Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Sport: ሂጓይን አርሰናል ይመጣል?

$
0
0

በመጨረሻ…፣ በመጨረሻ አርሰናል ከፍተኛ ገንዘብ ሊያወጣ ነው? በመጨረሻም ትልቅ ተጨዋች ሊገዛ ነው? ይህ ያለፉት ሳምንታት ወሬ ነው፡፡ ባለፉት ዓመታት አብዝቶ ፋይናንሳዊ የጥንቃቄ ጉዞ እያደረገ የዋንጫ መደርደሪያውን ባዶ ላስቀረው የክለብ ደጋፊዎች ይህ ትልቅ ዜና ነው፡፡ አርሰን ቬንገር በስልጣናቸው እያሉ ትልልቅ ተጨዋቾች ሲገዙ መመልከት ለክለቡ አፍቃሪዎች ያጓጓል፡፡ የከዋክብት መምጣት በስኬት ማጣት ፊታቸው የጠቆረባቸውን የኢምሬትስ ታዳሚዎች በደስታ ይሞላል፡፡ ሆኖም የትኞቹ ትልልቅ ተጨዋቾች? የሚለው ጥየቄ ብዙ ያነጋግራል፡፡
በእርግጥ ይህ ክረምት በኢምሬትስ ትልቅ ተጨዋች እንዲያመጣ ይጠበቃል፡፡ ይህ ጥያቄ ባለፉት ዓመታት ተመሳሳይ ወቅቶች ሲነሳ ቢቆይም አሁን ወሳኝ ጊዜ ላይ ደርሷል፡፡ የውድድር ዘመኑ ከተጠናቀቀ ወዲህ አርሰናል የዝውውር ገበያው ዜናዎች ማጣፈጫ ሆኗል፡፡ እስካሁን ጠብ ያለ ነገር ባይኖርም የክለቡ ስም ከዌይን ሩኒ፣ ስቴፋን ዩቬቲች፣ ጎንዛሎ ሂጓይን እና ባለፉት ቀናት ደግሞ ከሉዊስ ሱአሬዝ ጋር ተነስቷል፡፡ ከእነዚህ ሁሉ ተጨዋቾች ዝውውሩ እውን ሊሆን የተቃረበ የሚመስለው የሂጓይን ነው፡፡ ክለቡ አርጀንቲናዊውን አጥቂ በማስፈረም የደጋፊዎችን እምነት መልሶ ለማግኘት የቆረጠ ይመስላል፡፡

