Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

እስር ላይ የሚገኘው አንዷለም አራጌ አዲሱን የአንድነት አመራር “ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት”አላቸው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በዘ-ሐበሻ አንባቢዎች ዘንድ የ2005 ዓ.ም የዓመቱ ምርጥ ሰው ሽልማትን ያገኘውና በ እድሜ ልክ እስራት በገዢው መንግስት ተበይኖበት ቃሊቲ የሚገኘው አንዷለም አራጌ ዛሬ ጠዋት ሊጠይቁት የሄዱትን አዳዲሶቹን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች “ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት፤ ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋ አለኝ” ማለቱን ከአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ገልጸዋል።
Andualem aragie
ባሳለፍነው ሳምንት የፕሬዚዳንት ነጋሶ ጊዳዳን እና ካቢኔያቸውን በምርጫ አሰናብቶ በአዲስ የሾመው አንድነት ፓርቲ፤ አዳዲሶቹ ተሿሚዎች ስልጣናቸውን ከተቀበሉ በኋላ የመጀመሪያ ሥራቸውን ያደረጉት በ እስር ቤት የሚገኙትን የፓርቲዎቻቸውን አባላት መጠየቅ ነበር። በዚህም መሠረት አዳዲሱ አመራር እስር ቤት ከሚገኙት የድርጅቱ አመራሮችና አባላት የሚያበረታቱ ምክሮችን መቀበሉን ከዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ዘገባ ለመረዳት ተችሏል።

አንዷለም አራጌ በአዲሱና በወጣት በተገነባው የአንድነት ፓርቲ አመራር ደስተኛ መሆኑን ገልጾ “ሕዝቡን ለመብቱ እንዲታገል አንቁት፤ ሕዝቡ መብቱን አውቆ ለመብቱ እንዲነሳ በማንቃት ለውጥ ለማምጣት ጠንክራችሁ ሥሩ፤ እንደምታደርጉትም ተስፋ አለኝ” ብሏቸዋል። ይኸው የአንድነት ፓርቲ አመራር እዛው ቃሊቲ የሚገኙትን እነ ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ጨምሮ ሌሎች የሕሊና እስረኞችን ለመጠየቅ ጠይቆ መከልከሉ የታወቀ ሲሆን ወደ ዘዋይ ያመራው የአንድነት ፓርቲ ቡድን እዛው እስር ቤት የሚገኙትን ን የአንድነት የብሄራዊ ምክር ቤት አባል አቶ ናትናኤል መኮንንና በዚያ የሚገኙ ሌሎች እስረኞችን መጎብኘታቸውም ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በሕወሓት/ ኢሕአዴግ አስተዳደር “በሽብርተኝነት ወንጀል” ተከሷል፤ በሌሎች ኢትዮጵያውያን ዘንድ ደግሞ የሕሊና እስረኛ ነው የሚባለው አንዷለም አራጌ ከዚህ ቀደም ከ እስር ቤት ተቃዋሚዎች የእኔን እስር ቤት መማቀቅ ልትጠቀሙበት አልቻላችሁም፤ ሕዝቡን ለማታገል ልትጠቀሙበት ትችሉ ነበር ሲሉ የነበረውን ድክመት መግለጹን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ አይዘነጋም።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>