አብርሃ ደስታ ከመቀሌ እንደዘገበው ይህ ዜና እየተዘገበ ባለበት ሰዓት (ሓሙስ 08/05/06 ዓም ከቀኑ 11:30 ጀምሮ) በትግራይ ክልል በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ (ጣብያ ሩባ ፈለግ ቁሸት ሕኔቶ) በህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል (በውኃ አጠቃቀም ምክንያት) በተፈጠረ አለመግባባት ሃይለኛ አምባጓሮ ተፈጥሯል። ፖሊሶች ተኩስ ከፍተዋል። እንደ አብርሃ ዘገባ ከ11:30 እስከ 11:40 ሰዓት ባለግዜ ለሰላሳ ሰባት (37) ግዜ ተተኩሷል።
“ምልሻዎች በተጠቀቅ ይገኛሉ።” ያለው የአብርሃ ዘገባ “የመንግስት የሚድያ ሰዎች ሂደቱ እየቀረፁት ነው። የቆሰለ ውይም የሞተ ሰው ስለሞኖሩ ወይ አለመኖሩ በግርግሩ ምክንያት ለማወቅ አልተቻለም። ተኩሱ እየቀጠለ ነው።” ብሏል።
አብርሃ በፌስቡክ ገጹ ጨምሮም በአፅቢ ወንበርታ ወረዳ ህዝብና አስተዳዳሪዎች መካከል ባጋጠመ ግጭት ፖሊስ ቢተኩስም ችግሩ ከፖሊስ አቅም በላይ በመሆኑ አሁን አስተዳደሩ የመከላከያ ሰራዊትን እርዳታ ጠርቷል። አሁን የመንግስት ምልሻዎች በአካባቢው እየተሰማሩ ይገኛሉ። በግጭቱ የተሳተፈው ኗሪ ህዝብ ከሺ በላይ ይሆናል። እስካሁን ድረስ የኗሪው ህዝብ ተወካዮች የነበሩ አራት ሰዎች የት እንደገቡ አይታወቅም። ፖሊሶች ህዝቡን ለመበተን ሃይል ቢጠቀሙም ህዝቡ ግን አራቱ ተወካዮቹ ካልተለቀቁ ላለመበተን አድማ መቷል። ህዝብ እየተሰባሰበ ነው። (የተኩስ ድምፅ በስልክ አስደምጠውኛል)።
በዚህ ዜና ዙሪያ ዘ-ሐበሻ ዘርዘር ያለ መረጃ ከደረሳት ለማቅረብ ትሞክራለች።