(ዘ-ሐበሻ)፡ በተለያዩ የራድዮ ጣቢያዎች አዝናኝ የሙዚቃ ሥራዎችን በማቅረብ ተወዳጅነትን ያተረፈው ጋዜጠኛና የሙዚቃ አማካሪ ተወልደ በየነ በአይነቱ ልዩ የሆነው “በዘፈን እናውራ” የተሰኘ አስቂኝና ቁምነገር የያዘ ሲዲ ይዞ ቀረበ። ይህ በሕዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኛል በሚል ከወዲሁ ግምት የተሰጠው ሲዲ የፊታችን እሁድ በቨርጂኒያ መዓዛ ሬስቶራንት እንደሚመረቅ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመልክቷል።
ከዚህ ቀደም ሽገር ሬዲዮ አሁን ደግሞ በኢሳት ራድዮና ቴኤቭዥን በሚያቀርባቸው የመዝናኛ ዝግጅቶች ተወዳጅነትን ያተረፈው ዜጠኛና የሙዚቃ አማካሪ ተወልደ በየነ በአይነቱና በአቀራረቡ ለየት በሚል መልኩ ይዞት የቀረበው የሲዲ ሥራ “በዘፈን እናውራ” ይሰኛል። በዚህ አዝናኝ ሲዲ ተወዳጁ ጋዜጠኛ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመሪ ጅምሮ እስከ ተቀዋሚ ያሉትን በዘፈን እያወራቸው ያስቃል፤ ያዝናናል ተብሏል።
ከመሪዎች በተጨማሪም ድምፃዊያኑንም በዘፈን እንደሚያወራቸው የተጠቀሰ ሲሆን በስራቸው ለተጠየቁት ምላሽ ከሰጡት ድምፃዊያን መካከልም ጥላሁን ገሠሠ፣ አስቴር አወቀ፣ ነዋይ ደበበ፣ ቴዎድሮስ ካሳሁን፣ ይገኙበታል ተብሏል:
የተቦርነ በየነው ይህ በአይነቱና በአቀረቡ የመጀመሪያ የሆነው ሲዲ ሴፕቴምበር 24 በመአዛ ሬስቶራንት ከ 8:30pm ጀምሮ ከተመረቀ በኋላ በመላው ዓለም ለአድማጭ እንደሚሰራጭ ይጠበቃል። በሲዲው ምረቃ ላይ መገኘት ለምትፈልጉ የመአዛ ሬስቶራንት አድራሻ 5700 Columbia Pike Falls Church, VA 22941 ነው። የሬስቶራንቱ ስልክ ቁጥርም (703) 820-2870 ነው።
መልዕክቱን በድምጽ ያድማጡ፦