በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ በፌስቡክ ገጹ እንደዘገበው፦
የዛሬው የሽሜሲ መጠለያ ሁከት …
የጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ” ህጋዊ ሰነድ የማታሟሉ ወደ ሃገር ቤት ግቡ! ” ያወጣውን ተደጋጋሚ መረጃ ተከትሎ ከአምስት ቀናት ጅምሮ ወደ ሽሜሲ መጠለያ በአስር አውቶቡስ በላይ ሆነው የገቡ ኢትዮጵያውያን ሜዳ ላይ ተጥለው ለከፋ መጉላላት መዳረጋቸው ገልጸዋል። አኒሁ ቅሬታ አቅራቢ ዜጎች በማከልም የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ዛሬ ጠዋት ሊያነጋግሯቸው የመጡ ቢሆንም ” ተረጋጉ እንመለሳለን !” ብልዋቸው መፍትሄ ሳይሰጧቸው እንደሄዱ ገልጸውልኛል። የሃላፊዎች ሙሉ ቀን መጥፋት ያበሳጫቸው ነዋሪዎች ዛሬ ከቀትር በኋላ በነፍሰ ጡር ፣ በህጻናት ላይ እያደረሰ ያለውን መንገላታት እየጎዳቸው መሆኑን በመግለጽ ለሳውዲ ሃላፊዎችን መፍትሔ ቢጠይቁም ” መፍትሄው በእናንተ ሃላፊዎች እጅ እንጅ ፣ በእኛ እጅ አይደለም! ” በማለት እንደመለሱልቸው እና ነዋሪው በብስጭት አስወጡን በሚል ወደ በሮች ቢጠጋም በወታደሮች መከልከላቸው በምሬት ገልጸውልኛል። ለሶስት ሰአታት በመጠለያው ውስጥ በተከሰተው ተቃውሞ የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ጉዳዩን አሳሳቢነት በመረዳት ወደ ቦታው በመሄድ ነዋሪውን አለማረጋጋታቸውን ብዙዎችን አሳዝኗል ።
ዛሬ በሽሜሲ መጠለያ የተነሳው ግርግር መንስኤነት በጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች እና በሳውዲ የመጠለያው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጋር በተከሰተ አለመግባባት እንደሆነ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረጉት ሙከራ ለመረዳት ችያለሁ! የአለመግባባቱ ምንጭም መኖሪያ ፍቃዳቸውን ጥለው ወደ ሃገር የሚገቡ ዜጎችን ሰነድ ማጓተት ተከትሎ የቆንስል ሃላፊዎች ” ወደ ሃገር መግባት የሚፈልጉ ዜጎቻችን የመውጫ ሰነድ እስካልተሰጠ ድረስ ሰነድ አንሰራም!” አስገዳጅና ጠቃሚ መከራከሪያ በማቅረባቸው እንደሆነ ያሰባሰብኳቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ! ጉዳዩን ለማጣራት ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ስልክ በመደወል ያደረግኩት ሙከራ አልተሳካም ።
የሽሜሲ ተቃውሞ እልባት ሳያገኝ በዚህ መልኩ ከቀጠለ እና ነዋሪዎች በሁኔታው ተማረው በሚወስዱት ተቃውሞ ለረብሻና ሁከት ሰበብ እንዳይሆን ሊታሰብበት የሚገባ ሲሆን ነዋሪውም ምግብና ውሃ በአግባቡ እስከ ቀረበ ድረስ ጉዳዩን በትዕግስት ሊጠባበቁ እንደሚገባ ይመከራል! በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ ሃገር እንግባ በሚል በግላቸው ወደ ሽሜሲ መጠለያ የሄዱት በመቶዎች የሚቆጠሩ ዜጎችም በመጠለያው በት በመጉላላት ላይ መሆናቸውን ገልጸውልኛል። አቤቱታቸውን በተደጋጋሚ ያቀረቡልኝ ነዋሪዎች እኔን ሳይቀር “ድምጻችን አታፍንብን ፣ ለአለም አሰማልን! “ሲሉ ሃይለ ቃልን ጨምረው ወቅሰውኛል !
ቸር ያሰማን