Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የፈጣሪ ሥጦታ ንጡህ አዬርም ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ሹማምንት ፈቃድ ይጠዬቅበታል –በጨለማው ዘመን

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ  30.07.2015 /ሲዊዘርላንድ ዙሪክ/

ይድርስ ለፌስ ቡኩ የውጭ ጉዳይ ሚ/ር  ለአቶ ቴውድርስ አድህኖም – አዲስ አባባ።

Commentአዎን! በሶሻሊስታዊ ፋሽስታዊ ጎጣዊ ሥርዓት ዬተለያችሁ ናችሁ። እናንተን የሚመሰል ዝብርቅ ሥርዓት ዓለም በ21ኛው ምዕተ ዓመት አለም አታስተናግድም እና። እንዲህ – ትቀልዳላችሁ፤ በተፈጥሮ – ትሳለቃላችሁ፤ በፈጠሪ ጥበብ – ታባጭላላችሁ፤ በፋሽስት ተግባራችሁም – ትንደላቀቃላቸሁ፤ በናዚያዊ ዬጭካኔ ድርጊታችሁ – ትዝናናላችሁ፤ በስው ልጆች ፈጣሪያዊ ጸጋ – ትራገጣላችሁ — ፈጣሪ በመረቀለን ሰብዕዊ ነፃነትም – ትንጠራራላችሁ፤ ተወጣጠራችሁ፤ ምን እናንተ የማትሆኑት አለና /// መሳቂያዎች! ጥብቆ – መንጠቆ።

አሁን – በአሁኑ ጊዜ ስለምን ዬአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌን ሁኔታ መረጃ በለበጣ ለመስጠት አስፈለጋችሁ?! መቼም ስትፈጠሩ ሃፍረት የሚባል ነገር ሰርቶላችሁ አያውቅም፤ ዓይን አውጣ – ጉረኞች!

መቼም ኮረኮንች ናችሁና የደረደራችሁትን አሽዋማ – እኛም ውጪ ሆነን በኢንተርኔት እዬሳቅን ጎብኘት – እናደርገዋለን። የማላገጥ ጊዜ ሲያበቃ የመሸሸጊያ ትንሽ ቁጥቋጦ ካገኛችሁ …. ደባችሁን – ጠይቁት። የጭካኔ ሸራችሁ ይምልስላችኋል … አድራሻችሁ የት ሊሆን እንደሚችል አሳምሩ – ያረዳችኋል። ጥጋቡም ይተነፍሳል —-

ጠይቁን ብላችሁ አምልክታችሁ ዬሰጣችሁትን ቃለ ምልልስ – አዳምጠናል። የሰሞኑ መንደፋደፍ በትርምስ ተያይዛችሁታል። መጀመሪያ ድፍረት ይኑራችሁ፤ አርበኛችን ያሰራችሁበትን ቦታ ለመግለጽ። አርበኛችን የእኛ እንጂ የእናንተ ባልመሆኑ ሊዩት የናፈቁት ቆራጥ አርበኞች በመዲናች አሉ። መንፈሱ ሊቅ ነው። መንፈሱ የድል ሞገድ ነው። መንፈሱ የነገ ገድል ነው።

ለነገሩ እኮ ቆራጣ እፍረት ያለሰራላችሁ ስለመሆናችሁ እኮ፤ የ100 ዓመት ታሪኩ ተገልብጦ ባለታሪክ እናንተ – ሆናችሁ ዓይናችሁን በጥሬጨው ያጠባችሁ – ጉዶች፤ ለዛውም የሰው ልጆች ፍጥረት መገኛ የሆነችውን ድንቅነሽን ከዓለሙ መሪ ከክቡር ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ በክህደታችሁ እዬተንዘፈዘፋችሁ አብራችሁ ቁማችሁ – እዬሳቅንባችሁ አዬናችሁ። ዋንጫውንም አብራችሁ አነሳችሁ – መሳቂያዎች¡ እንዲህ ናት ኢትዮጵያ ማለት ከእግር ሥር የምታንበረክክ –  የኃያሎች ኃያልፍጹም ልቅና ያላት የዓለም ሁለመና።

እናንተ ለሰው ልጆች መብት ተቆርቋሪዎች ሆናችሁ ደግሞ¡ – ወይ ማላገጥ፤ እንዲህ ትቀልዳላችሁ፤ እንዲህም ታፌዛላችሁ፤ ከመለሲዝም ናዚዝም ብጣቂ ነገር እንደማይገኝ ህቅ እሲካላችሁ ድረስ ስትጋቱት ሰንበታችኋል – እራሳችሁ በተሞሾራችሁበት፤ አታሞዋን ስታስነኩበት በሰነባባታችሁት መድረክ እንዳዬነው ደብቁቁኝ  – ደብቁኝ ብላችሁ ዬእንብርክክ ስትሄዱ፤ ዝናብ ያበሰበሰው ካፖርት ትመስሉ ነበር ደመመን ተጫጭኗቸሁ፤ ማፈሪያ! የዓለም መሳቂያ መሆናችሁን ማን – በነገራችሁ?! ምን አልባት የዛሬው ቃለ ምልልስ ተብዬው የደመር ውሎ ሊሆን ይችላል። የለቅሶ ሰሞናታችሁን በወል – የምታወራርዱበት። እፍረት የሚባል ነገር። ለነገሩ እናንተ አልሰራላችሁ – ዝክንትሎች። ዝልብልቦች፤

ትውልዱ አክ እንትፍ ብሎ አንቅሮ ከተዋችሁ እኮ ዓመታት – ተቆጠሩ። ደባውም፤ ሴራውም፤ ሽፋኑም፤ ግርዶሽም አልቆ፤ ውልቅልቅ ብላችሁ አውላላ ሜዳ ላይ ባዶአችሁን እንዲህ – ትንቀዋለላችሁ። ይልቅ እርስዎ ነጠል ብለው ወጥተው፤ ወደ ጥሩ የሥራ መስክ – ሽግግር አድርገዋል። ሥራ ስሌለዎት ዬፌስ ቡክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነቱን በዶክተሬትነት በመወስደዎት  – ዕድለኛ ነዎት¡ ከልጆቾዎት ጋራ እንዲህ ሰኞ – ማክሰኞ፣ እቃ – ዕቃ፣ ዝላይ፣ ሽግ – ሽጎሽ፣ አዬሁሽ አላዬሁሽ …. ጎሽ¡ መደበዎት ይህ ነው …. ጥሩ ምርጫ …. ልክዎትና –  ተረድተዋል፤

አርበኛችን የሚፈልገው የሸፍጥን ፎቅ – ድልዝ ተግባርን – አይደለም። የታላቋን ብርታንያ  – ያ በነፃነት እፎይ ያለውን፤ በሥልጣኔ መሠረትነት በዘላቂነት የተገነባውን አፓርትመንት፤ የሐገሪቱን ዬሥልጣኔ ሁለገብ – አውታራትን፤ የፍትህ ተቋማትን ሙሉ ነፃነት፤ የሰው ልጆችን የእኩልነት ተቋማት መንፈስን፤ እንዲሁም የሚወዳቸውን ቤተሰቦቹን ትቶ ነው የሀገሩን ነፃነት ፍለጋ መከራን አብዝቶ – የተቀበለው። በደረጃም – በጸጋም – በብልህነትም – በተግባር ሰውነትም – በማስተዋል ልቅናም – ይበልጠወታል!

የአርበኛችን ፍልስፍናው በመሳሪያ ኃይል፣ በጎጥ ዛር ፍዳ የምታይ፣ አሳር የከተመባት ሐገር ሳይሆን፤ እንደ የሰው ልጆች መፈጠሪያነቷ፤ እንደ ሥልጣኔ ቀደምትነቷ፤ እንደ ጥቁሮች ዬነፃነት ዓርማነቷ፤ እንደ ሁለገብ ብቁ – አብነቷ፤ እንደ ታሪክ – ማህደርነቷ፤ እንደ አፍሪካ ህብርትና የተባበሩት መንግሥታት – መሥራች አባልነቷ፤  በህዝብ ፈቃድና ውሳኔ በጸደቀ ህገ መንግሥት፤ በምልዕት ፍላጎት በሚመረጡ – ልጇቿ፤ በህግ እኩልነት የምትዳደር – ሐገርን ማዬት ነው የሚሻው።

