”ወደ ሀገሬ መግባት እፈልጋለሁ እርዱኝ !“
ከቀናት በፊት ከደረሱኝና ሰላሜንና ውስጤን የረበሸው ነፍስ የማታውቀውን ለሚስን “ ገድላለች ” ተብላ በሳውዲ መዲና በሳምንቱ መጀመሪያ አንገቷ የተቀላው የአተርፍ ባይ አጉዳይ እህቷ የዘምዘም መጨረሻና የለሚስ አሳዛኝ ፍጽሜ ብቻ አልነበረም ። ባሳለፍነው ሳምንት መጨረሻ “ የወገናችን ጉዳይ ያገባናል ” ካሉ እህቶቸ የደረሰኝ የእህት ገላዬ ከድርን ተማጽኖ ልብ ይሰብራል ፤ በደላላ ተታላ ወቅ ለማፈስ በኮንትራት ወደ ሳውዲ የመጣችው እህት ገላዬ ”ወደ ሀገሬ መግባት እፈልጋለሁ እርዱኝ !“ የሚለው ተማጽኖን ጠልቆ የተሰማኝ ያለ ነገር አልነበረም ። የገላዬ ህመም ብርታት ስሜት ፡ የወደፊት ተስፋዋና የህመም ስጋቷን ከወላጆችዋ ፍቅር ናፍቆትና ስስት ጋር አውጥቸ አውርጀው ስመለከተው ወደ ራሴ አለም እዘፈቅና ህመሟን ታመምኩት ፤ ህልም ፍላጎቷን በውስጤ ፡ የራሴ አድርጌ ሳብሰለስል ፤ ስመለከተው የገላዬን ጭንቀት ከምንም በላይ ረበሸኝ … :(
አዎ ! የሰው ልጅ ህይዎት የሚቆረጠው በአንድ አምላክ ፈቃድ ቢሆንም እህት ገላዬ ከያዛት ውስጠ ደዌ በሽታ ታክማና አገግማ ወላጆቿን ወላጆጆችዋን የማግኘት ተስፋዋ ከህመሙ በላይ ሃሳብ ሆኗታል … እና ” የመጨረሻ ቀናቶቸን የወላጆቸን አይን ሀገሬን ልይ … ወደ ሀገሬ እንድገባ እርዱኝ !” እያለች ነው ። ስለ ኮንትራት ሰራተኛዋ እህት ገላዬ ከደረሰኝ መረጃ በተጨማሪ በስልክ ደውዬ ገላዬን አነጋግሬያት ነበር ። ከሃገር ቤት እስከ ሳውዲ ያደረሳትን መንገድ አጫውታኛለች … በዚህ መረጃ ቅበላም ለመልዕክቷ ደጋፊ የሆነውን ብቻ አቅርቤዋለሁ ተከታተሉት !
…
አሁንም አልመሸም !
=============
አሁንም አልመሸም … በኮንትራት መጥተው ደመወዝ ሳይቀበሉ ፣ በስራ ብዛት ታፍነው መውጫ መግቢያ የጠፋቸው ፣ በስቃይ ላይ የሚገኙ ሞልተው ተርፈዋል … እነዚህን ወገኖች መታደግ ገጽታን መገንባት ነው …እነዚህን እህቶች ለችግር ጭንቀታቸው መድረስ ተበሳጭተው ወንጀል ከመፈጸም እንዲታቀቡ መርዳት ነው … ከዚህ በተረፈ የተቸገሩትን ማዳን ከተፈለገ ይቻላል ! የታመሙ ፣ የደከሙትን ለመርዳት ልባችሁ ቀናኢ ከሆነ የተበተኑትንና በችግር ላይ ያሉትን ዜጎች ድምጽ ስምታችሁ ወደ ሀገራቸው መላክ ይቻላችኋል ፤ ብቻ ቅና እዝነ ልቦና ይኑራችሁ !
ምስጋና !
=======
እህት ገላዬ ከድር በሳውዲ ሪያድ ሽሜሲ በተባለው ሆስፒታል ህክምናዋን በመከታተል ላይ ትገኛለች ፤ መረጃውን ላደረሱኝ ወገኖች ምስጋናዬ ይድረሳችሁ !
ለመረጃ ያህል !
=========
እህት ገላዬን በሚመለከት መረጃውን ላደረሱኝ ወገኖች ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከተውን በሪያድ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ሃላፊዎችን ስልክ ቁጥር ከቀናት በፊት ሰጥቻቸው ነበር። ይህ ቪዲዮ እስከተለቀቀበት ሰዓት ድረስ ከኢንባሲው በኩል
እህት ገላዬን ወዳለችበት የሄደም ሆነ ያጣራ ሰው አለመኖሩን መረጃ ደርሶኛል ። የዚህች እህት ጉዳት ተሰምቷችሁ ወደ ሃገሯ እንድትገባ መርዳት ለምትፈልጉም ሆነ ማናቸውም እርዳታ ማድረግ ለምትፈልጉ ከዚህ በታች ባለው ተንቀሳቃሽ
ስልክ ቁጥር 09966 538182140 ማግኘት ትችላላችሁ !
ቸር ያሰማን !
https://t.co/UXnzsDEKX2
ነቢዩ ሲራክ
መስከረም 19 ቀን 2009 ዓም