Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በረከት ስምዖን ሞቶ አንዳርጋቸውን ሆኖ ተነሳ ( ሄኖክ የሺጥላ )

$
0
0

simon
አማሪካዊው ጠሐፊ ዊልያም ጀምስ ስለ ( pragmatism, radical empiricism, and pluralism) ብዙ የፍልስፍና አዲስ መሰረተ ሃሳቦችና እና የ ሃሳብ ፍሰቶችን ያመጣ ( ያመነጨ ) ፣ የጻፈ ፣ ያሳወቀ እና የሞገተ ፣ ግሩም የፍልስፍና ሊቅ ነው ። ይህ ሰው << We live forward, we understand backward >> በሚለው ሃሳቡ እና የሃሳብ ትርጉም ፣ ውስጠ ሚስጥራዊ ጥናት ይታወቃል ። ለነገሩ አብዛኛው ሰው ፣ የዚህንን አባባል ባለቤትነት ለዊልያም ጀምስ ቢሰጠውም ፣ ራሱ ጀምስ ይህንን አባባል ለመጀመሪያ ጊዜ የሰማው ፣ እ ኤ አ በ 1904 ዳን ሀራልድ ሆፍዲንግ [ Dane Harald Høffding (1843-1941)] በጀምስ ተጋብዞ ፣ በጀምስ ፍልስፍናዊ አስተሳሰቦች ላይ ፣ በይበልጥም (pragmatism, radical empiricism, and pluralism) ላይ ፣ ለጀምስ ተማሪዎች ፣ በሃርፋርድ ዩኒቨርስቲ ተገኝቶ ፣ ማብራሪያ በሰጠበት ወቅት ፣ ከ ዴንሹ የፍልስፋና ሊቅ Kierkegaard ( ኪኢርክጋርድ ) እንደ ጥቅስ ወስዶ የተናገረው ነበር ። እኔም ዛሬ በዚህ ጥልቅ እና ትልቅ አባባል ዙሪያ ፣ ስለ ማህበረሰባዊ የአስተሳሰብ ክሸፍቶች ፣ ስለ ማንነት ብክነቶች ፣ ህዝቦች የሚመሩበት ንዑስ ስርዓት ሲዝግ ፣ ህገ-መንግስት በራሱ በመንግስት-ሲናድ ፣ እና ያ የምንግስት አካል ፣ በማናለብኝነት እና ምን አገባኝ ጉልበት ታጅሎ ፣ ሕዝብ አስገድዶ ለመምራት ሲያስብ ፣ ማህበረሰቡ በእውነት እና እውነት ባልሆነ ነገር መሃከል ያለውን ልዩነት ፍጹም መለየት እስከማይችልበት ደረጃ እንደሚደርስ ፣ ይህም በውሸት ላይ የተመሰረተ የለት-ተለት ኑሮ ፣ በሀገር ህልውና ላይ ስላለው ተግዳሮቶች እና የተግዳሮቶቹ መስተጋብር የሚያትት ይሆናል ። በመጨረሻም አንዳንድ የምሳሌ ዘውጎችን አነሳለሁ ።

በመጀመሪያ ጀምስ << We live forward, we understand backward >> የሚለውን አባባል ደጋግሞ የተጠቀመው በ << radical empiricism>> ትንተናው ላይ ሲሆን ፣ ይህም በ 1905 ባሳተመው መጽሐፉ ውስጥ ይመስለኛል ፣ በዚህም አተኩሮ የሚዘግበው << the relationship between reflection on a prior experience and the experience itself>> << በቀደመ ልምድ ( ገጠመኝ ) ነጸብራቃዊ ትዝታ እና በትዝታው ምንነት መሃከል >> ስላለው ዝምድና የሚያትት ሲሆን ፣ የሰው ልጅ በቀደመው ታሪኩ ያሳለፈው ማንነቱ ፣ ወደፊት ሊሄድ ሲል እየመዘዘ የሚያወጣው የማንነት መለኪያ መስፈርቱ እንደሚሆን ይናገራል ። ይህም ማለት ፣ ሰውየው ገበሬ ከነበረ እና ፣ በቀጣይ ህይወቱ ነጋዴ ቢሆን ፣ የነጋዴነቱ ስኬት ወይም ውድቀት የሚለካው ፣ ገበሬ በነበረ ጊዜ በነበረው ጥንካሬ ወይም ስንፍና ነው ወይም ይሆናል ፣ እንደማለት ነው ። ይህም <> የሚለውን አባባል በደንብ እንደሚዘክረው ያብራራል ። ከዚህ አገላለጽ ተነስተን ደሞ ፣ ስለተለያዩ ጉዳዮች ሰፋ ያለ ማብራሪያ መስጠት እንችላለን ማለት ነው ። ለምሳሌ ህውሃት ( ወያኔ ) ፣ ወደፊት እየኖረ ወደ-ሗላው ብቻ የሚረዳ ስርዓት ለመሆኑ ከበቂ በላይ መረጃ አለን ። ለምሳሌ ፣ ዛሬም ደርግን ስለመጣሉ ያወራልሃል ፣ ዛሬም እኔ ጀግና ነኝ ፣ አንተ ግን አይደለህም ይልሃል ፣ ዛሬም ነገሮችን ሁሉ በጉልበት ለመወሰን ብቻ እንደሚችል የነገሮች ሁሉ አዛዥ እና ነዛዥ እሱ ብቻ እንደሆነ ይነግርሃል ፣ ዛሬም ተራራው ፣ ደኑ ፣ ሳሩ ፣ ቅጠሉ ለሱ እንደሚንቀጠቀጡ ፣ ለሱ እንደሚረግዱ ፣ እሱ ብቻ በደሙ የታደጋቸው ተራርሮች፣ ያለሱ ቢዘሩ እንደማያበቅሉ ፣ ቢታረሱ እንደማያፈሩ ፣ ቢጎለጎሉ እንደማይለሙ ይነግርሃል ። ከምንም በላይ ፣ ታሪካዊ ውሸታምነቱን አጠናክሮ መቀጠሉ ፣ የሃውዜን ማንነቱን ትናንት በነ- አኬል-ዳማ ሲደግመው ፣ ዛሬ ደሞ- <<በአንዳርጋቸው መጽሐፍ ጻፈ>> የቅጥፈት ዜና አጠናክሮት ሊያደልበው እንደተዘጋጀ ስንረዳ ፣ ጀምስ እንዳለው << We live forward, we understand backward>> የሚለውን አባባል ያለ አንዳች ግድፈት እየፈጸመ ያለ ስርዓት ስለመሆኑ እንረዳለን ።
እውነቶችን ወይም ኩነቶችን ከራሳችን ልምድ ብቻ ተነስተን ለማርቀቅ ስንተጋ ፣ የዛሬ ማንነታችን ሙሉ በሙሉ <<የኛ ታሪክ ብቻ>> ባልነው ሲገደብ ፣ ከኛ ወዲያም ወይም ከኛ ወዲህ ያሉትን እውነቶች ስንጥል ፣ ስለ-ራሳችንም የምናወራው ወይም እኛ ነን ብለን የምንናገረው ፣ የገሃዱ ዓለም እኛ ምን እንደሆንን በአደባባይ የሚመሰክረውን ግድፈታችንን ሳይሆንን ፣ ቀባብተን ያቀረብነውን ሰባራ ሸክላ መሳይ ስብእናችንን ሲሆን ፣ የጥንካሪያችን መለኪያ ፣ የለውጣችን ማሳያ አስረጅ ሲነጥፈው ፣ ያለፈ የጦርነት ታሪካችንን ከፊት እያስቀደምን << ብትቀበል ተቀበል ፣ አለበለዚያ እኛ ደርግን የጣልን ጀግኖች ነን >> ፣ በሚል ማስፈራሪያ ለመኖር ስንተጋ ፣ እኛ እውነትም ወደፊት እየኖርን ፣ ወደ- ሗላ የምንረዳ ስለመሆናችን ምንም ነጋሪ እና ነዛዥ አያስፈልገውም ።

