁራን እየገለፁት ያሉትን እንቅስቃሴ በመንግስት አካላት ከአለማቀፉ የሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ለማገናኘት እየተደረገ ያለው ሙከራ፣ ሙስሊሙን የኢትዮጵያዊነት ጠላት አድርጎ የመሳል ሁኔታ (ባንዲራ አቃጠለ ወ.ዘ.ተ. እያሉ)… ወ.ዘ.ተ. መኖሩ ነው። የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችን በቀጥታ እያጠቃ ነው ብለን ለመደምደም ‘የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ’ አባላት መታሰር ብቻ በቂ ሊሆን አይችልምና ተጨማሪ ማስረጃዎችን መፈለግ ያሻል። ስለዚህም እነሆ: -
የፌደራል ዓቃቢ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 225/06 በ25/09/06 ዓ.ም. ባቀረበው ‘የሽብርተኝነት’ ወንጀል ክስ ‘የሙስሊሙ መፍትሔ አፈላላጊ ከተባለ የሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አላችሁ’ በማለት
  1. ኤልያስ ከድር ሽኩር
  2. ሙባረክ ከድር ሀሰን
  3. ቶፊቅ መሀመድ ዑመር
  4. ፈይሰል አርጋው ኡመር
  5. አብዱልመጅድ አብዱልከሪም
  6. እስማኤል ሙስጠፋ ሀሰን
  7. ሬድዋን አብደላ አህመድ
  8. አንዋር ሱልጣን መሀመድ
  9. አብዱላዚዝ ፋቱደን በድሩደን
  10. ዳፋር ደጋ ሀሰን
  11. ፋሩቅ ሰዒድ አብዶ
  12. መሪማ ሀያቱ ዑመር
  13. መሀመድ ዓሊ ሀሰን
  14. መሀመድ አይለየን ገማ
  15. አቡበክር ሰልማን ሙላና
  16. ሙዓዝ ሙደስር አወል
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 7(1) ተጠቅሶባቸው ክሳቸውን በእስር ሆነው እየተከታተሉ ይገኛሉ።
በተመሳሳይ በየ/ፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 216/06 በተከፈተ ሌላ ክስ
  1. አብዱልአዚዝ ጀማል አብዱ
  2. ጅብሪል ይመር አበጋዝ
  3. ስዑድ ሙሳ ሁሴን
  4. ሀያት አህመድ ረዲ
  5. ሳላሀዲን ሙሀመድ አህመድ
የተባሉ ግለሰቦችም የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ አንቀፅ 7(1) ተላልፈዋል፤ ‘ራሱን የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ በማለት ከሰየመው የሽብርተኛ ድርጅት ጋርም ግንኙነት አላቸው’ በማለት ተመልክቷል።
በዚህ ብቻ አያበቃም። የፌደራል ዓቃቢ ሕግ በመዝገብ ቁጥር 164/06 ባቀረበው ‘የሽብርተኝነት ድርጊት ወንጀል’ ክስ ደግሞ
  1. አህመድ ኢድሪስ ገበየሁ
  2. አንዋር ኡመር ሰዒድ
  3. ሷሊህ መሀመድ አብዱ
  4. አደም አራጋው አህመድ
  5. አብዱራህማን እሸቱ መሀመድ
  6. ኢብራሒም ሙሔ ይማም
  7. ዑመር ሁሴን አህመድ
  8. ይመር ሁሴን ሞላ
  9. ሙባረክ ይመር አየለ
  10. እስማኤል ሀሰን ይመር
  11. ከማል ሁሴን አህመድ
  12. አብዱ ሀሰን መሀመድ
  13. አህመድ ጀማል ሰይድ
  14. ሙሀመድ ዩሱፍ መሀመድ
ላይ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁን አንቀፅ 3(1)፣ (6) እና (7) በመጥቀስ የአሸባሪነት ክሶችን አቅርቦባቸዋል።
በአጠቃላይ በአሁኑ ወቅት ሙስሊም ሆኖ መታሰር የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን አንቀፆች የሚያስጠቅስ እስኪመስል ድረስ ሕጉ የሙስሊሙን ሕይወት አክብዶታል። የታሪካዊ ጭቆናዎች ሰለባ የነበረው ኢትዮጵያዊ ሙስሊም አሁን ደግሞ ‘የሽብር ምህዳሩን’ አጣቦት ይገኛል። የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ተግባራዊነት እና ሰለባ እያደረጋቸው ያሉት የኅብረተሰብ ክፍሎች ስንመለከት ‘ሕጉ ኢስላም ጠል (Islamo-Phobic) ነው’ እንድንል ያደፋፍረናል። አሁን ለዚህ ጽሁፍ ማጣቀሻነት ሲባል የተጠቀምንባቸውን የክስ ፋይሎች ስንመለከት አንኳን 48 ሙስሊሞች በተለያየ የክስ ፋይል ተከሰው እናገኛለን፡፡
(ማስታወሻ: ሁሉም በዚህ ንዑስ ርዕስ ስር የተጠቀሱ የክስ መዝገቦች በቀጠሮ  ላይ ያሉና የመጨረሻ ፍርድ ያላገኙ መሆናቸውን ልብ ይሏል።)
ዴሞክራሲን ‘ያንበረከከው’ ሕግ 
 ኢህአዴግ ስልጣን በያዘባቸው የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ሲወደስባቸው ከነበሩት ተግባራት ዋነኞቹ ነፃ ተቋማትና የፖለቲካ ፓርቲዎች በነፃነት ይንቀሳቀሱ ዘንድ ፈቃድ መስጠቱ እና ለነፃ የፕሬስ ተቋማት እውቅና መስጠቱ የሚጠቀሱ ናቸው። በሒደት በተለይም ምርጫ 97ን ተከትሎ ግን ገዢው ፓርቲ ነፃ ተቋማትን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎችንና የግል ፕሬሱን በመያዶች ሕግ፣ በፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ እንዲሁም የፕሬስ አዋጅ በማውጣት ገዢው ፓርቲ የተወደሰባቸውን ተግባራት አንድ ባንድ መደፍጠጥ ጀመረ። ከሁሉም አስከፊውና ሁሉንም ከመንግስት መዋቅር ውጭ ያሉ ተቋማትን በአንድ ላይ ዝም ያስባለው እና ትንሽ እንቅስቃሴ በታየ ቁጥር ብቅ  ያለ ወደ እስር የሚወረውረው በ2001 ዓ.ም. የወጣው የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጅ ነው።
በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ ትግል ለማድረግ የወሰኑ ግለሰቦች ‘ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አድርጋችኋል’ በሚል ምክንያት (pretext) የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የተመዘዘባቸው እና እስከ እድሜ ልክ እስራት የተፈረደባቸው እንደ አንዷለም አራጌ እና በቀለ ገርባ ያሉ ግለሰቦች በፊተኛው ረድፍ እናገኛለን። የጋዜጠኝነት የሙያ ግዴታቸውን እየተወጡ እያሉ በመሀሉ ‘አሸባሪዎች’ ናችሁ ተብለው በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የተወነጀሉትን እንደ እስክንድር ነጋ፣ ርዕዮት ዓለሙ እና ውብሸት ታዬ ያሉ ጋዜጠኞችን እናገኛለን። ክሳቸው በሒደት ላይ የሚገኙ ግለሰቦችን ጉዳይ መመልከታችን የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ማንን ለማጥቃት የተመዘዘ እንደሆነ በግልፅ ያስረዳናል።
የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ከፀደቀበት ጊዜ ጀምሮ ብዙም ባልተለመደ መልኩ ፖሊስ በመጀመሪያ በመደበኛ የወንጀል ሕግ አግባብ መሰረት ‘ሕገ-መንግስታዊ ስርዓቱንና ሕገ-መንግስቱን በሀይል ለማፍረስ በመሞከር ወንጀል ሙከራ’ ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት ስድስት ጦማሪያንንና (ማለትም በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ አጥናፉ ብርሃኔ፣ ዘላለም ክብረት እና አቤል ዋበላ) እንዲሁም ሶስት ጋዜጠኞችን (ማለትም አስማማው ኃ/ጊዮርጊስ፣ ኤዶም ካሳዬና ተስፋለም ወ/የስ) ከሶ የጊዜ ቀጠሮ እየጠየቀ ቢሔድም የመደበኛው የወንጀል ሕግ ስነስርዓቶች አልተመቹትምና የሁሉም ማጥቂያ ወደሆነው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ጉዳዩን በመውሰድ እና ጦማሪ ሶልያና ሽመልስን በመጨመር በ10 ተከሳሾች ላይ በቀን 09/11/2006 በፌ/ዓ/ሕ/መ/ቁ 05/07 በተዘጋጀ ክስ “ግንቦት ሰባት የተባለ የሽብርተኛ ድርጅትን መመሪያ በመቀበል፣ ኦነግ የተባለ የሽብርተኛ ድርጅትን መመሪያ በመቀበል እንዲሁም በክሱ ላይ ስሙ ያልተጠቀሰ (ምናልባትም ዞን 9) የሽብርተኛ ድርጅትን በማቋቋም ‘የሽብርተኝነት ድርጊቶችን’ (ድርጊቶቹ የትኞቹ እንደሆኑ በክሱ አልተጠቀሰም) ለመፈፀም ሲያሴሩ፣ ሲያቅዱ፣ ሲዘጋጁና ሲያነሳሱ ተይዘዋል።” በማለት ክስ አቅርቧል። የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉም የተለመደውን ጋዜጠኞችን የማሰር ሒደቱን አጠናክሮ በመቀጠል ብዙም ያልተለመደውን ጡመራንም (Blogging) አካቶ፣ በነፃነት የተደራጀ ማንኛውም ዓይነት ስብስብ ‘የሽብርተኛ ስብስብ ነው’ ወደ ሚል አስደንጋጭ ደረጃ ከፍ አድርጎታል።
