ዘ-ሐበሻ በዛሬ ጠዋት ሰበር ዜናዋ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ውስጥ 10 በነፃ እንዲሰናበቱ፣ 14ቱ ዋና ዋና መሪዎች እንዲከላከሉ፣ ሌሎች 4ት ተጠርጣሪዎች የሽብርተኝነት ክስ ዝቅ ተደርጎ ሰውን በማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ መወሰኑን መዘገቧ ይታወሳል። ለአንባቢዎቻችን ግልጽ እንዲሆን በማሰብ ማን እነማን ተከላከሉ እንደተባለ፣ ማን እንዲፈታ እንደተወሰነ፣ ማን ክስ ዝቅ እንዲደረግለት እንደተደረገ ስም ዝርዝራቸውን ይዘናል። በነጻ የተሰናበቱት የእስር መፍቻ እንዲጻፍላቸው እና ይከላከሉ የተባሉት ደግሞ መከላከያ ማስረጃዎቻቸውን እንዲያሰሙ ከጥር 22 ጀምሮ ፍርድ ቤቱ ተከታታይ 5 ቀናት በተለዋጭ ቀጠሮ ለሕዝብ ክፍት በሚሆን ችሎት እንደሚያቀርቡ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል።
1. ኡስታዝ አቡበከር አህመድ
2. ኡስታዝ አህመዲን ጀበል
3. ኢንጅነር በድሩ ሁሴን
4. ኡስታዝ ያሲን ኑሩ
5. ኡስታዝ ካሚል ሸምሱ
6. አሕመድ ሐጂ ሙስጠፋ
7. ኡስታዝ ሰኢድ አሊ
8. ጋዜጠኛ አቡበከር አለሙ
9. ሙኒር ሼኽ ሑሴን
9. ሙባረክ አደም ጌቱ
10. ሷቢር ይርጉ ማንደፍሮ
11. ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸው ዘውዴ
12. ካሊድ ኢብራሂም
13. አብዱረዛቅ አክመል
14. ሙሐመድ አባተ
የቀረበባቸው የሽብርተኝነት ክስ ዝቅ ተደርጎ ሰውን በማነሳሳት ወንጀል እንዲከላከሉ የተወሰነባቸው
1. ሸኽ መከተ ሙሄ
2. ወንድም ኑሩ ቱርኪ
3. ኡስታዝ ባህሩ ዑመር
4. ወንድም ሙራድ ሽኩር
በነፃ እንዲሰናበቱ የተደረጉት፦
1. ዶ/ር ከማል ገለቱ፣
2. ሸኽ አብዱረህማን፣
3. ሸኽ ሃጂ ኢብራሂም፣
4. ሸኽ ጣሂር አብዱልቃድር፣
5. ሸኽ ሱልጣን አማን፣
6. ወንድም ሀሰን አሊ
7. ኡስታዝ ጀማል ያሲን፣
8. ወንድም አሊ መኪ፣
9. ወንድም ሀሰን አቢ እና
10. ወ/ሮ ሃቢባ መሃመድ