ከማስረሻ አህመድ
ከአኗኗራችን፣ ከአመጋገባችን፣ ከአካባቢያችን እንዲሁም በሌሎች አያሌ ምክንያቶች የጤና እክል ይገጥመናል፡፡ እነዚህን እክሎች ደግሞ ለማስወገድ ወደየህክምና ማዕከሎች ጎራ ማለትና ህክምና ማግኘት የተለመደ ነው፡፡ ይሁን አንዳንድ የጤና እክሎችን አሣልፎ ለዶክተሮች መንገር እንዲሁም ማማከር በሀፍረት አልያም በሌላ ምክንያት ደብቀን መፍትሄ የማናገኘበት ደረጃ ተደርሶ ለአያሌ ጉዳቶች እንዳረጋለን፡፡ በዛሬው ጤና አምዳችን በመላው አለም የሚገኙ የወንዶቻችን ችግር ስለሆነው አነስተኛ የብልት መጠን ችግር ነው፡፡ እንደሚታወቀው ይህችግር ህክምና የሚያስፈልገው በውል የታወቀና ባይስተካከል ችግር የሚያስከትል እንከን ነው፡፡ በመሆኑም የዘረፉ ባለሞያዎች አነስተኛ የብልት መጠን ላላቸው ወንዶች የተለያዩ የመፍትሔ አማራጮችን መጠቀም እንደሚቻል ይመክራሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው፡፡
1. የሆርሞን ህክምና፡-
ይህ ቴስቴስትሮን የተባለውንና የወንዳወንድነት ባህሪ የሚያላብሰውን ሆርሞን በመርፌ መልክ በመስጠት የሚደረግ ህክምና ሲሆን ብዙውን ጊዜ በህፃንነት ሲሰጥ ውጤታማነቱ የጎላ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በጎልማሳነት ዕድሜ ላይ መውሰድ አናሳ ውጤታማነት ያለው ነው፡፡
2. ቀላል ዘዴ፡-
አንዳንድ ወንዶች ሰውነታቸው በመወፈሩ የተነሳ ጉያቸው (የብልታቸው አካባቢም) በትርፍ ስብ የሚሞላ ነው፡፡ ይህ መሆኑ የፍትዎት አካለ መጠኑ አንሶ እንዲታይ ያደርገዋል፡፡ በመሆኑም የሰውነት ክብደትን በመቀነስ ብቻ ከበፊቱ የተሻለ የብልት መጠን እንዲኖራቸው በቀላሉ ማድረግ ይችላሉ፡፡
3. መድሐኒቶች፡-
እነዚህ በሚዋጥና በቅባት መልክ ተዘጋጅተው የሚወሰዱ የህክምና ዘዴዎች ሲሆኑ የሚዘጋጁትም ከአንዳንድ ዕፅዋት ነው፡፡ በእነዚህ ዙሪያ የተደረጉ ጥናቶች እንዳስረገጡት ከሆነ መድሀኒቶቹ ውስጥ አንዳንድ ጎጆ በካይ ነገሮች ተገኝቶባቸዋል፡፡ መድሀኒቶቹን በኢንተርኔት በኩል ለሽያጭ የሚቀርቡ ናቸው፡፡
4. ፓምፕ፡-
ይህ በብልት ላይ የሚገጠም አነስተኛ መሳሪያ ሲሆን ትንሽዬ በእጅ የሚሰራ መዝውር ያለው ነው፡፡ ዋና አላማውም በብልት ውስጥ በ4 ያለ ደም እንዲገባ በማድረግ የብልትን ውጥረት በመጨመር መጠኑን ለመጨመር ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ይህ የሚሆነው በብልት ላይ የሚገጠመው መሳሪያ ‹‹ኔጌቲቪ ፕሬዠር›› በመፍጠር የመሳብ ሃይሉም ደምን ከደምስሮች ወደ ብልት ውስጥ በደንብ እንዲገባ ማድረግ ነው፡፡ ልክ ነዳጅን በቱቦ በኩል በአፉ ስቦ እንደማስተላለፉ ይቆጠራል የመዘውሩም ጥቅም ኔጌቲቭ ፕሬዥሩን ለመፍጠር ነው፡፡ ይሁን እንጂ ይህ ሁናቴ ማለትም የመሳብ ሀይሉ ከበዛ ወደ ብልት የሚገባው የደም መጠን በጣም ስለሚጨምር የብልትን ውስጣሚ ለስላሳ አካላት ላይ ጉዳት ሊያስከትልበት ስለሚችል የግፊት አጨማመሩ በፋብሪካው ትዕዛዝ መሰረት ብቻ መሆን ይኖርበታል፡፡ ይህፓምፕ አንዳንዶች ራስን በራስ ለማርካት ዘዴም ይጠቀሙበታል፡፡ በዚህ በኩል ለየት ያለ እውቅና ያተረፈው ደናልድ ቶምስን የተባለው ዳኛ ሲሆን በፍርድ ሂደት ወቅት ማሸኑን በመጠቀም ማስተርቤሽን ሲፈፅም ስለተደረሰበት የአራት አመት እስራት ተፈርዶበት በታሪክ ይዘከራል (እ.