ምናልባትም በሰላማዊ መንገድ የሚታገሉ ፓርቲዎች ላይ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የማይደርስ የሚመስለው ካለ ቀጣዮቹ ተጠቂዎች (victims) ጥሩ ማስረጃዎች ይሆኑታል። የግንቦት ሰባት ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን፥ ሰንዓ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው በተሰጡበት ቅፅበት ከተለያዩ  ሰላማዊ ትግል ለማድረግ ተመዝግበው እየተንቀሳቀሱ ካሉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ አባላትን በሽብርተኝነት ድርጊት ወንጀል ጠርጥሬያቸዋለሁ በማለት ፖሊስ አስሮ በፌደራል የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነ ይታወቃል።
በዚህም መሰረት አብርሀ ደስታ ከአረና ለፍትህና ለነፃነት የፖለቲካ ፓርቲ፣ ሀብታሙ አያሌውና ዳንኤል ሺበሺ ከአንድነቱ ለፍትህና ለዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የሺዋስ ወንድማገኝ ከሰማያዊ ፓርቲ በማሰር በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አማካኝነት ከሶ  ይህ ፅሁፍ በተፃፈበት ወቅት ፖሊስ የጊዜ ቀጠሮ እየጠየቀ በፌደራል የወንጀል ምርመራ ዘርፍ ማረፊያ ቤት አስሯቸው ይገኛል። በተጨማሪም ቀደም ብለው ተከሰው በፌደራል የወንጀል ምርመራ ዘርፍ (ማዕከላዊ) የሚገኙትን አቶ አፍሪካ ከበደ ከኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ (ኦፌስ) እንዲሁም አቶ ታምራት ታዬ ከመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) አብረን ስናየው የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ በሀገሪቱ ውስጥ እየተንቀሳቀሱ የሚገኙትን ዋነኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች በጠላትነት በመቁጠር ከሁሉም ፓርቲዎች የተለያዩ ግለሰቦችን የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ ሰለባ (booty) አድርጓል።
በአጠቃላይ ለዴሞክራሲ ማደግ ዋነኛ መሰረቶች የሆኑትን ነፃ ፕሬስ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና ነፃ ስብስቦችንና ተቋማትን የፀረ-ሽብርተኝነት አዋጁ ድል አድርጓቸዋል። ዴሞክራሲንም አሁን ባለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ምህዳር ቦታ የሌለው ሀሳብ እንደሆነ በተግባር (by implication) ተበይኗል።
የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ የበላይነት (Rule of Anti-Terrorism Law)
የፀረ-ሽብርተኝነት ህጉ እያዳረሰ ያለውን ሁለንተናዊ ጉዳት ከነሰለባዎቹ ማንነት በዚህ ፅሁፍ ማቅረባችን የችግሩ መነሻና መድረሻ ሕጉ ነው በሚል አይደለም። ይልቁንም የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የአምባገነንነት መገለጫ (An epitome of dictatorship) ነው ወደሚል አቅጣጫ ስለሚያመራንም ጭምር ነው። ከሕጉ ጀርባ ዴሞክራሲያዊ ሕልምን የመጨፍለቅ ዓላማ ያለው አካል መሳሪያ ሆኖ የቀረበ አዋጅ ነው።
ሕጉ የማያንኳኳው ቤት አይኖርም። ከሕጉ ‘ባለቤት’ ውጭ። በአፈፃፀሙም ማንኛውንም ዓይነት ድርጊት ከሳሹ መንግስት በፀረ-ሽብርተኝነት ህጉ አማካኝነት መክሰስ ይችላል ወደሚል የፍርድ ቤት ትርጉም ደርሰናል። ከሕጉ አፈፃፀሙ ይከፋል። የዜጎችን ሕገ-መንግስታዊ መብቶች ‘ወንጀሉ እኮ ሽብር ነው’ በሚል አስገራሚ ምክንያት ወደጎን ተደርጓል። አቃቢ ሕግ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን በመጥቀስ እያቀረባቸው ያሉት ክሶች በሙሉ በመደበኛው የወንጀል ሕግ የተሸፈኑ ቢሆንም ‘ጉዳዩ  እኮ ሽብርተኝነት ነው’ በሚል የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አድማሱን በማስፋት መብቶቸን ለመጣስ የተለየ የህግ ማእቀፍ በመፍጠር ግዳይ መጣሉን ቀጥሎበታል።
በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ አንቀፅ 36(1) ላይ እንዲህ ተደንግጓል: -
“ከዚህ አዋጅ ጋር የሚቃረን ማናቸውም ሕግ፣ ደንብ፣ መመሪያ ወይም የአሰራር ልማድ በዚህ አዋጅ በተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ተፈፃሚነት አይኖረውም።”
ይህ ተራ አዋጅ አይደለምና ከላይ በአዋጁ አንቀፅ የተገለፀው ‘ማናቸውም’ የሚል ቃል በእርግጥም ሕገ-መንግስቱንም ይጨምራል። ከሕገ-መንግስት የበላይነት ወደ የፀረ-ሽብርተኝነት ሕግ የበላይነት የተሸጋገረች ኢትዮጵያ! በፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ እየተመራችም የ2007 ዓ.ም. አምስተኛውን ሀገራዊ ‘ምርጫን’ ‘ፍትሀዊና ሰላማዊ’ በሆነ መንገድ ለማከናወን ደፋ ቀና እያለች ሲሆን ጥያቄው ደግሞ ምርጫው እየተቃረበ ሲሄድ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ‘የሽብርተኛ ድርጅትነት’ ይረጋገጥ ይሆን? የሚለው ነው።
_______________________________________________________________________________________________________________________
[1] በሰኔ 2006 ዓ.ም. ከሞያሌ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አባላት ታፍኖ ይህ ፅሁፍ እስከተፃፈበት ጊዜ ድረስ በፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ዘርፍ የሚገኘው የ14 ዓመት ልጅ ሲሆን። ፖሊስም ‘የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ)ከተባለ የሽብርተኛ ድርጅት ጋር ግንኙነት አለህ’ በማለት የፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉን በመጥቀስ የ28 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ እየጠየቀበት በእስር ላይ ይገኛል።
[2] ከፀረ-ሽብርተኝነት ሕጉ የመጀመሪያ ሰለባዎች አንዱ የሆኑት አቶ ፅጌ ገብረማርያም አሁን በእስር ላይ የሚገኙት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ አባት ሲሆኑ፤ ልጃቸውን ለመጠየቅ ወደ እንግሊዝ ሀገር በሔዱበት ጉዳይ ‘ከሽብርተኞች ጋር ግንኙነት አድርገዋል’ ተብለው የ8 ዓመት ፍርድ በተፈረደባቸው ወቅት የ80 ዓመት አዛውንት ነበሩ።
[3] ይሄን ስምን ቀይሮ አንድን ጉዳይ የማቅረብ አካሄድ የወሰድነው William Easterly የተባሉ ምሁር ‘The Tyranny of Experts’ ባሉት መፅሐፋቸው Uganda ውስጥ የደረሰን የአካባቢ ውድመት America, Ohio ውስጥ እንደደረሰ አድርገው ለአንባብያን ይገባ ዘንድ ካቀረቡበት አካሄድ ነው።
[4] የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የልደታ ምድብ በአሁኑ ወቅት ካሉት 20 ችሎቶች ውስጥ ሁለቱ፣ ማለትም አራተኛ እና አስራ ዘጠነኛ ወንጀል ችሎቶች ‘በፀረ-ሽብርተኝነት’ ሕጉ አማካኝነት የሚቀርቡ ክሶችን የሚመለከቱ ሲሆን በችሎቶቹ የሚሰየሙት ዳኞችም በየጊዜው ይቀያየራሉ። ነገር ግን በችሎቶቹ በቋሚነት ተሰይመው ‘የሽብርተኝነት’ ክሶችን እየተመለከቱ ያሉት ዳኞች ባህሩ ዳርቻ፣ ብስራት ተህልቁ፣ ቀናቴ ሆና፣ ሸለመ በቀለ፣ ወ.ዘ.ተ.