አርበኛችን – በዕዳ የተዋጠች – በልማና እና በብድር ትንፋሿ ታፍኖ ጠግባ ሳታድር በራህብ እዬተቆላች ጉሮሯዋ ደርቆ፤ መንፈሷ ተሰንጎ መከራ ስንቋ የሆነች የዕንባ ሐገርን – አይደለም። የአርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ራዕይ በራሷ አቅም፤ ባለት በቂ ቅምጥ የከርሰምድር ሃብታት – ጥሪትና ንብረት ዕውቅ ሳይንቲስቶቿ፤ ፈላስፋዎቿ፤ ሙሁር ልጆቿ ዘመኑ የፈቀደላቸውን ቡራኬ በአኩልነት ያገኙ ዘንድ በሙሉ ነፃነት ሙሉ ተሳትፎ የሚያደርጉበት አዲስ ብሄራዊ ሥርዓት በመፍጠር፤ ልዕልት ኢትዮጵያ – ቀለማም፣ ውብ፣ አስዳች፣ ተናፋቂ፣ ተጎብኝ ሀገር እንድተሆን ነው – ራዕዩ። ያ እሱ የናፈቀው ሥርዓት ሲዘረጋ ሁሉም ይሆናል …. በመዳፍ ያለ ነው። ኢትዮጵያዊነትን የዋጡ፤ እትዮጵያዊነትን ክብራችን ብለው የሆኑበትም ውድ ልጆች ንግሥት ኢትዮጵያ አላት። እሳት የሆኑ – ታታሪ – ትንታግ  – ባተሌ ለቃላቸው ያደሩ ልጆች አሏት እናት ኢትዮጵያ።

እንደ እርሶዎ በቧልተ ሊጥ ተቦክቶ ያልተጋገረ ስላልሆነ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ እሱ ምራቁን የወጠ የቁምነገር ፈላስፋ ነው። የሚገርመውና የሚደንቀው ደግሞ አሁንም እንዴት እንደምትፈሩትና የእሱ መንፈስ እንዴት በረድፍ በተጠንቀቅ በመደዴ እንዳሰለፋችሁ፤ እንደሚያንቀጠቅጣችሁም – ልባችሁ ያውቀዋል። የሰሞናቱ ስምሪት ይሄው ነው እሱ – በእሱ። ግን አሞራው በረረ ቅሉም ተሰበረ ነው …. ዕጣችሁ። የቀጠላችሁ ካርቦኖች።

ይህ ያደረጉት ከረባት፤ ይህ የለበሱት ሽክ ያለ ገበርዲን በደም የተጨማለቀ ነው፤ በምልዕቱ ዕንባ – የተዘፈዘፈ ነው። መጠን ሊወጣለት ባልቻለ ጽንስን በግፍ – በረገጠ የጨቀዬ ነው። ህሊና ቢኖራችሁ ለብሶ ለመታዬት በቀፈፋችሁ ነበረ። ግን አልሰራላችሁም ህሊና – የሚባል ነገር። መቃብር ነው የእናንተ የማስተዋል ደረጃ። አንድ ቀን አዎን አንድ ቀን እንዲህ መረን የለቀቀው የበዛ መቀናጣት የጨው ሐውልት እንደሚያደርጋችሁ –  እሰቡ። እናንተ ማሰብ – ይፈቀድላችኋል። ብዙኃኑ ግን ገና ልተሰብ ነው ተብሎ በግፍ ወደ እስር ይጋዛል – ይደበደባል። አውሬዎች!

የወያኔ ሐርነት የጎጥ ሽማምንቶችና እንዲሁም ዬማንፌስቶ ውሸት ያልቃል – ቅጥፈቱም  ይቀበራል፤ – ሽዋዳውም – ይሞታል –  ዕብለቱም ይደረመሳል – ማባጭሉም – ይደቃል – መሳለቁም – ይተናል፤ ደባውም – ይቃጠላል፤ ግፉም – ያበቃል። መሬት ተከፍታ እንደትውጣችሁ ኤሉሄ አሌሄ የምትሉበት ጊዜ – ይመጣል። ዝምታ የጨዋውና የአስተዋዩ ህዝብ አመጻዊ ዬችሎት አደባባይ ነው። እወቁት –  ዕውነት በተባ ተግባር ያሸንፋል። ያ እንዳለፈው ሁሉ ይህም ዬጨለማ ዘመንም – ያልፋል። ይነጋል – በያነጋል!

የኔዎቹ መሸቢያ ጊዜ።

ምንጭ – http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45438

ክብር ለአርበኞቻችን!

አርቦኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ፤

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>