(ዘ-ሐበሻ) አክቲቭስት እና አርቲስት ታማኝ በየነ የኢሳት ራድዮና ቴሌቭዥን የቦርድ ሊቀመንበር መሆኑን የዘ-ሐበሻ ምንጮች ገለጹ::
ታማኝ በየነ የኢሳት ቦርድ ሊቀመንበርነቱን ቦታ የተረከበው ከነአምን ዘለቀ እንደሆነ የገለጹት እነዚሁ የዘ-ሐበሻ ምንጮች ከጁላይ መጀመሪያ ጀምሮም በቦታው እየሰራ እንደሚገኝ ታውቋል::
ከደቡብ አፍሪካ እስከ አውስትራሊያ ከአውሮፓ እስከ አሜሪካ በተለያዩ ከተሞች በመዘዋወር ለኢሳት ገቢ ማሰባሰብ ከፍተኛውን ሚና እየተጫወተ የሚገኘው ታማኝ የኢሳት ቦርድ ሊቀመንበር ከሆነ በኋላ ቴሌቭዥኑ በዚህ ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ የሚያሰራጨውን የ24 ፕሮግራም መጀመሩን መግለጹ ይታወሳል::