አገሩን ያልተቀማው ተመስገን!

$
0
0

ከጌታቸው ሽፈራው

ህዝብን ተስፋ ካስቆረጠው 97 ምርጫ በኋላ አዲስ ነገረ ጋዜጣ የመረጃ ምንጭ፣ የመወያያ መድረክና ነቃሽ መሆን ችላ ነበር፡፡ ብዕርን አብዝቶ የሚፈራውና ህዝብ አማራጭ መረጃ ሲያገኝ እንቅልፍ የሚያጣው ገዥ ፓርቲ የአዲስ ነገር ጋዜጠኞችን ማዋከቡን ተያያዘው፡፡ ጫናው እየተጠናከረ በሄደበት አንድ ቅዳሜ ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽ ‹‹ይህ አገር የማን ነው?›› በሚል ስርዓቱ የሚያደርገውን አፈና፣ አዲስ ነገር ላይ እየደረሰ ያለውን በደል ዘርዝሮ አስረዳ፡፡ አገሩ የኢትዮጵያውያን ቢሆንም ገዥዎቹ እንደነጠቁን፣ መስራት እንዳልተቻለ በድንቅ የጽሁፍ ችሎታው ቀምሮ አስነበበ፡፡ ተወዳጇ አዲስ ነገር ከዛ ቀን በኋላ ለአንባቢዎች አልደረሰችም፡፡ አገራቸውን የተነጠቁት የአዲስ ነገር ጋዜጠኞችም የተቀሙትን አገር ትተው ተሰድደዋል፡፡
temesgen desalegn

አዲስ ነገር ከተዘጋች በኋላ አውራምባ ታይምስ በአማራጭነት አንባቢዎች እጅ መድረስ ጀመረች፡፡ አሁን ደግም ገዥዎቹ ሙሉ አቅማቸውን ወደ አውራምባ አዙረዋል፡፡ በአንድ ማስክሰኞ ጠዋት ላይ የያኔው ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ የጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽን ርዕስ ተውሶ ‹‹ይህ አገር የማን ነው?›› የሚል መጣጥፍ አሰነበበ፡፡ ርዕሱን ፊት ላይ ላየው አንባቢ መልዕክቱ ግልጽ ነበር፡፡ አስደንጋጭ መልዕክልት፡፡ ‹‹አውራምባዎች ሊሰደዱ ነው፡፡›› የተፈራው አልቀረም ዳዊት ከበደ ተሰደደ፡፡ አውራምባ ተዘጋች፡፡

ከዚህ በኋላ ፍትህ ሌላ አማራጭ ሆና ወጥታለች፡፡ አርብ አርብ ‹‹ፍትህ ምን አለች?›› ብለው ተቀዳድመው የሚገዟት ተበራክተዋል፡፡ በተለይ በፊት ገጽ ላይ ይዛው የምትወጣው የፎቶ ቅንብር መልዕክቱን በግልጽ የሚያስተላልፍ በመሆኑ የማያነበውን አልፎ ሂያጅ ህዝብም ጭምር የሚስብ ነበር፡፡

ግን አሁንም ገዥው ኢህአዴግ ነው፡፡ አፈናው በዛ እንጅ ሊቀንስ አልቻለም፡፡ እናም ፍትህ ላይም አፈናው ተጠንክሮ ቀጥሏል፡፡ ፍትህ በምትጠበቅበት አንድ አርብ ጠዋት ላይ ያ አስደንጋጭ ርዕስ ለሶስተኛ ጊዜ ተደገመ፡፡ አንባቢዎች ደነገጡ፡፡ ‹‹ይህ አገር የማን ነው?›፡፡ መልዕክቱ ግልጽ ነበር፡፡ ፍትሆች መሰደዳቸው ነው፡፡ ጽሁፉን የጻፈው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ነው፡፡ አብዛኛው የጽሁፉ ክፍል ጋዜጠኛ መስፍን ነጋሽም ሆነ ጋዜጠኛ ዳዊት ከበደ ከጻፉት ጋር የሚስማማበት፣ የአፈናውን አስከፊነት የሚገልጽበት በመሆኑ ተመሳሳይ ነው፡፡ ይህ ጽሁፍ የሚለየው በድምዳሜው ብቻ ነው፡፡

ተሜ! አገሩ በገዥዎች ቁጥጥር ስር ብትሆንም ለማንም ጥሎ እንደማይሄድ ቃል ገባ፡፡ ‹‹አልሰደድም!›› አለ፡፡ የመጣው ቢመጣ ያለመሰደድ ምልክት ሆነ፡፡ ተሜ! አገሩ በሌሎች እጅ ቢሆንም አገሩን አምኖ ያልተቀማው ጋዜጠኛ ነው፡፡ ፍትህ ስትዘጋ አዲስ ታይምስ፣ እሷም ስትዘፋ፣ በፋክት በመምጣትም ተስፍ ያለ መቁረጥም ምልክት ሆነ፡፡

ተመስገን ደሳለኝ በየጊዜው ከሚከፈቱበት ክሶች ባለፈ በ‹‹ሙስሊም›› ስም ኢሜል እንደተላከለት፣ ከአልሻባብ ጋር ግንኙነት እንዳለው በማስመሰል ‹‹ሊጠልፉት›› ሞክረዋል፡፡ እሱ ግን ቀድም ‹‹አልሸባብና ፍትህ ምን አገናኛቸው?›› ሲል የሚሰራበትን ሴራ አጋልጧል፡፡ ከአገር እንዲወጣ በተለያየ መንገድ እንደገፋፉት ተሰምቷል፡፡

በአንድ ወቅት ስፖርት፣ አሊያም ፋሽን ጋዜጣና መጽሄት ላይ ሲሰሩ የነበሩ ሚዲያዎች የ‹‹ፖለቲካው ገበያ›› ሲደራ ስምና ቅርጽ እየቀየሩ ሲመጡ ይታያል፡፡ በዚህም ምክንያት ሚናውን ለይቶ የሚገባ ሚዲያና ጋዜጠኛ ቁጥሩ አነስተኛ ነው፡፡ ተሜ ለአገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታ ያስፈልጋል ያለውን የሚዲያ ሚና (የአርነት ሚዲያ) ለይቶ የገባ ጋዜጠኛ ነው፡፡ ቢከስር፣ ቢታፈንበት፣ ማስታወቂያ ባይኖረው፣ ማከፋፈያውና ሌላው ቦታ ላይ ችግር ቢኖር ‹‹ያበላል›› ወዳለው አላወላወለም፡፡ ፍትህ፣ አዲስ ታይምስ፣ ፋክት ሚናቸው ተመሳሳይ ነበር፡፡ ከኢንተርኔት እየቃረሙ ከሚያሳትሙት፣ በገዥው ፓርቲ ጎትጓችነት ሳይቀር ማስተዋቂያ የሚቸራቸው፣ በነጻ በሚባል ዋጋ ጋዜጠኛውን ከሚበዘብዙ ሚዲያዎች ጋር እየተወዳደረ ከቆመበት ሚና ወደኋላ አላለም፡፡ ‹‹አገሬ በገዥዎቹ ስር ብትሆንም፣ ለእኔም አገሬ ናት፡፡ አልሰደድም!›› ያለው ተመስገን አገሩን አሰልፎ፣ አምኖ አልተቀማምና እስከመጨረሻው በዓላማው ጸንቷል፡፡

በስርዓቱ አፋኝነት ምክንያት ብዙዎቹ ምሁራን በገዛ ፈቃዳቸው አፋቸውን አፍነዋል፡፡ ጋዜጠኞች ብዕራቸውን ድርቋል፡፡ ብዙው ደግሞ ከዝምታም በላይ አድር ባይ ሆኗል፡፡ አገሩን ከመቀማቱ በፊት አሳልፎ ሰጥቷል፡፡ ተሜ! ሀሳብን በነጻ መግለጽ ባልተከበረበት ሀሳቡን በነጻነት ለመግለጽ ይጥራል፡፡ ህግ በሌለበት ህጉን አክብሮ ስለ ህግና ፍትህ ያወራል፡፡ ገዥዎቹ አገር ቀማን ሲሉ እሱ ግን ‹‹አገሩማ የእኔ ነው!›› ብሎ ደፍሮ ይጽፋል፡፡ አገሩን አልተቀማምና ተመስገን የድፍረትም ተምሳሌት ነው፡፡

አንድ ጋዜጠኛ ስለ ተመስገን ድፍረት እንዲህ አወራኝ፡፡ ይህ ጋዜጠኛ ተመስገንን ‹‹አቤን ድፍረቱ!›› ይለዋል፡፡ በአንድ ወቅት ነው፡፡ በርከት ያሉ ጋዜጠኞች ተከሰው (ማዕከላዊ ነው መሰለኝ) ይቀርባሉ፡፡ ፖሊስና ደህንነት ጋዜጠኞቹ ላይ ከጸያፍ ስድብ ጀምሮ ‹‹ለምን አርፋችሁ አትቀመጡም፣ ይቅርባችሁ!›› አይነት ምክር ያቀርቡላቸዋል፡፡ ደግሞም ያስፈራሩዋቸዋል፡፡ ጋዜጠኛው ‹‹ሁላችንም ጸጥ አልን፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ስህተት እንደሰራን በመግለጽ ጭምር ከመጣብን መከራ ለመዳን ጣሩ፡፡›› ይላል፡፡ የተመስገን ድፍረት ግን ይገርመዋል፡፡ ተመስገን ስድብ ሲወርድባቸው፣ ያልረባ ምክር ሊሰጡ ሲሞክሩ፣ ሲያስፈራሩዋቸው እንደሌሎቹ ዝም አላለም፡፡ ተከራከራቸው፡፡

አገሩን የራሳቸው አድርገው የሚወስዱት ደህንነቶችና ፖሊሶች ህግ ጠቀሰ አልጠቀሰ አገር እንዳለው ሰው ደፍሮ የሚናገር ሰው ያበሳጫቸዋል፣ በምክንያት ቢያምኑ የተሸነፉ ይመስላቸዋል፡፡ በምክንያት መከራከር አይችሉምና ስድብ፣ ዛቻ፣ ከዛም አለፍ ሲል ኃይል ነው ምርጫቸው፡፡ በተሜ ላይም ይህ ሁሉ ተፈጽሞበታል፡፡ ይህ ሁሉ ሲደረግ ሌሎቹ ጋዜጠኞች ‹‹በቃ! ገደሉት!›› እያሉ ለተሜም ይፈሩለታል፡፡ እሱ ግን ክርክር ከማይችሉት ጋር ይከራከራል፣ ምክንያት የማያውቁትን ህግ ለማስረዳት ይጥራል፡፡ በስተመጨረሻ እንደማያምኑለት ሲያውቅ፣ እሱንም በኃይል ለማሳመን ሲጥሩ የተለመደው አቋሙን ገለጸላቸው፡፡ ‹‹ይህኮ አገሬ ነው!›› አገርን ሌሎች ቢይዙትም አምኖ ያልተቀማ ‹‹አገሬ ነው!›› ያለ ደፍሮ ይናገራል፣ ደፍሮ ይጽፋል፣ ደፍሮ ይታሰራል፡፡ እንደ ተመስገን ደሳለኝ፡፡

ተሜ! በርታልን!

ማኅበረ ቅዱሳን ተካሔደብኝ ባለው የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅ/ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጠው ጠየቀ

$
0
0

·ኑፋቄአቸውና ሕገ ወጥ ጥቅማቸው እንዳይጋለጥ የሚሰጉ አካላት ያስተባበሩት ነው
· የብፁዓን አባቶች ስም እየተጠቀሰ የወረደው የስድብ ናዳ በእጅጉ አሳዝኖናል
· በፈቃዳችን በነፃ የምንፈጽመውን የአገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው
· ግለሰቦቹ በስም ማጥፋት ዘመቻቸው ከቀጠሉ ማኅበሩ በሕግ ይጠይቃቸዋል
(በሰንደቅ ጋዜጣ ሪፖርተር)

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሥር አገልግሎቱን የሚፈጽመው ማኅበረ ቅዱሳን፣ ፓትርያርኩ በተገኙባቸው ስብሰባዎችና ስለ ስብሰባዎቹ በሚዘግቡ ሚዲያዎች ላይ የማኅበሩ ስም እየተጠቀሰ የሚካሔድበትን የስም ማጥፋት ዘመቻ ቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እንዲሰጥበት መጠየቁ ተገለጸ፡፡
Mhbere Kidusan
ማኅበሩ ጥያቄውን ያቀረበው ‹‹በሚዲያና በተለያዩ ስብሰባዎች የተከፈተው የስም ማጥፋት ዘመቻ አግባብ አለመኾኑን ስለመጠየቅ›› በሚል ርእስ ጥቅምት 1 ቀን 2007 ዓ.ም. በአድራሻ ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በግልባጭ ደግሞ ለቅዱስ ሲኖዶስ ጽ/ቤት፣ ለመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ለኾኑት ለኹሉም ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ባሰራጨው ደብዳቤ ነው፡፡

