Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በሚኒሶታ የደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ምእመናን “የሕዝብ ድምጽ ይከበር”ሲሉ መግለጫ አወጡ

$
0
0

የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ በገለልተኝነት እንዲቆይ በሕዝብ ድምጽ ብልጫ መወሰኑ ይታወሳል። ሆኖም ግን ይህን ውሳኔ የቤ/ክርስቲያኑ ካህናት ለመቀልበስ ጥረት በማድረግ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙት ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ምእመናን የሚከተለውን መግለጫ አውጥተው በትነዋል።

12/26/2013

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ ፤አሜን!

ለሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ ምዕመናን

የሕዝብ ድምጽ ይከበር!!! የምንኖርበትን አገር ሕግና ሥርዓትም እናክብር!!!

deb

ባለፈው ዲሴምበር 15/2013 ዓ.ም የቤተክርስቲያናችን ጠቅላላ የአባላት ጉባኤ የደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ገለልተኝነት አስመልክቶ ባለበት እንዲቀጥል በከፍተኛ የአብላጫ ድምጽ መወሰኑ ይታወቃል። ይህም ታሪካዊና አርአያ የሆነ፤ ዲሞክራሲያዊ አሰራር የሰፈነበት ስብሰባ ይበል የሚያሰኝ ነው።

የሕዝብ ውሳኔም ከማንምና ከሁሉም በላይ ስለሆነ ማክበርና ማስከበር ደግሞ የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ይሁን እንጂ አንዳንድ የአስተዳደር ቦርድ አባላት ድርሻና ኃላፊነታቸውን በቅጡ ያልተረዱ ካሕናት ይህንን የሕዝብ ውሳኔ በተዛባ መልክ በመተርጎም የተላለፈውን ውሳኔና ወደፊት ቢደረጉ ይጠቅማሉ ተብለው በሀሳብ ደረጃ የቀረቡትን በመደባለቅ ሰላምና አንድነትን ለማወክ የሚደረገው አካሔድ እጀግ አሳዝኖናል አስቆጥቶናል።

በተለይም የቤተክርስቲያኑ ተቀዳሚ ካህን/ መንፈሳዊ አባት ከኃላፊነታቸው ውጪ የጠቅላላው ስብሰባ ውጤትን ካሕናቱ ባቀረብነው ሃሳብ መሰርት ነው የተወሰነው በማለት ሕዝቡ ከወሰነው ውሳኔ በተዛባ መልኩ መናገራቸው የሕዝብን ድምጽ እንደመናቅ ሆኖ አግኝተነዋል። ሕዝቡ በምን ላይ ድምጹን እንደሰጠ ጠንቅቆ ያውቀዋል። የስብሰባውንም ውጤት ለሕዝብ የመግለጽ ሥልጣንና መብት ያለው የቦርዱ ሊቀመንበር ብቻ ናቸው።

በቤተክርስቲያናችን የመተዳደሪያ ደንብ አንቀጽ 6 ክፍል 3 ፊደል ’ሀ’ ተ.ቁ. 6 ላይ የቤተክርስቲያኑ ይፋዊ/ኦፊሴሊያዊ/ ቃል አቀባይ የቦርዱ ሊቀመንበር መሆኑን በግልጽ ይደነግጋል። በመተዳደሪያ ደንቡ አንቀጽ 7 በፊደል ‘ሠ’ ላይም የቤተክርስቲያኑ ተቀዳሚ ካህን እንደማንኛውም የባላአደራዎች ቦርድ አባልነታቸው ለቤተክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ ድንጋጌዎች ሁሉ ተገዢ ናቸው ይላል። ስለዚህ ይህ አካሔድ በአስቸኳይ ሊታረም ይገባዋል እንላለን።

ከዚህም በተጨማሪም በሥርዓተ ቅዳሴ ም.2 ቁ 43 ላይ ማንም ቅዳሴውን ማወክ እንደማይገባው እንዲህ በማለት ይገልጻል። ‘ ክቡር ሚስጢርን ለመቀበል የተሰበሰቡ ምእመናን ሁሉ የእግዚአብሔርን ነገር ለመስማት ከቤተክርስቲያን ውስጥ በጸጥታ ይቁሙ። የሚናገርም የሚስቅም አይኑር፤ቤተክርስቲያን የነገር ቦታ አይደልችምና የጸሎት ቦታ ናት እንጂ። ’ ይህንን የሚያውቁ ካህናት ግን የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማናጋት የሕዝቡን ውሳኔ ላለመቀበል ከሚያንገራግሩ ሰዎች ጋር ወንጌል እየተሰበክ በመቅደስ ውስጥና ከመቅደስም በመውጣት ስብሰባ በማድረግ ቆመንለታል የሚሉትን ሥረዓተ ቅዳሴ ራሳቸው ሲጥሱት ተስተውለዋል። ይህም ድርጊት ፈጽሞ መደገም የማይገባው ነው በማለት እንመክራለን።

የምንኖርበትን አገር ሕግና ሥርዓት ተከትሎ በሰላም እያመለከ ያለን ግለሰብም ሆነ ስብስብ በማንኛውም መንገድ መረበሽና ሰላምን ማደፍረስ፣ ረብሻን ማነሳሳትና ከሥረዓት የወጣ ድምጽ ማሰማትም ሆነ ተቃውሞ ማድረግ በአሜሪካ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ 9/42 መሰረት የሚያሰቀጣ ነው።

ምንም እንኳን ክርስትና ወንድምን/እህትን በአለማዊ ፍርድ ቤት ከሶ ማስቀጣትን ባይደግፍም ለቤተክርስቲያናችን ሰላምና ሥርዓት መከበር ስንል ከሥርዓት በመውጣት ሰላማችንን ለማደፍረስ

የሚሞክሩትን ሁሉ ለሕግ አካላት የምንከስ መሆኑን አበክረን እናስገነዝባለን። ሕግን አለማወቅ ከቅጣት አያድንም እና!

በሕዝብ በተላለፈው ውሳኔም ሆነ በቤተክርስቲያኑ አስተዳደር አቋም ላይ ቅሬታ አለኝ የሚል ሁሉ ይግባኙን አግባብንት ላለው አካል በሕጋዊ መንገድና ሥርዓትን በተከተለ መልኩ ብቻ ማቅረብ ይኖርበታል። ካሕናቱም ቢሆኑ በዚህ አገር የቤተክርስቲያናት ማቋቋሚያ ሕግጋት የሚመሩና የሚተዳደሩ እንጂ አሜሪካን አገር ላይ በሥራ ሊውል በማይችል የኢትዮጵያ የቤተክርስቲያን ማስተዳደሪያ ደንብ መሰረት የሚተዳደሩ እንዳልሆኑ ሊያውቁ ይገባል።

ስለሆነም የክርስትና ሕይወታቸው ብቻ ሳይሆን ሥጋዊ ሪከርዳቸውና ሕይወታቸውም ቢሆን ችግር እንዳይገጥመው ሊያስቡበት ይገባል እንላልን። ሕግን ባለማወቅ ወይንም ባለመረዳት በሌሎች አካባቢዎች ሁከት በመፍጠር በቤተ ክርስቲያን ላይ የደረሰው ሥርዓት አልበኝነት በሚኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ላይ ፈጽሞ እንዲከሰት አንፈቅድም።

ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>