ከምኒልክ ሳልሳዊ
በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙ ቁጥራቸው ወደ 2500 የሚጠጉ ታሳሪዎች & የማረሚያ ቤቱን ጠባቂ ፖሊሶች በውሃ እጥረት ከፍተኛ ችግር ላይ መውደቃቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡
በማረሚያ ቤቱ በተፈጠረው የውሃ እጥረት ምክንያት ለምንም አይነት አገልግሎት የሚሆን ውሃ መጥፋቱ ተሰምቷል፡፤ ይህ የውሃ እጥረት የማረሚያ ቤቱን ጠባቂ ፖሊሶችን ሳይቀር ችግር ውስጥ እንደከተታቸው እየተገለጸ ነው፡፡
ይህንን ከባድ ችግር ለመፍታት የማረሚያ ቤቱ አስተዳደር እስካሁን ምንም እያደረገ አለመሆኑ ተገልፆል፡፡ ውሃ ለሰው ልጅ ለመኖር ወሳኝ ግብአት እንደሆነ እየታወቀ ከ2500 በላይ ታሳሪዎች ባሉበት ማረሚያ ቤት በውሃ እጥረት ምክንያት ታሳሪዎች በውሀ እጥረት እንዲሰቃዩ ማድረግ ኢ ሰብአዊ ድርጊት መሆኑ እየተገለጸ ነው::
ማረሚያ ቤቱ አስተዳደር አፋጣኝ እርምጃ በመውሰድ ከ 2500 በላይ እስረኞችን ሂወት ሊታደግ እንደሚገባ መልዕክታችን ነው፡፡