የህወሓት ቀኝ እጅ የሆኑ ባለ ሃብቶች በስውር እተገደሉ መሆናቸው ታወቀ፡፡ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ሕዝብ ግንኙነት ባሰራጨው ዜና የመለስ ዜናዊ የቅርብ ሰው የሆነ እና ከአዜብ መስፍን ጋር በአየር ባየር ንግድ እጅና ጓንት ሆኖ ይሰራ የነበረው ሀጎስ ወ/ገሪማ የተባለው የናጠጠ ቱጃር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ተገድሏል፡፡
ሀጎስ ወ/ገሪማ የህወሓት ታጋይ የነበረ ህወሓት በዘመኑ ከፈጠራቸው የናጠጡ ቱጃሮች መካከል አንዱና ዋነኛው ሲሆን ሀምሌ 13 207 ዓ.ም ከምሽቱ 4፡45 ላይ አ.አ ኮድ 2 ሰሌዳ ቁጥር 03220 የሆነች ውሃ ሰማያዊ ላንድ ክሩዘር መኪና በማሽከርከር ላይ እንዳለ አዲስ አበባ መስቀል ፍላወር አካባቢ ተገድሏል፡፡
ሀጎስ ወ/ገሪማ ከሳሞራ እና ከሌሎች የህወሓት ጀነራሎች ጋር ጥብቅ የሆነ ቁርኝት ያለው የንግድ ድርጅቶቻቸውን እንቅስቃሴ የሚያቀላጥፍ ነበር፡፡
በተጨማሪም ከትግራይ ወደ ሳንጃ በመሄድ በከፍተኛ ንግድና የእርሻ ልማት የተሰማራ አማረ የተባለ የህወሓት ባለ ሀብት በአካባቢው ሚሊሻዎች በጥይት ተደብድቦ ተገድሏል ሲል የአርበኞች ግንቦት 7 ዘገባ ያመለክታል::