Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በቬጋስ ላለፉት ሁለት ወራት በሥራ ማቆም አድማ ላይ የነበሩ የታክሲ አሽከርካሪዎች በድል ወደ ሥራ ተመለሱ

$
0
0


የሀበሻውን ህ/ሰብ ላደረገላቸው እገዛ አመስግነዋል
የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ተቃውሞ ቀጥሏል

በቬጋስ ለሁለት ወራት በዘለቀ የስራ ማቆም አድማ ላይ የቆዩት የየሎ ቼከር ስታር የታክሲ አሽከርካሪዎች በዩኒየኑ አማካኝነት ሲያደርጉት የነበረውን የኮንትራት ድርድር የኩባንያውን ማሻሻያ ተቀብለው ወደ ስራ ለመመለስ ዛሬ በቬጋስ የኩባንያው ቅጥር ግቢ ዛሬ ሐሙስ ሜይ 2/2013 ባደረጉት ስምነት ወደ ስራ ለመመለስ ወሰኑ።የአሽከርካሪው ተወካዮች 75 በመቶ ድል አግኝተናል ሲሉ ገልጸዋል።
vegas ethiopian and erirtian taxi drivers
አቶ ሽመልስ ደረሱና አቶ ቢኒያም ሰመረአብ የአሽከርካሪዎቹ የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪዎች ሁለቱ በጋራ ለህብር ሬዲዮ ዘጋቢ በሰጡት መግለጫ በስራ ማቆም አድማው ሲጠይቋቸው ከነበሩ በርካታ ጥያቄዎች መካከል የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም የተወሰነ ሳንቲም ጭማሪ፣የፔሮል አከፋፈል ግልጽ እንዲሆን መደረግ፣ በአድማው ላይ የነበሩ አራት ዓመት ድረስ ሲገቡ የስራ ዋስትና እንዲከበርላቸው መደረጉ፣ የዓመት ፈቃድም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንደተጠበቁ መሆን በዋና ዋናነት ይጠቀሳሉ።
<<ለስራ ማቆም አድማው ስኬት የኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አሽከርካሪዎች በአንድ ላይ መቆም ነው ውጤት ያመጣው..>> ያሉን እነዚህ የተቃውሞ አስተባባሪዎች በከተማዋ የሚኖሩ የቢዝነስ ተቋማት፣የተለያየ ሙያ ያላቸው ግለሰቦችና ተቃውሞው በቀጥታ የማይመለከታቸው በስራ ላይ ያሉ አሽከርካሪዎች ህብር ሬዲዮም ላደረገው ሙያዊ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
<<ማርች 29 ተቃውሞ የጀመሩትና ዛሬም በስራ ማቆም አድማ ላይ የሚገኙት የፍሪያስ ኩባንያ በአብዛኛው ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን አሽከርካሪዎች ችግር ስላልተፈታ ውጤት እስኪያመጡና እንደኛ በድል እስኪገቡ አብረናቸው ነን>> ያሉት ሁለቱ የተቃውሞ አስተባባሪዎች ለነሱ ስራ ቢጀምሩም <<ቢኬት ላይን>> በእረፍታቸው ከመቆም ጀምሮ ሙሉ ድጋፋቸውን እንደሚሰጡ የቀረውም ህ/ሰብ የጀመረውን ድጋፍ እንዲቀጥልላቸው ጠይቀዋል።
<<በፍሪያስ የሚሰሩ 72 በመቶ የሚሆኑ ሀበሾች ቢተባበሩ የእኛን ያህል ሳይቆዩ ለውዐጥ ማምጣት ይችላሉ።የሚያሳዝነው ብዙዎች ለጋራ የመብት ትግል የቆሙ ወገኖቻቸውን ችላ ብለው አሁንም ይሰራሉ።ከነዚህ ከሶስቱ ሁለቱ ተቃውሞውን ቢቀላቀሉ ውጤት ይመጣል።እነዚህ ወገኖች የእኛን ድል አይተው ከወገኖቻቸው ጎን ሊሰለፉ ይገባል አሁንም አልረፈደም ሊያስቡበት ይገባል>> ያሉት አቶ ሽመልስ ደረሱ በስራ ላይ ሆነውም የፍሪያስ አሽከርካሪዎች ተጽዕኖ ለመፍጠር የሚያደርጉትን ማንኛውንም እንቅስቃሴ በዕውቀትም ስራ የጀመሩት ሁሉ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።
በዛሬው የኮንትራት ስምምነት መሰረት የየሎ ቼከር ስታር የኩባንያው 1800 ታክሲ አሽከርካሪዎች ለሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በአዲሱ የኮንትራት ስምምነት መሰረት ይሰራሉ።በቬጋስ ካሉት የታክሲ ኩባንያዎች ዛሬ ከስራ ማቆም አድመኞቹ ጋር የተስማማው ሁለተኛው ሲሆን አሁን በተቃውሞ ላይ የቀሩት አሽከርካሪዎች የሚሰሩበት ፍሪያስ ኩባንያ አንደኛው ትልቁ ሲሆን ሁለት ሺህ አሽከርካሪዎች ሲኖሩት ከነዚህ ውስጥ 72 በመቶ የሚሆኑት ኢትዮጵያውያንና ኤርትራውያን ቢሆኑም ከዚህ ቀደም ሲያነሱት ለነበረው የጋራ መብታችንን የሚያስከብር ኮንትራት ይኑር ጥያቄ የስራ ማቆም አድማ ሲያደርጉ ተከፋፍለው መቆማቸው ለእርስ በእርስ የቃላት ጦርነት ውስጥ ገብተዋል። ችግሩ ወደ ከፋ ማህበራዊ ቀውስ ከመሄዱ በፊት በአንድ ላይ እንዲቆሙ ተደጋጋሚ ጥሪ ሲደረግ ቆይቷል።
ዮናስ ተሰማ የፍሪያስ የስራ ማቆም አድማ አስተባባሪ ለህብር ሬዲዮ በሰጠው መግለጫ በየሎ ቼከር ስታር አሽከርራሪዎች ድል አግኝተው መግባት መደሰቱን ገልጿል። የፍሪያስ አሽከርካሪዎችም በአንድ ላይ ቆመው ውጤት እንዲያመጡ ማመን እና ለመብታቸው የጀመሩትን ትግል በውጤት እንደሚያጠናቅቁ ያለውን ተስፋ ገልጾ ዛሬም በታቃውሞ ላይ ያሉ ባልደረቦቹን እንበርታ በአንድ ላይ እንቁም ሲል ጥሪ አስተላልፏል።
በቬጋስ የታክሲ አሽከርካሪዎች ታሪክ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ይህ ተቃውሞ አሁን የተጀመረው የመብት ጥያቄ ውጤት ካስገኘ በሁዋላ እያንዳንዱ አሽከርካሪ የራሱን ሜዳሊያ ለማግኘት በጋራ ቆሞ የሚታገልበትን ስልት ወደፊት እንደሚነድፉ አስተባባሪዎች ጠቅሰዋል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>