ላለፉት 23 ዓመታት በቅዱስ ሲኖዶስ በወጣለትና በተፈቀደለት ሕግና ደንብ መሠረት በቤተ ክርስቲያን ሥር ተዋቅሮ ኹለንተናዊ አገልግሎቷን ለመደገፍና ለማጠናከር የድርሻውን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጸው ማኅበሩ÷ በማያውቀው፣ ጥፋትም ካለ ተጠርቶ ባልተጠየቀበትና መልስ ባልሰጠበት ኹኔታ ፓትርያርኩ ባሉባቸውና በተለያዩ ጊዜያት በተጠሩ ስብሰባዎች የተፈጸምበት የስም ማጥፋት ዘመቻ መደጋገም ደብዳቤውን ለመጻፍ እንዳስገደደው ገልጧል፡፡

ማኅበሩ በደብዳቤው፣ በየስብሰባዎቹ የሕዝብ መገናኛ አውታሮች እየተጠሩ በማኅበሩ አገልግሎት ምክንያት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የኾኑ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት በስም እየተጠቀሱ ተራ የስድብ ናዳ እንደወረደባቸው ገልጦ፣ ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻው እኛንም ኾነ እውነተኛ የቤተ ክርስቲያን አባቶችንና ምእመናንን በእጅጉ አሳዝኖናል፤›› ብሏል፡፡ ስብሰባው የተቀረፀበትንና ‹‹አስነዋሪ›› ሲል የገለጸውን ቪዲዮ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ሕጋዊ ድረ ገጽ ላይ በኢንተርኔት መለቀቁ፣ የቤተ ክርስቲያን አካላት ነን ከሚሉ ሰዎች የማይጠበቅና ‹‹ቤተ ክርስቲያንን ለጠላት መሳለቂያ ለማድረግ›› በጥፋት መልእክተኞች የተቀናበረ እንደኾነ አመልክቷል፡፡

ትውልዱ በእምነትና በዕውቀት ታንፆ በሞያው፣ በገንዘቡና በጉልበቱ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያገልግልና ሐዋርያዊ ተልእኮዋ እንዲፋጠን ማኅበሩ ያበረከተው አገልግሎትና ስኬት አኹን ላለበት ደረጃ የደረሰው በብፁዓን አባቶችና በሊቃውንት ምክርና ጸሎት ተደግፎ እንደኾነ ደብዳቤው አስታውሷል፡፡ የቤተ ክርስቲያን እምነቷና ሥርዓቷ ሳይበረዝና ሳይከለስ ተጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ጥብቅና በመቆሙ፣ ከዚኽም አንጻር ‹‹አፅራረ ቤተ ክርስቲያን›› ናቸው ካላቸው አካላት የሚሰነዘሩ ‹‹የተሐድሶ ሽምቅ ደባዎች››ን ለቅ/ሲኖዶስ በማስረጃ አስደግፎ በማጋለጡና ማስረጃው ተጠንቶና ተረጋግጦ በመወገዛቸው ምክንያት በአገልግሎቱ ላይ ግልጽና ስውር ፈተናዎች እየተፈጠሩ መቆየታቸውን አስረድቷል፡፡

ማኅበሩ ‹‹አስነዋሪ›› ያለውና በተጠቀሰው መምሪያ ሕጋዊ ድረ ገጽ ላይ የተለቀቀው ቪዲዮ መስከረም 27 ቀን 2007 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አዳራሽ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን አስተዳደራዊ አስተሳሰብ ማበልጸግ›› በሚል ርእስ የተካሔደውን የግማሽ ቀን ስብሰባ የሚያሳይ መኾኑ ታውቋል፡፡ ፓትርያርኩ አቡነ ማትያስ በጽሑፍ የተደገፈ ገለጻ የሰጡበትና በልዩ ጸሐፊያቸው የተመራው ይኸው ስብሰባ፣ የገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎችና ጸሐፊዎች የተካፈሉበት ሲኾን የማኅበረ ቅዱሳንን ስም በመጥቀስ ማኅበሩ ‹‹ለአባቶች አይታዘዝም፤ መዋቅር ጠብቆ አይሠራም፤ ሒሳቡን አያስመረምርም፤ ዐሥራት ይሰበስባል፤ የፖሊቲካ ዓላማ አለው፤ አክራሪና አሸባሪ ነው…ወዘተ›› በሚሉ ሐሳቦች ዙሪያ ያተኮሩ የስም ማጥፋት ዘመቻ እንደተፈጸመበት ደብዳቤው ዘርዝሯል፡፡
mahibere-kidusan
ማኅበሩ በስብሰባው ላይ ‹‹ስም ማጥፋት›› የተባለውን ድርጊት የፈጸሙበት ግለሰቦች ማንነት እንደየ ምክንያታቸው ሊለያይ እንደሚችል በተለያዩ ጊዜያት ያካሔዳቸውን ጥናቶች መነሻ በማድረግ አመልክቷል፡፡ እኒኽም ራሳቸውን ደብቀው የምንፍቅና ዓላማን ያነገቡና ማኅበሩ ለዓላማቸው መሳካት ዕንቅፋት እንደኾነባቸው የሚያምኑ፤ የቤተ ክርስቲያንን ንብረት በመጠቀም የግል ሀብት የሚያካብቱና ማኅበሩ ሊያጋልጠን አልያም ምቹ ኹኔታ ፈጥሮልን የኖረውን የሒሳብና ሌሎች አሠራሮች ክፍተት ሊደፍንብን ይችላል በሚል የሚፈሩ፤ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር በተማረ ኃይል በመሙላት ቦታ ያሳጣናል በሚል የሚሰጉ፤ ማኅበሩን በመቃወም ማኅበሩን ከሚጠሉ አካላት ጥቅም ለማግኘት ወይም በተሳሳተ መረጃ የማኅበሩን አገልግሎት ጥቅም ባለመረዳት የሚቃወሙ እንደኾኑ ነው ያስረዳው፡፡

የማኅበሩ አገልግሎት ችግር ይኖርበታል ተብሎ ቢታሰብ እንኳ ትክክለኛው አካሔድ ማኅበሩ በጉዳዩ ተጠርቶ፣ ተጠይቆና ችግሩ ተረጋግጦ እንዲያርም ማድረግ ነው ያለው ማኅበረ ቅዱሳን፣ የስብሰባው አካሔድ ‹‹ድብቅ ዓላማ አንግቦ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማደናቀፍ የተቀናጀ ሤራ ነው›› የሚያሰኝ ጥያቄ ሊያሥነሳ እንደሚችል ገልጧል፡፡ ‹‹ቅዱስነትዎም ይህ ኹሉ ሲኾን የማኅበሩን አመራር አካላት አንድም ቀን ጠርተው አለመጠየቅዎ እንደ ልጅነታችን አሳዝኖናል›› በማለትም ከስብሰባው ቀደም ሲል ከፓትርያርኩ ጋራ የውይይት መርሐ ግብር እንዲያዝለት በተደጋጋሚ ያቀረበው ጥያቄ ተቀባይነት ባላገኘበት ኹኔታ መሠረት በሌላቸውና ከእውነትነት በራቁ የሐሰት ክሦች ‹‹የስም ማጥፋት ዘመቻ›› እንዲከፈትበት በመደረጉ ቅር መሰኘቱን አስታውቋል፡፡

