Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው (ሄኖክ የሺጥላ )

$
0
0

minilikኣጤ ምኒልክን ሲወቅስ 100 ኣመት የፈጀው ትውልድ ፥ እሱ የኖረበትን መቶ ኣመት ምን ሰራበት ? ቀዳማዊ ሃይለ ስላሴን ሲተች የኖረው « ያ ትውልድ » ንጉሱ ከወደቁ ወዲያ እሱ የኖረበትን 42 ኣመታት ምን ጠቃሚ ነገር ኣደረገበት ? ደርግን 17 ኣመት በርሃ ሲታገል የኖረው ህውሃት ስልጣን በእጁ ላይ ኣስገብቶ የኖረበትን 25 ኣመታት የእርዳታ ስንዴ ከመለመን ውጪ ፥ የቀደሙ ስርዓቶችን በደልን እየዘከዘከ ፥ ባለፈ ስርኣት በደል ኣይን ንፁህ ነኝ ቢለንም በስራው ስንለካው ፥ ጨካኝ ከሚባለው የደርግ ዘመነ መንግስት የባሰ ጠርናፊ እና ገዳይ መሆኑን ነው ያየነው ።

እኛስ 25 ኣመት በኣንድ ጨቋኝ ስርኣት ክርን ስንደቆስ ፥ እንደ ባቢሎኖች መግባባት ኣቅቶን ከመናከስ ውጪለሃገራችን የሚበጀውን ነገር ለማድረግ ምን ሰራን ? የሃገራችን ቁስል የውሻ ቁስል እንዲሆን ኣንድነትን ከመምረጥ ይልቅ ፥ በክክል በጎጥ በብሄር ተቧድኖነን ፥ በቁስላችን ላይ እንጨት እየሰደድን ፥ ማንነታችንን መርዘኛ የጎሳ ተውሳክ እንደ ማር ኣልሰን ፥ በቀበሌ ልክ ሃገር መስለን መታየት ኣሻን እንጂ ፥ እንደው ምን ሰራን ?

ትናንት ቤተ እምነቱን በመናቅ ፥ የሶሻሊስት እምነት ኣራማጆች የነበሩት ፥ በሃሉን ለማያከብሩለት ህብረተሰብ ስለ ህብረተሰባዊነት እየደሰኮሩ፥ እምነቱን የግሪክ ኣማልክት ዘመነኛ ተረት እንደሆነ በኣደባባይ እያወሩ፥ ስለ ኣንድነት ቢሰብኩም ፥ ስለ ሃገር ፍቅር እጃቸውን « ኢትዮጵያ ወይም ሞት » ብለው ወደ ሰማይ እንደ ሮኬት ቢለቁም ፥ ኢትዮጵያ ሳትሞት እነሱ ግን ካፈሯ ስር ተቀብረዋል ። ዛሬም የለውጥ ፥ የእድገት ፥ የመሻል እና የመሻሻል ማሳያዎቻችን በሰው ላይ ሳይሆን በድርብርብ ብሎኬቶች የተሰሩ ፎቆች ማንነት ላይ የቆሙ በማስመሰል ፥ ህዝቡ እየተራበ « ልማት » ብለው ሲደሰኩሩ ፥ ንፁሃን ዜጎቿን እንደ ከብት በ ቃጫ እያሰሩ የብሄር ብሄሬሰቦች መብት እያሉ በሃገር ዱካ ላይ ሲያሴሩ እያየን ነው ። እጅግ የሚያሳዝነው ደሞ ቢያንስ ሰው መሆናቸውን ኣለማወቃቸው ፥ ደካሞች ፥ ተሰባሪዎች ፥ ሟቾች መሆናቸውን ኣለመገንዘባቸው ።

እኛ ዛሬ ላይ ኣድራጊ ፈጣሪዎቹ ፥ ዛሬ ላይ ባለ ጉልበቶቹ ፥ ዛሬ ላይ ባለ ሰራዊቶቹ ፥ ያለፈውን ስንጠላ ፥ ስናጣጥል እና ስናብጠለጥል እኛ ግን በነበርንበት ዘመናችን ፥ በኖርንበት የጉብዝና ወራታችን ምን ሰራን ? የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው።

