(ዘ-ሐበሻ) ከሳዑዲ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎችን እንዳጓጓዘ ቢገልጽም አሁንም በሳዑዲ ያሉ እህቶች በቪድዮ የተደገፈ ስቃያቸውን ለዓለም እያሰሙ ነው። የኢትዮጵያ ህዝብ ይድረስልን እያሉ የሚናገሩት እነዚሁ እህቶች ለ2 እና ለ3 ወራት እስር ቤት እንደቆዩም ይናገራሉ። አንዳንድ የደረሱን መረጃዎች ደግሞ የኢትዮጵያ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ ወደ ሃገር እያሳፈረ ያለው የስርዓቱ ደጋፊ የሆኑ፣ ኢምባሲው በሚጠራቸው ስብሰባዎች የሚገኙ፣ ገንዘብ በሙስና ለሚከፍሉ ነው የሚሉና ሌሎችም ናቸው። አንድ ዜጋ የመንግስትን አገልግሎት ለማግኘት የግድ የመንግስት ስብሰባዎች ላይ መገኘትና የነርሱን ፖለቲካ አቀንቃኝ መሆን የለበትም፤ መንግስትን መደገፍም መቃወምም የሰው ልጅ መብት ሲሆን መንግስት ደግሞ የሚጠላውንም የሚወደውንም የማገልገል ሃላፊነት አለበት። ሕሊና ያለው መንግስት የሚያስበው ይህን ነው። የእህቶቻችንን ጥሪ ይመልከቱ፦
↧
አሁንም የድረሱልን ጥሪ ከሳዑዲ አረቢያ እስር ቤት (Video)
↧