Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በኮንሶ እናቶች እንደአውሬ ተደብድበው ታስረዋል –ዛሬም የሚፈጸምባቸው ኢሰብአዊ ድርጊት ቀጥሏል

$
0
0

Zehabesha-News.jpg

ከከበደ ካቱሳ

ከትላንት ጀምሮ በኮንሶ ህዝብ ላይ የክልሉ መንግሥት እየፈፀመ ያለው ኢ ሰብዓዊ ድርጊቶች

1ኛ በወረዳው ሁለቱ ገበያ የካራት እና ኮልሜ ገበያ ውስጥ ስገበያይ የነበረውን ህዝብ ካለአንዳች ምክኒያት በመከላከያ ሠራዊት እና የክልሉ ልዩ ኃይል በትነዋል:: ሀሙስ 9:09 ገደማ በዕለቱ ወደ መጨሎ እና ቡሶ ቀበሌዎች በ5 መኪና የታጨቁ ወታደሮች ከእርሻ እና ቤት ውስጥ የዕለት ምግብ ለልጆቻቸው እያዘጋጁ ያሉ እናቶች ብዙ ሰዎችን እንደ አውሬ ደብድበው አስረዋል ፡፡ በዚህ ብቻም አላበቁም ያገኙትን ሰው የማሳደድ ተግባራቸው በመቀጠላቸው ምክንያት በዱራይቴ ፣ ዳራ ፣ ናላያሠገን ፣ ቡሦ፣ መጨሎ ፣ ጋሞሌ እና ጎጫ ቀበሌዎች አርሶ አደሩ ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሎ በትላንትናው ዕለት ቤቱ አላደረም ፡፡ በፋሻ አገልግሎት ደግሞ ወደ ገሠርጊዮ ፣ ሠውገመ ፣ ጋሆ እና ደበና ቀበሌዎች ሄደው የምታ ጫሌ እና የአባቱን ቤት እንድሁም የመምህር ጫሬ ቦያ ቤት በመስበር 31,000 ሺህ ብር ወስደዋል ፡፡
በዛሬው ዕለት ደግሞ ፡-
በሦስት መኪና ወደ ገሠርጊዮ ፣ በአራት መኪና ሠውገመ ቀበሌ ፣ በስምንት መኪና መጨቄ ፣ በሁለት መኪና ጋሆ በአምስት መኪና ጌራ ፣ ከአሥራ ሁለት በላይ መኪና በዶካቱ ፣ ቡሦ ፣ ና/ሠገን ፣ መጨሎ እና ጋሞሌ ቀበሌዎች ላይ ሠራዊት እስካሁን በየቀበሌ ት/ት ቤቶች ውስጥ ሠፍሮ ህዝብን እንያሳደዱ ይገኛሉ ፡፡ እስካሁን ከሦስት መቶ በላይ ሰዎች የታሰሩ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ የካራት ዲስቲሪክት ሆስፒታል ሥራ አስኪያጅ እና ሰው ሀብት ይገኙበታል ፡፡ ስለሆነም የአለም ህዝብ ይወቅ የደቡብ ክልል ክፍ እና በደል ፡፡ ሁሉም የኮንሶ ተወላጆች ወንድሞቻችሁ ፣ አባትና እናቶቻችሁ እያለቁ መሆኑን እንድታውቁ::


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>