Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

በ15ኛው ዙር ሊዝ ጨረታ በመርካቶ ለቀረቡ ቦታዎች ከፍተኛ ዋጋ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል

$
0
0

–ላፍቶ አካባቢ ለጨረታ የቀረቡ ቦታዎች መሰረዛቸው እያነጋገረ ነው

merkato-addis-ababa-copyረቡዕ ሐምሌ 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በሚከፈተው 15ኛው ሊዝ ጨረታ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ መርካቶ አካባቢ የቀረቡት አራት ቦታዎች ከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ ይቀርብላቸዋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዚሁ ጨረታ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ላፍቶ ሞል ፊት ለፊት የሚገኙ ሁለት ቦታዎች በመጨረሻ ሰዓት መሰረዛቸው እያነጋገረ ነው፡፡

በ11ኛው ሊዝ ጨረታ መርካቶ አካባቢ ቀርቦ ለነበረው 449 ካሬ ሜትር ቦታ በካሬ ሜትር 305 ሺሕ ብር መቅረቡ ይታወሳል፡፡ ለዚህ መሬት በከተማው ታሪክ ክብረ ወሰን የሆነውን የመጫረቻ ዋጋ ያቀረበው ዝዋይ ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ያቀረበው ገንዘብ ከፍተኛ መነጋሪያ ሆኖ ስለነበር፣ ወደ ኋላ በማፈግፈግ በተሰጠው ጊዜ ውል ሳይዋዋል ቀርቷል፡፡

የአዲስ አበባ መሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ይህንን መሬት በ15ኛው ሊዝ ጨረታ አካቶ አቅርቧል፡፡ ከዚህ መሬት በተጨማሪ በዚያው በመርካቶ ከይርጋ ኃይሌ የገበያ ማዕከል ጀርባ 222 ካሬ ሜትር ቦታ ለጨረታ ቀርቧል፡፡ ሰባተኛ አካባቢም 150 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ሁለት ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ እነዚህ ቦታዎች ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሄድባቸው በመሆኑ፣ በርካታ ባለሀብቶች ቦታዎቹን ለመግዛት የጨረታ ሰነድ መግዛታቸው ታውቋል፡፡

እነዚህን ለመግዛት ከፍተኛ የመጫረቻ ዋጋ እንደሚቀርብ ለመሬት ሊዝ ጨረታ ቅርብ የሆኑ ምንጮች እየተናገሩ ነው፡፡ ከእነዚህ ቦታዎች በተጨማሪ ለ15ኛው ሊዝ ጨረታ ከቀረቡት ትኩረት የሳቡ ቦታዎች የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የሚገኙ ቦታዎች ናቸው፡፡

እነዚህ ሁለት ቦታዎች ከላፍቶ ሞል ፊት ለፊት 2,100 ካሬ ሜትር እና 1,800 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ቦታዎች ለጨረታ ቀርበው ነበር፡፡ በጉብኝት ወቅት እነዚህ ቦታዎች እንዳይታዩ ሲደረግ መቆየቱንና የጨረታ መክፈቻ ጊዜ ሲቃረብ ቦታዎቹ እንዲሰረዙ መደረጉ መነጋሪያ ሆኗል፡፡

ቦታው ለንግድና ኢንቨስትመንት ሥራ አመቺ በመሆናቸው የበርካቶችን ትኩረት የሳቡ ሲሆን፣ የከተማው መሬት ባንክ ቦታዎቹ ለሽያጭ መቅረብ ይችላሉ በማለት ለገበያ ቢያቀርብም፣ ግልጽ ባልሆነ ምክንያት ከጨረታ ዝርዝር ውስጥ ተሰርዘዋል፡፡

በ15ኛው ሊዝ ጨረታ በአቃቂ ቃሊቲ 70፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ 44፣ በአዲስ ከተማ አራትና በኮልፌ ቀራኒዮ በርካታ ቦታዎች ለጨረታ ቀርበዋል፡፡ ጨረታው ከሐምሌ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ በአዲስ አበባ ባህልና ቴአትር አዳራሽ ይከፈታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>