በደብዳቤው እንደተብራራው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ለቤተ ክርስቲያኒቱን ኹለንተናዊ አገልግሎት የሚያበረክተው፣ ከዋናው ማእከል አንሥቶ በሀገር ውስጥና በውጭ አህጉረ ስብከት በተዘረጋው መዋቅሩ ሲኾን ይኸውም ከየሀገረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ በመመካከርና መመሪያ በመቀበል የሚከናወን ነው፡፡ በየጊዜው ዕቅዱን በማሳወቅ በየስድስት ወሩ የዕቅድ አፈጻጸምና የሒሳብ ሪፖርት ለጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት ያቀርባል፡፡ ሒሳቡን በየጊዜው በውስጥ ኦዲተር የሚያስመረምር ሲኾን በየዓመቱ ደግሞ ዓለም አቀፍ ዕውቅና ባለው ሕጋዊ የውጭ ኦዲተር አስመርምሮ ለሚመለከታቸው የቤተ ክህነቱ አካላት እያቀረበ ይገኛል፡፡ በዚኽም ከየትኛውም አካል ጥያቄ፣ ነቀፌታ ይኹን እርማት ቀርቦበት ባያውቅም ባቀረባቸው ሪፖርቶች የሚሰጠውን መመሪያ ተከትሎ አገልግሎቱን እያከናወነ ኻያ ሦስተኛ ዓመቱን ማስቆጠሩን በደብዳቤው ተመልክቷል፡፡

ማኅበሩ ‹‹እንኳን የራሱን የሒሳብ አያያዝ የቤተ ክርስቲያንዋ የሒሳብ አሠራር በሙሉ ዘመናዊና ለኦዲት የሚመች እንዲኾን የሚያግዝ ነው፤›› ያለው ደብዳቤው፣ ማኅበረ ቅዱሳን ዘመናዊና የኹለትዮሽ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት (double entry accounting system) የሚከተል በመኾኑ የቤተ ክህነቱን የነጠላ የሒሳብ አያያዝ ሥርዐት ለመከተል እንደተቸገረ አልሸሸገም፡፡ ይኹንና የቤተ ክህነቱ የቁጥጥር አገልግሎት ባስፈለገው ጊዜ ማኅበሩ በውስጥ ይኹን በውጭ ኦዲተር ያስመረመረውን ሒሳብ ማየት፣ በአካልም ተገኝቶ ማረጋገጥ እንደሚችል ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ማስታወቁን አውስቷል፡፡ ‹‹ማኅበረ ቅዱሳን ወዶ ፈቅዶ አባቶችን ለማገልገል፣ የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት በፈቃደኝነት ለመደገፍ የተቋቋመ በመኾኑ የመታዘዝ ይኹን በሞያ የተደገፍ የሒሳብ አያያዝ የመተግበር ችግር የለበትም፤›› በማለት ለመዋቅሩ ያለውን ታማኝነት አጽንቷል፡፡

ማኅበሩ ‹‹ከምእመናን የዐሥራት በኵራት ገቢ ይሰበስባል›› በሚል በስብሰባው ላይ የተሰነዘረበትን ‹‹ስም ማጥፋት›› ፍጹም ሐሰት በማለት አጣጥሎታል፡፡ በሰጠው ምላሽም ማኅበረ ቅዱሳን አገልግሎቱን የሚያከናውነው ከአባላቱ ገቢ በሚሰበስበው የኹለት በመቶ ወርኃዊ አስተዋፅኦ እንደኾነ፣ ለቅዱሳት መካናትና ለስብከተ ወንጌል ማስፋፊያ ፕሮግራሞች ደግሞ ፕሮጀክቶችን በመቅረፅ ከገባሬ ሠናይ ምእመናን ድጋፍ እንደሚያፈላልግ ገልጧል፡፡ አገልግሎቱ የበጎ ፈቃድና የትሩፋት መኾኑን በተደጋጋሚ የገለጸው ማኅበሩ ከአባላቱ የሚሰበሰበው የኹለት በመቶ ወርኃዊ አስተዋፅኦ፣ እያንዳንዳቸው ለየሰበካቸው የሚጠበቅባቸውን ዐሥራት ወይም የሰበካ ክፍያ ከፈጸሙ በኋላ የሚያበረክቱት እንደኾነ አረጋግጧል፡፡

ማኅበሩ ረብ የለሽ ሲል ውድቅ ካደረጋቸው የአንዳንድ ተሰብሳቢዎች ክሦች ውስጥ ግንባታውን የተጠናቀቀውንና የሚገለገልበትን የጽ/ቤት ሕንፃ የሚመለከት ይገኝበታል፡፡ ሕንፃው ያረፈበት ቦታ የተገዛው የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የወቅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በሰጡት ውክልና መኾኑን ማኅበሩ በደብዳቤው ገልጦ፣ አባላቱ የወር ደመወዛቸውን በተደጋጋሚ በማዋጣት የገነቡትና በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበረ ቅዱሳን ስም በሕግ ተመዝግቦ የሚገኘውንና በማኅበሩ የሒሳብ ሪፖርትም በቋሚ ንብረትነት ተይዞ በየወቅቱ የሚገለጸውን ሕንፃ አመራሩ ይኹን አባላቱ የመጠበቅና የመገልገል እንጂ ለሦስተኛ ወገን አሳልፎ የመስጠት ይኹን የመሸጥ ፍላጎት እንደሌላቸው አስታውቋል፡፡

በቅዱስ ሲኖዶስ በጸደቀውና እየተመራበት በሚገኘው መተዳደርያ ደንቡ መሠረት ማኅበሩ በማንኛውም የፖሊቲካ አመለካከት ጣልቃ እንደማይገባና አገልግሎቱ ሰማያዊ እንጂ ምድራዊ እንዳልኾነ ያረጋገጠው ማኅበሩ፣ የፖሊቲካ ዓላማ እንዳለው ለተሰነዘረው ውንጀላ መረጃው ቀርቦ በሚመለከተው አካል ሊታይና ሊጣራ እየቻለ የማይመለከታቸው አካላት ከሜዳ ተነሥተው ስም ለማጥፋት ሊጠቀሙበት እንደማይገባ አሳስቧል፡፡ ማኅበሩ ‹‹አክራሪ ነው፤ አሸባሪ ነው›› ማለትም ‹‹ውንጀላን ከማዳመቅ›› ያላለፈ ፋይዳ የሌለው መሠረተ ቢስ ክሥ ነው ብሏል፡፡

ማንም ግለሰብ ይኹን ኅብረተሰብ የፈለገውን እምነት ሊከተል እንደሚችል እምነቱ እንዳለውና የማንንም ሰብአዊና ሕገ መንግሥታዊ መብት እንደማይነካ በአጽንዖት የገለጸው ማኅበሩ፣ ማንም የራሱን እምነት ከማራመድ አልፎ በሌላው እምነት ጣልቃ መግባት ስለሌለበት፣ ‹‹በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዐት ጣልቃ ገብተው የሚያውኩትን የተሐድሶ መናፍቃን የመከላከልና ቤተ ክርስቲያንን የመጠበቅ ተልእኮዬን አጠናክሬ እቀጥላለኹ፤›› ብሏል፤ ‹‹እናቱን አውሬ ሲበላት ቆሞ የሚሥቅ ልጅ የለም›› ሲልም አቋሙን አስረግጧል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በተጣለባቸው ታላቅ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊነትና አባትነት በማኅበሩ ላይ የሚካሔደውን የስም ማጥፋት ዘመቻውን በአጽንዖትና በተረጋጋ መንፈስ እንዲመለከቱ ማኅበረ ቅዱሳን በአቤቱታው ተማፅኗል፡፡ ግለሰቦቹን በሕግ ለመጠየቅ ሊገደድ እንደሚችል ያስታወቀው ማኅበሩ ‹‹አስነዋሪና የቤተ ክርስቲያን ነን ከሚሉ አካላት የማይጠበቅ ነው›› ያለው ድርጊት ‹‹በቤተ ክርስቲያን ልጅነታችን በፈቃዳችን ገንዘባችንን፣ ጉልበታችንንና ጊዜአችንን አስተባብረን የምናደርገውን ነፃና የፈቃድ አገልግሎት መብታችንን የሚፃረር ነው፤›› ሲል አስገንዝቧል፡፡ ኹኔታው በተመሳሳይ መልኩ ከቀጠለ ቤተ ክርስቲያንን እርስ በርሷ የማትናበብ፣ ማእከላዊ አሠራር የሌላት የሚያስመስልና ለአገልግሎቷ ዕንቅፋት የሚፈጥር በመኾኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጉዳዪን በጥንቃቄ መርምሮና አጣርቶ አስቸኳይ ውሳኔ እንዲሰጥበት ጠይቋል፡፡

