የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 13 ቀን 2006 ፕሮግራም
<... ሻምበል ፍቅረ ስላሴ ወግደረስ አዳዲስና ከዚህ በፊት የማናውቃቸውን ጉዳዮች በመጽሐፋቸው አንስተዋል ...ራሳቸው ሁለት ጊዜ ሕይወታቸው አጣብቂኝ ውስጥ የገባበት ሁኔታን ጨምሮ የተለያዩ ወሳኝ መረጃዎችን አንስተዋል። ይህም መጽሐፍ ለታሪካችን አንድ ማስረጃ ነው...>አቶ ኤልያስ ወንድሙ የጸሐይ አሳታሚ ባለቤትና ስራ አስኪያጅ ከሶስት ቀን በሁዋላ ለገበያ ስለሚቀርበው የሻምበል ፍቅረ ስላሴ <<እኛና አብዮቱ>> መጽሐፍ ከህብር ሬዲዮ ተጠይቆ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ ሙሉውን ያዳምጡት
<<... በኢትዮጵያ ያለው አገዛዝ በዘር ላይ የተመሰረተ የአፓርታይድ ስርዓት ነው። ...በኢትዮጵያ ያለው የጎሳ ችግር ከደቡብ ሱዳን የበለጠ ነው። ተቃዋሚዎች ብቻ ሳይሆኑ ሚዲያው፣የሐይማኖት አባቶች በአጠቃላይ ሁሉም ዜጋ በሱዳን የተከሰተው የዘር ግጭት እንደ ትልቅ ማስተማሪአ ወስደን በኢትዮጵያ እንዳይከሰት መስራት አለብን...>> አቶ ኦባንግ ሜቶ ስለ ደቡብ ሱዳን የሰሞኑ ግጭት ለህብር ከሰጡት የተወሰደ
የሱዳኑ አልበሽር ኢትዮጵያና ኤርትራን በእርግጥ ለማስማማት ወይስ ሁለቱ መንግስታት በተቃዋሚዎቻቸው የሚደርስባቸውን ለመከላከል? እውነት ይስማማሉ? አቶ መለስ የሰጉበትን የጓዶአኤርትራን ፍላጎት ዕውን ሕወሃት ማሟላት ይችላል ? የተቃዋሚዎቹስ ሚና(ትንታኔ)
የኦባማ ኬር የመጀመሮያ ዙር ምዝገባ ሰኞ(ከአቶ ተካ ከለለ ጋር ከአትላኢታ ቲኪ ዲሴምበር 23 ይጠናቀቃል።…ኢንሹራንስ ያለውም ተመዝግቦ የገበያ አማራጩን ማየት አለበት? (ስለ ኦባማ ኬር ከአቶ ተካ ከለለ ጋር )
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
- በደቡብ ሱዳን የተከሰተው የጎሳ ግጭት በኢትዮጵያ እንዳይከሰት የሚመለከታቸው ሁሉ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ተጠየቀ
- ማንዴላን ያሰለጠኑት ኢትዮጵያዊ መኮንን ለቀብሩ ለመሔድ ቪዛ መከልከላቸውን በምሬት ገለጹ
- ኢትዮጵያ በደቡብ ሱዳን ጉዳይ እጇን እንዳታስገባ ተጠየቀ
- በጋዜጠኛ ርዮት ዓለሙ ላይ የተሰጠው የፍርድ ውሳኔ የዳኛው የእጅ ጽሑፍ ሳይሆን የሌላ ሰው መሆኑ ተገለጸ
- ምስጢሩ ሰኞ በርዮት የ30ኛ ወራት እስራት ይፋ ይሆናል
- በሳውዲ በሸሚሴ መጠለያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ አቀረቡ
- ከሳውዲ የመጡ እና በአገር ቤት ያሉ ወጣቶች ተፋጠዋል
ሌሎችም ዜናዎች አሉን