Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

እናቱ እስር ቤት የገባችበት እና እናቱ ሲኒማ ቤት የገባችበት እኩል ያለቅሳል!?

$
0
0

በአበበ ቶላ ፈይሳ
ሰሞኑን የሶማሌ ክልል ፕረዘዳንት የትግራይ ህዝብ ጥቃት እየደረሰበት እንደሆነ ነግረውን ከትግራይ ህዝብ ጎን እንደሚቆሙ በሰልፍ እና በስበሰባ አጀብ ነግረውናል።
ከዚህም በተጨማሪ እነ ራዲዮ ፋና የትግራይ ህዝብ ዛቻ ደርሶበታል ይሄ ነገር ባስቸኳይ መቆም አለበት የሚል አዝማሚያ ያለው ውይይት ሲያደርጉ አይተናል።
እዚህም እዛም ያሉ ለመንግስት ቅርብ የሆኑ ወዳጆቻችን በሙሉ የትግራይ ህዝብ ተገላመጠ፣ የትግራይ ህዝብ ላይ ጮሃቹበት፣ የትግራይ ህዝብ ሲጣራ ቶሎ ብላችሁ አቤት አላላችሁም… የሚሉ የሚመስሉ ወቀሳዎችን በሌላው ማህበረሰብ ላይ በተለይም ውጪ ሃገር የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ላይ ጣታቸውን እየጠቆሙ ነው።
እንደኔ እምነት የትግራይ ህዝብ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምስኪን ህዝብ ነው። የትግራይ ህዝብ ከማንም ተለይቶ የተለየ ጥቅምም ሆነ የተለየ ጥቃት እንዲደርስበት አልሻም!
ግን ምን ሆነ ነው የተባለው?
እኛ አሁን ባለን ጥርት ያለ መረጃ በመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በአማራ በኦሮሚያ እንዲሁም በደቡብ ክልል በተለይም በኮንሶ ህዝብ ላይ መጠነ ሰፊ ጭፍጨፋ እንዳካሄደ እና እያካሄደም እንዳለ ነው። ታድያ ትግራዮች ምን ሆነው ነው ይሄ ሁሉ ጠበቃ የቆመላቸው?
ሶማሌ እና አፋር እንዲሁም የመንግስት ሚዲያዎች (እነ ራዲዮ ፋና) ሁሉ ስለ ትግራይ ህዝብ እንዲህ የተጨነቁት ለምንድነው?
መነሻው ባለፈው ጊዜ ከመተማ ተፈናቀሉ የተባሉ ትግራዮች ናቸው። ተፈናቀሉ የተባሉት ትግራዮች እውነት የአካባቢው ማህበረሰብ አፈናቅሏቸው ነው ወይስ መንግስት ለገዛ ፖለቲካው ሲል የተፈናቀሉ አስመሰለ….? የሚለው የሚጣራ ቢሆንም ሰዎቹም ግን ዘለው ሱዳን መግባታቸው እና ከሱዳንም ተንቀባረው ወደ ትግራይ ክልል ያለ እንከን መጓዛቸው ነገሩ በጥርጣሬ እንዲታይ የሚያደርገው ነው።
ቢሆንስ ግን በአሁኑ ግዜ አጋርነት የሚያስፈልጋቸው እነማን ናቸው? በኦሮሚያ በአማራ እና በኮንሶ ያሉ ፍትህ ያጡ ወገኖች ወይስ ከመተማ ወደ ቤተሰቦቻቸው ጋ የሱዳን ታክሲ ክንትራት ተይዞላቸው በሰላም የሄዱ ሰዎች…. ?
በተለይ እነ ሱማሌ ክልል ካጠገባቸው ያለው ኦሮሚያ ላይ የሚወርደው የጥይት ናዳ ሳይታያቸው እንዴት እ……ዛ ማዶ ትግራዮች ሳይጎዱ አይቀሩም የለው ተሰማቸው!?
ይሄ ሁሉ የሚያስረዳው መንግስት የትግራይ ህዝብን እንደ ቼዝ ጠጠር እየተጫወተበት እንደሆነ ነው!
እወነት የትግራይ ህዝብ በደል ደርሶብኛል እያለ ከሆነ ግን፤ በሌሎች ላይ እየደረሰ ካለው አንጻር እናቱ እስር ቤት የገባችበት እና እናቱ ሲኒማ ቤት የገባችበት እኩል ያለቅሳል…. ነው የሚሆንበት!

Abe-Tokchaw-Satenaw


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles