ከኢሳያስ ከበደ
ዶ/ር ቴዎድሮስ በፌስቡክ በያዙት የቁጥር ጨዋታና በሳዑዲ መንግስት ገንዘብ ከተመለሱት ኢትዮጵያውያን ጋር በተነሱት ፎቶ ግራፎች የተነሳ አንዳንዶች ጥሩ ሥራ እየሰሩ ነው በማለት ሲያሞካሿቸው ይደመጣሉ። በተለይ በሳዑዲው ጉዳይ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ትንፍሽ እንዳይሉ በተደረገበት ሁኔታ፤ ዶ/ር ቴዲ በቀጣዩ ምርጫ ለጠ/ሚ/ርነት የሚያደርጉትን የሕልም ሩጫ ለማሳካት፤ ወደ ሃገራቸው የሚመለሱትን ዜጎች በሳዑዲ መንግስት ገንዘብ መሆኑን አንድም ሳይነገሩን፤ የሳዑዲውን የወገን ስቃይ ቁጥር በፌስቡክ እየተጫወቱበት ለራሳቸው ፖለቲካዊ ጥቅም እያዋሉት ነው። ዶ/ር ቴዲን በቁጥር ጨዋታ ተሸውዳችሁ Good Job ለምትሉ ሰውዬው ያልተናገሩት ወይም ያላደረጓቸውን 8 ነገሮችን ጥሩ ሕሊና ያለው አንብቦ ያገናዝብ፦
1. በጠንካራ ቃላት የተዘጋጀ የውግዘት መግለጫ፤
2. የጥገኛውን ሀገር አምባሳደር በመክሰስ የብጥብጡን ሁኔታ እንዲረዳና በፖሊስና በህገወጦች የሚፈጸመውን ህገወጥ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲያስቆም ማድረግ፡
3. ከዚህም በላይ አደሃኖምም ሆነ ወይም ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው ከሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር የሚኖርን ተቃውሞ በይፋ ለህዝብ አላሳወቁም፡፡
4. በሳውዲ አረቢያ በሚኖሩ ኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣ በሚመለከት የአፍሪካ ህብረት የውግዘት መግለጫ እንዲያወጣ ማድረግ፤
5. (በነገራችን ላይ ይህ ሁሉ ስቃይ በኢትዮጵያውያን/ት ዜጎች ላይ ሲፈጸም የይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአገር ውስጥ ነበሩን? ኢትዮጵያውያን በሳውዲ አረቢያ “የዘር አደን” እየተፈጸመባቸው መሆኑን አስመልክቶ ቃል ትንፍሽ ሲሉ የሰማ ይኖራልን?)
6. አስቸኳይ ምርመር እንዲካሄድ ለተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን (UNHCR) ኮሚሽነር ማሳወቅ፣
7. ጉዳዩ በተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ኮሚሽነር/UNHCR እና በተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ጽ/ቤት/OHCHR ቀርቦ እንዲጣራ ቅሬታን ማስመዝገብ፤
8. የኢትዮጵያ ዜጎች ከሳውዲ አረቢያ ኤምባሲ ፊት ለፊት ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ እንዲያደርጉ መፍቀድ፤
ቴዎድሮስ የሠሯቸው 3 ነገሮች
1ኛ. ለፌስቡክ የሚሆን ፎቶ ከተመላሾች ጋር መነሳት
2ኛ. የተመላሾችን ቁጥር በ13 ሺህ በመሸቀብና በመጨመር የፌስቡክ ገጻቸውን ማሳመር
3ኛ. የሳዑዲውን የወገን ስቃይ ለፖለቲካ ጥቅም ማዋል
(ከፕ/ር አለማየሁ ገ/ማርያም – ጽሑፍ ውስጥ ተመርጦ የወጣ)
ሙሉው ጽሁፍ እዚህ አለ፦
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/10028