በአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርት (አንድነት) በሰላማዊ ትግልና ባህሪያቱ ክፍል አራት በአቶ ግርማ ሞገስ በስካይፕ የሚሰጠው ስልጠና ተጠናቋል። ዝርዝሩ ዝቅ ብሎ ቀርቧል።]
አምባገነኖች ስልጣን ላይ ለመቆየት ህጋዊነት፣ የህዝብ ድጋፍ እና ትብብር፣ የአገር ተፈጥሮ እና የኢኮኖሚ ሃብት ባለቤትነት የተባሉትን የፖለቲካ ኃይል ምንጮች መቆጣጠር አለባቸው። የፖለቲካ ኃይል ምንጮች የሚኖሩት ሰማይ ውስጥ ወይንም አምባገነኖች ደም ውስጥ ሳይሆን ባለቤታቸው ከሆነው ህዝብ ጋር እንደሆነ በስልጣና ክፍል ሶስት አጥንተናል። እርግጥ አምባገነኖች በእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ላይ ያላቸውን ቁጥጥር የሚያገኙት ህዝብ ፈቅዶላቸው ወይንም ፈርቶዋቸው ወይንም የተወሰነው ህዝብ ፈቅዶላቸው የቀረው ህዝብ ደግሞ ፈርቷቸው ሊሆን ይችላል። ያም ሆነ ይኽ የእነዚህ የፖለቲካ ኃይል ምንጮች ባለቤት እራሱ ህዝብ እንደሆነ ግልጽ ነው። ለዚህም ነው የፖለቲካ ኃይል ምንጭ ማለትም የመንግስት ስልጣን ምንጭ ወይንም ባለቤት ህዝብ ነው የሚባለው። ህዝብ የፖለቲካ ነፃነቱን የሚነጠቀውም ይኽን የፖለቲካ (የመንግስት) ስልጣን ባለቤትነቱን በኃይል በአምባገነኖች ሲነጠቅ ነው። ነፃ ሆኖ የተወለደ የሰው ዘር ለምን ነፃነቱን ለጥቂት አምባገነን ገዢዎች አስረክቦ ካለነፃነት መገዛትን ይቀበላል? የሚለውን ጥንታዊ የፖለቲካ ፈላስፎች እና ተመራማሪዎች ጥያቄ አንስተን በክፍል ሶስት ማጥናታችን ይታወሳል።
ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