Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የደርብ ከፈለኝ አስተያየት በእኔ እይታ –መሠረት ከቴክሳስ

$
0
0

‘አህያውን ፈርቶ ዳውላውን’ በሚል ርእስ በተክለሚካኤል ላይ የስድብ ውርጅብኝ ያወረዱት ደርብ ከፈለኝን ሳስብ በእኛ በኢትዮጵያውያን ውስጥ በብዙ ሰዎች ዘንድ የማየው በሽታ ታወሰኝ። ይኸውም ታዋቂን፣ሀብታምን፣ባለስልጣንን እንደው ብቻ በማናቸውም መልኩ በማህበረሰቡ አይን ውስጥ የገባን ሰው ማሞካሽት፤ ቢሳሳት እንኳን ስህተቱን ስህተት ነው ብሎ ደፍሮ ከማረም ግለሰቡ ከተናገረው ይዘት ጋር በማይገናኝ ሁኔታ አቃንቶ እንዲህ ለማለት ፈልጎ እኮ ነው ብለው የሚሉ ብዙ ሰዎችን አውቃለሁ። እንዲህ አይነት ሰዎች ከባለ ጉዳዩ በላይ ተቆርቋሪ ሆነው ከስህተቱ እንዳይማር መንገድ የሚዘጉ፣እንደዚያ አይነት ሰው ስህተት ቢፈጽም እንኳን ይቅርታ መጠየቅ የማይገባው መሆኑን እስከመግለጽ ይደርሳሉ።

             ይህን መሰል አንድ እውነተኛ ታሪክ ላጫውታችሁ። በአሜሪካን አገር ውስጥ አንድ የአበሻው ብዛት ከሁለት ሺህ አይበልጥባትም በምትባል ከተማ ውስጥ አበሾች ተሰባስበው ቤተክርስቲያን ይተክላሉ። ቤተክርስቲያኗም የምትተዳደረው አቡነ ይስሐቅ በሚባሉት ጳጳስ ስር ነበር። አቡነ ይስሐቅ ነፍሳቸውን እግዚአብሔር በገነት ያኑርልንና በዘመናቸው የኢትዮጵያን ቋንቋ የማይናገሩ ህዝቦችን አስተምረው የእኛን ኦርቶዶከስ እምነት አለማቀፋዊ ይዘት ያላበሱ ትልቅ አባት ነበሩ። እሳቸው ከሞቱ በሁዋላ ቤተክርስቲያኗ ከአገር ውስጥም ከውጨውም ሲኖዶስ ሳትሆን ከምእመናን በተውጣጡ የቦርድ አባላት እየተመራች ባለችበት ሁኔታ ውስጥ የቤተክርስቲያኗ ካህን ምእመኑን ለመከፋፈል እራሳቸውን አንዴ የወሎ ሰው ነኝ ብለው ወሎዬውን ሲሰብኩ ሌላኛውን ጎጃሜነኝ ሲሉ ሌላውንም ሌላ እያሉ ምእመኑን እየፈተሹ ባሉበት ሂደት ውስጥ አንድ ቀን ያልታሰበ ዱብዳ ተፈጠረ ። ይኸውም ካህኑ ከአራት አባት ምአመናን ጋር የቆመችውን ሴት የተናገሩትን ለመድገም በሚያሸማቅቅ ቃላት ዘለፉዋት። መንፈሳዊው አባት ሲሳደቡ ምእመን አባቶች ቆመው ታዘቡ። በትዝብት ማለፉ አስተማሪነት የለውም በሚል በአደባባይ በደፈናው ስህተት መፈጸማቸውን አምነው ይህቺን ሴት በቤተመቅደስ ቆመው ይቅርታ እንዲጠይቁ ከ4ምእመናን ሶስቱ ጠየቁ። አራተኛው ግን ይህ ነገር በእኛው መሀል ይቅር፣ ሴትየዋን እኛ ይቅርታ ጠይቀን ለሌላም ሰው እንዳትናገር እናግባባት በሚል አቋም ይይዛሉ። የተቀሩት ሶስቱ ግን ይህ በተአምር አይደረግም ብለው ጉዳዩን ምእመኑ ፊት ይዘውት ቀረቡ። ብዙዉ ምእመን ካህን ቢያጠፋ እግዜር ይጠይቀው እንጂ ሰው ምን አገባው ባይ ሆነና ለካህኑ የቆመው ሰው ጉልበት አገኘ። እነኝህኞቹ እውነትን ይዘው ካህኑን ሞገቱዋቸው። ካህኑም ስለ እውነት ስንት ነገር እያስተማሩ ፊትለፊታቸው እውነት ሲያፈጥባቸው አልቻሉምና ልክናችሁ ልጆቼ ብለው ለይቅርታ ንስሀቸውን መናዘዝ ሲጀምሩ ከአራቱ አንዱ የሆነው ሰው ‘ልጅ እንጂ አባት ይቅርታ እንዴት ይጠይቃል’ በማለት ሌላውን ምአመን ምን ዝም ትላላችሁ በማለት ሲያነሳሳ ካህኑም ወዲያው ሀሳባቸውን ገልብጠው ጥፋተኛ አይደለሁም በማለት ጉባኤው በብጥብጥ ተበተነ። ይህቺ አጋጣሚ ለካህኑ የትልቌ እድል በር ከፈተችና ለእውነት ሲሙዋገቱ የነበሩት ምእመናንና ተከታዮቻቸው ሲቀሩ የተቀሩትን ይዘው ቤተክርስቲያኗን ለአባ ጳውሎሱ ሲኖዶስ የእጅ መንሻ አድርገው በማቅረብ እሳቸውም የጳጳስነት ሹመታቸውን በማግኘት ሂደቱ ተጠናቀቀ።

