የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 27 ቀን 2006 ፕሮግራም
ለክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ
<...ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ሰማያዊ ተጋዮች ናቸው... ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት እስካሁን በተጓዙባቸው ከተሞች ሁሉ አስቸጋሪ ጥያቄ አልተጠየቁም .....> አቶ ከባዱ በላቸው በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ ፓርቲ ድጋፍ ኮሚቴ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ለሕብር ሬዲዮ ከተናገሩት(ሙሉውን ያዳምጡ)<... ኢትዮጵያዊያን ሳውዲ ባወጣችው የሁለት ወር የመኖሪያና የስራ ፈቃድ እድሳት እንዳይዘናጉ ..... በሳውዲ ያፈሩትን ንብረት አገራቸው ይዘው እንዲገቡ ሊፈቀድላቸው ይገባል ...> ከሳውዲ ያደረግነው ቃለመጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)
በኦባማ ኬር አንዱን ኢንሹራንሰ ከሌላው እንዴት ማበላለጥ እንችላለን? ምንን የሚአሟሉ ኢንሹራንሶችን ነው መግዛት ያለብን?
ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ለጥያቄዎቻችን የሰጡት ውይይት
የገና በዓልን አስመልክቶ ቃለ ምዕዳን ከብጹዕ አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳና የአሪዞና ሊቀ ጳጳስ ጋር ቆይታ አድርገናል
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
- ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በርካታ አፍሪካዊያን ስደተኞች ከመስጠም በጣሊያን በጠረፍ ጠባቂዎች ህይወታቸው ተረፈ
- የሙስሊሙ ሰላማዊ እንቅስቃሴ አራማጆች በእስር ላይ የሚያገኙ መሪዎቻቸውን ለመዘከር እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገለፁ
- አንዷለም አራጌ አዲሱ የአንድነት አመራር ለውጥ ለማምጣት እንዲችሉ መልእክት አስተላለፈ
- ከ63 ሚሊየን ሽልንግ በላይ የሚያወጣ አደንዛዥ እፅ በሆዱ ይዞ በኢትዮጵያ አየር መንገድ ለመሄድ የሞከረው ተያዘ
- ሳውዲ አረቢያ ለመኖሪያና ለስራ ፈቃድ እድሳት ተጨማሪ የሁለት ወር ጊዜ ሰጠች
- የቀድሞው ፕሬዝዳንትና ልጃቸው ለደላላ ባለመክፈላቸው ተከሰሱ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን