Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ሽራፊ ይቅርታ –ትንታ! (ሥርጉተ ሥላሴ)

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 24.07.2015 /ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ/

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ - ዙሪክ)

ከሥርጉተ ሥላሴ 02.023.2014 (ሲዊዘርላንድ – ዙሪክ)

ጤና ይስጥልኝ ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ እንዴት – ሰነበትክ? ደህና ነህ ወይ? ይቅርታ መጠዬቅ ለመኖራችን – ዓምድ ነው። የምድር ብቻም ሳይሆን ወይንም የገሃዱ ዓለም ብቻ ሳይሆን የመንፈሳዊው አለምም መርኽ ነው። እርግጥ ብዙም አይደፈረም። እራስን ዝቅ ማድረግን – ስለሚያጎላ። ይቅርታ – ንሥኃ ነው። ንሥኃ ደግሞ መንጨቧረቅን ሳይሆን ደህና አድርጎ ውስጥን መታጠብን – ይጠይቃል። ዬይፍቱን ብልህ ልብ ለማግኘት። ለማንኛውም ይቅርታ – በገኃዱ ዓለም ሲታይ ፈሊጡ ለማን? ለምን? መቼ? እንዴት? ወዴት? ዬት? የሚሉትን የሥነ – ጥያቄን ውስጠ አካል የማብራራት አቅም ሊኖረው – ይገባል። በተለይ ይቅርታው አደባባይ መዋል ካሰኘው። ከዚህ አንፃር ጅምሩ መልካም በመሆኑ – መከበርም እንዳለበት ሆኖ፤ ነገር ግን ተሸብልሎ የቀረበው ይቅርታ ተብራርቶ መቅረብ አለበት – ቁስለኛን ሆነ ጉዳተኛ የሆኑ ዬተደበደቡ የሥነ – ልቦና መንፈሶችን ለመፈወስ በቂ የሚጥን ወይንም የሚክስ አቅም ሊኖረው – ይገባዋል። እርግጥ ደጅ ጥናቱ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ዬዘውድ ዘመን የተከሰስክበትና የሞት ፍርድ ያሰጠኽህን ዓብይ በኽረ ጉዳይ ተለዋጭ መስመር ስለ አሰገኘ በአመክሮ ሊያሰርዝ ይችል – ይሆናል። ይህም ያው – ተከድኖ። ገዢዎቻችን ምድር ስለሆኑ በውስጠ ወይራው ዘያቸው ተሸብልሎ ይተከዝበት – ይሆናል። ያው ጠርዝ ለጠርዝ ሲሄዱ ማደር ነውና … እነቶኔው።

የሆኖ ሆኖ ወንድም ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ – ትናንት የቅንጅትን መንፈስ በቀጣይነት ይዞ የተነሳውን ዬአንድነትን ፓርቲ ከብሄራዊ መሪው ጀምሮ እንኩት – አደረገክ፤ ዛሬ ያ ብሄራዊ ፓርቲ በዘመንተኛው የወያኔ ሃርነት ትግሬ ትዕቢት መፍረሱን ስታረጋግጥ ደግሞ ለሰላማዊ ትግል አርበኛ ሆነህ ተገኘኽ – ሌላውን የተስፋ ቅኝት ደግሞ ለመናድ – ታጥቀኽ ተሰለፍክ፤ ህፈረት የሚባል ነገር አለ። ችግርህ ኃላፊነትን በትከክል ለይቶ የማወቅ፤ ተጠያቂነት በድርሻ የመውሰድ ችግር በጉልህ ያለብህ ይመስለኛል፤ የሆነ ሆኖ በመንተፍረቱ ዛኒዛነውን ቆሞ ኤሎሄ የሚለው ይቅርታህ እንዲህ ይፈተሻል – አጀንዳዬ አንተው ነህና አብረን እላለሁ …. በትሁት መንፈስ።

የተሸበለለው የጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ ሽራፊ ይቅርታትንታ፤

ተረፍ ብላ፣ ጠብ እንዳትል፣ በመቁንን፣ ተቀንጥባ – የረባ ወይንም የመጋኛ ሀገረ ሰብዕዊ መዳህኒት ይመስል በአውራጣት ጫፍ ተለክታ፤ ወቅታዊ ዒላማዋን እንድትመታ የተሰላቸው ይቅርታ እንኳንስ በራህብ የተቦረቦረውን አንጀቴን ጎሮሮዬንም ረጠብ – አላደረገችውም። ይሄውና ወንድምአለም አለሁልህ ራህቡ እያገላበጠኝ  …. የጥማቱ ወላፈንም – እዬላጠኝ፤ ወሳፈቴም  እዬተጯጯኽ ነው፤ ምን አልባትም ስካይፒ በሚሉት አንተኑ ፍለጋ ሌልኛ ስደትም አሰኘን – ይላሉ፤ … ሸብረክ የምትል ብናኝ ተጨማሪ ሽራፊ ይቅርታ ብትገኝ ብለው ምሰና ጀምረዋል – በወልዮሽ።

