(ዘ-ሐበሻ) የእፎይታ ጊዜ ወስዶ የነበረው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች እንስቃሴ ዛሬ በኢትዮጵያና በአንዳንድ የዓለማችን ክፍሎች ቀጠለ። ‹‹730 ቀናት ለሃይማኖት ነጻነት›› በሚል ለዛሬ የተጠራው የአርብ (ጁምዓ) መርሀ ግብር በአዲስ አበባ የአንዋር መስጊድ ቁጥሩ በ100 ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ተገኝተው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል። ይህ የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች “የ730 ቀናት የሃይማኖት ነፃነት” እንቅስቃሴ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በሚገኙባቸው የዓለም ክፍላት የሚቀጥሉ ሲሆን በሚኒሶታ ሴንትፖል ከ11:30 ጀምሮ እንደሚደረግ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
ድምፃችን ይሰማ ለዘ-ሐበሻ እንደላከው መረጃ ከሆነ ዛሬ በአንዋር መስጊድ የተደረገው እንቅስቃሴ ከመቼውም ጊዜ በላይ የሕዝብ ወኔ የታየበትና ጥያቄውም እንደሚቀጥል የሚያሳይ ነው።
ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች እስር ቤት የሚገኙት ኮሚቴዎቻቸው እንዲፈቱ ቢጠይቁም፤ ከመንግስት በኩል የተሰጠ ምንም ምላሽ የለም። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች በአደባባይ ድምጻቸውን እስከዛሬ ድረስ ቢያሰሙም መንግስታዊ ሚድያዎች “የሃይማኖት አክራሪነት ወንጀል ነው” የሚሉ ቪድዮችን ከማሳየት ውጭ አንዳችም ቀን ጥያቄያቸውን ዘግበው አለማወቃቸው ሙስሊሞቹን እያስቆጣ የሚገኝ ጉዳይ ነው ተብሏል።
በአንዋር መስጊድ የነበረውን በትንሹ በቪድዮ ለማየት፦