(ዘ-ሐበሻ) በሶማሊያ ዋና ከተማ ሞቃድሾ በማረፍ ላይ የነበረ አንድ የኢትዮጵያ ወታደራዊ አውሮፕላን ዛሬ ማለዳ ላይ መከስከሱን ከአዲስ አበባ የመጡ ዜናዎች አረጋገጡ። የኢትዮጵያ መንግስትም ይህንን ዜና ያረጋገጠ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 4 መድረሱንም አስታወቋል።
የወታደራዊ እቃ ማጓጓዣ አውሮፕላኑ አደጋ የደረሰበትለማረፍ በሚሞክርበት ወቅት እንደሆነ ዓለማቀፉ የሚዲያ ተቋም ሮይተርስ ሲዘግብ በአውሮፕላኑ ውስጥ ተጭነው ከበነበሩ 5 ሰዎች ውስጥ 4ቱ ሕወታቸው ማለፉም ተዘግቧል።
(ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን)