Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

ታማኝ በየነ እና ኦባንግ ሜቶ ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ያደረጓቸው ንግግሮች

$
0
0


ታማኝ በየነ እና ኦባንግ ሜቶ ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ የኦሮሞ ተወላጅ ኢትዮጵያውያን ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ያደረጓቸው ንግግሮች

ታማኝ በዬነ ያደረገው ንግግር፦

“የኦሮሞ ሕብረተሰብ ለኢትዮጵያ መገንባት ቅድሚያውን ቦታ የያዘ ነው፤ ወዴት ነው ይህን ሀቅ የምንሸሸው?የ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ያለ ጥላሁን ገሠሰ ያምራል?የኢትዮጵያ ሥነ-ጽሁፍ ያለ ጸጋዬ ገብረመድህን ያምራል?የኢትዮጵያ ስፖርት ያለ ደራርቱ ቱሉ ያምራል? ….ይሄ ሁሉ ዝም ብሎ የሆነ ነገር አይደለም። ትናንት ኢትዮጵያን እንደ ሀገር ለማቆዬት የሞቱትን ጀግኖችም ማሰብ ያስፈልጋል።የአርበኝነት ምሳሌያችንኮ አብዲሳ አጋ ነው!ትናንት ሶማሊያ አዲስ አበባ ድረስ እመጣለሁ ስትል እነኮሎኔል ባጫ፣እነ ጀነራል ደምሴ ቡልቶኮ ናቸው ለኢትዮጵያ መቆዬት የተዋደቁት!!ይህን ሀቅ ለማን ነው የምትሸሹት?! ማንንስ ነው የምትሸሹት?!ኢትዮጵያን የፈጠረ ኢትዮጵያን አፍርሶ ሌላ አዲስ ሀገር ሊመሰርት አይችልም!!
” …ጋናው፣ቻይናው፣ አፍጋኒስታኑ፣አረቡ፣ እኛ ሁላችንም ለምንድነው እዚህ አገር የሚኖረው?ህግ ስላለ ነው።ኢትዮጵያንም የህግ አገር እናድርጋት! ኢትዮጵያንም የእኩልነት አገር እናድርጋት!!አብረን ቆመን ይህን የመከራ ጊዜ እንለፈው!በየተራ እየሞትን፣በየተራ እየወደቅን አንዘልቀውም! አንድ ላይ እንቁም!!ደምቢዶሎ በልጇ አስከሬን ላይ እንድትቀመጥ የተደረገችውን እናት የመጨረሻዋ አዛኝ ወላጅ እናድርጋት!ከሷ በኋላ ኢትዮጵያ ውስጥ እናቶች እንዳያለቅሱ የእያንዳንዳችን ኃላፊነት ነው!!ይሕን እንድናደርግም ደምቢ ዶሎ በልጇ አስከሬን ላይ ቁጭ ባለችው እናት እማለዳችኋለሁ!!
እያንዳንዱ ኦሮሞ፣ እያንዳንዱ አማራ፣ እያንዳንዱ ጋምቤላ… የሚሞተው ሞት ፤የሁላችን ሞት ነው! የሚፈሰው ደም የሁላችን ደም ነው!! ይህን አምነንና በዚህ ተስማምተን ይህን ክፉ ጊዜ በአንድነት ቆመን ለማለፍ በጋራ እንነሳ!!! አመሰግናለሁ።”


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>