Photo Credit: Skysports

Photo Credit: Skysports


የሪያል ማድሪዱ ተጨዋች ትልቅ ግዢ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሆኖም ለዚህ ልጅ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ማውጣት ይገባል? የሚለው ጥያቄ ከብዙዎች አዎንታዊ መልስ ቢያገኝም ጥቂቶች ደግሞ ተጨዋቹ ቡድኑን ከሚጠቅመው ይልቅ ክለቡ የደጋፊዎችን ልብ ለመደለል ሊጠቀምበት ሊሆን ይችላል ሲሉ ይጠራጠራሉ፡፡
ሂጓይን ጎል ጨራሽ ነው፡፡ በየውድድሩ ዘመኑ ከ20 በላይ ጎሎች ለማስቆጠርም አይቸገርም፡፡ ሆኖም ይህ ለአርሰናል ዋንጫ ያመጣል? ይህንን የሚጠራጠሩ ብዙ ናቸው፡፡ ምክንያቱም አርሰናል ሻምፒዮን ለመሆን ከጎል አግቢም በላይ ያስፈልገዋል፡፡
የሂጓይን መምጣት በኦሊቪዬ ዢሩ ቀጣይ ሚና ላይ ጥያቄ ያስነሳል፡፡ ፈረንሳዊው ጎል ከማስቆጠር መሰረታዊ ችግሩ በስተቀር የተሟላ አገልግሎት ይሰጣል፡፡ ሂጓይን ሊፈፅማቸው የማይችሉ እና የእንግሊዝ እግርኳስ አጥብቆ የሚጠይቃቸውን ብቃቶችን ይዟል፡፡ ቬንገር ሁለቱን አጥቂዎች በአንድነት ለመጠቀም ፍላጎቱም ሆነ ዕድሉ የሚኖራቸው አይመስልም፡፡ ስሊዘህ ዢሩ ወደ ተጠባባቂ ወንበር ወርዶ ሂጓይን በቋሚነት የፊት መስመሩን ይመራል ማለት ነው፡፡ ይህ ግን ብዙ ጥያቄዎች ያስከትላል፡፡ ዘመናዊው እግርኳስ በተለይም በፕሪሚየር ሊጉ የሚተገበረው አጨዋወት ቴክኒካዊ እና ጎል ጨራሽ ተጨዋቾችን ብቻ የፊት አጥቂነት መጠቀም አያስመርጥም፡፡ በዚህ ረገድ ሲታይ ለአርሰናል ከሂጓይን ይልቅ ሌሎቹ ስማቸው ከክለቡ ጋር የተያያዙ አጥቂዎች ይሻሉታል፡፡
ለሂጓይን ይከፈላል ተብሎ የሚጠበቀው የዝውውር ሂሳብ 25 ሚሊዮን ፓውንድ አካባቢ ነው፡፡ ሆኖም ከአርጀንቲናዊው በተለይ በፕሪሚየር ሊጉ ምርጥነታቸውን ያስመሰከሩት ሩኒ ወይም ሱአሬዝ ከ30-35 ሚሊዮን ፓውንድ ቢበዛ ያስወጣሉ፡፡ እነዚህ ተጨዋቾች ጎል አግቢዎች ብቻ አይደሉም፡፡ ወደ ኋላ እየተመለሱ ኳስን ከመሀል ይዞ መውጣት እና እንደ ፕሌይ ሜከር ሌሎቹን የቡድን ተጨዋቾችን መርዳት እንዲሁም ከማጥቃት በተጨማሪ የመከላከል አጨዋወቱን ማገዝ ያውቁበታል፡፡
ቬንገር ብዙ ጊዜ የወደፊቱ ጊዜ በመመለከት ችሎታቸው ቢታወቁም ለሂጓይን ዝውውር ሊከፍሉ ያሰቡት ዋጋ የወቅቱን የአውሮፓ እግርኳስ ዝንባሌ ችላ ያሉ አስመስሏቸዋል፡፡ ከርናቢዩው ልጅ ይልቅ በአነስተኛ 10 ሚሊዮን ፓውንድ ለገበያ የቀረበውን ካርሎስ ቴቬዝ ዝም ብለው ከማሳለፋቸውም ሌላ ለዝውውሩ 25 ሚሊዮን ፓውንድ ይበቃዋል እየተባለ ያለውን ሮቤርት ሌቫንዶቭስኪ ለመግዛትም ገፍተው አልሄዱም፡፡ ሌላው ቀርቶ የሂጓይን ዝውውር በተለያየ ምክንያት ቢደናቀፍ በሚል በዋጋ ረከስ የሚሉትን ዴቪድ ቪያ ወይም ሚቹን ለማስፈረም ሙከራ አላደረጉም፡፡
እነዚህ ሁሉ ተጨዋቾች ዘመናዊው እግርኳስ የሚፈልጋቸው አይነት አጥቂዎች ናቸው፡፡ ጎሎች ያገባሉ፣ የጎል እድሎች ይፈጥራሉ እና ቀዳዳዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ሂጓይን እና ዢሩ የዘመናዊውን እግርኳስ
ቬንገር ሂጓይንን አስፈርመው የፊት መስመሩ ዋነኛ መሪ ካደረጉት ቡድኑ ትንንሽ ቡድኖችን ሲያገኝ በርከት ያሉ ጎሎች ሊያስቆጥር ይችላል፡፡ ሆኖም ከትልልቆቹ ጋር ሲፋጠጥ በአማራጭ ማጣት ይቸገራል ሲሉ ስጋታቸውን የሚያብራሩ ጥቂት አይደሉም፡፡ ቡድኑ ጎሎች እንዳያገባ ሲከለክል ተስፋ መቁረጥ እና መርበድበድ ይጀምራል፡፡ ይህ በራሱ የአርሰናል ትልቅ ችግር ጎል ያለማስቆጠር ሳይሆን የመከላከል ድክመት እና የአዕምሮ የበላይነት ማነስ መሆኑን ያሳያል፡፡ ባለፉት በርካታ ዓመታት የመድፈኞቹን ክፍተት በሚገባ ላስተዋለ ቬንገር ሁለት ምርጥ አጥቂዎች በ60 ሚሊዮን ፓውንድ ገዝተው ችግሮችን ሁሉ እንደማይፈቱ ግልፅ ነው፡፡
