ምን አለ ብትተዉኝ መሬቴን ባለማ
ምን አለ ብታርፉ ወገኔ ቢሰማማ
……..
ወገን ደራሽ መሰሎ ሆዱን እየሞላ
ጎርፍ ሆኖ ሊወሰደው የቀይባሕር ሞላ
ምን አለባት የዚህ ግጥም መንደርደሪያ አንባቢያንን ግራ ሊያጋባ ይችል ይሆናል ብዬ ሰግቼ ነበር፤ ሆኖም ኢትዮጲያዊያን ወገኖቼ በርካታዎቹ ““ድጓ ጾመዱጓ ፤ የደገሙ““በመሆናቸው መልዕክቱ በቀጥታ ምን ማለት እንደሆነ እንደሚረዱ አምናለሁና ልቀጥል።
“”ይቺ፤ ምራቅ ሳትደርቅ፤”” ይባል ነበር አሉ ድሮ፤ ይግርማል” ሰለ ሻአቢያ ደባ አውርትን ሳንጨርሰ፡ እንደተመለከታችሁት የሻአቢያው መሪ በኤርትራው ቲቪ መሰኮት ብቅ ብለው በሁለት እጃቸው ወገባችውን ይዘው ጥርሳቸውን እያንቀጨቀጩ አንዳንዴም ጠያቂው (ጋዜጠኛው) መግቢያ መውጫ እሰኪጠፋው፤ አይናችውን እያጉረጠረጡ ለመሆኑ ኢትዮጲያ ማን ናት ? ?;;;;;;፤ ይቺ ከሁለተኛው አለም ጦርነት ማግሰት የተፈጠረች አገር ? ? ;;;;;;;’ ኤርትራን ኮሎኒ ;;;;;;፤ አድርጋለች እየተባለ የሚወራው ? ? ;;;;፤ ይሄማ ለ ኢትዩጲያዊያን ትልቅ ክብር መሰጠት ነው። በሚል ፌዛዊ አነጋገር ኢትዬጲያ ትላንት ወያኔ ሲገባ እንደተፈጠረች አይነት አድርገው ለማሰቀመጥ ሲሞክሩ መሰማት ምን ያኸል አሳዛኝና አሁንም ኢትዬጲያን የማጥፋት አባዚያችው እንዳልበረደላቸው አሰረግጠውልናል።
እንግዲህ ልብ በሉ ከእኚህ የ ኢትዬጲያ ሰም ሲጠራ ከሚያንገሸግሻችው ሰው ጋራ ነው ለኢትዮጲያ አሳቢ ናቸው፤ በሙሉ ልባቸው ወያኔ በኢትዬጲያ ሕዝብ ላይ የሚደረሰውን ግፍ ድጋፍ ለመሰጠት ቆርጠዋል። ድጋፋቸውም ወደር የሚገኝለት አይደለም ። እየተባለ ጠዋትና ማታ የሚለፈፈው። እኔ በበኩሌ እንዲገባኝ ለማድርግ ብዙ ጥረት አደረግኩ ። ብዙም ወደሖላ ተመልሼ ለመመልከት ሞከርኩ። አንዱም የሻአቢያ ተግባር ለ ኢትዬጲያ በጎ ነገር እንደሌለው እንጂ አንድም በጎ ተግባር እንደሌለው ነው መረጃው በሙሉ እሰካሁኗ ደቂቃ ድረሰ የሚያሳየኝ እና አንባቢያን ሆይ እባካችሁ እንደገና ቆም ብለን እንመርምር በሻአቢያ እርዳታ አገር ነፃ አይወጣም። ሻአቢያ ከወያኔ ጋር ተባብርው ቀይባሕር እንዳይከቱን እንጠነቀቅ።
ይልቅ አገርውሰጥ ያለውን የሰላማዊ ትግል መደገፉ ጠቃሚና አሰፈላጊነቱን በሚከተሉት ሦሰት ነጥብ ለማሰቀመጥ ልሞክር እንሆ፦———
