Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የጅዳ ቆንሳ ጽ/ቤት በዜጎቻችን ዙሪያ እይሳየ ባለው ቸልተኝነት የአንዲት ኢትዮጵያዊት ህይወት ጠፋ።

$
0
0

2cdf193e-db45-4fa1-8ddf-e37ad6f87242በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት መጠለያ ማዕከል መፀዳጃ ክፍል ውስጥ ታንቃ ለሞተቸው ወጣት የቆንስላው መጠለያ ሹማምንቶች በቀጥታ ሃላፊነትን መወሰድ እንደሚገባቸው የሚናገሩ የአካባቢው ምንጮች ተጠላዩች የተስተካከለ የመኝታ ቦታም ሆነ የምግብ አቅርቦት የሌላቸው እና በፊት ከነበሩበት አካባቢ ተለውጠው ጉራንጉር ውስጥ እንዲኖሩ ከተደረገ ወዲህ መጠለያ በሚገቡ ዜጎቻችን ላይ እየደረሰ ያለው የአይምሮ መታወክ አሰሪዎቻቸው ከሚፈጽሙባቸው ግፍ እና በደል የከፋ መሆኑን ይናገራሉ። ወደተጠቀሰው መጠለያ የሚመጡ ዜጎቻችን በአሰሪዎቻቸው የተፈፀመባቸውን የመብት ጥሰት ተከታትሎ ማስፈፀም ይቀርና ዜጎችንን በወጉ ለሃገራቸው በማብቃቱ ረገድ የአቅም ውሱንነት የሚታይባቸው የቆንስላው ሃላፊዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች ወደ መጠለያ ለሚገቡ እህቶቻችን ደህነት ትኩረት ሰጥተው ሲንቀሳቀሱ አይታዩም ይላሉ ።

በተለይ ወደ መጠለያው ማዕከል ጤናማ ሆነው የሚገቡ ዜጎቻችን አይምሮቸው ታውኮ የሚወጡ ከመሆኑም በላይ በትክክል በማይታወቅ ምክንያት ሁለት ወር እና ከዛም በላይ ለሆኑ ጊዜያት የመጠለያ መዕከሉ ተቆልፎ ባቸው የሚኖሮ ዜጎች እንዳሉ ይነገራል። እራሳቸውን በማጥፋት ከዚህ የመጠለያ ማዕከል ጭንቀት ለመገላገል የሚሞክሩ እህቶች እንዳሉ መስማት የተለመደ ነው የሚሉ ወገኖች ዛሬ ቆንስላው ግቢ ውስጥ የተሰማው አሳዛኝ ነገር ሊከሰት እንደሚችል እየታወቀ በአካባቢው የአይምሮ ህመምተኞች በራሳቸው እና በሌላው ህይወት ላይ አደጋ እንዳያደርሱ ከወዲሁ መክላከል ሲቻል በቆንስላው መጠለያ ሃላፊዎች እንዝላልነት ህይወት ሊጠፋ ችሏል ብለዋል። ዛሬ ጠዋት ከጓደኞቾ ጋር በመልካም ሁኒታ ስትስቅ ስትጫወት እንደነበረች የሚናገሩ ባልጀሮቾ አሰሪዎቾ ባደረሱባት በደል አልፎ አልፎ ጤንነት እንደማይሰማት እና ወደ ቆንስላው ጽ/ቤት መጠለያ ከገባች ወዲህ የተሻለ ነገር ባለማግኘቷ ትበሳጭ እንደነበር ገልጸዋል። ወጣቷ ሃገሬ ምን ይዤ ገባለሁ ቤተሰቦቼ ከኔ ብዙ ነገር እየጠበቁ የነሱ ተጧሪ ለመሆን ሃገር ከምገባ እዚሁ ሞቴን እመርጣለሁ ባለች በሰዓታት ልዩነት የመጠለያ መጸዳጃ ክፍል ውስጥ ገብታ መታነቋን ይናገራሉ። ተመሳሳይ የሆነ የአይምሮ ችግር ያለባቸው ኢትዮጵያውያን ተጠላዮች ቆንስላው ጽ/ቤት እንዳሉ የሚገልጹ ውስጥ አዋቂ ዎች አሁንም የቆንስላው ጽ/ቤት ሃላፊዎች ዜጎቻችን እራሳቸውን ሊያጠፉ የሚችሉባቸውን የኤሊክትሪክ መስመር ስለት ነክ ነገሮችን ጨምሮ የተጠቀሱት ተጠላዩች በቀላሉ ሊታነቁ የሚችሉባቸውን ጠንካራ ማገሮችን በማስወገድ ለተጠቀሱት ዜጎቻችን የምከር አገልግሎት በመስጠት የዜጎች ህይወት መታደግ ሲቻል በዜጎች ላይ የመጠለያውን በሮች ከርችሞ ለረዥም ወራት ያለምንም ውጤት ማቆየት መፍትሄ ሊሆን እንደማይችል ይጠቁማሉ።

Ethiopian Hagere Jed Bewadi

The post የጅዳ ቆንሳ ጽ/ቤት በዜጎቻችን ዙሪያ እይሳየ ባለው ቸልተኝነት የአንዲት ኢትዮጵያዊት ህይወት ጠፋ። appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>