የቀድሞው የቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጥፋተኛ ተባሉ

$
0
0

የተለያዩ የመንግሥት ቤቶችን የኪራይ ዋጋ በመቀነስና በዜጎች መካከል ልዩነት በመፍጠር፣ መንግሥት 370,476 ብር ጉዳት እንዲደርስበት ለማድረግ ሥልጣናቸውን ያላግባብ በመጠቀም የሙስና ወንጀል የተከሰሱት፣ የቀድሞ የመንግሥት ቤቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥፋተኛ ተባሉ፡፡

288f8a3dዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተፈሪ ፍቅሬ ጎሳዬ የፌዴራል የሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን ባለፈው ዓመት የመሠረተባቸውን ክስ ሲመረምር የከረመው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አንደኛ ወንጀል ችሎት ነው ጥፋተኛ የተባሉት፡፡

አቶ ተፈሪ በሥልጣን ላይ እያሉ፣ በቀድሞ ወረዳ 23 ቀበሌ 12 የቤት ቁጥር 106 የሆነውና በውጭ ምንዛሪ ተከራይቶ የነበረን ቤት፣ የኤጀንሲውን መመርያ አንቀጽ 13 (5) ውድቅ በማድረግ ለኢትዮጵያዊ ማከራየታቸው፣ በቀድሞ ወረዳ 21 ቀበሌ 01 የቤት ቁጥር 112/40 ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ለንግድ በጨረታ አሸንፎ የነበረውን ቤት በመመሳጠር ወደ መኖሪያ ቤት በመቀየርና ኪራዩን በመቀነስ፣ በቀድሞ ወረዳ 18 ቀበሌ 05 የቤት ቁጥር 008/14 ውስጥ ተከራይ የነበሩትን የምክር ቤት አባል ከጠቅላይ ሚኒስትሩ የተጻፈ የድጋፍ ደብዳቤ ሳይኖር በመመሳጠርና በምክር ቤት አባላት ላይ ልዩነት በመፍጠር እንዲከራዩ በማድረግና ሌሎችንም ተጨማሪ ቤቶች ሥልጣናቸውን በመጠቀም ኪራይ ቀንሰው እንዲከራዩ በማድረግ በመንግሥት ላይ ጉዳት ማድረሳቸውን ክሱ ያብራራል፡፡

ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ የሰነድና የሰዎች ምስክሮችን በማቅረብ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ፍርድ ቤቱ በብይኑ ገልጾ፣ አቶ ተፈሪ እንዲከላከሉ በማዘዝ ተከላክለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ የሆኑት ዶ/ር ካሱ ኢላላና የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አማኑኤል አብርሃን ጨምሮ ሌሎች መከላከያ ምስክሮችን ያቀረቡት አቶ ተፈሪ፣ የቀረበባቸውን ክስ በከፊል ሊከላከሉ እንዳልቻሉ ፍርድ ቤቱ ገልጾ፣ ጥቅምት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ጥፋተኛ ብሏቸዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በፍርዱ እንደገለጸው አቶ ተፈሪ የቀረበባቸው ክስ በሥልጣን ያላግባብ የመገልገል ወንጀል ሲሆን፣ ክሱ አንድ ሆኖ በአራት ጭብጥ የተከፋፈለ መሆኑን አብራርቷል፡፡

አቶ ተፈሪ የዓቃቤ ሕግን ክስና ማስረጃ የተወሰነ ክፍል በበቂ ሁኔታ መከላከላቸውንም ፍርዱ ይገልጻል፡፡ የግል የንግድ ድርጅት የሆነውን ባሰፋ ትሬዲንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና ወ/ሮ ሶሻል ይልማ የተባሉት ግለሰብ የተከራዩትን ቤት በተመለከተ የኪራይ ተመናቸው እንዲቀንስ ያደረጉት አቶ ተፈሪ በመሆናቸው፣ ይኼንን ለማድረግ የተሰጣቸው ሥልጣን እንደሌለ ፍርድ ቤቱ አስታውቋል፡፡ በመሆኑም በዚህ በኩል ጥፋተኛ እንዳላቸው ፍርድ ቤቱ አስታውቆ ቅጣት ለመወሰንም ለጥቅምት 18 ቀን 2007 ዓ.ም. ቀጥሯል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

የዞን9 ጦማርያኑ እና የወዳጅ ጋዜጠኞች የዛሬው ፍርድ ቤት ውሎ

$
0
0

ከሁለት ወር ቆይታ በኋላ በነሶልያና ሽመልስ የሽብር ወንጀል የክስ መዝገብ ልደታ ፍርድ ቤት የቀረቡት ስድስቱ የዞን9 ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ቀጠሮ ችሎቱ ከ20 ቀን በኃላ እንዲቀርቡ ተለዋጭ ቀጠሮ በመስጠት ተጠናቀቀ።
zone 9

zone 9 ethioia1

zone 9 today
ፍርድ ቤቱ በዛሬው ውሎው የተከሳሽ ጠበቆች ክሱ ላይ ያቀረቡትን የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ አይቶ ምላሽ እንዲሰጥበት የተቀጠረ ሲሆን በዚያም መሰረት ለተከሳሽ ጠበቆች የክስ መቃወሚያ አቃቤ ህግ የፅሁፍ ምላሽ ሰጥቷል ።

ፍርድ ቤቱም የጠበቆችን የክስ መቃወሚያ እና የአቃቤ ህግን ምላሽ መርምሮ በክሱ ሂደት ላይ ብይን ለመስጠት ለተጨማሪ ሃያ ቀን ለጥቅምት 25 ቀጠሮ ሰጥቷል።

በተጨማሪም የሴት ተከሳሾችን በጓደኛና በቤተሰብ አለመጎብኘት ተከትሎ ያቀረቡትን አቤቱታ እንዲያስረዳ የማረሚያ ቤቱ እንዲገኝ ጥሪ ቢደረግም አለመገኘቱን እና በፓሊስ በኩል ምላሽ ይዞ መቅረቡን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ በሚቀጥለው ቀጠሮ የማረሚያ ቤቱ ሃላፌ እንዲገኙ ትእዛዝ አስተላልፎ ነበር። ነገር ግን ሴት ተከሳሾች በተለይ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳየ የመጎብኘት መብት መሰረታዊ መብታቸው በመሆኑ 20 መቆየት እንደማይገባ በመጠየቃቸው ፍርድ ቤቱ የሴት ተከሳሾችን የጉብኝት መብት አስመልክቶ ለማየት ለጥቅምት 11 አጭር ቀጠሮ ሠጥቷል ።

በዛሬው እለት ነጭ በመልበስ የተገኙት ተከሳሾች በመልካም ፈገግታ እና በጠንካራ መንፈስ የነበሩ ሲሆን በፈገግታ ወዳጅ እና ጓደኞቻቸውን ሰላም ሲሉ ተስተውለዋል።

በመጨረሻም የሚቀጥለው ቀጠሮ ለጥቅምት 25 የተወሰነ ሲሆን የሴት ታሳሪዎችን የጉብኝት መብት ጥያቄ አስመልክቶ በጥቅምት 11 ችሎቱ ቀድሞ ይሰየማል ተብሎ ይጠበቃል።