  • እኔ እንደማስበው አንተ በኤርትራ በኩል የትጥቅ ትግልን ታራመድ በነበርክበት ጊዜ ደጋፊዎች – ይኖሩኃል። ሃሳቡን ደግፈው የተንቀሳቀሱ ዛሬ የማይነሱ ሰማዕታትም በሞት – አልፈዋል፤ ጦርነት የካርታ ጨዋታ – አይደለም። ሲያስፈልግህ መንገድ ነው ብለህ አወጅክ፤ እንዲህ ሲያሻኽም ደግሞ ትክክል አይደለም ብለህ ዘመቻ – ጀመርክ። ስለዚህ የነፍስ ጥፋት፣ የትውልድ እልቂት፣ የታሪክ ብክነት የጀግንነት ውሎና ውሉ እንዲህ ከፍተህ እንደምትጠጣው ዬቧንቧ ውሃ፤ ከጠጣህ በኋላ የምትዘጋው፤ ሲጠማህ ደግሞ የምትከፈትው ሊሆን – አይገባም። ለዛን ጊዜ መርሁን ተከትሎ ለፈሰሰው ደም ተጠያቂነትህን በውል አልዳሰሰም – ይቅርታኽ። ሰውን የትኛው ገብያ ይሆን ሸመት አድርገህ – የምትገዛው? ወይንስ የትኛው ፋብሪካ ላይ ይሆን የሰው ልጅን አምርተህ – የምታወጣው? ወይንስ ሰው ጣጣውን የጨረሰ ሆኖ ጎልምሶ መወለድ ይችላልን /ready made/ ዓይነት? ታሪክ ሠርተው ታሪክ አልባ ያደረካቸው ጀግና አርበኛ ወገኖቻችንስ ጉዳይ ከቶ በምን ይከተት ብለህ ታስባለህ? አንተ ዘመትኩ ለምትለን ዘመቻ ጊዜ፣ ገንዘብ፣ ጉልበት፣ ህይወት፣ ትዳር፣ ቤተሰብ፣ ወጣትነት፣ ኑሮ፣ መከራን ተቀብሎበታል ያ ያዬሕው ጀግና እና መከረኛ። የአንተው ላፒስ ደግሞ እንዲህ ባንኖ ሰርዟቸዋል …. ታሳዝናለህ?! ይህ የአርበኞች መሥራችነት ያልተገባ ክብርም በሚመለከት ግራ ነገር ነው ለእኔ፤ እነ ጀግና አበጀ በለው እኮ ደርግ እያለ በተደራጀ የሽምቅ ውጊያ ጥበብ በቋሚ ሙሉ ኃይል ሲያንቀሳቅሱት ነበር – በባዕታቸው፤ …. በትግራይ ነፃ አውጪ ግንባር የጎንደር መሬት ተከለለ ሲባል ጎንደር ወሰናቸን ማን ደፍሮት ብለው ቀደም ብለው ረቂቅ መስዋዕትነት – አያሌዎች ከፍለውበታል። አረበኞቹ ጎንደር ላይ ከወያኔ ሃርነት ትግራይ /ከታላቋ ትግራይ – ቅዠት/ ጋር በነበረው ዬ18 ቀኑ ጦርነትም ሙሉ ተሳትፎ – ነበራቸው። ያን ጊዜ የመንግሥት ሠራዊት በሙሉ ቀደም ብሎ ወደ ማህል አገር – ስለተሸኘ። ከዛ በኋላ የሀገሬው ተሳትፎ ኮማንድ ፖስቱ ወደ ላይ አርምጭሆ – ተዛወረ። ስለዚህ ስሌቱ በቀደመ መልኩ በተደራጀው ላይ – ተሰለስን ወይንም ተዘለልን፣ ከዛ ደግሞ እንዳሻን ሆንበት  …. ቢባል ያስኬዳል ….
  • የኢትዮጵውያን ሌላው የተመክሮ ማሳ እንደሚያመለክተው በአንድ ወቅት የተነሳን ሃሳብ ያልደገፉ ወገኖች ምን ያህል በጫና ብዛት ድካማቸው፣ ልፋታቸው፣ አቅማቸው ቅስሙ ተሰብሮ በቋሳ ሆነ በቁርሾ አዝማችነት ከጨዋታ ውጭ እንደሚሆኑ – ይታወቃል። አብሶ ሴቶች ተመልሰው ብቅ – አይሉም። ሴቶችን አልባ ምንም ዓላማ ከዕሳቤ ደረጃ – እንደማይደርስም ልምድ ዘለቅ ተመክሮኽ ግልጽ ሆነህ ከቀረብከው ሊነግርኽ እንደሚችል አስባለሁ፤ ለነገሩ አንተና ሴቶች?! እም! – በቀነ ቀጠሮ፤ ከዚህም ሌላም በተፈጥሯቸው ቁጥብ የሆኑ ተብዕቶችም ብቅ ሲሉ ገጀሞ ከጠበቃቸው ሰብሰብ ብለው „የወንድ ልጅ ዕንባው በሆዱ“ እንዳለው የቅኔው ልዑል ብላቴ ጌታ ሎርዬት ጸጋዬ ገ/መድህን ዋጥ አድርገው የሀገራቸው ግፍና መከራ እያቃጠላቸው – እያንገበገባቸው – እዬተርመጠመጡ – ያለፉ፤ የታመሙ – የተገለሉ ሊኖሩ – ይችላሉ፤ በይቅርታህ መንፈስ ውስጥ ቦታቸው የት ላይ ሊሆን እንደሚችል አላውቅም – ምን አልባት ጠፍጥፈኸው ወይ አጣጥፈኸው አልፈኸው ሊሆን ይችላል? ልክ እንደ ታጣፊ አልጋ – አሁንም – ታሳዝናለህ?
  • የአንተን ሃሳብ የደግፉ ግን አንተን በተመክሮ – በልምድ – በዕውቀት በእጥፍ የሚበልጡትንም ቢሆኑ ኢጎህ ምን ያህል ከትክቶ አፈር ድሜ አስግጦ ቀብራቸውን በማወጅ በተጨማሪ አቅም ላይ አንተ ተረማምደህ አንቱታን ስታገኝ፤ ዬዬቤቱ ኮከብ ስትሆን፤ እነሱ ደግሞ እንዲፈልሱ መሆናቸው በማናቸውም ህዝባዊ እንቅስቃሴ ያዬሁት አምክንዮ ነውና በዚህ ዘርፍም ይቅርታህ ድቡልቡል ሆኖ ነው ያገኘሁት ….. ታሳዝናለህ?
  • ሙያህ ጋዜጠኝነት ነው። የሄድከው መረጃዎችን ለታሪክ በሚያመች መልኩ ማቀናበር ብቻ ሳይሆን ዓላማው ከእውነት ጋር ያለውን ተዛምዶ በማብራራት በዓይን ምስክርነትህ ሠራዊቱ የበቃ ደጋፊ እንዲያገኝ የአድቦኬት ተግባር ለመከወን – ይመስለኛል። ነገር ግን ፎቶህን ስመለከተው ህልምህ ሆነ ራዕይህ እንዲሁም ፍላጎትህ ሌላ ጉዳይ ነበር ልበል ይሆን? ህ!  የሥልጣን መንበር አራት ኪሎ ላይ – የከነዳ … እንዲህና እንዲያ ….  ወዲያና ወዲህ … ውዝውዝ —

http://ecadforum.com/2015/07/11/when-the-going-gets-tough-observing-shady-reporting-or-wishes/