1ኛ) የሰላም ትግል ማለት እኮ የሕብረተሰብን አሰተሳሰብና አመለካከት በጠመንጃ ሣይሆን በተሻለ አሰተሳሰብና አመለካከት የዲሞክራሲ ሰርአት እንዴት ማምጣት እንደሚቻል ማሰተማርና ማደራጀት ነው። ኢትዮጲያ በአለም ላይ ደሃ አገሮች ተብለው ከሚጠሩት አንዶና፤ ሕዝቦ በድህነትና ፍትሕ በማጣት፤ በጉሰቁልናና በሰደት፤ በበሽታ፤ በመፈናቀል፤ የምትታወቅ በመሆኗ፤ ይኸን አለማቀፍ ጉሰቁልና ለመቅረፍና የዲሞክራሲን ሂደት ለማምጣት በ አገር ውሰጥ የተጀመረው የሰላም ትግል ከጦርነት ትግል በላይ ዋጋ የሚያሰከፍል እንደሆነ የተረዱ ወጣት ታጋዬች ዋጋ እየከፈሉ እናዳለ በውል መረዳትና አንዳሰፈላጊነቱም ከያለንበት እንዳወጣጣችን ወደህገር በመመለሰ የሰላሙን ትግል በመቀላቀል በሐገር መሬት ላይ አሰፈላጊውን ዋጋ ለመክፈል የቆረጥን መሆን እንጂ በሻአቢያ ብብት ሰር ለመውደቅ መዘጋጀት መፍትሄ አይሆንም”። ከሁሉ በላይ የሰላሙ ትግል ሙሉ የሕዘብ ዽጋፍ ያለው ሲሆን ጦርነት ግን እንኳን እንደኛ ያለ ድሃ አገር ቀርቶ ዛሬ ባለማቀፍ ደረጃ ተደጋፊነት የለውም።
2ኛ) ሻአቢያ ሲጀመርም፤ አሰካሁኖም ደቂቃ ደረሰ ለኢትዬጲያ መፈረሰ እንጂ፤ ግንባታ ሰርቶ አያውቅም ሊሰራም አይችልም። ባገር ውሰጥ እየተካሄደ ያለውን የሰላም ትግል ባገር ውሰጥ ያሉት የመንግሰት አካላትም ሆኑ በሚሊቴሪው ክፍል፤ የሚገኙ አካላት ፖሊሱንም ጨምሮ በየቀኑ እየተከታተሉና፤ የወያኔ ግፍ አገዛዝ ምን ያኸል ሰርአተ አልበኛ እንደሆነ እየተገነዘቡና ሊቆጣጠሩት ከሚችሉት በላይ እንደሆነና የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በሰተቀር ይኸንኑ የሰላም ትግል እንደሚቀላቀሉ በተለያየ ሁኔታ ምልክቶች እየታየ እንደሆነ በማሰተዋል መመልከት አሰፈላጊ ነው። ለምሳሌ በቅርቡ አገር ኮብልለው የወጡት ቱባ ቱባ የመንግሰት ባለሰልጣናትና የጦር ኦፊሻልሰ መመልከት አሰፈላጊ ነው። ያኮበኮቡትን አግዚአብሔር ይቁጠረው። ይኸ ሁሉ የሰላሙ ትግል ውጤት እንጂ ሻአቢያ በሰጠው ድጋፍ የተገኝ ውጤት እንዳልሆነ መረዳት በጣም አሰፈላጊ ነው።
3ኛ) ወያኔ በሰላሙ ትግል በከፍተኛ ደረጃ ተዳክሟል። ለዚህ መረጃዎቹ መንግሰትነኝ ተብዬው አንዴ የሰላማዊ ሰልፍ ፍቃድ መሰጠትና ትርጉም በማይሰጥ ምክነያቶች መልሦ መከልከልና፤ ቀን ማራዘም ከብዙው በጥቂቱ ናቸው። ሌላውና ሊሰመርበት የሚያሰፈለገው ነጥብ ወጣቶቹ የሰላም መሪዎች በየጊዜው ከአንደበታቸው የሚሰማው የቆራጥነት አቆም አገራችን ምን አይነት ብርቅና ድንቅዬ ቆራጥ የሰላም ታጋዬች እንዳሏትና ምንም እንኳን የድሉ ጊዜ ቢረዝም ኢትዬጲያ በቆራጥ የሰላም ታጋይ መሪዎቾ ተሰፋዋ የለመለመ እነደሆነ ያረጋግጣል። በ ሺ፤ የሚቆጠሩ ተከታዬችም እያፈሩ እንደሆነ በመረዳት ይኸንን የሰላም ትግል መደገፍና የሰላም መሪዎችን ማበረታታት እጅግ ጠቃሚና ወቅታዊ ነው እላለሁ።
ኢትዮጲያ’’’’’’’በሰላም ‘’’’’’’’’ታጋዮች’’’’’’’’ቆራጥ’’’’’’’አመራር’’’’’’’ድል’’’’’’ትቅዳጃለች ! !
በቸር ይግጠመን ፤ Saturday, September-21-13