በአዲስ ጎማ አካባቢ አቃቂ ቃሊቲ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና አባላት ደህንነቶችና ፖሊሶች ባዘጋጁት የክስቻርጅ ላይ በግዳጅ እንዲፈርሙ ጫናዎች ቢደረጉባቸውም አንፈርምም በሚለው አቋማቸው ፀንተዋል፡፡ ደህንነቶቹና ፖሊሶቹ ያዘጋጁት የክስ ቻርጅ ፡- 1ኛ. “አንድነት ፓርቲን በጥቂቱ ይተዋወቁ” በሚል ርዕስ በተዘጋጀው ብሮሸር ላይ “ኢህአዴግ መራሹ መንግስት በመሳሪያ አፈሙዝ ታግዞ በይስሙላ ምርጫዎች ተመረጥኩ በማለት ሀገራችንን ከጀመረ 22 ዓመታት ተቆጠሩ፡፡” በማለት የቀረበው በቂ ማስረጃ የለውም፡፡ 2ኛ. “የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት በኢትዮጵያዊ አንድነት ወደ ተስፋ ጉዞ” በሚል ርዕስ የተዘጋጀው በራሪ ወረቀት ላይኢህአደድግ በየጊዜው በሚያወጣቸው ህዝብን ማፈኛ አዋጆች የታሰሩ ጋዜጠኞች፣የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎችና የእምነት ነፃነት እንዲከበር የታገሉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት በአስቸኳይ ፣ የፀረ ሽብር ህጉ ህገ-መንግስቱን በግልፅ የሚንድ ስለሆነ እንሰረዝ የሚለው ግልፅ ስላልሆነ እንዲሰረዝ” የሚለው ግልፅነት ይጎድለዋል፡፡ በሀይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ ማበጣበጥ ነው፡፡ 3ኛ. ወደ ፖሊስ ጣቢያ ሂዱ ስትባሉ ፍቃደኛ ባለመሆን ሁከት ፈጥራችኋል፡፡ የሚሉ ክሶችን የያዘ ነው፡፡ #Millionsofvoicesforfreedom #Ethiopia #UDJ #ADDISABABA -
↧