ባለፈው ዓመት በ2014 ዓ.ም. ኢትዮ–ምዩኒክ ባዘጋጀው የኢትዮጵያውያን የአውሮፓ ስፖርትና ባህል የ13ኛውን ዓመት በዓል የማዘጋጀት እድል የተሰጠው ለኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት ነበር፡፡በዚህ መሰረት ኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት የ13ኛውን ዓመት የኢትዮጵያውያን የስፖርትና ባህል ዝግጀት ሃላፊነት ተሰጥቶት፥ በፍራንክፈርት ከተማ ጀርመን አገር ከጁላይ 15 ቀን 2015 ዓ.ም. እስከ ጁላይ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ዝግጅቱን አቀናብሮ እውን እንዲሆን አስችሏል፡፡
ለዚህም ፍራንክፈርት–ሬብስቶክ በሚባል ከተማ ውስጥ ሶስት የእግር ኩኣስ መጫወቻ ሜዳዎችን፥ የመጀመሪያ እርዳት ስጪ ባለሙያዎችና አንድ መኪና፥ የጀርመኖች አጨዋች ዳኞች ልብስ መለወጫ ክፍል፥ ሽንት ቤቶች ለሴቶችና ወንዶች፥ ለፌዴሬሽኑ የስራ አስኪያጅ ኮሚቴ አባላት መቀመጫ ቢሮ፥ ለተጨዋቾች ከሞላ ጎደል የመልበሻና መታጠቢያ ክፍሎች፥ ለሽልማት አስፈላጊ የሆኑ ዋንጫዎችንና ሌሎች ሽልማቶቸን፥ መጠጥናን ምግብ አቅርቦት፥ የሙዚቃ ማጫወቻ መሳሪያና አጨዋቾች፥ ቆሻሻ የሚጣልባቸው ሰማያዊ ላስቲኮች በየቦታዎቹ፥ ቆሻሻና ክፍሎቹን የሚያፀዳ ግብረ ሃይል፥ የኢትዮጵያ ቡና በአገር ባህል አቅርቦት የሚስተናገድበት፥ የተለያዩ በሽያጭ መልክ አቅርቦት(አገራዊ ልብሶች፥ ካኔቴራዎች፥ ባርኔጣዎች፥ …ወዘተ)፥ …ወዘተ የኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት በማመቻቸት ድርሻውን ተወጥቷል፡፡
የኢትዮጵያውያን የስፓርትና ባህል ፌዴሬሽን ሊቀ መንበር አማካይነት የበዓሉን መክፈቻ ንግግር በማድረግና የበዓሉ የክብር እንግዳ የነበሩት አቶ ስዩም አባተን ለህዝቡ አስተዋወቀዋል፡፡አቶ ስዩም አባተም አጠር ያለ ንግግር አድርገው የመክፈቻው በዓሉ ተጠናቁኣል፡፡በቅድሚያ ግን የስፖርት ፕሮግራሙ ተጀምሮ ነበር፡፡
በተጨማሪም የምግብ አቅርቦት፥ የመጠጥ አቅርቦት፥ የአገር ባህል ነክ የሆኑ ነገሮችን፥ መፃህፍት የሚሸጥበት፥ የኢትዮጵያ ቡና የሚጠጣበት፥ህፃናት የሚጫወቱበትና በውሃ የሚቀዘቅዙበትን ሁኔታ በግለሰብ ወይም በግሩፐ ከሚያቀርቡ ጋር ተዋውሎ እውን ተደርገዋል፡፡
የዝግጅት ስፍራ ሙዚቃ እንደልብ ማታም ሆነ ቀን ለማጫወት የመኖሪያ አካባቢ ባለመሆኑ የተመቸ ሲሆን፥ ሶስቱ የእግር ኩኣስ ሜዳዎች ሁለቱ ሳር አንዱ አሸዋ ሜዳ ነበሩ፡፡ሁለቱ ሳር ሜዳዎች መብራት የለሽ ሲሆኑ፥ የአሸዋው ሜዳ መብራት ነበረው፡፡በተቻለ ሶስቱም መብራት ያላቸው ቢሆኑ ይመረጣል፡፡አንድ ጨዋታ በሜዳ ሁለት ቁጥር ላይ ሐሙስ ማታ የተደረገው መደረግ የሌለበት ነበር፡፡የዚህ ዓይነቱ ሁኔታ ወደፊት እንዳይደገም ጥንቃቄ ሊደረግበት ይገባል፡፡
በስፖርት ሜዳው አካባቢ የነበረው የሙዚቃው ቅንብር የኢትዮጵያን ባህላዊ ሙዚቃዎች ይዘት ብቻ ሊኖራቸውና በዓሉ የኢትዮጵያውያን ባህል የሚደረግበትና ኢትዮጵያዊ ጭፈራዎች የሚታዩበት መድረክ ሊሆን ይገባል፡፡የኢትዮጵያ ሙዚቃ ያልሆኑ ሙዚቃዎች ፈጽሞ በዚህ በዓል ላይ አስፈላጊ አይደለም፡፡የፌዴሬሽኑም አንዱና ዋናው ዓላማ የኢትዮጵያን ባህል ማስተዋወቅና ማሳደግ ሊሆን እንደሚገባውና ግዴታውም እንደሆነ ነው፡፡ይህ በዓል የኢትዮጵያውያን በዓል ሲሆንም ሙዚቃውም የኢትዮጵያ ሙዚቃዎች የሚደመጡበት በዓል ሊሆን ይገባል፡፡
የሙዚቃው ድምፅ የእግር ኣሁ ሂደት እንዳያውክና የዳኞች ፊሽካ ድምፅ ለተጨዋቾቹና ለተመልካቹ እንዳይሰማና ችግር እንዳይፈጠር፥ ሙዚቃውን ጨዋታ በሚካሄድበት ወቅት ማቆሙ ተገቢ ነው፡፡ጨዋታ በማይካሄድበት ወቅት ሙዚቃውን በደንብ ማስጮኽ አስፈላጊ ከሆነ ይቻላል፡፡
አጨዋች ዳኞች
አብዛኛውን የእግር £ስ ጨዋታዎች የጀርመን የእግር £ስ ዳኞች ተመድበው በፊፋ የእግር £ስ ሕጎች መሰረት ሲዳኙ፥ የጀርመኖቹ ዳኞቹ ሙቀቱ በጣም ሃይለኛ ስለነበርና ስለደከማቸው ሁለት ሶስት ግዜ ተደብቀው እንደነበር ነው፡፡የኢትዮጵያውያን ዳኞች የመጨረሻ ጨዋታዎችንና የሕፃናትና ወጣቶች ውድድር በማጫወትና በመሃከልም ጀርመኖቹ ዳኞቹ በማገዝ የተወሰኑ ጨዋታዎች አጫውተዋል፡፡በተጨማሪ እንደ አራተኛ ዳኛ በመሆን የተጨዋቾችን መታወቂያዎች በመቆጣጠር ተንቀሳቅሰዋል፡፡
ባሁኑ ውድድር ወቅት ለጀርመኖቹ አጨዋች ዳኞች የልብስ መቀየሪያና መታጠቢያ እንዲኖራቸው ሲደረግ፥ ለኢትዮጵያውያኖቹ አጨዋች ዳኞች ግን አልተደረገም፡፡ይህ ለወደፊቱ ሊታሰብበት የሚገባ ጉዳይ ነው፡፡ለሁሉም ዳኞች የጋራ የሆነ የልብስ መለወጭያና መታጠቢያ ቦታ አስፈላጊ ነው፡፡
የመጫወቻ £ስ ለእያንዳንዱ የአጨዋች ዳኞች ግሩፕ ቢያንስ አንድ £ስ ተዘጋጅቶ ሲቀርብ ተመሳሳይ መለያ ልብሶች ለለበሱ ሁለት ተጋጣሚ ቡድኖች ከላይ የሚለበሱ ሌላ ቀለም ያላቸው መለያዎች በፌዴሬሽኑ በኩል ተዝጋጅቶ እንደነበር ለመገንዘብ ችለናል፡፡ፌዴሬሽኑ ለወደፊቱ የአጨዋች ዳኞች ማራገቢያ 8 ወይም 6 ቢኖረው ችግሮቹ ሲከሰቱ መፍትሄ ለመሻት ያመቻል፡፡ሁለት አጨዋች ብቻ ከኢትዮጵያውያን ዳኞች የራሳቸውን ማራገቢያ ይዘው ስለመጡ፥ ሶስተኛው ሜዳ ላይ ሌላ ጨርቅ ይዘው ሁለት ዳኞች ለማራገብ ተገደዋል፡፡ከኢትዮጵያውያን ዳኞች መሃከል ፊሽካ የሌለው ዳኛም እንደነበረ ሹክ ብለውናል፡፡በአጠቃላይ የኢትዮጵያውያን ዳኞች ለአንድ አጨዋች ዳኛ አስፈላጊ የሆኑ ትጥቆችን አሟልተው መቅረብ ግዴታቸው ሊሆን ይገባል፡፡
ኢትዮ–ስዊዝ ከኢትዮ– ኖርዌይ ቡድን ጋር ያጫወቱትን ዳኛ አንድ የኢትዮ–ስዊዝ ቡድን ተጨዋች ጨዋታው ሲያልቅ አጨዋቹን ዳኛ የሚጨብጥ መስሎ ጠጋ በማለት እንደሰደባቸው ነው፡፡እኝህ ኢትዮ–ስዊዝ ከኢትዮ– ኖርዌይ ቡድን ጋር ያጫወቱት ዳኛ ጨዋታውን የእግር £ስ ሕጎች በሚፈቅዱት መሰረት ለመዳኘታቸው በበኩላችን ምንም ጥርጥር የለንም፡፡የዚህ ዓይነት ጨዋነት የጎደላቸው ተጨዋቾች ግን ፌዴሬሽኑ ተገቢውን እርምጃ በመውሰድ እንዲቀጡ ማድረጉ በእኛ ብኩል ተገቢ ነው እንላለን፡፡የኢትዮ–ኖርዌይና ኢትዮ–ስዊዝ ጨዋታ ለተመለከቱ የስፖርት አፍቃሪዎች የኢትዮ–ኖርዌይ ቡድን በጣም በጨዋታ በልጦ በስፖርታዊ ጨዋነት ለማሸነፉ፥ ስፖርትን በስፖርትነቱ ለተከታተልን ስፖርት አፍቃሪዎች ሁሉ ግልጽ ነበር፡፡ታዲያ ለምን አጨዋቹ ዳኛውን ምክንያት ማድረግ አስፈለገ? ይህ ሲባል የኢት–ስዊዝ ቡድን ሳይሆን አንድ ስፖርታዊ ጨዋነት የጎደለው ተጨዋች ብቻ ተወቃሽ መሆኑን አስምረን ማለፍ እንሻለን፡፡
የአጨዋች ዳኞችን ልብስ የቀለም ዓይነት በሚመለከት ፌዴሬሽኑ ቀደም ብሎ አጨዋች ዳኞቹን በመሰብሰብ ለአራት ቀናት የሚሆኑ የተለያዩ ቀለማት ያሏቸው የአጨዋች ዳኛ ከላይ የሚለበሱ መለያዎች አዝጋጅተው እንዲመጡ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡ለምሳሌ ለአራቱ ቀናት አምስት ዓይነት ቀለማት ያላቸው ከላይ የሚለበሱ የአጨዋች ዳኛ መለያ ጥቁር፥ ቢጫ፥ ሰማያዊ፥ ቀይ፥ ግራጫ ከተስማሙ ሁሉም አጨዋች ዳኞች እነዚህን ይዘው ሊመጡ ይገደዳሉ፡፡ከዚያም ለመጀመሪያው ቀን ጨዋታ ሁሉም ጥቁር፥ በሁለተኛው ቀን ሰማያዊ፥ በሶስተኛው ቀን ቀይ፥ በአራተኛው ቀን ቢጫ ወይም ግራጫ ይዘው እንዲመጡ አስቀድሞ ተነግሯቸው ተግባራዊ ማድረግ ይኖረባቸዋል ማለት ነው፡፡
የኢትዮጵያውያን አጨዋች ዳኞች መሃከል ሊሻሻል የሚገባቸው ነገሮች ቢኖሩ፥ የሕፃናት ጨዋታዎች ሲያጫውቱ ያለዳኛ ትጥቅ ያጫወቱ እንደነበሩና ይህ መቅረት እንደሚኖርበት ነው፡፡ትክክለኛውን የአጨዋች ዳኛ ትጥቅ አድርገው እያንዳንዱን የህፃናትና ወጣቶች ጨዋታዎች ሊመሩ ይገባል፡፡ሁለት የህፃናት ቡድኖች በጣም ተመሳሳይ የሆኑ መለያ ለብሰው ሲጫውቱ ታይቷል፡፡አጨዋቹ ዳኛ ከላይ የሚለበሱ ባለሌላ ቀለም ከፌዴሬሽኑ መቀመጫ ቢሮ በመውሰድ አንዱ ቡድን በእጣ እንዲለብስ ማድረጉ ተገቢ ሲሆን ግን አልተደረገም፡፡ይህም ወጣቶቹንም እንዲማሩ ይረዳል፡፡
የመጀመሪያው ቀን የኢትዮጵያውያን ዳኞች በረዳት ዳኝነት ያለትጥቅ አንድ ዳኛ ሜዳ ሁለት ቁጥር ላይ ሲያራግቡ እንደነበር ነው፡፡ሶስት ሌሎች ዳኞች ያለገንባሌ ሲዳኙና ሲያረግቡ የመጀመሪያው ቀን ታይቷል፡፡ ይህ ለወደፊቱ ሊደገም አይገባውም፡፡እያንዳንዱ ዳኛ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን አሟልቶ የመቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
የሁለት ለባዶ መሸነፍ ጉዳይ
በውድድሩ ላይ የተወሰኑ ቡድኖች በተባለው ሰዓት በሜዳው ላይ ባለመገኘታቸው ምክንያት ሁለት ለባዶ ተሸናፊ እንዲሆኑ ተደርገዋል፡፡ለምሳሌ ኢትዮ– ሽቱትጋርትና ኢትዮ– አዲስ ፍራንክፈርት2 መጥቀስ ይቻላል፡፡የሚገርመው ደግሞ የኢትዮ– አዲስ ፍራንክፈርት2 እንደ አዘጋጅ በተባለው ሰዓትና ቦታ ባለመገኘቱ ትንሽ ሰዉን አስገርሞታል፡፡ኢትዮ– ሽቱትጋርትም ሆነ ሌሎች ቡድኖች በግዜው በቦታው ያለመገኝት ችግር „የአበሻ ቀጠሮ“ በሚለው የደካሞች አስተሳሰብ ምክንያት አንደሆነ ተነግሮናል፡፡ይህ „የአበሻ ቀጠሮ“ የሚለው መጥፎ ባህል ሊወገድ የሚገባው የተስቦ በሽታ ሲሆን፥ ፌዴሬሽኑ በዚህ ጉዳይ ላይ የወሰደው እርምጃ እሰየው የሚያሰኝ ነው፡፡እኛ ቀጠሮ ይከበር ያላከበረ ይቀጣ የምንል ነን፡፡
የምግብ አቅራቢ ቅሬታዎች
የምግብ አቅራቢዎቹ በአንድ አካባቢ አንድ ላይ መደረጋቸው ትክክል ቢሆንም፥ በአካባቢው የመጠጥ አቅርቦት ቢኖርም ትኬት ለመግዛት የነበረው ሁኔታ ግን በጣም ሩቅ ነበር፡፡ሁለት የትኬት መቁረጫ ማድረግ ሲቻል አለመደረጉ ለተመጋቢዎች የሚጠጣ ለማግኘት አስቸጋሪ ነበር፡፡መጠጣት ለሚፈልግና ትኬት አስቀድሞ ላልቆረጠ ሰው ምግቡ ከሚሸጥበት አካባቢ ረጅም መንገድ
መሄድ ግድ ነበር፡፡ቅዳሜ እለት ግን የምግብ ሽያጮቹ እራሳቸው ድንኩኣን ውስጥ የጠርሙስ ቢራ በ3€ ሲሸጡ ታይተዋል፡፡ ቢራም በÙ ሮ በኩል በአጥሩ ላይ ሲገባ ለማየት ችለናል፡፡ ሀጋዊ ይሁን አይሁን ግን አናውቅም፡፡ይህ ለሚቀጥለው ዓመት ዝግጅት ትምሀርት ሆኖ ተሻሽሎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
ሌላው ባላፈው ዓመት ማለትም 2014 ዓ.ም. በኢትዮ–ምዩኒክ የተዘጋጀው ዝግጅት ላይ ለኢትዮጵያውያን አጨዋጭ ዳኞች የምግብና የመጠጥ ትኬት ለፌዴሬሽኑ በመስጠት ፌዴሬሽኑ ደግሞ ለዳኞቹ በመስጠት ዳኞቹ የመረጡትን ምግብና መጠጥ የመጠቀም ሁኔታ ተግባራዊ ተደርጎ ነበር፡፡በአሁኑ የኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት የ2015 ዓ.ም. ዝግጅት ላይ ግን ለየት ባለ መልኩ ተግባራዊ ተደርÙ ል፡፡እዚህ ላይ መነገር ያለበት ፌዴሬሽኑ ትኬቶቹ እንዲሰጠውና ለዳኞቹ እንዲያድል ጠይቆ በኢትዮ– አዲስ ፍራንክፈርት በኩል ፈቃደኛነት አልነበረም፡፡የሆነው የኢትዮጵያውያን ዳኞች „አዋሬ“ በሚባል ድን£ን ውስጥ ብቻ ሄደው እንዲበሉ የኢትዮ– አዲስ ፍራንክፈርት ወስኖ በዚሁ መሰረት ምግብ እዚያ እንዲበሉ ተደርÙ ል፡፡የሚጠጣ ውሃ ወይም ለስላሳ ከአንድ የመጠጥ መሽጫ ቦታ ዳኞች እንዲጠጡ ተወስኖ ተግባራዊ ተድርÙ ል፡፡ ይህም ብዙም አመቺ አልነበረም፡፡ምክንያቱም ዳኞቹ ትኬት ይዘው ስለማይቀርቡ ማለት ነው፡፡ለዳኞች ውሃ ፌዴሬሽኑ ቢሮ ውስጥ በብቃት ቀርቦ ዳኞች ተጠቅመዋል፡፡
ይህ አንድ ቦታ ብቻ ዳኞች እንዲበሉ በኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት መደረጉን አንዳንድ ዳኞች በቅሬታ መልክ አንስተውታል፡፡ቅሬታውም ለምን አንድ ቦታ ብቻ እንዲበሉ እንደተደረጉ ነው፡፡ግልጽ ለማድረግ ፌዴሬሽኑ ኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርትን ትኬት እንዲሰጠው ጠይቆ ትኬት ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ተግባራዊ የተደረገ እንደሆነ ነው፡፡በዚህም ምክንያት አንድ ጥሩ ክትፎ በመሆኑ የሚደነቀው አቅርቦት ባለቤቶች ይህን የዳኞች አንድ ቦታ ብቻ መመገብ ሰምተው ቅሬታቸውን በምሬት አሰምተዋል፡፡ትክክልም እንዳልሆነ በግልጽ ተችተዋል፡፡በዚህ ነጥብ ፌዴሬሽኑ ፈጽሞ ሊተች እንደማይገባውና ትችቱ ወደ አዘጋጁ ኢትዮ– አዲስ ፍራንክፈርት ሃላፊዎች ማምራቱ ተገቢ እንደሆነ ነው፡፡ምክንያቱም ፌዴሬሽኑ ለእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ዳኛ 8 ትኬት ለአራት ቀን ምሳና እራት የሚሆንና ለሚጠጣም ነገር እንዲሁ 8 ትኬቶች በቅድሚያ እንዲሰጠውና ፌዴሬሽኑ ለዳኞቹ ለማከፋፈል ጠይቆ አልተሳካለትም፡፡ለወደፊቱም ፌዴሬሽኑ ይህንን አቅጣጫ ተክትሎ ተግባራዊ ማድረጉ ይጠበቅበታል፡፡
የምግቡና የመጠጡ ዋጋዎች ተመጣጣኝ ነበሩ፡፡ይህም የፌዴሬሽኑ ሚና እዚህም ውስጥ ለወደፊቱም ዝምብሎ ለንግድ ብቻ ለሚመጡና ውድ ዋጋዎች በማስከፈል መክበር ለሚፈልጉት ፍሬን እንዲይዙ የሚያደርግ ሃላፊነቱን በተገቢው ሊወጣ ይገባል፡፡ዋጋው ውድ ቢሆን የተሳታፊው ህዝብ የመግዛት አቅም ያንስና የሚፈለገውም ሽያጭ አይገኝም፡፡ያሁኑ የዋጋ ተመን ጥሩ ነበር ማለት ይቻላል፡፡
የተለያዩ አማራጮች መቅረባቸውም ከሽሮ ወጥ፥ ጥብስ፥ ክትፎ፥ የፆም በያይነቱ፥ ቅቅል፥…ወዘተ ለተመጋቢው ህዝብ ሲቀርብ፥ ከድን£ኖቹ ሁኣላና ፊት ተመጋቢው ተቀምጦ የሚበላበትም ቦታ ተዘጋጅቷል፡፡ ይህ መልካም ነው፡፡
