ነቢዩ ሲራክ
* በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ የተጀመረውን ፍተሻ በማረጋገጥ ህጋዊ ሰነድ የሌላቸው ዜጎች በሰላማዊ መንገድ በአስቸኳይ ለጸጥታ አስከባሪዎች እጅ በመስጠት ወደ መጠለያ በመግባት ወደ ሃገር እንዲገቡ ማምሻውን ባወጣው ማስታወቂያ አሳስቧል ። ካለፉት ሳምንታት ወዲህ በሪያድ መንፉሃ በኢንባሲውና በሃገር ሽማግሌዎች የተቋቋሙ የመረጋጋት ኮሚቴ አባላት ወደ መንፉሃና ኢትዮጵያውያን በሚበዙባቸው ምንደሮች በመንቀሳቀስ ዜጎች ያለ ምንም ጉዳት እጃቸውን ሰጥተው ወደ ሃገር ለመግባት እንዲዘጋጁ የመከረ ቢሆንም ጥረቱ አልተሳካም ነበር ። የሪያድ ኢናባሲ የሽማግሌዎች ኮሚቴ አባላት ባደረጉት ቅስቀሳ ወደ ሃገር ለመግባት ባልተጨበጠ ተስፋ የተዘናጉ ህጋዊ መኖሪያ ፈቃድ ያልያዙ ወደ ሃገር በመግባቱ ላይ እንዳያቅማሙ መምከራቸው ይጠቀሳል !
* አሁን በተጀመረው የመንፉሃ ፍተሻ ማዋከብ የለበትም ። ህጋዊ መኖርያ ፍቃድ የሌለውን ብቻ እንደሚይዙና ከአሰሪው (ከከፊሉ) ጋር ይሰራል አይሰራም የሚባል ማጣራትም ሲካሔድ አልተስተዋለም ተብሏል ።
* ከአሰሪው ጋር የማይሰራ እንደ ህገ ወጥ እንደሚቆጠር የሳውዲ ህግ በግልጽ ያሳወቀ ሲሆን የጅዳና የሪያድ ኢንባሲ ይህ ህግ እንደሚጸና ተደጋጋሚ ማስታወቂያ በማውጣት “በሰላም ወደ ሃገራችሁ ግቡ!” በማለት ሲመክሩና ሲወተውቱ ሰንብተዋል።
* በቀጣዩ መጠነ ሰፊ የማጣራት ዘመቻም ከአሰሪው (ከከፊሉ) ጋር የማይሰራ እንደ ህጋዊ ስለሚቆጠር የሳውዲ መንግስት በፈቃደኝነት እጃቸውን የሚሰጡት ወገኖች ወደ ሃገር መስደድ እንደተጠናቀቀ አንወጣም ባሉት ላይ ፍተሻ በማድረግ በእስራትና በገንዘብ እንደሚቀጣ በኢንባሲና በቆንስል መስሪያ ቤቶች በኩል ባስተላለፈው ማስጠንቀቂያ አስታውቋል ።
* ቁጥራቸው በሽዎች የሚገመቱ ዜጎች እስካሁንም ድረስ ወደ ሃገር ግቡ የሚለውን ጥሪ ባለመቀበል የተዘናጉበት ሁኔታ ይስተዋላል ። ይሁን እንጅ ካለፉት ሁለት ቀናት ወዲህ መንቀሳቀስ ያልጀመረው የጅዳ አካባቢ በርካታ ነዋሪዎች ወደ ሃገር ቤት ለመግባት ወደ ተዘጋጀው መጠለያ በመግባት ላይ ናቸው ። ከአሰሪያቸው ጋር ስለማይሰሩ ህገ ወጥ የተባሉት ግን አሁንም እንቅስቃሴ አለማሳየታቸው ይመለከታል ።
* የጅዳ ቆንስልና የወገን ለወገን ደራሽ ኮሚቴውም አውቶቡስን በአፋጣኝ እንዲቀርብ በማድረጉ ረገድ ከቆንሰሉ ሃላፊዎች ጋር በመተባበር ለነዋሪው ድጋፍ በማድረግ ላይ ናቸው ። ህጋዊ ሰነድ የሌላችሁ አስፈላጊውን ውሳኔ መውሰድና በእድሉ መጠቀም ይጠበቅችኋል። እድሉን መጠቀም መቻል ብልህነት ነው !
ጀሮ ያለው ይስማ
ነቢዩ ሲራክ