ለዚህም ነው ዋናውን የሄድክበት ክቡር ሙያ ገፋ አድርገህ፤ የስደት ሽግግር መንግሥት ኤርትራ ላይ ለመመሥረት እንደ ነበር ከራስህ ከአንደበትህ ከወጣው ቃለ ምልልስ መረዳት ብቻ ሳይሆን፤ ዛሬ በፕሬስ ነፃነት ሥም የስደት ሽግግር መንግሥት ለማቋቋም ከተቻለም በቁልፍነት ለመቀመጥ፤ እንዲህ ሙያዊ ታማኝነት … ክህደት ሲገጥመው በምን ሂሳብ ቢወራረድ ካሳ ይገኝለት ይሆን? አኔ አላውቅም —

ያን ወደህ ፈቅደህ ዬሞት ፍርድ ያሰጠህን፣ በአንፃሩም ዬብዙኃኑ የክብር አክሊል የለገሰህን የጋዜጠኝነት ሙያህን፤ የህዝብ ፍቅር ተንበርክከኽ የዛቅበትን ተወዳጁን ኪዳን የሳተ ተግባር ስትከውን፤ ቢያንስ ያን የክብር ሰንደቅ የሆነውን የጋዜጠኝነት ሙያውን ይቅርታ በመጠዬቅ እረገድም በኩል በንሥኃኽ የውስጥ ለውስጥ መንገድ ወይንም ጓዳ ያዬሁት ብጣቂ ነገር የለም። ወደ ሌላ የፍላጎት አቅጣጫ መሄድ ወይንም ሽግግር ማድረግ ሙሉ መብትህ ቢሆንም፤ በሽፋንነት የተጠቀምክበትን ሙያንም በመቅድምነት ምህረት ልትጠይቀው ይገባል ባይ ነኝ። እንደ ሰው ሊታዘብህ ወይንም ሊሂስህ ባይችልም ግን ዬሥነ ምግብሩ ችሎት ህሊናህ ነውና በርከክ ብለኽ ይቅርታ ልትጠይቀው – ይገባል። ሁለቱንም ይዤ እዬሄዳለሁ ካልክም ጊዜ የሚፈታው ይሆናል። ከዚህ ጋር አያይዤ በትህትና ልጠቁምልህ የምፈልገው ቁምነገር፤ ጋዜጠኛ የመራው የህዝብ እንቅስቃሴ ለግብ በቅቶ አይቼ አለማወቄ – ነው። ጋዜጠኛ በብሄራዊ ሙሴነት ለወንበር መትጋት እንደ ዜጋ መብት ቢሆንም፤ ግን የሙያው ተፈጥሮ ከዚህ መስመር በእጅጉ በጣም የራቀ፤ ሥነ ምግባሩ ባለድንበር መሆኑን ነው እኔ – የምረዳው። በጋዜጠኝነት ህይወት ውስጥም በብራናው ሆነ በብዕሩ እንዲሁም በልሳኑ፤ በተጨማሪም በዛ ቅናዊ የታማኝነት መንፈሱ ውስጥ የወንበር አጀንዳ  የተነነ ስለሆነ፤ በዚህ መስመር ሄደው ለድል የበቁ ካሉ ከአንተ ለመማር – ዝግጁ ነኝ። እንደ አንተ በአጥቢያነት ያዬሁት ስሌለ ለእኔ በግል የተለዬ – ሁኖብኛል። ጥምር ፍላጎት – በዝንቅ መንገድ። ያስኬድ ይሆን? ይህን አንተ – ታውቀዋለህ። የሆነ ሆኖ በስንት ፍዳና መከራ በረጅም የስቃይ ጉዞ የተደራጀውን የአርበኝነት አቅም በመስበር እረገድ …. የትናቱ ላይበቃ፤ ዛሬም በክቡሩ ሙያ ሥር ተመሳሳይ ወለምታ ሲደመጥ እጅግ – ያማል። ፈቅደህ ለሰጠኸው ድካምና መስዋዕትነት – ፈቅደህ ውሉን ፈታኸው …. ሸፈትክበትም። መ – ስ – ዋ – ዕ – ት – ነ – ት – ህ -ም ተሸብሽቦ የምር አለቀሰ = አነባ!

ሴቶችና ዬጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ – ህቅታ፤

ይህን ጹሑፍ ስጽፍ ከልቤ እያዘንኩብህ እንደሆነ ልገልጽልህ – እሻለሁ። የመጀመሪያዋ ሴት የብሄራዊ ፓርቲ መሪ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ዬአንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ሊቀመንበር። https://en.wikipedia.org/wiki/Birtukan_Mideksa

በዘመኑ – ይህ አቅም፤ ይህ ብልህነት፤ ህግን የመተርጎም ቅንነት ሆነ ብቃትን ያሰጋው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ድርጅት ብቻ አልነበረም። በስውርም በግልጽም በነፃነት ትግሉ አካል አባል ቤተኛ ነኝ የሚለው እንደ ነበር – እረዳለሁ፤ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ አንተ ነበርክ። አንድ ጋዜጠኛ በአደባባይ የሴቶችን የእኩልነት አቅም ሲሰብር በመላ ዓለም የጋዜጠኛ ታሪክ አንተ የመጀመሪያው – ትምሰለኛለህ። ኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ዲስከሽን ፎረም /ተቋም/ በነበረህ ቆይታ እሷ በግፍ ለሁለተኛ ጊዜ ታስራ፣ ሃልዬ እያለቀሰች፣ አዛውንት እናት እንግልት ላይ ሆነው የሰጠኸወውን ቃለ ምልልስ – ታሰተውሰዋለህን?! „የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም።“  እ.አ.አ ግንቦት 22 – 2009 ያን ጊዜ ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዳኛ ብረቱካን ይብልጣሉ! ብርቱካን ምን አላት?¡ ቦንብ የላትም! ፕሬዚዳንቱ ግን ቦንብ አላቸው !“ብለህን ነበር – በኩራት። በዕለቱ በነበረህ የከረነት ቆይታ በክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ዙሪያ የቀረበውን ጥያቄ ሁሉ እንዴት ትረገጥው እንደ ነበር፤ እራሱ ዬቶንህ ምቱ በንቀት ታንቡር ቲፍ ብሎ ሞልቶ ነበር – ያዳመጥነው። እሰበው – ከልብህ ሆነህ። ያን ጊዜ በትንታጉ የከረንት ወጣት አድሚን በዱዱዬ መሪነት ሆ! ብለን ተነስተን በጥያቄ ስናጣድፍህ አባጨልክ – ቀለድክ – ተሳለቅክ። ዬቅንጅት መንፈስ ቀጣይነት የታጠቀውን ዬአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ብሄራዊ ፓርቲን አቅመ ቢስ አድርገህ – አቃለልከው፤ ተስፋውንም – ተረማመድክበት፤ ምን ያህል ግዙፍና አስፈሪ አቅም እንደነበረ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዒላማ ሆኖ ይኸው – ፈረሰልህ። ያን ጊዜ በጸጋዬ ድህረ ገጽና በራዲዮ ፕሮግራሙ ሰፊ ሽፋን ተሰጥቶት – ነበር። እርግጥ አንተ ባለ ዙፋን ስለነበርክ፤ ዘለፋህን ከሃቁ ጋር ለማነፃፀር ደረጃውም ወቅቱንም ያልጠበቀ ቢሆንም „የነጠረው ወርቅ የቅዱስ መንፈስ ጥበቃ አይለዬውም“ የሚል አንድ መጣጥፍ ጽፌ ነበር።

እንደ እኔ እርር ያሉ በርካታ ወገኖቼ በአደራሻችን አዎንታዊ አስተያዬታቸውን ሰጥተውን ነበር። ያን ጊዜ የጸጋዬ ድህረ ገጽ እጅግ ተወዳጅና ተፈቃሬ፤ በጽኑ አቋሙ የተከበረ፣ ታታሪ ድህረ ገጽ ስለነበር ታዳሚዎቹ በዕውነቱ ዙሪያ እንደ ከተሙ – እርግጠኛ ነኝ። የትናቷ ሥርጉተ ዛሬም በቆመችበት መሥመር ላይ ዝንፍ ሳትል ዕውነትን ከብክባ ተስፋዋን – ትጠብቃለች።

አዬህ ወንድሜ … ያ አቅም በእንጭጩ አንተንና አንተን የመሰሉ የውስጥ አርበኞች ባይጠቀጥኩት ኖሮ፤ ዛሬ ያለው ሁኔታ መልኩ ቀለማም በሆነ ነበር። ሴቶች የትንግርት እምቤቶች ናቸው። ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ንጹህ መንፈስ የነበራት፤ የጸዳች፤ ወጣቱን – ሴቱን – ትውልዱን ሙሁሩን በአግባቡ በብሄራዊ ደረጃ ልትወክልና በጎ ተጽዕኖ ማሳደር የምትችል የምንም ዓይነት ሥነ ምግባር ብክለት ያልነበረባት፤ ተጨማሪ አማራጭ መንገዳችን – ነበረች። ከሊቅ አስከ ደቂቅ ፍቅርን እንደ ፏፏቴ የሰጣት – በአጭር ጊዜ በምልዕቱ ቅዱስ መንፈስ የታቀፈች ዕንቁ ነበረች። በአጋጣሚው ቀስተደመናን እና አንድነት ፓርቲን ከልብ – አመሰግናለሁ። ዛሬ ተውሎ የሚታደርበት መከረኛው ልዩ መክሊት ትምራኝ ብሎ ፈቅዶ – ነበር፤ ለቅንጅት ምሥረታ ውክልናውንም ደስ ብሎት ነበር በሐሤት – የፈቀደው። ምክንያቱም ሌላው ያለው እሱ ዘንድም እንዳለ ጠንቅቆ – ያውቃልና። እንዲያውም ባብላጫ –

ለእኔ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እንደ ገናናዋ  María Eva “Evita” Duarte Perón ማሪያ ኢቫ ኤቪታ ዱአርቴ ፔሮ ሁሉ የመንፈሷን ብስለትና ብሩኽነት በፍጹም ተስፋ እጠብቀው – ነበር። እንደ ኢቪታ ፔሩ በአማርኛ /ህይዋን ፔሩ/ ገና ከጅምሩ ብርቴም ብርቱ ተደመጭነት ነበራት – ሁሉንም ነበረችና። ኢትዮጵያ ሀገራችን ሥልጡን አዕምሮ፤ የቀደመ ብልህነት ያላቸው ቀንዲል ሴቶችን አላጣችም ነበር። ግን በዬት ታልፎ?! ጋሬጣ – በጋሬጣ —–

ለመሆኑ ኢቫ ፔሩ ማን ናት? በጥቂቱ

ኢቫ የድሃ ሴቶች አናት፣ የስሜን አሜሪካ የሴቶችን እኩልነት በትግሏ በተግባር ያስከበረች የሚሊዮኖች ዘላለማዊ አባባ ናት። ኢቫ ዓለምን – አወሮፓን በፍቅር የገዛች፣ ለጀርመኖች የልብ ደም ሥር በመሆን፤ ለእንግሊዞች የጥበብ እናት በመሆን ከአብነት በላይ አብነት ነበረች። ዬኢቫ ፎቶዋ ቤቴ ውስጥም በክብር አለ። ኢቫ ፔሩ የተወለደችው በሀገረ አርጀንቲና ግንቦት 7 ቀን 1919 በሎስ ቶዶለስ  Los Toldos በሚባል ከተማ ነበር። ኢቫ ከትዳር ውጪ የተወለደች በመሆኑ በወላጅ አባቷ የተገባ ክብካቤ ያላገኘች፤ እናቷም ከጋብቻ ውጪ ስለወለደች በማህበረሰቡ የተገፋች – ነበረች። ኢቫ ከእናቷ ጋር ስታድግ እጅግ በዝቅተኛ ኑሮ ነበር። ኢቫ የልጅነት ጊዜዋን በት/ቤት የቴያትር ክበብ፣ የሥነ ጥበብ ሀሁ ፊደል የቆጠረች ሲሆን፤ በረዳት በደጋፊ እጦት በታዳጊ ወጣትነት ዕድሜዋ ተገዳ ወደ ከተማ – መሄዷ፤ የገባችበት ዬሥራ መስክ የሴቶችን ኑሮ በጥልቀት በጽሞና እንድታይ – አድርጓታል። ህይወቱን ሆና አይታዋለችና። በወጣትነቷ በትናንሽ ሙቢዎች፣ የራዲዮን ድራማዎች ስትሳተፍ ቆይታ በኋላም Radio Belgrano ራዲዮ ቤልግራኖ ሁለገብ ፕሮግራም ጀምራ በዚህ ዙሪያ መስራት እንደ ቀጠለች በአንድ ዬሰብዕዊነት ዝግጅት ከባለቤቷ ከፕሬዚዳንት ፔሩ ጋር – ተዋወቀች፤ ኢቫ አጋጣሚው ረድቷት የአርጀንቲና ቀዳማይ እምቤት – ሆነች። በድርጊት የነፃነት ጥመኛው የቼጎቢራም አምሳያው – ሆነች። ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ በአብዛኛው የሥራ ቀናት እሰከ 20 ሰዓት ትሠራ እንደነበር ዝክረ ታሪኳ  ይናገራል፤

ድንቋ – ዕድሉን አልተኛችበትም ወይንም እንጎልቻ እንዲዘፍነበት – አለደረገችውም። ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ በመጀመሪያው ረድፍ ተግባሯ የሴተኛ አዳሪ ሴቶችን እውቅና – አሰጠች። ድርጅት መሰረተች፤ ሴቶች በማንኛውም መስክ እኩል ድርሻና ክብር እንዲኖራቸው በህገ መንግሥት በአንቀጽ ውስጥ እንዲረቀቅ አስደረገች፤ ነባሩ ህገ መንግሥት እንዲሻሻል – አስቻለች – አጸደቀች። ኢቫ በመጨረሻ ለም/ፕ ተወዳደረች። ሚሊዮኖች ደገፏት። ግን በነበረባት የካንሰር በሽታ ምክንያት በወጣትነቷ – በሥጋ አረፈች። በዕለተ ሞቷ በመላ አርንጀንቲ ትናንሽ ሱቆች ሳይቀር አበባ ማግኘት አይቻልም ነበር። መንገዱ በሙሉ በአበባ እና በዕንባ ዝንብ ራሰ። ሃዘኑ ለመላ ላቲን አሜሪካ መራርና ድንገተኛ ነበር። ግን እንሆ ዛሬ አርጀንቲና ውስጥ ወንዶች ሲወዳደሩ ሚስቱ ማን ናት ይባላል? ገና እኛ አብላጫዎች ያልደረስንበት፣ ያለንካነው ረቂቅ ሥርነቀል የፆታ እኩልነት አብዬት አርጀንቲናዎች በኢቫ ፔሩ አማካኝነት ከዚህ ዘመን ጀምሮ በተግባር እውን አደረጉት። ዛሬ አውሮፓ እንኳን ሲመጡ የአርጀንቲና ሴቶች በራስ የመተማመናቸው ጥንካሬ፤ ዬድፍረታቸው አቅም ፏፏቴ ከተምሳሌይቱ ሁለገብ እናታቸው ከኢቫ – ይቀዳል። እንዲያውም በአውሮፓ የሴቶች እኩልነት ከመንፈስ ጥንካሬ አንፃር ዬአርንጀንቲና ሴቶችን – አያረካቸውም። በአዲሱ የእኩልነት የለውጥ ሂደት ተጠቃሚ የሆኑት አርጀንቲናውያን ብቻም – አይደሉም። ጠቅላላ የላቲን አሜሪካ መንግሥታዊ የሥልጣን ተዋረድ፤ የተቀባይነት አድማስ ቢጠሩት ዛሬ – አይሰማም። በረቂቅ ቅዱስ መንፈስ አጋዥነት ተጨባጭ ለውጥ – አስገኘች። በብዙ የላቲን አሜሪካ ሀገሮች በሀገር መሪነትና በቁልፍ ቦታዎች ሴቶች ከላቀ ደረጃ የደረሱት በኢቫ አብዮት ነው። ኢቫ በትውና – በሙዚቃ – በፖለቲካ መሪነት – በሰብዕዊ መብት ተሟጋችነት – በሚስትነት – በፖለቲካ አማካሪነት – በራዲዮ ጋዜጠኝነት –  በፓርቲ አደራጅነት – በዳናስና በንግግር ጥበብ ሁሉንም የሰጣት የዘመን ኮከብ ነበረች። ቀለማም ምዕራፍ! የቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ አንዱ ነጠላ የትውና ዜማ „don’t cry for me argentina“  የዓለምን ውቅያኖስ ጨምሮ የሚክል መጠነ ሰፊ ተደመጭነትና የዓለም የታሪክ መጽሐፍ መሆን ችሏል፤ ቀዳማይ እመቤት ክብርት ኢቫ ፔሩ የሀገሪቱን ታላቅ ብሄራዊ ሽልማትም – ወስዳለች። /In June of 1952 she was awarded the title “Spiritual Leader of the Nation“ ሞት ቀደማት እንጂ የኖቬል ሽልማቱም ሂደት ላይ ነበር።

ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ  /Democratic Union alliance/ ይህን ፓርቲ በመደገፍ ለትዳሯ ማገር በመሆን የመጀመሪያዋ የአርጀንቲ ቀዳማይ እምቤትነቷን ለቀይ ስጋጃ ምንጣፍ ዕይታ አላወለችውም – ነበር። ትዳሯን በመደገፍ ቀጥተኛ ተዋናይ በመሆን የላቀውን ደረጃ መውሰድ – ችላለች። ትዳሯ በነበረው የምርጫ ውድድር አሸናፊነትም የመሠረት አስኳል – ነበረች። ድንቋ ክብርት ኢቫ ፔሩ ለጡረተኞች፣ ለሴቶች ትርጉም ላለው እኩልነት፣ ለሠራተኞች አብሶ ለድሃ ወገኖቿ መብትና ርትህ እንዲሁም አርነት፤ በተጨማሪም ፋውንዴሽን በመመስረት ብቻ ሳትወሰን፤ ለነጡት የህግ ጥብቃ እንዲኖር በህገመንግሥት ደረጃ የለወጥ ሐዋርያ በመሆን ድርጊት ላይ እንዲውል – አስደርጋለች። በዛ ቀላማም የንግግር ጥበቧ የዓለምን ህዝብ በፍቅር – አስጊጣለች፤ ዕድሜዋ አጭር ቢሆንም የዕድሜዋን ሦስት ዕጥፍ ያህል ዓለምን በአዲስ ዘመን ለመለወጥ አቅምን – ገንብታ፣ አስተምራ – በቋሚ ተግባር – ተቋም /Century/ ሆና አልፋለች፤ ኢቫ በምክትል ፕሬዚደንትነት ስተወዳደር ደጋፊዎቿ ሚሊዮኖች ነበሩ። ነገር ግን በምርጫው ውድድር ዋዜማ ላይ /July 26, 1952 at 8:37 in the evening. She was 33 years old/  አለፈች። ዓለም በእሷ ዙሪያ የምርምርና የጥናት ተግባሩ እንደቀጠለ ሲሆን ጀርመኖች ደግሞ የላቀውን ድርሻ በመውሰድ ይህንን ክብር አጎናጽፈዋታል።

/Evita im Berliner Theater des Westenshttps://de.wikipedia.org/wiki/Evita_(Musical)#/media/File:Berlin_Theater_des_Westens_Sep_2002.jpg/

እናንተ ደግሞ የኢትዮጵያ ሴቶች አቅም ብቅ ሲል በቀንበጡ ቅንጥስ ብሎ ተሰብሮ – በለጋው አፍሮ እንዲቀር – በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ትተጋላችሁ፤ ስለ ቀዳማይ እምቤት ኢቫ ፔሩ ያነሳሁትም በመሠረታዊ በምክንያት ነው። እንደ ሚዲያ ሰውነትህ ልታበረታታ – ልትረዳ – ልታግዝ ሲጋባ፤ ኃላፊነቱን – በእጅጉ ተላለፍከው። ዕድሉን አግኝታ ቢሆን እንዲያ ብጣቂ እራፊ ሳትደርብላት ያጣጣልካትና ያብጠለጠልካት የእኛዋ ዕንቁ ብርቴ ትሆነው ነበር። ይህን የመሰለ ተስፋ ነበር ተቀጭቶ – ተቀብሮ – የቀረው። መቃብሩን ከማሱት ጋር በመንፈስ ሃዲድነት ተገናኝተህ እምሽክ – አደረከው። አንዲት ዘለላ ግድፈት ምን ያህል ተፈጥሮን እንደሚንድ – ተመልከተው። የአዲስ ዘመን ተስፋንም – እንደሚደረምስ፤ እርግጥ ነው የኢትዮጵያ ሴቶች የፈለገ ጠንካራ ቢሆኑ፤ ከጎናቸው ብረት መዝጊያ የሚሆን ሰው ከሌላቸው አቅማቸው አድዬ አበባ ነው፤ ፈንደቅ ብሎ – ክሰም። ብርቴም ከአንተ ጀምሮ እንደዛ እርብርብ ባይደረግባት ኖሮ ////  ኖሮ ወይንም ብረት መዝጊያ አቅም አጋር የትዳርም ይሁን የሥጋም ቢኖራት ኖሮ ዘመነ ጣይቱ ለኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪካ በሆነ – በነበረ።

እና አቶ ወንድም ይህንስ ስለምን ትዘለዋለኽ? የሴቶችን አቅም እንኩት ያደረገው፣ ድቅቅ ያደረገው ትዕቢትህን ለማስተንፈስስ ይቅርታው ምነው በጎሬጥ – አዬው?! ያ ደም የሚተፋ ያመረቀዘው በደል እኮ አይረሳም? እንዲያውም ዒላማህ አቅምን ማደን ነውና – ያገረሻል። ከዛችን ዕለት ጀምሮ እኔ ከድህረ ገጽህ ትውር ብዬ – አላውቅም። አካል ተቆርሶ የትም ተጥሎ እንዴት ዝምድና ይኖረን?  ቀድሞ ነገር ከዚህ መሠረታዊ የእኩልነት መርህ ንድፍ አንፃር አንተኑ ለመተርጎም እንደ ነፃ ጋዜጠኛ ሆነ እንደ ሰብዕዊ መብት ተሟጋችም ለማዬትም እኔን – ይቸግረኛል፤ ስለምን? በፋሽስት እግር ብረት ለነበረች ብሄራዊ ዬፓርቲ መሪ ለትውልዱ የመጀመሪያ ቀንድ ደንዳና አንጀትኽ በክብርህ ላይ ጥቁር ቀን አውጇል እና – ፍቀት። ከዚህም በኋላ ቀልብህ ሌላ ሴት ጀግና ላይ – አረፈ። እኮ – ለምን ፈለግኸው? ሆድህ –  ያውቀዋል። አዬህ ገፈፍከው ክብርህን እራስህ፤ — እናትህን —– እህትህን —– ሚስትህን –  ዘለህ፣ ንቀህ ህይወት የለም፤ ኖሮም አያውቅም፤ ቢኖርም ብቻውን ነው የሚያወጋ  ወይንም የሚዋጋ የገደል ማሚቶ ነው የሚሆነው። ለነገሩ ዛሬ ላይ ሆኜ ሳዬው የሥልጣን ህልመኛ ስለሆንክ፤ ያ የሴቶች ደማቅ – ጉልበታም – ጉልህ አቅም አስፈርቶኽ መሆኑን ትናንት ብቻ ሳይሆን ዛሬ ፏ ፍንትው ብሎ  – ታዬኝ። ዘወርከው አቅጣጫውንም – አስቀዬርከው፤ ስለዚህ የአሁኑ ሽርፍራፊ ይቅርታኽ ለሌላ ተልዕኮ፤ ሌሎችን ደግሞ ቡጢህን ያልቀመሱትን እንደ ቀደመው በጎመራህ አስገብተኽ ለማንደድ ስለሆነ የሚቀበልህ ሊኖር አይገባም ባይ ነኝ። የኢትዮጵያ ሴቶች ሰብዕና ቢያንስ በአቅማችን ላይ ንቀት – ስርዘት ያለውን መንፈስ ሊጸዬፈው ይገባል ባይም ነኝ። „ድምፃችን ይሰማ!“

