(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን እና በደቡብ በተከፈተበት ወታደራዊ ጥቃት ከፍተኛ መደናገጥ ውስጥ የገባው የሕወሓት መንግስት ከትናንት ማማሻውን ጀምሮ በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞች ወጣቶችን ሲያፍስ መዋሉ ተዘገበ::
ዘገባዎች እንደሚጠቁሙት ከሆነ ከ4 ሺህ የማያንሱ የአዲስ አበባ ወጣቶች በትናንትናው እና በዛሬው ዕለት ታፍሰዋል:: አንዳንድ የዜና ምንጮች ለዘ-ሐበሻ እንደሚገልጹት ከሆነ የታፈሱት ወጣቶች በአብዛኛው ለውጥ ሊያመጡ ይችላሉ የተባሉት ናቸው:: በተለይም የአርበኞች ግንቦት 7ን ጥቃት ተከትሎ እነዚሁ ወጣቶች በአዲስ አበባ ከተማ ለለውጥ ሊነሱ ይችላሉ በሚል ስጋት ይህ አፈሳ እንደተካሄደ ይነገራል::
እነዚህ ወጣቶች መገናኛ አካባቢ የሚገኝ አንድ ትልቅ ስፍራ ውስጥ ታጉረው ከቆዩ በኋላ ወደ አልታወቀ ስፍራ በአውቶቡሶች ተጭነው መወሰዳቸውን የጠቆሙት የዜና ምንጮች ወደየት እንደተወሰዱ ለማረጋገጥ እንዳልቻሉ ገልጸዋል::