ከጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ
ለአለም አቀፉ የጤና ድርጅት ዳይሬክተር ጄኔራል ለመሆን በወዳደር ላይ ያሉትን ቴድሮስ አድሃኖምን የምርጫ ዘመቻ እንዲመራ ታዋቂው የህዝብ ግንኙነት ካምፓኒ ሜርኩሪ ፓብሊክ አፌይርስ (Mercury LLC Public Affairs) እና የኢትዮጵያ መንግስት በከፍተኛ ገንዘብ መፈራረማቸው ታውቋል።
ሜርኩሪ ፓብሊክ አፌይርስ በተደጋጋሚ ደንበኞቹን ውጤታማ ለማድረግ አለም አቀፍ ተቋማትን፣መንግስታትንና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች(NGO) ላይ ጫና መፍጠርን የተካነ ካምፓኒ ነው። ባለፈው አመት እንኳን የናይጀሪያ የእርቫ ሚንስትር የነበሩትን አኪንዉሚ አዴሲና (Akinwumi Adesina) አቶ ሶፍያን አህመድን አሸንፈው የአፍሪካ ልማት ባንክ (African Development Bank) ዳይሬክተር እንዲሆኑ ከፍተኛ የማግባባት ስራ (Lobby) ሲሰራ የምናስታውሰው ነው።
የኢትዮጵያ መንግስትና ተቀማጭነቱን ለንደን እንግሊዝ ያደረገው ሜርኩሪ በምን ያህል ገንዘብ እንደተፈራረሙ ለጊዜው ያልታወቀ ቢሆንም የኢትዮጵያ መንግስት ቴድሮስ አድሃኖም የአውሮፓ ተፎካካሪዎቻቸውን አቨንፈው ቦታውን እንዲይዙ ካለው ፍላጎትና ጥቅም አንፃር በ10 ሚሊዮን ዶላሮች ሳይሆን እንደማይቀር ይገመታል። የሜርኩሪ ከፍተኛ አመራሮች ከቴድሮስ አድሃኖም የምርጫ ዘመቻ ቡድን አባላትና ከመንግስት ተወካዮች ጋር በ አዲስ አበባ ከተወያዩ በኳላ ወደ ለንደን ተመልሰዋል።
ከጉዳዩ ጋር የተያያዙ ሌሎች ተጨማሪ መረጃዎችን ይዤ እመለሳለሁ።