Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የ12 ሚሊዮን ብር ወሬ: መንግስት ይህን ዘገባ በአዋሽ ባንክ ዙሪያ ለምን ማቅረብን ፈለገ?

$
0
0

AWASH_INTERNATIONAL_BANK_LOGOመንግስታዊ ሚድያዎች በአዋሽ ባንክ ዙሪያ ዘመቻ የጀመሩ ይመስላል። መቼም ስም መስጠት ስለምንወድ በተለምዶ በሃገራችን የኦሮሞዎች ባንክ ተብሎ የሚፈረጀው አዋሽ ባንክን በሚመለከት በምርመራዊ ጋዜጠኝነት ያገኘነው መረጃ ነው በሚል “ልዩ የምርመራ ዘገባ የአዋሽ ባንክ ፕሬዚዳንቶች የ12 ሚሊዮን ብር ብድር ጉዳይ አነጋጋሪ ሆኗል” ሲሉ ያቀረቡት ዘገባ ከጀርባው ምን እንዳለ አነጋጋሪ ሆኗል። የሕወሓቱን ወጋገን ባንክ ለመፈተሽ ድፍረት የሌላቸው መንግስታዊ ጋዜጠኞች ይህን ምርመራ ለምን ሊያቀርቡ ቻሉ? ምላሽ ያላችሁ በአስተያየት ላይ ጻፉት መንግስታዊ ሚዲያዎች ያቀረቡትን ግን ለግንዛቤ እንደወረደ እንካችሁ።
በአዋሽ ኢንተርናሽናል ባንክ ፕሬዚዳንቶች ከባንኩ የተወሰደው 12 ነጥብ 35 ሚሊዮን ብር ብድር አነጋጋሪ ሆኗል።
የባንኩ ፕሬዚዳንት አቶ ፀሐይ ሽፈራው 6 ነጥብ 65 ሚሊዮን ብር የመኖሪያ ቤት ብድር የወሰዱ ሲሆን፤ የብድርና ሪስክ ማኔጅመንት ምክትላቸው አቶ ባጫ ጊና ደግሞ 5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ብር ተበድረዋል።
ፕሬዚዳንቶቹ ብድሩን የወሰዱት ባለፈው ዓመት ነሐሴና ዘንድሮ በጥቅምት ወር ቢሆንም ጉዳዩ በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ዘንድ የታወቀው በጥር ወር አንድ የባንኩ ባለአክስዮን መረጃውን ከሰጡ በኋላ መሆኑን የቦርዱ ሰብሳቢ አቶ ወሌ ጉርሙ ተናግረዋል።
እንደ አቶ ወሌ ገለጻ፤ የፕሬዚዳንቶቹንም ሆነ የሌሎች የሰራተኞችን ብድር በተመለከተ የቦርዱ እውቅናና ፈቃድ አያስፈልግም። ያም ሆኖ ቦርዱ የፕሬዚዳንቶቹ የብድር ጉዳይ እንደደረሰው በተለያዩ አካላትና ኮሚቴዎች አስመርምሮ በባንኩ የብድር ፖሊሲ አግባብ የተወሰደ ብድር መሆኑን እንዳረጋገጠ አቶ ወሌ ገልጸዋል።
የአገሪቱን ባንኮች የመከታተልና የመቆጣጠር ስልጣን ያለውና የአዋሽ ባንክ ቃለ ጉባዔ በእጁ የሚገኘው ብሔራዊ ባንክ ጉዳዩን ማጣራት የጀመረው ሰዎች ስለ ብድሩ ቅሬታ ካደረሱት በኋላ መሆኑና ጉዳዩ ከስምንት ወራት በላይ ቢያስቆጥርም እስካሁን በማጣራት ሂደቱ የደረሰበት ደረጃ አለመታወቁ ነገሩን ይበልጥ አነጋጋሪ አድርጎታል።
አዲስ ዘመን ጉዳዩን በመመርመር መረጃ በማሰባሰብ ላይ እያለ ፕሬዚዳንቱ ቤቱን ሸጠው ብድሩን መመለሳቸው ከአቶ ወሌ ጉርሙ የተገለጸለት ከመሆኑም በላይ ጋዜጣውም ይህንኑ አረጋግጧል።
የብድር ውሎቹ እንደሚያሳዩት ፕሬዚዳንቶቹ ገንዘቡን የወሰዱት «የሰራተኞች የመኖሪያ ቤት ብድር» በሚል በሰባት በመቶ ወለድ ቢሆንም፤ አቶ ጸሐይ በብድሩ የገዙት ቤት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሠራተኞች መከራየቱን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ቤቱ ከሚገኝበት ወረዳ ገቢዎች ጽህፈት ቤት ጋር በመሆን ደርሶበታል። አቶ ጸሐይ ቤቱን አከራይተው የቆዩ ቢሆንም ከቤት ኪራይ ከተገኘው ገቢ ግብር እንዳላስገቡም የገቢ ጽህፈት ቤቱ አረጋግጧል።
ቤቱ ለኪራይ አገልግሎት ከዋለ ደግሞ ባንኩ እንደሌሎቹ የቢዝነስ ብድሮች በ16 በመቶ ወለድ ገንዘቡን ማበደር እንደነበረበት ተገልጿል።
ፕሬዚዳንቱ ዓምና በሰባት ሚሊዮን ብር የገዙትን ቤት በቅርቡ በ11 ሚሊዮን ብር የሸጡት ቢሆንም፤ በገቢ ግብር ዓዋጁና በደንቡ መሰረት የመኖሪያ ቤቱን በማስተላለፍ ከተገኘው ጥቅም ግብር እንዳልከፈሉ ተረጋግጧል።
ጋዜጣው በጉዳዩ ላይ ባደረገው ጥልቅ ምርመራ በተለይም የፕሬዚዳንቱ የብድር መያዣ በህግ ፊት የማይጸና መሆኑንና ብድሩም የተወሰደው ያለመያዣ እንደነበር አረጋግጧል።
የባንኩ የኮምፒዩተሮችና የተሽከርካሪዎች ግዥም እየተመረመረ ይገኛል። የፕሬዚዳንቶቹ ብድር ለቦርዱ መታወቁን ተከትሎ በቦርድ አባላት መካከል በተፈጠረው ውጥረት አንድ የቦርድ ዳይሬክተር ከቦርዱ ራሳቸውን አግልለዋል።

በዚህ መንግስታዊ ሚድያዎች ባቀረቡት ዘገባ ላይ አስተያየትዎ ምንድን ነው?


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>