የመጠጥ ትኬት ሽያጭ የሌብነት አሰራር፤
የኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት ብዙ የሚመሰገንባቸው ነጥቦች ቢኖሩትም፥ በጣም የሚያስወቅሰውን የሌብነት ስራ በመጠጥ ትኬቶች ሽያጭ ላይ ተግባራዊ አድርÙ ል፡፡ይህም ከተራ ሌብነት ወይም ስርቆት የሚለይ አይደለም፡፡ ለምን ለሚለው? የመጠጥ ትኬት ሽያጩ ላይ በየቀኑ የተለያዩ ቀለማት ያላቸውንና ቀን የተፃፈባቸው ትኬቶችን በማዘጋጀት ለምሳሌ ዓርብ እለት አርንÙ ዴ ቀለምና BON 17.07. የተፃፈበትና ቅዳሜ ደግሞ ቀለሙ ሰማያዊ ሆኖ BON 18.07.የተፃፈበትን መጥቀሱ ጠቃሚ ነው፡፡ዓርብ እለት ማለትም ብ17.07.2015 ሰዎች ብዙ ትኬቶች አረንÙ ዴ ቀለም ያለውን ገዝተው ቅዳሜ እለት 18.07.2015 ለመጠቀም ቢፈልጉ መጠቀም አይችሉም፡፡ይህ የተደረገው በምስጢር መሆኑን የሚያጋልጠው ሻጮቹ ለገዢዎቹ ትኬቱ ለአንድ ቀን ብቻ እንደሚሰራ ፈጽሞ አይናገሩም ነበር፡፡ምክንያቱም በብዛት ለነገም ተነጎዲያ የሚገዙና የሚከስሩ እንዳሉ ያውቃሉና ነው፡፡ይህ የሌብነት አሰራር ለተጠቃሚው ህዝብም ሆነ ለፌዴሬሽኑም የተነገረ እንዳልሆነ ነው፡፡ለህዝቡ በድምፅ ማጉያ ከተነገረ ሁሉም ሰው የዛሬውን ብቻ ትኬት ይገዛል፡፡ በዚህ መልክ ብዙ ቅጥል ያሉ የስፖርት አፍቃሪዎች ሲንጫጩ አይተናል፡፡ የኢትዮ–አዲስ ከስፖርት አፍቃሪዎች ብዙ ብር ቢራ ሳይሰጥ ኪሱ አስገብቷል፡፡ ይህ ሌብነትና ዘረፋ ነው፡፡በዚህ ትኬት ዓርብ ጁላይ 17 ቀን 2015 ዓ.ም. ብቻ መጠጥ መግዛት እንደሚቻልበት ነበር፡፡በዚህ ትኬት ቅዳሜ ጁላይ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. መጠጥ ማግኘት አንድ ሰው ቢፈልግ እንደማይችል ነው፡፡ለምን? ዓርብ እለት ትኬቱ ስለገዛውና ቅዳሜ እንዳይጠቀም ተደርጎ የተዘጋጀ የስርቆት ዘዴ በመሆኑ ነው፡፡ለምሳሌ አንድ ሰው በ30 ኢሮ 15 የመጠጥ ትኬቶች ዓርብ ዕለት ቢገዛ፥ እነዚህን ትኬቶች ቅዳሜ እለት የሚጠጣ ነገር ለማግኘት ቢፈልግ መጠጥ አያገኝም፡፡ምክንያቱ ቀኑ አልፏል በማለት ነው፡፡ይህ ማለት የኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት የ€30 ቢራ ሳይሰጥ ሰረቀ ማለት ነው፡፡በዚህ ድርጊት ምናልባትም ብዙ ሰዎች ብዙ ገንዘብ በመሰረቃቸው በጣም ሲናደዱ ታይተዋል፡፡ትኬት ሻጮቹም ትኬቱ ለአንድ ቀን እንደሚያገለግል ምንም ነገር ትንፍሽ እንዳላሉ ለረጅም ግዜ ተከታትለን አረጋግጠናል፡፡ ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑም ከዚህ ዓይነቱ የሌብነት አሰራር ራሱን ነፃ አድርጎ መንቀሳቅስ ይኖርበታል ብለን እናምናለን፡፡ ለዚህ ድርጊቱ ኢትዮ–አዲስ ፍራንክፈርት የስፖርት አፍቃሪዎችን ይቅርታ በመጠየቅ ትኬት ላላቸው የዘረፈውን ገንዝብ ሊመልስላቸው ይገባል ባይ ነን፡፡
ሺሻና ጫት
በእፅ ሱስ የተጨማለቁ የአደንዛዥ እፅ ሺያጮች አስመልክቶ ምዩኒክ ጀርመን ዝግጅት ጋር ሲነፃፀር እጅግ በጣም ቀንሷል፡፡ይህ መልካም ሲሆን ጥቂቶች በስፖርት ሜዳው ግቢ አጥሩ ጥግ ጥግ ሆነው ሺሻ ሲያጨሱና ጫት ሲበሉ ቅዳሜ እለት ተመልክተናል፡፡ለወደፊቱ ግን ፈጽሞ ስፖርቱ ቦታ አካባቢ እንደነዚህ ዓይነት ሰዎች እንዳይደርሱ በሕግ መከልከልና እምቢ ካሉም ለአካባቢው ፖሊስ አስታውቆ በፖሊስ አስፈላጊውን እርምጃ ማስወሰድ ተገቢ ነው፡፡በዚህ ስፖርት አካባቢ ብዙ ታዳጊ ህፃናትና ወጣቶች በዚህ የአልባሌ የአድንዛዥ እፅ የእሳት እራት እንዳይሆኑ ፌዴሬሽኑ ነጋዴዎቹን ያለምንም ይሉኝታ ማስወገድ ግዴታው ነው፡፡
የስፖርት ሜዳው ላይ ጭፈራ
ከቀኑ አስራ አንድ በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር ጀምሮ የተመልካቹ ቁጥር በየቀኑ የሚጨምርበት፥ ሙቀቱ በመጠኑም ቢሆን ቀዝቀዝ የሚልበት፥ የዲስክ ውይም ፍላሽ ሙዚቃዎች እየተለቀቁ እንግዶች በኢትዮጵያ ባህል የሚወዛወዙበት ወቅት ነበር፡፡ጭፈራው፥ ምግቡና መጠጡ ጎን ለጎን ሆነው ሕዝቡ እየበላ እየጠጣ ቢያንስ እስከ ሌሊቱ ስድስት ሰኦኣት ድረስ የተቆየበት ሁኔታ ነበር፡፡ለዚህም በአሸዋው ሜዳ ላይ የነበረው መብራት ስለነበረ ወለል ብሎ ይታይ ነበር፡፡ይህ የሜዳ መብራት ባይኖር ኦሮ ሙዚቃውና እስክስታ ወራጆቹ ምን ይውጣቸው ነበር? ሙዚቃው ግን አንዳንድ ቀን ከኢትዮጵያዊው የባህል ሙዚቃ ወጣ ይል ነበር፡፡በዚህ የኢትዮጵያውያን የባህል በዓል ላይ በዲስክና ፍላሽ ማጫውት የሚገባው የኢትዮጵያን ሙዘቃ ብቻ ሊሆን ይገባል፡፡ በዓመት አንድ ግዜ ለሚደረገው በዓል የኢትዮጵያን የተለያዩ ሙዚቃዎችን መርጦ ማጫወቱ፥ ኢትዮጵያውያን ወጣጦች የባህላቸውን አጨዋወት ሊማሩበትና ጎልማሶች ያላቸውን የመወዛወዝ ችሎታቸውን የሚያሳዩበት መድረክ ሊሆን ይገባል፡፡ምክንያቱም በዓመት አንድ ግዜ ለኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የሚዘጋጅ የባህል ሙዚቃ በመሆኑ ነው፡፡እንዲያውም ለወደፊቱ ፌዴሬሽኑ ትናንሽ ሽልማቶችን ለወጣቶችና ለጎልማሶች ቢያዘጋጅ ብዙ ተመልካቾችን የሚስብ ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡
ሁለት የተደነቁ ቡድኖች
በዚህ የኢትዮ አውሮፓ ስፖርትና ባህል ፌዴሬሽን በፍራንክፈርት–ጀርመን ከጁላይ 15 ቀን እስከ ጁላይ 18 ቀን 2015 በተካሄደው የእግር £ስ ውድድር በጥሩ አጨዋወታቸው በብዙ ሰዎች ሲደነቁ የሰማነው ከዲቪዢን A የኢትዮ–ኖርዌይ ቡድን ሲሆን፥ ከዲቪዢን B ደግሞ ኢትዮ–ካታንጋ ነው፡፡እነዚህ ሁለት ቡድኖች በእግር £ስ አጨዋወታቸው ሲደነቁ፥ በአባዛኛው በወጣቶች የታቀፉ ቡድኖች ናቸው፡፡የኢትዮ–ካታንጋ ቡድን ጠገብን የማያውቁ £ስን በደንብ መጫወት የሚችሉ፥ በወጣቶች የተገነባ ቡድን ነው፡፡ለምንስ ዲቪዢን B ውስጥ እንዳሉ ብዙ ሰው ተገርሟል፡፡ አንዳንድ ተጨዋቾች ወደግጭት የገፉበት ሁኔታ ተከስቷል፡፡ለምሳሌ ከአውስትሪያ ጋር ሲጫወቱ አንድ የውጭ አገር ዜግነት ያለው ወጣት ተጨዋች ለግጭት ሲጋበዝ እንደነበር ታይቷል፡፡ይህ የማያስፈልግና ለወደፊቱም ለቡድኑም ጠቃሚ ያልሆነ ድርጊት ነበር፡፡በተረፈ ቡድኑ £ስን ይጫወታል፡፡በርቱ ቀጥሉብት እንላቸዋለን፡፡
የኢትዮ–ኖርዌይ ባለፈውም ዓመት ባሁኑም ውድድር በሁለተኛነት ደረጃ ያጠናቀቀ፥ £ስን በተቀናጀና ውጤታም በሆነ መልኩ መጫውት የሚችል ቡድን መሆኑን አስመስክሯል፡፡ከኢትዮ–ለንደን ጋር ባደረገው የዋንጫ ውድድር በጨዋታው ወቅት ያገኘውን የፍጹም ቅጣት መት ቢያገባ አሽናፊ የመሆን እድሉ ያመዘነ ነበር፡፡ ግን አልተሳካለትም፡፡ሁለት ግዜ ሁለተኛ በመሆን ግን አንደኛ ነው፡፡በጣም የተጠና አጨዋወት ስልት ኢትዮ–ኖርዌይ እየተጠቀመ እንደነበር ማሳበቅ ይቻላል፡፡ብዙ ጥሩ ችሎታ ያላቸው ወጣቶች ያሉበት ቡድን በመሆኑ በርቱ እንላቸዋለን፡፡