አርሰናል ከ2004ቱ ጠንካራ ቡድን መፈራረስ በኋላ የአሸናፊነት ስነልቦናቸው ከፍ ያለ፣ መሪዎች እና ታጋዮች ይጎድሉታል፡፡ የቶኒ አዳምስ እና ፓትሪክ ቪዬራ አይነት ተጨዋቾች አሁንም የሉትም፡፡ በቴክኒኩ ረገድም ክለቡ አንድ በአንድ ያጣቸውን ሴስክ ፋብሪጋዝ እና ሮቢን ቫን ፔርሲን የመሳሰሉ ከዋክብት አልተሳካም፡፡
ሂጓይን ዋንጫ ያመጣል?
የአጥቂው ዝውውር ብዙ ከመጓተቱ የተነሳ ለአድማጭ አሰልቺ ሆኗል፡፡ በስፔን እግርኳስ እውቀቱ እና በውስጥ አዋቂ ምንጮቹ የሚታወቀው ጋዜጠኛው ሲድ ሎው ሳይቀር ተጨዋቹ ከአርሰናል ጋር የሶስት ዓመት ውል እንደሚፈርም እና በሳምንት 100 ሺ ፓውንድ ደመወዝ እንደሚከፈለው እንዲሁም ባለፈው ሐሙስ አመሻሹ ላይ የህክምና ምርመራውን እንደሚያደርግ ቢናገርም በተግባር አልታየም፡፡ በሳምንቱ መጨረሻ የመጡ መረጃዎች ደግሞ ዝውውሩ የተጓተተው ሪያል ማድሪድ በመጨረሻ ሰዓት የሽያጩን ገንዘብ ከፍ በማድረጉ መሆኑን ያትታል፡፡ የተጫዋቹ ዝውውር አሁንም ከመልሶቹ ይልቅ ጥያቄዎች እንደበረከቱበት አለ፡፡
ሂጓይን ወደ ኢምሬትስ ያመጣዋል የተባለው ከ22-25 ሚሊዮን ፓውንድ ለአርሰናሎች ትልቅ ገንዘብ ነው፡፡ ለማንቸስተር ሲቲ፣ ቼልሲ እና ማንቸስተር ዩናይትድ ግን ብዙ አይደለም፡፡ የአጥቂው ሪከርድ በወረቀት ላይ ሲታይ ግሩም ነው፡፡ ታዲያ ሌሎች ክለቦች እንዲህ በተጓተተው የሂጓይን ዝውውር እጃቸውን ከማስገባት የተቆጠቡት ለምንድነው? ቢያንስ ባለፉት የውድድር ዘመናት አብረውት የሰሩት ጆዜ ሞውሪንሆ ከፈርናንዶ ቶሬስ እርሱ ይሻለኛል ለምን አላሉም?
ሞውሪንሆ ብቻ ሳይሆኑ አሁን የማንቸስተር ሲቲ አሰልጣኝ የሆኑት ማኑዌል ፔሌግሪኒም አርጀንቲናዊውን አሰልጥነውታል፡፡ ታዲያ ለምን ወደ ኢቲሀድ ሊያዘዋውሩት ሳይፈልጉ ቀሩ? በተጫዋቹ ላይ የአርሰናል ብቸኛ ተፎካካሪ የነበረው ጁቬንቱስም ቴቬዝን በአስነተኛ ዋጋ ሲያገኝ ፍላጉቱን አንስቷል፡፡
ሂጓይን ሪያል ማድሪድን ሲለቅ መሆኑን የተነገረው ቀደም ብሎ ቢሆንም ከአርሰናል እና ጁቬንቱስ የበለጠ በትኩረት ወደ ዝውውሩ የገባ ሌላ ክለብ የለም፡፡ በአንፃሩ ሱአሬዝ በአንፊልድ እንደሚቆይ እየተነገረ እያለም ፒኤስጂ፣ ሪያል ማድሪድ እና ማነቸስተር ሲቲ በኋላም አርሰናል እየተረባበረበበት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ለሂጓይን ይህ ሁሉ የለም፡፡
ምናልባት ሌሎቹ ክለቦች ጣልቃ ላለመግባት የተደረጉት አርሰናል ቀደም ብሎ በመርህ ደረጃ ተጫዋቹን ለማስፈረም ስለተስማማ ነው የሚሉ አሉ፡፡ አርሰናል አጥቂውን ድንገት አስፈርመውት ቢሆን ኖሮ በደጋፊዎቹ ዘንድ ሊፈጠር ይችል የነበረው ደስታ ከዚህ በኋላ የሚኖር አይመስልም፡፡ክለቡ በይፋ ዝውውሩ መጠናቀቁን ቢገልፅ እንኳን ከእፎይታ የዘለለ ምላሽ ከደጋፊዎች መጠበቅ የዋህነት ነው፡፡
የክለቡ ደጋፊዎች ለሂጓይን ዝውውር ብቻ ሳይሆን ለስምንት ዓመታት ያለዋንጫ ጉዞም በትዕግስት ሲጠብቁ ኖረዋል፡፡ ሆኖም የክለቡ አስተዳደር የደጋፊዎቹን የትዕግስት ዋጋ በተገቢው መንገድ አልከፈለም፡፡ ይባስ ብሎ እንዲያውም የስታዲየም ቲኬት ዋጋቸው እየጨመረ መጥቶ አሁን በእንግሊዝ የማይደረስበት እጅግ ውዱ ሆኗል፡፡ በደጋፊዎቹ ልብ እየገዘፈ የመጣውን ለመቀነስ ምናልባት ክለቡ የቀረው ብቸኛ አማራጭ ምርጥ ተጨዋቾን በአስፈላጊው ቦታ ሁሉ ገዝቶ በውድ ዋጋም ቢሆን ወደ ስታዲየም መግባታቸውን እንዲወዱት ማድረግ ነው፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን አጋማሽ የተነሳው እና እየተሟሟቀ ሄዶ የነበረው ፀረ ቬንገር ጩኸት ይጀመራል፡፡ ሰውየው የደጋፊውን ልብ ለመመለስ እና የራሳቸውን እየደበዘዘ የመጣ ታሪክ መቀየር ከፈለጉ ዋንጫ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ዋንጫ ለማምጣት ደግሞ ከዋክብት ያስፈልጋሉ፡፡ አሁን ደጋፊዎቹ የሂጓይንን ዝውውር ከጥርጣሬ የሚመለከቱትም ለዚህ ነው፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>