Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: አመለ ሸጋው ጊግስ “40 ዓመት ካለፈኝ በኋላም ኳስ እጫወታለሁ”ይላል

$
0
0

Ryan Giggs
ከዳዊት በጋሻው

በርካታ የእግር ኳስ ተጫዋቾች ዕድሜ ያቸው ከ30 በላይ ሲሆን፤ ብቃታቸው እየወረደ ከእግር ኳሱም ለመገለል የቀረቡ ይመስላቸዋል። በተለይ 35 ዓመት የሆናቸው ተጫዋቾች ችሎታቸው እየቀነሰ አስተዋጽኦአቸው እየቀነሰ ሲሄድ ይስተዋላል። የማንቸስተር ዩናይትዱ ባለ ግራ እግር አማካይ ግን የእዚህ ሰለባ አለመሆኑን አሁንም እያስመሰከረ ነው።

እግር ኳስን 40 ዓመት ከሞላውም በኋላ እንደሚጫወት ትናንት የልደት በዓሉ በተከበረበት ዕለት ያስታወቀው ዌልሳዊ ለማንቸስተር ዩናይትድ የመጫወትና የማገልገል ራዕዩ አሁንም እንዳለ ተናግሯል።
ራያን ጆሴፍ ጊግስ የተወለደው የታላቋ ብሪታኒያ አካል በሆነችው ዌልስ በፈረንጆቹ ህዳር 29 ቀን 1973 ነው። ምንም እንኳን ዕድሜው ቢገፋም እርሱ ግን አሁንም ለክለቡ አገልግሎቱን በሚገባ እየሰጠ ይገኛል።
በእንግሊዝ ፕሪሜር ሊግ ለበርካታ ዓመታት የተጫወተው ራያን ጊግስ ለማንቸስተር ዩናይትድ የመጀመሪያውን ጨዋታ እ.ኤ.አ በ1990/91 የውድድር ዓመት ያደረገው የግራ ክንፍ ተጫዋች በመሆን ነው። የማንቸስተር ዩናይትድ መደበኛ ተጫዋች መሆን የጀመረው ደግሞ እ.ኤ.አ በ1991/92 የውድድር ዓመት ነበር።
ዌልሳዊው ማንቸስተር ዩናይትድን ከተቀላቀለ በኋላ ከውጤታማው አሠልጣኝ ሰር አሌክስ ቻፕ ማን ፈርጉሰን እኩል 13 የፕሪሚየር ሊግ ዋንጫዎችን ማሸነፍ ችሏል። ከፕሪሚየር ሊግ በተጨማሪም አራት የኤፍ ኤ ካፕ ፣ ሦስት ሊግ ካፕ (የአሁኑ ካፒታል ዋን ዋንጫ) አንድ የዓለም ክለቦች ዋንጫ እና ሁለት የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫዎችን ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር ማሸነፍ ችሏል።
የግራ እግሩ ንጉሥ ቀይ ሠይጣን የማንቸስተር ዩናይትድ አምበል መሆን የቻለ ሲሆን፤ በተለይ እ.ኤ.አ በ2007/08 የውድድር ዓመት የክለቡ የመጀመሪያ አምበል ጋሪ ኔቭል መጎዳቱን ተከትሎ የቡድኑ ቋሚ አምበል መሆን ችሎ ነበር።
አማካዩ ከማንቸስተር ውጤታማነት ጎን ለጎን ራሱንም ከምርጦች ጎራ ማሰለፍ ችሏል። ለአብነት ያህልም እ.ኤ.አ በ1992 እና 1993 የዓመቱ ምርጥ ወጣት ተጫዋች ተብሎ መመረጥ ቸሏል። በተጫወተባቸው የውድድር ዓመታት በሙሉ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ግብ በማስቆጠርም ሌላ ታሪክ ሰርቷል።
ሪያን በማንቸስተር ዩናይትድ ቆይታው ባሳካቸው ድሎቹ ከምዕተ ዓመቱ የፕሪሚየር ሊጉና የኤፍ ኤ ካፕ ተጫዋቾች ተርታ ውስጥ መሰለፍ ችሏል።
የዓለማችን በዕድሜ አንጋፋ የሆነው የእንግሊዙ ኤፍ ኤ ካፕ ውድድር ላይ ከተቆጠሩ በርካታ ግቦች ውስጥ በምርጥነቷ የተመረጠችው ግብ ደግሞ በዚሁ ባለ ግራ እግር ዌልሳዊ የተቆጠረች ግብ ነች። ሪያን ግቧን ያስቆጠረው ደግሞ ከታሪካዊ ተቀናቃኛቸው አርሴናል ላይ መሆኑ እና ኤፍ ኤካፑ ውድድር ወደ ፍጻሜ ያሳለፈች ብቸኛ ግብ መሆኗ የግቧን ምርጥነት ብቻ ሳይሆን ወሳኝነትም ያሳያል።

ለአጥቂዎች ግብ የሚሆኑ ጣጣቸውን የጨረሱ 271 ኳሶችን በማቀበል በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ታሪክ የሚስተካከለውም የለም።
በዌልስ ብሔራዊ ቡድን በወጣትነቱ የተጫወተው ታታሪው ጊግስ ከብሔራዊ ቡድን አባልነቱ እ.ኤ.አ ከሐምሌ 2 ቀን 2007 ጀምሮ ራሱን አግሏል። በወጣትነቱ አገሩን የወከለ ብቸኛ ተጫዋችም መሆን ችሏል። እ.ኤ.አ በ2012 የብሪታኒያን የኦሎምፒክ ቡድን በአምበልነት ከመራ ጀምሮ በታላቋ ብሪታኒያ ከሚጫወቱ በዕድሜ ትላልቅ ተጫዋቾች ተርታ ተመድቧል።
እ.ኤ.አ መስከረም 5 ቀን 2001 የዌልስ ብሔራዊ ቡድን ከኖርዌይ ጋር ሲጫወት ብቻ በሁለት ቢጫ ካርዶች ከሜዳ የወጣው ጊግስ በማንቸስተር ዩናይትድ ቆይታው 953 ጨዋታዎችን ተጫውቶ አንድም ጊዜ ቀይ ካርድ አልተመዘዘበትም። በርካታ ተጫዋቾች በየጨዋታው የቀይ ካርድ ሰለባ በሆኑበት ዓለም ዌልሳዊው ሜዳ ላይ አመለ ሸጋ መሆኑን አስመስክሯል። ከዚህ በመነሳትም በርካታ ዓለም አቀፍ ተቋማትና ድርጅቶች ለጊግስ ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥተውታል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>