የዞን9 ጦማርያን የክሱን ፈጠራነት፣ የጦማርያኑን እና ጋዜጠኞቹ በመአከላዊ ምርመራ ያለፉበትን የመብት ጥሰት እያስታወስን የፍትህ ስርአቱ የሚታማበትን የፓለቲካ መጠቀሚያነት ክስ ወዳጅ ጋዜጠኞችን እና ተከሳሽ ጦማርያንን በነፃ በማሰናበት ፍርድ ቤቱ ይህንን ታሪካዊ አጋጣሚ እንደሚጠቀምበት ተስፋ እናደርጋለን።

Source: Zone9

ለወንዶች የሚጠቅሙ አምስት ምግቦች

$
0
0

በዶ/ር ብርሃኔ ረዳኢ

  1. የቲማቲም ሶስ

best food for menቲማቲም፣ የቲማቲም ሶስ ወይም ፒዛ አዘውትረው የሚመገቡ ወንዶች ራሳቸውን ከፕሮስቴት ካንሰር በጥሩ ሁኔታ እየተከታተሉ እንደሆነ በሃርቫርድ ተመራማሪዎች የተደረገ ጥናት አረጋግጧል፡፡ በጥናቱ ላይ 47ሺ ወንድ የጤና ባለሙያዎች ተካተዋል፡፡ በውጤቱም በሳምንት ከሁለት እስከ አራት ጊዜ ቲማቲም ነክ ምግቦችን የሚመገቡ ወንዶች በፕሮስቴት ካንሰር የመጠቃት እድላቸው በ35 ከመቶ ቀንሶ ተገኝቷል፡፡ ቲማቲም በከፍተኛ መጠን ይዞት የሚገኘው carotenoid ለዚህ ውጤት መገኘት ወሳኝነት አለው ተብሏል፡፡ ተመራማሪዎቹ ካሮቲኖይድን የያዘው ላይኮፔን የተሰኘ ንጥረ ነገር በቶሎ ከሰውነት ጋር እንዲዋሃድ ቲማቲሙ ከቅባት ጋር አብሮ መብሰል አለበት ያሉ ሲሆን ለዚህ ደግሞ ፒዛ ተመራጭ ሆኖ ተገኝቷል፡፡

  1. ኦይስተር

ይህ ከባህር ውስጥ የሚገኝ ምግብ በኛ ሃገር(ኢትዮጵያ) ብዙም የሚታወቅ አይደለም፡፡ ይህ ግን ጠቀሜታውን ከመንገር አያግድም፡፡ በጥንት አፈ ታሪክ ኦይስተር የፍቅር ምግብ ይባል ነበር፡፡ ሳይንስም ከዚህ ጋር ሳይስማማ አይቀርም፡፡ በቀን ሁለት ወይም ሶስት አይስተር ለተመገቡ ወንዶች ለእለቱ የሚያስፈልጋቸውን ዚንክ ይሰጣል፡፡ ይህ ሚነራል የወንድ የመራቢያ ክፍል የተለመደ ስራውን በአግባቡ እንዲወጣ ያስችላል፡፡ ሳይንቲስቶች ‹‹ባለፉት 50 ዓመታት የወንዶች ስፐርም ቁጥር (sperm count) አሽቆልቁሏል፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ የአካባቢያዊ ሁኔታዎች መበላሸት ነው›› በሚለው ነጥብ ላይ የተከፋፈለ አቋም አላቸው፡፡ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በአንዳንድ ጥናቶች ላይ የቴስቶስትሮን መቀነስን አሳይቷል፡፡ በቂ ዚንክ ማግኘት ለዚህ መልስ ነው፡፡ ለወንዶች በቀን 11 ሚሊ ግራም ዚንክ በቂ ሲሆን ከ40 ሚሊግራም በላይ ከሆነ ግን ጉዳት ያመጣል፡፡ የቴስቶስትሮንና የስፐርም መጠናቸው ቀንሶ የተገኙ 22 ሰዎችን ያሳተፈ አንድ የሙከራ ጥናት ተካሂዶ ነበር፡፡ እነዚህ ሰዎች በየእለቱ 45-50 ቀናት ዚንክ እንዲወስዱ ከተደረጉ በኋላ የቴስቶስትሮንና የስፐርም መጠናቸው ጨምሮ ተገኝቷል፡፡

  1. ብሮኮሊ

በሃርቫርድ የተደረገ አንድ የቅርብ ጊዜ ጥናት እንደ ብሮኮሊ ያሉ ባለ አበባ አትክልቶች የሽንት ፊኛ ካንሰርን ሊከላከሉ ይችላሉ ብሏል፡፡ ይህ የካንሰር አይነት አሜሪካ ውስጥ ከሚታዩ ካንሰሮች ዋነኛው ሲሆን ወንዶች ላይ በስፋት ይታያል፡፡ በ50 ሺ ወንዶች ላይ ጥናት ያደረጉ ሳይንቲስቶች ባወጡት ሪፖርት ላይ በሳምንት አምስት ጊዜና ከዚያ በላይ ባለ አበባ አትክልቶችን የሚመገቡ ሰዎች ከማይመገቡት ጋር ሲነፃፀር በካንሰር የመጠቃት እድላቸው በግማሽ ቀንሶ ተገኝቷል፡፡

  1. የኦቾሎኒ ቅቤ

ልብዎ ጤናማ እንዲሆንልዎ ከፈለጉ ቁርስዎን ከኦቾሎኒ ቅቤ ይጀምሩ ይላል፡፡ በፔንስልቫኒያ ስቴት ዩኒቨርስቲ ተመራማሪዎች የተካሄደ አንድ ጥናት፡፡ የልብ በሽታ ፆታ ሳይመርጥ ሁሉንም ያጠቃል፡፡ ወንዶች በአረጋዊ እድሜያቸው ላይ በስፋት ይጠቃሉ፡፡ ተመራማሪዎቹ በአሜሪካ የልብ ማህበር የተዘጋጀውን step 11 የተሰኘ የአመጋገብ መመሪያንና በከፍተኛ ቅባት የበለፀገውን ኦቾሎኒን በሁለት ምድብ ለከፈሏቸው ሰዎች በመስጠት ለውጡን መዝግበውታል፡፡ የልብ ማህበሩ እቅድ ብዙ ካርቦሃይድሬትስን በመጠቀም ላይ ያተኩራል፡፡ የኦቾሎኒው እቅድ ደግሞ 36 ከመቶው ስብ ነበር፡፡ ከ24 ቀናት በኋላ በተገኘው ውጤት ሁለቱም መጥፎ (ጎጂ) የሚባለውን LDL ተሰኘ ኮሌስትሮል ቀንሰው ተገኝተዋል፡፡ ኦቾሎኒው በዚህም አላቆመም፡፡ የደም ስቦች (blood fats) ተብለው የሚጠሩትን (triglycerides) መጠን በመቀነስ ጠቃሚውን HDL ኮሌስትሮል ሳይነካ ቀርቷል፡፡ ተመራማሪዎች የኦቾሎኒ ቅቤው ጥቅሙ በእጅጉ ያመዘነ በመሆኑ አዘውትረን እንድንመገበው መክረዋል፡፡

  1. ሃብሃብ

ወንዶች እስከ 55 ዓመታቸው ድረስ ከሴቶች በበለጠ በከፍተኛ የደም ግፊት ይጠቃሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ በፖታሲየም የበለፀጉ ምግቦች በከፍተኛ የደም ግፊትና በልብ ድካም የመጠቃት እድልን ይቀንሳሉ፡፡ ሃብሃብ በፖታሲየም የበለፀገ ነው፡፡ በአንድ ተለቅ ያለ የሃብሃብ ቁራጭ ላይ 644 ሚሊ ግራም ፖታሲየም ይገኛል፡፡ ይህ ከሙዝ ወይም ከብርቱካን ጭማቂ ውስጥ ከሚገኘው ይበልጣል፡፡              

    

Viewing all 15006 articles
Browse latest View live