Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሚኒሶታ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዛሬ ባደረጉት ተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተደረገ ንግግር ሙሉ ቃል

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የ እፎይታ ጊዜያቸውን ጨርሰው ወደ ተቃውሟቸው መመለሳቸውን ጠዋት ላይ በዘ-ሐበሻ ላይ መዘገባችን ይታወሳል። የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ካልተፈቱ ተቃውሟችንን አናቆምም የሚሉት እነዚሁ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በ40 የኢትዮጵያ መስጊዶች፣ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ የተቃውሞ ሰልፍ አድርገዋል። በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢምባሲ ደጃፍ ያደረጉት የተቃውሞ ሰልፍ እና ሴንት ፖል ሚኒሶታ በስቴት ካፒቶል ውስጥ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ለዚህ ተጠቃሽ ነው።

ዛሬ (ጃንዋሪ 24 ቀን 2014 ዓ.ም) ሪሳላ ኢንተርናሽናል ባዘጋጀውና በሚኒሶታ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ የተደረገው ንግግር እንደሚከተለው አስተናግደነዋል።

እጅግ ሩህሩህና እጅግ አዛኝ በሆነው በፈጣሪአችን አሏህ ስም፡-
ውድ አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞች እና እህቶች በቅድሚያ በዚህ ከፍተኛ ቅዝቃዜ የህንን ሰላማዊ ሰልፍ ተግባራዊ ለማድረግ እዚህ በተገኛችሁ በሪሳላ ኢንተርናሽናል ስም እጅግ በጣም አመስግናለሁኝ፤ አሏህ ደግሞ ምንዳችሁን ይክፈላችሁ፡፡
Ethiopian muslims in minnesota
ውድ ወገኖቼ፡-
በዚህ ስፍራ ላለፉት ሁለት አመታት በተከታታይ ለተመሳሳይ አላማ ተሰባስበን ድምጸችንን ስናሰማ ቆይተናል፡፡ ለዚህ ምክንያት የሆነው የሃገራችን ሙስሊም መብት መገፈፍና ጭቆናው ከእለት ወደ እለት አድማሱ እያሰፋ መምጣቱ ነው፡፡ የእምነታችን መብት ጥሰትና የወገኖቻችን እንግልት እሰካላቆመ ድረስ እኛም ከአሏህ ጋር ድምጻችን ማሰማተችንና በተለያየ መልኩ ትግሉን መደገፋችን የቀጥላል፤እዚህ ሆነን ልናደርጋቸው ከምንችላቸው ተግባራት ውስጥ አንዱና ትንሹ ነውና፡፡ አንዳንድ ወገኖች የኛን ጩሀት ጥያቄ ውስጥ ይከቱታል፣ ነግር ግን ልንገነዘብ የሚገባው አጃችን አጣጥፈን በመቀመጥ የሚመጣ ውጤትም የለም፡፡ የህብረት ድምጻችን ቢያንስ በጭቆናው የእሳት ወላፈን የሚለበለቡ ወገኖቻችን ከፍተኛ የሞራል ጥንካሬና የትግል መነቃቃትን ፈጥሯል፤ ይሀውም በተለያዩ መንገዶች ሲገለጹ በተግባር ተመልክተናል፡፡ ስለዚህ ወገኖቼ አሁንም ደግመን ደጋግመን ድምጻችን ይሰማ! የእምነት መብት ይከበር እንበል! እስራቱና እንግልቱ ይቁም! መንግስት ለህግ ተገዥ ይሁን! እንበል፡፡
የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ ትኩረት በውድ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የተላለፈውን ፖለቲካዊ የምንግስት ውሳኔ በመቃወምና በተጓዳኝም ኮሚቴዎቻችን የእስር እንግልት ላይ ሆነው ስለትግሉ ቀጣይነት የሰጡት ታሪካዊ መግለጫ ከልብ በመደገፍ ምንጊዜም ከጎናቸው መሆናችንን ለመግለጽ ነው፡፡ ሪሳላ ኢንተርናሽናል ደግሞ ሶስቱን (ኢቅራዕ፣ ተውፊቅ እና ተውሂድ) ማህበረስብ ወክሎ የትግሉን የእለት ተእለት ሂደት በቅርብ የሚከታተል ሲሆን ከወራት በፊት በጀመረው የኦሮምኛ የሬድዮ ፕሮግራም ስርጭት ሂደቱንን በሳምንት ከ2-3 ቀናት ይዘግባል፤ ዝግጅቱን በድህረ ገጻችን (www.risalainternational.org) ወይንም በስልክ ቁጥር 712-432-7042 በስራም በእረፍት ላይ ሆናችሁ መከታተል ትችላላችሁ፡፡ በአሏህ ፈቃድ የአማርኛ ስርጭትም የሚጀመርበትን ሁኔታ በማመቻቸት ላይ ነን፣ ለሁሉም የናንተን እርዳታና የቅርብ እገዛ ለስኬቱ ወሳኝ ነው፡፡