ኤ.አ ኦገስት 2006)፡፡ በተለይ በስሜት የመነቃቃት እና የመወጠር ችግር ላለበት ብልት የተዋጣለት ዘዴ ነው፡፡ እንዲሁም ቶሎ የመርካት ችግር ላለባቸው ወንዶችም በሰፊው ጠቀሜታን የሚሰጥ ነው፡፡ መሳሪያው ለረጅም ጊዜ ብልት እንደተወጠረ እንዲቆይ በሰፊው ጠቀሜታን የሚሰጥ ነው፡፡ መሳሪያው ለረጅም ጊዜ ብልት እንደተወጠረ እንዲቆይ የማድረግ ብቃት ያለው ነው፡፡ መሣሪያው በልዩ ስሙ ‹‹ቫኪውም ፓምፕ›› በመባል የሚታወቅ ነው፡፡
5. ተወጣሪ ተቀባሪዎች፡-
እነዚህ የህክምና አማራጮች (Inflatable implards) በመባል የሚጠሩ ሲሆኑ በብልት ውስጥ የሚቀበሩና ከፍተኛ የተለጣጭነት ባህሪ ያላቸው ቀጫጭን ቱቦዎች በቀላሉ በመግባትና እነሱን በመለጠጥ የብልትን የውጥረት መጠን መጨመር ነው፡፡ እንደአስፈላጊነቱ የቱቦዎቹ መጠን ተለቅ ተለቅ ያሉ ማድረግ የሚቻል ሲሆን ለረጅም ጊዜም ብልትን እንደተወጠረ የማቆየት ሀይል አላቸው፡፡ ቱቦዎቹ በብልት ውስጥ የሚቀበሩት በቀዶ ጥገና ሲሆን መጥፎ ነገር የተቀበሩትን ቱቦዎች መልሶ ማውጣት የማይቻል መሆኑ ሲሆን ባይወጡ ግን ጉዳት አያስከትልም፡፡
6. የማለብ ዘዴ፡-
ይህ ዘዴ ዋና ዓላማው በብልት ውስጥ የሚገባውን የደም መጠን በመጨመር የብልትን ውጥረት በሂደት የመጨመር ዘዴ ሲሆን የሚደረገውም በእጅ ጣቶች ነው፡፡ በከፊል የተነሳሳ ብልትን በአውራ ጣትና በሌባ ጣት ጠበቅ አድርጎ በመያዝ ወደ ላይ የመግፋት ሁኔታ ሲሆን አላማውም ደምን ወደ ብልት የማስገባት ሂደት ነው፡፡ ዘዴውም የብለትን ውስጣዊ የደም አቀባበል ውሃ የተነከረን ጨርቅ ከጣቶቹ ስር አብሮ በመጠቀም መከወን የበለጠ ውጤት እንዳለውም ይታወቃል፡፡
7. ክላምፒንግ፡-
ይህ ዘዴ ደግሞ በአንድ የተወጠረ ብልት- ታችኛው ስር አካባቢ ጠበቅ ባለ ቀለበት ወይም የጫማ ማሰሪያ ማሰር ነው፡፡ ብልቱን የሚያስሩት ቀለበት ወይም ክር ዓለማው ወደ ብልት የገባው ደም ወደ ኋላ እንዳይመለስና ብልት በደንብ እንደተወጠረ እንዲቆይ የሚያደርጉ ሲሆን ብልትን በሚገባ ማሸት ዘለቄታዊ ደም የመቀበል አቅሙንና መጠኑን እንዲጨምር ለማድረግም ነው፡፡
8. መለጠጥ፡-
ይህ ዘዴ እንደሚመክረው ከሆነ የብልትን ጫፉ (ክርክሩ አካባቢ) ቀጠን ባለ ገመድ ማሰርና ከዚያም ከገመድ ሌላኛው ጫፍ ከበድ ያለ ነገር በማንጠልጠል ረዘም ላሉ ደቂቃዎች ማቆየት ነው፡፡ ዓለማውም የብለትን የመለጠጥ አቅም ማጎልበት ነው፡፡ ይህም የሚሆነው የብልትን ውስጣዊ ተለጣጭ ክፍል ማለትም (ቱኒካ አልጂኒያን) የተባለውን ክፍል በመለጠጥ ሲሆን ዘዴውም ርዝመትን ብቻ ሳይሆን የውፍረት መጠንንም እንደሚጨምር ይታወቃል፡፡
ውድ አንባቢያን ምንም እንኳን ሁሉም ዘዴዎች መሉ በሙሉ ውጤታማ ናቸው ባይባልም የተወሰነ ለውጥ ግን የሚታይባቸው የህክምና ስልቶች ናቸው፡፡ ይሁን እንጅ ከራስ በራስ ዘዴዎቹ ባሻገር ያሉት የቀዶ ጥገና ህክምናዎችና መድሀኒቶች ብዙም አይመከሩም ፡፡ ምንም ከማድረግ በፊት ግን ሃኪምዎን ማማከርዎን እንዳይረሱ ዘ-ሐበሻ ትመክራለች።