ወንድሜ – ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ እራስህን – አጥራው፤ ፍላጎትህንም አጽዳው – ባራኪና ካሰኛውም ዘፍዘፍ አድርግና ግድፈቱን አስለቅቀው – የኢጎኽን። ለአንተ ኢጎ ሲባል ዬሚሊዮኖች ክፍለ አካል የሆነው አቅም ሊረገጥ – አይገባም። ሊጠቀጠቅም – አይገባም። አንተ ሴት የመራችህ ዕለት ታንቀህ – ትሞታለኽ። የሚገርመኝ ሳይኖራቸው ሌትና ቀን ዬቡቃያ አቅም አድጎ እንዳይታይ ሲታገሉ የሚታዩ ዱዳ መንፈሶችን – አያለሁ። በዚህ ምክንያትም አካባቢውንም መላጣ አድርገውታል – አንተ ግን ያለኽ – አለኽ – ከበቂ በላይ መሆኑን አለማወቅህ ነው እዬሄድክ ካልሆነ ህልም ከርቸሌ – የምትቀረቀርው። ያንተን ያህል ዬሌላቸው ደግሞ በሥነ ምግባራቸው – ምራቁን በዋጠ የሰከነ ሥርአታቸው፤ በስልጡን ስልታቸው – በቋሚ የዕንባ አጋርነታቸውና በጽናታቸው በልጠውኽ – ይገኛሉ። ከልብህ ሆነህ –  ከህሊናህ ጋር ብትምክር ልትመራቸው ልታስዳድራቸው የምትችላቸው በርካታ ቦዶ ክፍት የሆኑ የሥራ መስኮች – ነበሩልህ። ቀዳዳችን ብዙ ነው። እንዛ ክፍት ቦታዎች ካለህ ብቁ አቅም ጋር ቢገናኙ በእውነት የነፃነት ፍላጎታችን አትራፊ በሆነ ነበር። እኛ ያለን ጥቂት አቅም ነው። እሱን ደግሞ አትፋለመው – ወያኔ ሃርነት ትግራይን ያህል እያመዘመዘ ደም የሚያወረዛ ተቀናቃኝ አስቀምጦ – ያሳዝናል። ምጥና ማጥ። ሌላው ማጥማጃ መሳሪያህም ብቅ ከሚሉ ቀንዲል ሴቶች ዞር – ይበል፤ እንዲሁም  በአርነት ትግል የውስጥ አስተዳደሩን በሚመለከትም በነፃነት የመምራት ኃላፊነት፤ በጣልቃ ገብነት የምትፈጥረው መልክ ጥፉ የመንፈስ ህውከትንም – አስታግሰው። „ድማፃችን ይሰማ!“

የቤት ምርጫ – ብንታ፤

ትክክለኛ ጋዜጠኛ ቤቱን – ያውቃል። ቤቱ የክብሩ ማማ መሆን – አለበት። በዕብነበረድ በተለበጠ ፈንጣጣማ ዓውድ እንዲሁም የብሄራዊ ክብራችን ግርማ ሞገሱ ሥርዓተ ቀበር በሚፈጸምበት ቦታ ዕዝነ ህሊናህ – እንደ ፕሬስ ሰውነትህ  – ይቅደም። በጠላት ወረዳ አንድ የነፃነት ትግል ጋዜጠኛ እንደ ቤቱ ሊዘናከትበት – ወይንም የእኔ ብሎ ሊወላዳበት – አይገባም። መሬቱን አፈሩን ጥርኙን በቀማው ጀሌ ቤት ላይ ሆኖ እሱነቱን ዘርግፎ – ሆድ ዕቃውን – ጨጓራውን ተጫዎቱበት ማለትም – አይገባውም። አቅሙን ለጠላቱ መሸለምም – አይገባውም። ካለቤቱ የተገኘ ጋዜጠኛ ቢያንስ የጠላትን መንፈስ – ዘርፎ፤ የወገንን አቅም መገንባት ሲገባው እራሱም ተዘርፎ በምርኮኛ አባልነት ሲደመር ማዬት የዛገ ብረት ነው ለእኔ – ለሥርጉተ። ጋዜጠኛ የላቀ የመንፈስ ብቃት ረቂቅ – ሥህን ነው። ተመክሮው ሲታከል ደግሞ ሊቅና ዓራት ዓይናማ – ያደርገዋል። የመንፈስ ቅኔ፤ የቃል ጣዝማ በመሆኑ አፍንጫው ረጅም ጆሮው ትልቅ ናቸው። ያዬሁትና የሰማሁት ግን ያጠረ – የተጣበቀ – ብነት የተጠናወተው ጉድ ነው። ቢያንስ ለራስ ሰብዕና እና ታሪክ እንዴት ባዕድ ይሆናል – አንድ ጋዜጠኛ? ? ? ?! ያደፈው ተመሳሳይ መፈለጉን እንዴት ማስተዋል ይሳነዋል አንድ ሥልጡን ጋዜጠኛ?! – ተመክሮው ቢያንስ ለምን እንደተፈለገ በዛ ባዕዳዊ ቦታ መፈልፈል እንዴት – ያቅተዋል አንድ የሚደያ ፍጡር? ሰሞኑን የተከበሩ ዶር ታደሰ ብሩ የአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራር አካል ያደረጉት ቃለ ምልልስ – ነበር። ያ ቃለ ምልልስ ዓይናማ ዳንቴል በውሃ አርሶ እርጥቡን መሬት ላይ ቢጥሉት ትቢያ ተሸክሞ – ይነሳል። ዶር. ታደስ ብሩ ለቃለ ምልልሱ ጥያቄ የሰጡት መልስ የተቆለፈ – ዬጠላትን ጎራ የአውጫጪኝ ትዕይንትን የማረከ ሲሆን – ትቢያ አቅሞ፤ ሃቅን ግን መንበሩ ላይ ያዋለ ጉልላት ነበር ማለት ይቻላል – ለነፃነት ትግላችን። ወሸኔ! የባሻ ዒላማ እንደ አዳመጥከው ድሆ ፍግም ብሎ አፈር ግጦ እንዲቀር – አደረጉት። „ልብ ያለው ሸብ“ ይላል ጎንደሬ …..