በውጭ ሀገር ሆነን ለምናደርገው የመብት ማስከበር የትግል እንቅስቃሴ መተባበርንና በአንድነት መስራት ወሳኝ በመሆኑ የዛሬው የተቃውሞ ሰልፍ በተለያዩ የአለማት ክፍል የሚደረጉ ሲሆን እኛም የዚሁ ማህበረሰብ (ጀማ) አካል በመሆን ድምጻችን በማሰማት ላይ ነን፡፡ ሪሳላ ኢንተርናሽናል ከዚህ ስብሰባ በተጨማሪ ሌሎች 18 ያህል የተለያዩ የሙስሊም ኮሚኒቲዎችን በማስተባበር ባለ 6 ነጥብ የጋራ የአቋም መግለጫ የወጣን ሲሆን የህንኑ በተለያዩ ድህረ ገጾችና የሬድዮ ዝግጅቶች ላይ ተለቀዋል፡፡ የህም የትብብራችን መጀመሪያ ሲሆን ይበልጥ ተጠናክረን ሌሎች ወገኖችንም በመጨመር የአሏህ ፈቃድ ሆኖ የበለጠ ስራ እንሰራለን፡፡
በአሁኑ ወቅት የወያኔ/ኢህአዲግ ቡድን አንድን ጥፋት በሌላ ተጨማሪ ጥፋት የሙስሊሙን የትግል እንቅስቃሴ ለማጨነገፍ እየጣረ ነው፡፡ አካልዴማ የኢቲቪ ትረኢት ከሰሞኑ ሌላ አካልዴማ ወልዷል፡፡ ሙስሊሙን ማሰርና ማንገላታት በሌላ ተጨማሪ እስራቶችን እንግልቶች ቀጥሏል፡፡ይህ ሁሉ የጥፋት እርምጃ ሙስሊሙ ለጠየቃቸው ቀጥተኛና ቀላል የመብት ጥያቄዎች ፈጽሞውን ምላሽ ሊሆን አይችሉም፡፡ ትግሉም የተጠየቁት መሰረታዊ መብቶች እስኪመለሱ የሚቀጥል ይሆናል፡፡ የእምነት ነጻነታችንና የእምነት ተቋሞቻችን ነጻ እስካልሆኑ ድረስ ክንዳችንም ሆነ አእምሮአችን ሊያርፍ የሚችልበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ መዳረሻችን ድላችን ነው፡፡ ድላችንም የእምነት ነጻነታችን ነው፡፡ ከዚህም በላይ አልጠየቅንም ከዚህ የተለየ ምላሽ ህዝባችንን ሊያረካው አይችልም፡፡
ውድ ወገኖቼ፡-
አሁንም ደግመን ደጋግመን በኢትዮጵያ ስልጣንን ለተቆጣጠረው ወገን ልናስገነዝብ የምንሻው የጭቆና እጁን ከእምነታችንና ከእምነት ተቋሞቻችን እንዲነሳልን ነው፡፡ የጭቆናው መጠን በዚህ መልኩ ከቀጠለና ማህበረሰባችን የመኖር ህልውና በመፈታተን መጨረሻው ለሁሉም ወገን አደጋ መሆኑን ማስገንዘብ እነወዳለን፡፡
የሀገራችን ዜጎች በሙሉ በተለይም የክርስትና እምነት ተከታይ ወገኖችን እሰካሁን በተያያዝነው ትግል የደረጋችሁልን የአጋርነት ሚና ከልብ የሚያስመሰግን ሲሆን፤ለወደፊቱ በምናደርገውም ተግል ከጎናችን ለመሆናችሁ አንጠራጠርም፡፡ የእመነት ነጻነት መከበር የሁሉም የሰው ልጆች ጥያቄ ነውና፡፡
በድጋሚ በዚህ ሰልፍ ላይ ለተገኛችሁ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን እያቀረብኩ በቀጣይነት ለምደርገው የትግል እንቅስቃሴ ከጎናችን እነድትሆኑ አሁንም ጥሪአችንን እናቀርባለን በተለይም የወጣቶችንና የሴት እህቶቻችን ተሳትፎ ወሳኝ በመሆኑ ሪሳላ ኢንተርናሽናል በጋራ እንድንሰራ ተደጋጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
• ተግላችን የእምነት ነጻነታችን እስኪከበር የቀጥላል!
• ዘወትር ከመፍትሄ አፈላላጊው ኮሚቴ ጎን እንቆማለን!
• በፍትህ ማላገጥ የቁም!
• የሙስሊም ተማሪዎች የእምነት ነጻነት የከበር!
• ፍትህ ለሁሉም!
• አንድነታችን ጥንካሬአችን ነው!
• እስላም ሰላም ነው!
• የድምጻችን ይሰማ ጥሪ ተግባራዊ እናደርጋለን!
• የኢቲቪ የውሸት ተካታታይ ድራማ አያወነብደንም!
• ድምጻችን ይሰማ!
• አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር! አሏሁ አክበር!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>