ኃያሉ ጎልያድን የገነደሰው ዳዊት ፣ በሐጸ- ዝሙት ተነድፎ ፣ ኃጢያት ነግሶበት ፣ የኦርዮንን ሚስት ሲቀማ ፣ ኦርዮንንም በደቂቀ አሞናውያን ሰይፍ ሲያስመታ ፣ የድሀውን ጠቦት ሲቀማ ፣ እሱንም ደግሞ ሲያስገድለው ፣ ዳዊትም ወደፊት እየኖረ ፣ ወደ- ሗላ ይረዳ ስለነበረ ነው ። ዛሬም አንዳርጋቸው በቅያፋ ፊት ሲቆም ፣ ሕግ በበደነበት ፣ እውነት በተረሳበት ፣ ታሪክ በተጨማለቀበት ፣ ይሉኝታ በፈገመበት ፣ ወደ- ፊት እየኖረ ወደ ሗላው በሚረዳ ስርዓት ፣ ሕግና ደንብ ውስጥ ፍትህ እና ፍርድ እንዲያገኝ ሲደረግ ፣ ከልብ ወለድ ፈጠራ ፣ ከሐሰት ክስ ፣ ከተምታታ መረጃ ፍርጃ ነጻ ይሆናል ብሎ ማሰብ ዘበት ነው ። በይበልጥም ሐሰት ከተንዠረገገብት ፣ ቅጥፈት ኩልል ብሎ ከሚፈስበት ፣ ክህደት እንደ ሰብል በማዳበሪያ ከሚያድግበት ፣ ልቃሚነት ከሚወደስበት ፣ ተራነት ከሚወደስበት ፣ ልቅነት ከነገሰበት፣ ከህውሃት መንደር እንዲህ ያለው ዜና ሲሰማ ፣ ሰሚውንም ተሰሚውን ግራ የሚያጋባ አዲስ ነገር ይሆናል ብለን አናስብም ። የሁሉም ቅጥፈቶች በሽታ ወደፊት እየኖሩ ወደ ሗላ ከመረዳት የመነጨ ነውና ።

አልክሳንደር ዱማስ ( The Three Musketers ) በሚለው መጥሀፉ ላይ ፣ በሶስተኛው ክፍል ፣ ስለ አንድ እስረኛ ያወራል ። በምጽሐፉ የመጀመሪያ ምዕራፍ ላይ ( The Prisoner ) በሚለው ክፍል ስር ፣ ፊቱን በብረት ከተሸፈነው እስረኛ ጋ ፣ አራሚስ የተባለው ገጸ ባህርይ ፣ ከ እስረኛው ጋ የሚያደርገውን ቃለ ምልልስ በጣም በጥቂቱ ይህንን ይመስላል

አራሚስ “Well, then, you ought, as a penitent, to tell me the truth.”
እስረኛው “My whole desire is to tell it you.”
አራሚስ “Every prisoner has committed some crime for which he has been imprisoned. What crime, then, have you committed?”
እስረኛው”You asked me the same question the first time you saw me,” returned the prisoner.
አራሚስ “And then, as now you evaded giving me an answer.”
እስረኛው”And what reason have you for thinking that I shall now reply to you?”
አራሚስ”Because this time I am your confessor.”
እስረኛው”Then if you wish me to tell what crime I have committed, explain to me in what a crime consists. For as my conscience does not accuse me, I aver that I am not a criminal.”
በነገራችን ላይ ዱማስ ይህህንን ታሪክ የጻፈው ከእውነተኛ ታሪክ ላይ ተነስቶ ነው ፣ የዱማስ የዚህን ታሪክ መጻፍ ተከትሎ ፣ ታታላላቅ ጸሐፍት ( እንደ ቮልቴር ያሉ ይህ የብረት ጭንብል ፊቱ ላይ አርጎ ( ተሸፍኖ ) ታስሮ ስለነበረው ሰው ሌሎች ታሪኮችን ጽፈዋል ። በአብዛኛው፣ የፈረንሳዩ ንጉስ የሊውስ 16ኛ ልጅ ነው ተብሎም እንደታመነ ካነበብኩት መረዳት ችያለሁ ።