ብይን ዬህሊና! ለቅን ወገኖቼ –

  • ቀደም ብዬ እንዳነሳሁት ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ በኢትዮጵያ ከረንት አፊርስ ተቋም በግንቦት 22 ቀን 2009 በሰጠው ቃለ ምልልስ „ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከዳኛ ብረቱካን ይብልጣሉ! ብርቱካን ምን አላት¡ ቦንብ የላትም፤ ፕሬዚዳንቱ ግን ቦንብ አላቸው“
  • የተከበሩ ዶር ሙሉአለም አዳሙ የ2009 ዓለምአቀፍ የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በነበረን የ24 ደቂቃ ቃለ ምልልስ ውስጥ ስለ ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ እንዲህ ነበር ያሉኝ „ … አንዳንዶቹ ወደ ኔልሰን ማንዴላ የሚያስጠጓት አሉ። በእውነት ይህ የሚገባት ጀግና ቆራጥ የፍትህ ሴት ናት። ለሴቶች መኩሪያ ተምሳሌነት ስትሆን ከዚያም አልፎ ብዙዎቻችን ዬብርቱካን ተምሳሌነት የተከተልን፤ inspire ያደረገችን፤ ወደ ትግሉ እንድንሳተፍ የሳበችን ወጣት ናት። ወደፊት ለኢትዮጵያ ብሩኽ ተስፋ ሊያመጡ ይቻላሉ ተብለው ከሚጠቀሱት በጣም ጥቂቶች ውስጥ አንዷ ናት።“
  • ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሜዴቅሳ ከእሥር ከተፈታች በኋላ ያደረገችው የመክፈቻ ንግግር በሀገረ አሜሪካ „እኛ የቅንጅት ለአንድነትና ለዲሞክራሲያ ፓርቲ መሪዎች የሰውን ልጅ ክብር ከምር በመውሰዳችን ይህን ክብር የሚመጠን እና የሚያረጋግጥ የዲሞክራሲያዊ ሥርአት በሀገራችን ላይ ለማዬት በመጓጓታችን፣ ለዚህ ጉጉት መሳካት ከዜጋ የሚጠበቀውን ለመስራት በመቁረጣችና እና ይህን በመተግበራችን …  “

ውድ ለሴቶች ብቃት ክብር ያላችሁ ወገኖቼ ይህን እንግዲህ በተንጣለለው የህሊና ችሎት ሚዛን ላይ አስቀምጡት። …   „የሰውን ልጅ ክብር ከምር በመውሰዳችን ….“ ይህ ኃይለ ቃልን ነው ቀዳማይ እመቤት ኢቫ ፔሩ በምድረ ላቲን አሜሪካ እውን ያደረገቸው።

የተከበራችሁ የሀገሬ ልጆች ክብሮቼ  የሀገሬን ሴቶች፤ ወንዶች ወንድሞቼም – እናቶችን፣ እህቶችን፤ የትዳር አጋራችሁን፤ አክስቶቻችሁን፤ ሴት ጓደኛችሁን ለምታከብሩ ሁሉ ይህን አቅም አንቱ ያለውን ክቡር ዶር. ሙሉአለም አዳሙን ወይንስ ያራካሰውን ጋዜጠኛ ክፍሌ የትኛው ይሆን ለመንፈሳችሁ ቅርቡ?! የትውልድ – ቅርሱስ ማን ይሁን ትላላችሁ? ለሰው ልጅ ተፈጥሮ ለዛውም ዬእናትነትን ጠረን  አስጠግታችሁ  – ዳኙት። ፍርድ ለራስ ነው …. ለዚህም ነው በአንድ ወቅት „ላቂያ“ በሚል እርእስ ውስጤ ለዶር. ሙሉአለም አዳሙ ያለውን ፍጹም የተለዬ አክብሮትና ታማኝት የገለጽኩት። በመንፈሴም አለኝ የምለው  – ጋሻዬም። የክብር – ሰዌም!

ክውና – አቶ ወንድም ጋዜጠኛ ኤልያስ ክፍሌ እንዲህ ሆነልህ – እግዚአብሄርን አመሰገንኩኝ፤ በቤተ ኢትዮጵያዊነት ተቋም የሴቶችን የእኩልነት አቅም እንዲሁም የቅንጅትን መንፈስ ቀጣይነት ያወጀችን ብቁ መሪ ካራከስክበት ዕለት ጀምሮ፤ በቤትህ ትውር አለማለቴ ዛሬ ክብሬ – ሆነልኝ። የፈልግኸውን ዓይነት መልስ ብትጽፍም ይህ የመጨረሻዬ – ይሆናል። ምን አልባት ለዚያ ቢያበቃን በልዕልት ኢትዮጵያ ትምህርተ ሥነ – እኩልነት የህሊና መሰናዶ ት/ቤት ተከፍቶ በተማሪነት ትምህርቱን ወስደህ የተመረቅክ ቀን እንታረቅ – ይሆናል፤ በህይወት – ከቆዬሁ። ማን ያውቃል? ነገ አዲስ ቀለም አዲስ ቀንም ነው። ጊዜ ታሪክን ይሠራል  – ይጽፋልም።  …. በተረፈ በቦሌ ጫካ ተገኝተህ የድሉን ደወል ዬማብሰር ትልመ – ጉዞህን በሚመለከትም መልካም ዕድል እምኝልሃለሁ ከልብ – Good luck! ቧልት እንዳይመስልህ። ድንግል ትጠብቅህ። መኖር ተቋም ነውና የሰው ልጅ ሰብዕና የገበጣ ጨዋታ ባለመሆኑ መማር ትችል ዘንድ ዕድሜውን ጨምሮ ይስጥህ – አባታችን። ደህና – ሁኑልኝ።

የጹሑፌ ምንጭ http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45140#sthash.lDgOQPc2.dpuf

የኔዎቹ መሸቢያ ሰንበት።

  • ማሳሰቢያ ለውዶቼ – ራዲዮ ሎራ ፕሮግራሙ የጸጋዬ ራዲዮን ጨምሮ ወደ 300 ዝግጅቶቹ በሙሉ የበጋ እረፍት ላይ ነው።

አርበኞቻችን መንገዶቻችን ናቸው!

ሴቶች ለነፃት ትግል ፍቱን ናቸው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>