መቼም ይሄ ጥፋት ህሊና ለአለው ሁሌም ሲያሳፍር የሚኖር ነው። ዛሬ በዚያ አካባቢ ለአንድ ቤተክርስቲያን የማይበቃ ህዝብ በአለበት፣ ሁለት ቤተክርስቲያን ተሰርቶ ሰዉም ቂም ቋጠሮ ያንን ክፉ ቀን በሁለቱም ወገን የማይረሱት ታሪክ ሆኖ ተቀምጧል። የያኔው ቄስ የዛሬው ጳጳስ እድሜ ሰጥቷቸው ይህን ማስተዋል ከቻሉ የህሊና ቁስል እንደሚሆንባቸው አልጠራጠርም። የእሳቸው ተቆርቋሪ ነኝ ብሎ ትልቅ ስህተት ውስጥ የጨመራቸውን ሰው ግን ያ ሰይጣን ባያሳስተኝ ኖሮ እኮ እንደሚሉ አሁንም በድጋሚ አልጠራጠርም። ሰውየው ካህን ተሳስቷል ከሚለው ሃሳብ ተሻግሮ ይቅርተቀ ይጠይቅ  የሚለው ሃሳብ  አሳፋሪ አድርጎ በውስጡ በማመኑና እምነቱን ከእራሱ አልፎ ለሌሎችና ባለጉዳዩንም የሃሳቡ ተጋሪ በማድረጉ  እራሱ መሳሳቱ ሳይበቃው ካህኑንና ሌሎችንም ከእውነት ጋር አጣልቱዋቸው ለብዙዎች የተረፈ የታሪክ ጠባሳ ጥሎ አልፉዋል። ደርብ ከፈለኝ በጽሁፎት ላይ ማጋነን ባይሆንብኝ ከ90 በመቶ በላይ ትችቱ ተክለሚካኤልን መዝለፍ  ነው። አንባቢም ሆነ ተተቺ እንዲሁም ተቺ እርሶ ትችቱን ስር በያዘና በጥሩ ምክንያቶች የእራስዎትን እይታ ቢሰጡ መልካም ነበር። መቼም ዶ/ር ብርሃኑ እንደቄሱ ደጋፊ ከአገኘሁ ብሎ ሽምጥጥ አድርጎ የእርስዎ ደጋፊ ሊሆን እንደማይችል እገምታለሁ። የእኔ ጽሁፍ አላማ በተክሌ ጽሁፍ አስተያየት ለመስጠት ባይሆንም ዶ/ር ብርሃኑ ግን የተክሌ ሀሳብ የእሱ ብቻ አለመሆኑን ሊገነዘበው እንደሚገባ አሳስባለሁ። ባለራዕዩ፣  ምሁሩ ፣ የምርጫ 97 ሞተሩ፣የእስርቤቱ ታሪክ ጸሐፊው እንዲሁም የግንቦት 7 ፈጣሪው ብርሃኑ እንደ ሰው ለፍጹምነት ሲሮጥ ያልፋል እንጂ ፍጹም አይደለም። እንደ ሰው የሚጎለውን ፊትለፈት ነግረነው አድመጭ መሪያችን እንዲሆን ማድረግ ይኖርብናል።  መተቸትን ዛሬ በቅርብ ሆኖ ካላስለመድነው ነገ ስልጣን የመያዝ አጋጣሚው ቢፈጠርና  አውሬ ሆኖ ቢበላን ጥፋቱ የእኛ እንጂ የእሱ አይሆንም። ለማንኛውም ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ እባክህን አስተያትህን ስጠን። ካልሆነ ግን ኢሳት ላይ ጠይቁት ከተባለ ይህቺ ጥያቄ የእኔ ናት።

መሠረት ከቴክሳስ

 

Pen

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>