ወደ ተነሳሁበት የእስረኛ እና የአናዛዥ የሃሳብ ምልልስ ስንገባ ፣ እጅግ አበክሬ፣ (በአሕጽኖት እንደሚሉት ማለት ነው ) መመልከት የምፈልገው አራሚስ ፣ << እኔ አናዛዥህ ነኝ ፣ እኔ ንስሐ አስገቢህ ነኝ >> <<"Because this time I am your confessor.">> የሚለው ላይ ነው ። አንዳርጋቸው ጽጌ ታፍኖ ከተወሰደበት ጊዜ ጀምሮ ፣ በያንዳንዷ ደቂቃ ፣ አናዛዦቹ << በል ንገረን ፣ ይህንን አውጣ ፣ ይህንን በል ፣ ይህ አልሆነም ወይ?!>> እያሉ ሲያሰቃዩት እንደከረሙ መገመት ሳይሆን እንዳደረጉት እናውቃለን ። አንተ ወንጀለኛ ነህ ሲሉት ፣ <<በመጀመሪያ ግን ወንጀል ምንድን ነው ?>> ሲላቸው ፣ << የምጠይቅህን መልስልኝ ?!>> ሲባል ፣ << የጠየከኝን እንድመልስልህ ዛሬ ምን የተሻለ ምክንያት ኖረህ >>ሲል ፣ ዛሬ የአንዳርጋቸው ሕይወት ፣ እንደ ሞንቴ ክርስቶው እንደራሲ ፣ እንደ ቄስ ፋሪያ ፣ እንደ ቄስ ቡሶኒ ፣ የልብ-ወለድ ምልዓት ተላብሶ ፣ በህውሃት ደሴቶች ላይ የተቀበረ የምኞት እንቆዎችን ፣ የሐሰት ክብሮችን ፣ የጭብርብር እድገቶችን፣ ጽፎ እንዲያመሰግን ፣ ሀሌ-ህውሃት እንዲል ፣ ዳጎስ ባለ መጥሃፋው የተረቺነት እና የተሸናፊነት ስነ ልቦና በሕዝቡ ልብ ውስጥ ለማስረጽ ፣ ስሙን ለማጥቆር የሚደረገው ነገር ሁሉ ፣ ህውሃት ዛሬም ወደፊት እያየ ወደ -ሗላው የሚረዳ ጨቋኝ አካል ከመሆን የዘለለ አንድም የሚያመጣው ወይም የሚነቀንቀው ስብእና እንደሌለን ይረዳ ዘንድ ፣ አራሚስ የሚጠይቀው እስረኛው መልስ ፣ የኛ አንዳርጋቸው ቃል እንደሆነም ለምናውቀው እኛ ፣ የአንዳርጋቸው መጽሐፍ ጻፈ ቅጥፈት ለ- ህውሀቶች ሌላ አኬልዳማዊ ድግስ ከመሆን አልፎ ፣ ሌላ ጅሃዳዊ ሐረካት ከመሆን አልፎ ፣ የተለየ ጭብጨባ እና መረዳት ያተርፍላቸዋል ብለን አናምንም ፣ አንጠብቅም ።

ዛሬ በረከት ስምዖን የሞተው ወይም የታመመው ፣ በአንዳርጋቸው ስም መጽሐፍ ሆኖ ሊነሳ ፣ የደደቢት ደሴቶች ግሁሣን ፣ የሞንቴክርሥቶ እንደራሲ ደራሲ ሆኖ ብቅ ልል ታስቦ እንደሆነም ሰምተናል ። በይበልጥም ፣ ለአድ ዓመት ከዘለቀው የአንዳርጋቸው ስቃይ ( ቶርቸር ) ውስጥ ምንም ያላገኙት ህውሀቶች ፣ ከሱ ጋ በርሃ ሳሉ ፣ ስለሱ በቅርብ ያውቁ ከነበሩ ሰዎች ( አንዱን እኔም በቅርብ አውቀዋለሁ ፣ በደቡብ አፍሪካ ይኖር የነበረ ልጅ አሁን ወያኔ ቪላ ቤት ሰጥቶ ፣ አቀማጥሎ የያዛቸው ሆድ አደሮችን ታሪክ በማሰናሰን ) ፣ ታሪኩ እውነት እንዲመስል ፣ በይበልጥም አንዳርጋቸው ሲያዝ ከ ላፕ-ቶፑ ውስጥ ያገኙትን መረጃዎች እንደ አንድ ትልቅ የመጽሐፉ ግብአት በመጠቀም ፣ ሕዝቡን ለማሳመን ፣ ሃያልነታቸውን ለማስያት ፣ የግንቦት ሰባት ደጋፊና አባሎችን ስም ዝርዝር በመጽሐፉ ውስጥ በማስቀመጥ ፣ ሰዎችን ይበልጥ ለማስፈራራት ፣ ከተቻለም ይቅርታ እንዲጠይቁ ለማግባባት የተጻፈ መጽሐፍ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለንም ።

ያም ሆኖ ፣ አሁንም ወያኔ ከመውደቅ አይድንም ። በወሬ የማንፈታ ፣ ስለምንም አይናችን የማይጨፈን ቆራጦች መሆናችንን ያውቁት ዘንድ ፣ ትግሉን በመቀላቀል ፣ እና በሙሉ ልብ በመደገፍ እንብታችንን እናሳያለን ። ደሞም እናሸንፋቸዋለን ። ምክንያቱም እኛ እነሱን ለማሸነፍ የተፈጠርን ልጆች ስለሆንን ። ወደፊት እየኖረ ወደ -ሗላ እያሰበ የሚኖር ስርዓት መጨረሻው ሽንፈት እና ውርደት ስለሆነ !


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>