በዚህ አጋጣሚ የኢትዮ–ለንደን ቡድን እን£ን ደስ ያላችሁ እንላለን፡፡
የድምፅ ማጉያ አጠቃቀም
አንድ የፌዴሬሽኑ የህዝብ ግንኙነት ተወካይ የድምፅ ማጉያ ይዞ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በየግዜው በተቻለ መጠን ለመጡ እንግዶችና ስፖርተኞች ሲያቀብል እንደነበር ነው፡፡ይሄ ጥሩ ጎኑ ሲሆን፥ መረጃውን በሚያስተላልፍበት ወቅት አንዳንዴ እሱ ራሱ ያለበትን ቦታ ዬት እንደሆነ በደንብ አይገልጽም፡፡ይህ መሻሻል ያለበትና ያለበት ቦታ በቀላል ቁኣንቁኣ ለአድማጮቹ መግለጹ እሱን በቀላሉ ለማግኘት ያስችላል፡፡
ሌላው ለሚቀጥለው ግዜ ግን ሶስት የድምጽ ማጉያዎች ሊኖሩ ቢችሉና አንዱ የፌዴሬሽኑ ስራ አስኪያጆች የሚቀመጡበት ቢሮ ውስጥ፥ አንዱ ለፈዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ተወካይና አንዱ ለአጨዋች ዳኞች ተወካይ ቢሆን፥ ከቦታ ወደቦታ መሯሯጡናን ድካምን አላስፈላጊ የግዜ መባከንን ይቀንሳል፡፡ሶስቱም ካሉበት ሆነው የሚፈልጉትን መረጃዎች በድምፅ ማጉያው ማስተላለፍና እርስ በእርስ ያለብዙ ድካም መገናኝት ሲችሉ የሚሰሩ ስራዎችም በተቀላጠፈ ሁኔታ ሊካሄዱ ይችላሉ የሚል እምነት አለን፡፡
የ“አበሻ ቀጠሮ“ ጠፍቶ ቀጠሮ ይከበር!
በዚህ ነጥብ ላይ አንዳንድ ቡድኖች ቀጠሮ የማክበር በሽታ ያልለቀቃቸው ቢኖሩም፥ በአብዛኛው ግነ ቡድኖች ቀጠሮ የማክበሩን ሁኔታ ተግባራዊ እንዳደረጉ ነው፡፡በፌዴሬሽኑም በኩል ይህ ቀጠሮ የማክበሩ ሁኔታ ከበፊቱ የተሻለ ቢሆንም፥ መሉ በሙሉ ተከብሯል ማለት አይቻልም፡፡ለምሳሌ የህፃናትና ወጣቶች ጨዋታው የሚጀመርበት ሰዓት ባለመከበሩ ወላጆች በጣም ሲነጫነጩ ታዝበናል፡፡መነጫነጫጨውም ተገቢ ነበር፡፡ፌዴሬሽኑ ውድድሩን ባለው ሰዓት ባለማስጀመሩ ነበር፡፡ይህ ሊሻሻል ይገባል፡፡
ሶስት እናቶች
የህጻናትና ወጣቶች እናቶች በጣም ጨዋነት በተሞላበት ሁኔታ ልጆቻቸውንም ሆኑ የእነርሱን ቡድን በስፖርታዊ መንፈስ በጋለ ስሜት ሲያበረታቱ ተመልክተናል፡፡ጎሽ አበጃችሁ የሚያስኝ ሲሆን፥ አንዷ እናት በሃይል በማፏጨት ቡድኗን ስታበረታታ እንደነበር ተመልክተናል፡፡
ለአንዳንድ ወላጆችና ቪዲዮ ቀራጮች ግን ሜዳው ላይ በመግባትና እዚያ በመቆም ሕግ እየጣሱ እንደነበርና ይሄ ለልጆቹ ጥሩ ስሜት ስለማይሰጥ ልክ እንደ ትልልቆቹ የእነርሱም ጨዋታ ሊከበር ይገበዋል፡፡ስለሆነም አንዳንድ ወላጆችን የቪዲዮ ቀራጮች ለወደፊቱ ጨዋታው ሜዳ ላይ ከመግባት እንድትቆጠቡ ማሳሰብ እንሻለን፡፡
የህፃናት ጨዋታዎች የፍጹም ቅጣት ምት ሲምታም ሆነ የትልልቆቹ የፍጹም ቅጣት ምት ሲመታም ተመልካቾች ከሜዳው መውጣት ነበረባቸው፡፡ሜዳው ላይ ሊኖሩ የሚገባቸው ተጨዋቾችና ዳኞች ብቻ ነበሩ፡፡ይህ በጣም ሊወገድና ለወደፊቱ ሊሻሻል የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡
የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓት
የሽልማት አሰጣጥ ስነ ስርዓቱ ከፍ ያለ ቦታ በመሆኑ ከዚህ በፊት ከነበሩት ሁሉ የተሻለ ነበር፡፡ለተጨዋቾች የተዘጋጁ የዋንጫ ሽልማቶች፥ ለዳኞች የምስክር ወረቀት፥ ለእያንዳንዱ ቡድኖች ምስክር ወረቀት፥…ወዘተ ከክብር እንግዳው ከአቶ ስዩም አባተ፥ ከፈዴሬሽኑ ሊቀ መንበርና የቴክኒክ ኮሚቴ ሃላፊ ከአቶ ዮሃንስና ከአቶ ከበደ ተሰጥተዋል፡፡በመጨረሻም የውድድሩ የአንደኛ ዲቪዚዮንና ሁለተኛ ዲቪዚዮን የዋንጫ ባለቤት ለሆኑት ለኢትዮ– ኤሚሊያና ለኢትዮ– ለንደን የተዘጋጁት ዋንጫዎች በሽልማት መልክ ተስጥተው የሽልማቱ ስነ ስርዓት ተፈጽሟል፡፡የሽልማት ቦታው ለወደፊቱ ከፍ ያለ ልዩ ቦታ ሊዘጋጅና ተመልካቾች በተወሰነ ርቀት ላይ ሆነው ተግባራዊ የሚሆንበትን ፌዴሬሽኑ እንድሚያሳካ ተስፋ እናደርጋለን፡፡
ልዩ ልዩ
የጠፉ ህፃናትና እቃዎች
ህፃናት ጠፍተው የፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ተጠሪ ጋ በመምጣት እየተናገሩ ቤተሰቦቻቸው ልጆቻቸውን እንዲያገኙ ተደርጉኣል፡፡የተለያዩ እቃዎች ወድቀው አግኝተው ለፌዴሬሽኑ በመስጠት በለቤቶቻቸው መጥተው የወሰዱበት ሁኔታ ተከስቷል፡፡ይህ እጅግ የሚያስደስት ሲሆን፥ ቤተሰቦች ግን ለልጆቻችሁ ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረጉ ተገቢ ነው እንላለን፡፡
የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት
ፌዴሬሽኑ በሶስቱም እግር ኩኣስ ሜዳዎች ላይ ይካሄዱ የነበሩትን ጨዋታዎች ዳኞች ጨዋታውን ለአንድ ደቂቃ አቁመው በሊቢያ፥ በደቡብ አፍሪካና በተለያዩ ዓረብ አገሮች ህይወታቸውን በግፍ ላጡ ኢትዮጵያውያን የአንድ ደቂቃ የሕሊና ጸሎት አስድርÙል፡፡ይህ በጣም ሊበረታታ የሚገባና ጥሩ ድርጊት ነው፡፡
የአውሮፓው የስፖርትና ባህል ዝግጅት ጉዳይ፤
እስካሁን ድረስ በክለቦች ይዘጋጅ የነበረው የአውሮፓው የስፖርትና ባህል ዝግጀት ከ2016 ዓ.ም. ጀምሮ በራሱ በፌዴሬሽኑ የሚዘጋጅ እንደሆነ መወሰኑ ነው፡፡ስለዚህ በሚቀጥለው ዓመት ማለትም በ2016 ዓ.ም. በፌዴሬሽኑ የሚዘጋጀው የመጀመሪያው ዝግጅት ይሆናል ማለት ነው፡፡ በሽኩሽኩታ እንደተሰማው ከሆነ የሚቀጥለው ዝግጅት በሆላንድ በዴንሃግ እንደሚደረግ ነው፡፡ግን ገና እርግጠኛ መሆኑ አልታወቀም፡፡
የስፖርት ቦታውን አድራሻ ዴንሃግ ከሆነ፥ ካሁኑ የስፖርት ሜዳውን ይዞ ቢያሳውቅ ለስፖርት ቡድኖችም፥ ለደጋፊዎችም፥ ለተመልካቾችም ፥ ለዳኞችም፥ ለፌዴሬሽኑም ዝግጀት እቅድ አውጥቶ ለመዘጋጀት በጣም ጠቃሚ ይሆናል ብለን እናምናለን፡፡ለማንኛውም ሁላችንንም የዚያ ሰው ይበለን!
የሙዚቃው ዝግጅት ከቴዲ አፍሮ ጋር
ቀደም ብሎ ቅዳሜ እለት ማለትም ጁላይ 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ምሽት ላይ የስፖርቱ ፕሮግራም ተጠናቆ በቴዲ አፎሮ ተዋናያነት የሚካሄደው የሙዚቃ ድግስ አይስ ስፖርትሃለ በሚባል የበረዶ ላይ መጫወቻ ስታዲዮም ውስጥ ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ለዚህም ዝግጅት መግቢያ ስፖርት ሜዳው አካባቢ በ€35 መግዛት ለሚፈልጉ ይሸጥ ነበር፡፡አስቀድሞ መግዛት ለማይፈልግ ደግሞ €40 በዝግጀቱ ቦታ እንዲሽጥ ተደርጉኣል፡፡
ከተንሳይት በቃና
ጁላይ 26 ቀን 2015 ዓ.ም.
Tsedal2009@gmx.de