Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት አንዷለም አራጌን እንዳይጠይቁ በልዩ ሀይል ተባረሩ

$
0
0

 

photo0977_001

የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ወጣቱን ፖለቲከኛና የፓርቲው አመራር አንዷለም አራጌን እንዲሁም ሌሎችን የፖለቲካና የህሊና እስረኞች  ለመጠየቅ ቅዳሜ መጋቢት 26 ቀን 2005 ዓ.ም የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ቃሊቲ ቢሄዱም ለመጠየቅ እንዳይችሉ መደረጋቸውንና እስካፍንጫቸው በታጠቁ ልዩ ሃይሎች በግድ ከአካባቢው እንዲርቁ መደረጋቸውን የህዝብ ግንኙነት ክፍሉ አስታወቀ፡፡

እንደፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ገለፃ ከፍተኛው ፍ/ቤት ይግባኝ ሰሚ ችሎት ወጣቱን ፖለቲከኛና ከፍተኛ አመራር አንዱአለም አራጌና ናትናኤል መኮንን ሽብርተኞች እንደሆኑና በሰላማዊ ትግል ሽፋን ሽብርተኝነትን እንደሚያራምዱ ተደርጎ የቀረበው ሀተታና ውሳኔ እጅግ ያሳዘናቸው በርካታ አመራሮችና አባላቱ በከፍተኛ መነሳሳትና ቁጭት ከ 20 በላይ የሚሆኑ የፓርቲው ሰዎች ከ 3፡00 ሰዓት ጀምሮ እንኳን አደረሳችሁ ለማለት ቢገኙም የተሰጣቸው ምላሽ አንዷለምን ምግብ ከሚያመላልሱለት ጥቂት ቤተሰቦቹ ውጭ ማንም መግባት እንደማይችል ተገልፆላቸው በታጠቁ ሃይሎች ከአካባቢው እንዲርቁ ተደርገዋል ብሏል፡፡

በዕለቱ ቃሊቲ እስርቤት ለመጠየቅ ከተገኙት መካከል ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ፣ ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው፣ የተከበሩ አቶ ግርማ ሰይፉ፣ ዶ/ር ያዕቆብ ሀይለማርያም፣ አቶ አክሉ ግርግሬ፣ አቶ ሙላት ጣሰው፣ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን፣ አቶ ተክሌ በቀለ፣ አቶ ትዕግስቱ አወሉ፣ አቶ ዳንኤል ተፈራና ሌሎችም የፓርቲው አመራሮችና አባላት እንደተገኙ የህዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡

የማረሚያ ቤቱ የወቅቱ ተረኞች የስም ዝርዝራቸውን መታወቂያቸውን እያዩ ከተመዘገቡ በኋላ ከአቅማቸው በላይ እንደሆነ ገልጠው ወደ ዋናው የአስተዳደሩ የመግቢያ በር በመግባት ሃላፊዎችን እንዲያነጋግሩ ነግረዋቸው ወደዚያው በማምራት ቢጠይቁም እንዲጠብቁ ከነገሯቸው በኋላ የተሰጣቸው ምላሽ መጠየቅ አትችሉም የሚል ነው፡፡ ከዚህ በፊት በተለይ አንዷለም አራጌን ከጥቂት ቤተሰቦቹ በስተቀር ማንም እንዳይጠይቀው የተደረገ ሲሆን በተደጋጋሚ ቢያመለክትም ምንም ምላሽ ማግኘት አለመቻሉ ይታወቃል፡፡ ከዚህ በፊት ግን የበዓል ቀናት ብቻ የፓርቲው አመራሮችና የስራ ባልደረቦቹ ለተወሰኑ ደቂቃዎች በጅምላ እንዲጠይቁት ቢደረግም በዘንድሮው የትንሳዔ በዓል ግን የገጠማቸው በልዩ የታጠቁ ሃይሎች መባረር ሆኗል፡፡ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ አካባቢውን ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታጣቂዎች ወረውታል፡፡ ለመጠየቅ የመጡት መጠየቅ መብታቸው እንደሆነ ለማስረዳት ቢሞክሩም እነዚህ ሃይሎች መሳሪያቸውን በተጠንቀቅ በመያዝ ፀብ ለማስነሳት ሙከራ አድርገዋል በማለት የህዝብ ግንኙነት ክፍል ገልፆልናል፡፡

http://www.fnotenetsanet.com/?p=4273


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles