Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

አርበኞች ግንቦት 7 ጥቃት መፈጸም ከጀመረ ወዲህ የወልቃይት ሕዝብ በስርዓቱ አንገዛም ብሎ በአንድነት መነሳቱ ተዘገበ

$
0
0

ESAT
አርበኞች ግንቦት 7 ራድዮ እንደዘገበው የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ስርዓት ክልል 1 እና ክልል ሦስት ብሎ የከፈለው የወልቃይት ህዝብ በስርዓቱ አንገዛም ብሎ በአንድነት ተነስቷል፡፡

የወልቃይት ህዝብ “ክልል 1 እና ክልል 3 የሚባል አናውቅም እኛ የጎንደር በጌ ምድር ተወላጆች ኢትዮጵያዊያን ነን” ሲል በአንድነት “ሆ” ብሎ በመነሳት ከእንግዲህ ወዲህ ህወሓት በዘረጋው የፌደራሊዝም ጭምብል ያጠለቀ የጎሳ አስተዳደር እንደማይመራ እንደ ብረት የጠነከረ አቋሙን በመግለፅ ላይ ነው፡፡

የወልቃይት ህዝብ እስካሁንም ድረስ እትብቱ የተቀበረበት መሬቱ ከሁለት ተሰንጥቆ ከፊሉ ክልል 1 ከፊሉ ደግሞ ክልል 3 ተብሎ በህወሓት ዘረኛ ቡድን መቆረሱንና አንድነቱን ሸርሽሮ ለማዳከም የተቀነባበረውን ስውር ደባ እጆቹን በማጣጠፍ ቆሞ አልተመለከተም ነበር፡፡

ከ1992 ዓ.ም አንስቶ እልህ አስጨራሽ ትግል በማድረግ ከፍተኛ መሰዋዕትነት ሲከፍል ኖሯል፡፡ ዘረኛው የህወሓት ቡድን የወለቃይትን የአንድነትና የነፃነት ጥያቄ ያነሱትን ልጆቹን በየጊዜው በመረሸን ህዝቡንም በጅምላ መጨፍጨፍና ዘር በማጥፋት ጥያቄውን በኃይል አዳፍኖት ሊቀር ብዙ ጥረት አድርጓል፡፡

ነገር ግን ዛሬ ህወሓት በወልቃይት መሬት ላይ ያዳፈነው ረመጥ ውስጥ ለውስጥ ሲቀጣጠል ቆይቶ ሳያስብው ግር ብሎ ነዶ ራሱን እየለበለበው ነው፡፡

በህወሓት የዘር አገዛዝ በእጅጉ የተማረረው የግፍና በደል ገፈትን ሲጎነጭ የኖረው የወልቃይት ህዝብ የህቡና ይፋዊ አስተባባሪ ኮሚቴዎቹን በመምረጥ በሚገባ ተደራጅቶ ህወሓትን በማንኛውም መስክ ሊፋለመው በአንድነት ተነስቷል፡፡
በመሆኑም ከአዲ ረመፅ 3፣ ከጠገዴ 3 እና ከቃፍታ 1 በድምሩ 7 ይፋዊ ኮሚቴዎችን መርጦ “ክልል 1 እና ክልል 3 አላውቅም፤ እኔ የጎንደር በጌምድር ኢትዮጵያዊ ነኝ” በማለት ከእንግዲህ ወዲህ የህወሓትን የጎሳ አስተዳደር ፈፅሞ የማይቀበለው መሆኑን እንዲያስታውቁለት ወደ አዲስ አበባ ልኳል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>