ለሁሉም ነገሮች መልስ ኣለኝ ለሚል ግን ኣንዱንም መልሶ ለማያውቅ ስርኣት እኛ የምን ኣይነት ቅሌታም መንፈስ ባለቤቶች ብንሆን ነው ይህን ሁሉ ዘመን ድንቁርናውን ተስፋ ኣድርገን የኖርነው ? በየትኛው የጀግንነት ስሌት ነው ሚኒሊክን የሚረግሙ ኣንደበቶች ለወያኔ ተንበርክከው የሚገዙት ? በየትኛው የሰውኛ ሂሳብ ነው መንግስቱ ሃይለማሪያምን ኣሰይጥነው የሚያቀርቡ ሚዲያዎች ስለ መለስ ራዕይ ሊነግሩን የቻሉት ? ምን ያህል ነው የተናቅነው ? ምን ያህልስ ነው ግድ የማይሰጠን ? ኣረ እንደውም « ወያኔ በደለን » ብለን እለት እለት ከምናላዝነው ምን ያህሉ ነው የወያኔ ? በወያኔ መበደልን እንደ « ጎመን በጤና ኑሮ » የምናይ ሰዎች እንደው በምን ኣይነት ግንዛቤ ነው ስለ ሌላ ስርኣት በደል ልናወራ የምንችለው ? ወያኔን ተሸክሞ የኖረ ትከሻ እንዴት ምኒሊክን ለማዋረድ ተውረገረገ ? ወያኔን ኣምልኮ የሚኖር ህዝብ እንዴት የኣሉላ ዘር ነኝ ብሎ ሊፎክር ይችላል ? 10 ሚሊዮን ህዝብ ተርቦ ኣድገናል የሚል መሪ ከመሃከላችን እስኪገኝ የት ነበርን ? ኣክሱም ለወላይታው ምኑ ነው የሚል ባለጌ ባለ ራዕይ ተብሎ ሲሞካሽ ፥ በሃገር ላይ ሬሳ ሲሳለቅ እኛ የት ነበርን ? ኣዎ የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው!

 

The post የዛሬው ማንነታችን ፥ ሁላችንም ባንድነት የወደቅንበት የጋራ ዋጋችን ነው (ሄኖክ የሺጥላ ) appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles


የባለቤቴ ፖርን (የወሲብ ፊልም) ማየት ልማድ ወደማልፈልገው ፍቺ እየመራኝ ነው |የዶክተሩን ምላሽ ከነመፍትሄው ያንብቡ


ምነው “ከኑግ የተገኘህ ስሊጥ አብረህ ተወቀጥ” አደረጉት? –ዓለም ባልከው


Health: ሴትን ልጅ ስቀርብ አልረጋጋም፤ በጣም እፈራለሁ፤ ምን ይሻለኛል?


ሕመም አንድም ለትምህርት አንድም ለሞት


Tamrat Desta - Ahun Teredahut አሁን ተረዳሁት (Amharic With Lyrics)


2009 ዓ.ም. የፋሲካ በዓል ዋዜማ በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ቅዱስነታቸው ባሳረጉት መስዋዕተ ቅዳሴ በድምቀት ተከበረ።


Health: ወንዶች ለእኔ ሣሙና የሆኑበት ምስጢር የ40 ቀን ዕድሌ በመሆኑ ይሆን?


ደብረ ዘይት፡- የዓለማችን ታሪክ ፍፃሜ ቅዱስ ተራራ በፍቅር ለይኩን


የአዲስ አበባ ጉዶች: በማሳጅ ስም የወሲብ ገበያ ደርቷል * ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም ‹ማግኔት› በሚል በውጭ ሚድያዎች...


በኢትዮጵያ ሙዚቃ እንደነገሠ 50 ዓመት የደፈነው አሊቢራ



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>