በዚህ ሳምንት ብቻ 12 ኢትዮጵያውያን ዚምባብዌ ፖሊስ ሕጋዊ ባልሆነ መንገድ ወደ ሃገሬ ገብተዋል በሚል የታሰሩ ሲሆን ክስ ተመስርቶባቸው ፍርድ ቤት መቅረባቸውን የዙምባዌ ሚዲያዎች ዘግበዋል።
በርካታ ኢትዮጵያውያን በሃገራቸው ያለው ችግርን መቋቋም ተስኗቸው በአራቱም አቅጣጫ እየተሰደዱ ሲሆን እነዚህ በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን መድረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉ እንደነበር ታውቋል። በአሁኑ ወቅት ቁጥራቸው የማይታወቅ በርካታ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በዚምባብዌ ውስጥ የሃገሪቱን ድንበር ካለ ህጋዊ ወረቀት አቋርጠዋል በሚል ክስ ተፈርዶባቸውና በክስ ሂደት ላይ ሆነ በእስር ላይ እንደሚገኙ የዚምባብዌ የዜና ምንጮች በተደጋጋሚ መዘገባቸው ይታወሳል።
እነዚህ ሰሞኑን በዚምባብዌ የታሰሩት ኢትዮጵያውያን የተገኙት ወደ ደቡብ አፍሪካ አሻጋሪያቸው ሊሆን ይችላል በተባለ ዚምባብዌ ቤት ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት የሃገሪቱ ዜጎች የቤቱ ባለቤቶች በጠቅላላ ህጋዊ ያልሆኑ ስደተኞችን በመርዳት ወንጀል እንደሚጠየቁ ዘገበዋል።
በዚምባብዌ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለመሻገር ከሚሄዱ ኢትዮጵያውያን ውስጥ በእንስሳ የሚበሉ፣ በመንገድ ላይ የሚሞቱ እንዳሉ በዚያ ቦታ ያለፉ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል።