የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ህዳር 8 ቀን 2006 ፕሮግራም
<<…ሳውዲ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመችውን ግፍ በመቃወም ነው ሰልፍ የወጣነው ሰልፉ እንዳይደረግ ቢሮ አካባቢ አንዳንድ አመራሮችነ ሲያግቱ ቦሌ ቶሎ ሄድኩ እዛ ስንደረስ ሕገ ወጥ ሰልፍ ብለው ደብድበውና…በእርምጃው በጣም አዝኜያለሁ…>> አቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ሀላፊ ሳውዲን ለመቃወም ወጥተው ስለደረሰባቸው እስርና ድብደባ ከገለጹልን የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)
<<…የሳውዲ መከላካያዎች ይዘውን ለመሄድ መጡ ኤምባሲ ካልመጣ አንሄድም አልናቸው ።አንዱን ኢትዮጵአዊ በመኪና ገጩተት ቆይተው ደግም ስድስት በጥይት ገደሉ።የኤምባሲው ተወከኢ ጋር ደውዬ አንስቶ ስልኩን ዘገአ ቆይቶ ሞባይሉን አጠፋው…>>
ሳሮን ጸጋዬ ባለፈው አርብ በኢትዮጵያውያን ላይ ስለተወሰደው የግድያ እርምጃ ለህብር ሲገልጽ( ቃለ መጠይቁን አዳምጡት)
<<…ተፋፍገን በአንድ ሰርግ በሚደግሱበት ቦታ ሶስት ሺህ ሴቶች ሆነን ነው ያለነው። ድምጻችን መዘጋት ጀምሯል ። በቂ መጸዳጃ የለም ውሃ ይዘጉብናል፣ኤምባሲው ምንም አላደረገልንም።ድምጻችንን አሰሙልን…>> ከጅዳ ማቆያ ኢትዮጵያዊቷ ስለ ችግሯ ከገለጸችልን
<… በአገር ቤት በሳውዲ የሚደርሰውን ግፍ ለመቃወም ዜጎቻችን በአገራቸው ወጥተው በመደብደባቸው እዚህም በችግር ውስጥ ያሉትም እኔም በጣም ሀዘንና ሐፍረት ነው የተሰማን…>>
ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ከሰጠን አስተያየት የተወሰደ
የምዕራባውያን በኢትዮጵያ ያለውን እውነታ አውቆ ዝምታን መምረጥ በመረጃ ሲገለጥ…>>
ሌሎችም ዝግጅቶች
ዜናዎቻችን
በሳውዲ ሪያድ ስድስት ኢትዮጵያውያን በጥይት ተገደሉ
አንዱ በመኪና ገጩት
ሀያ ሺህ ኢትዮጵአውያን በአንድ ስፍራ ተጉረዋል
የተላላፊ በሽታ ስጋት አለ
በሳውዲ የጎርፍ አደጋ ስምንት ሰዎችን ገደለ
ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ለተፈጸመው ግፍ የፈጣሪ ምላሽ እንደሆነ የሚያስቡ አሉ
የኢትዮጵያ ጦር በሶማሊያ ከአፍሪካ ህብረት ሀይል ጋር ልጣመር ያለው በፋይናንስ ችግር መሆኑ ተገለጸ
አልሸባብ ስማርት ፎንን አገደ
<<..መንግስት ለሳውዲ አግዞ ለሰልፍ የወጡትን በመደብደቡ አገርም መንግስትም የለንም…>> አብርሃ ደስታ ከመቀሌ
የሰውዲ ፖሊስ ለምርመራ በሚል ኢት ጵአ አንን ማሰር ቀጥሏል
ከኢትዮጵያ ተነስተው አውስትራሊያ ለመግባት ያሰቡ ኤርትራውያን ኢንዶኔዢያ ላይ ተጣሉ
አሰልጣኝ ሰውነት ከናይጄሪያ ጋር ለደረሰው ስንፈት ዳኛውን ተጠያቂ አደረጉ
ሌሎችም ዜናዎች አሉን