ዕዉቁ ዲፕሎማት፣ የፕሮቶኮል ሹም፣ የህዝብ ግንኙነትና የማስታወቂያ ሹም፣ እንዲሁም የሠራዊቱ የኢንፎርሜሽን መኮንን የነበሩት አምባሳደር ሻለቃ ፍሰሐ ገዳ በተወለዱ በ76 ዓመታቸው አረፉ፡፡ በሰሜን ኮሪያ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣ የኢትዮጵያ ሆቴሎችና ቱሪዝም ኮሚሽነር፣ የርዕሰ ብሔሩ የፕሮቶኮል ዋና ሹም፣ የ3ኛ ሻለቃ ክፍለ ጦር ባልደረባና የሆለታ ጦር አካዳሚ ምሩቅ የነበሩት፣ ተወዳጁ መኮንን፣ አምባሰደር ፍሰሐ ገዳ ያረፉት ጁላይ 15 2015 በቨርጂኒያው መኖሪያ ቤታቸው ነው። የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ሰኞ ጁላይ 20/2015፣ በቨርጂኒያ 9902 Braddock Rd. Fairfax VA 22032, በሚገኘው Braddock Funeral Home and Cemetery ከጧቱ 9፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚፈጸም ከቤተሰቡ የተገኘው ኢንፎርሜሽን ያስታውቃል።
↧