Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የኢትዮጵያ መንግስት ኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ኢላማ ሊሆኑ ከሚችሉ አገራት መካከል ባለመመደቧ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ ገባ!

$
0
0

ድምጻችን ይሰማ
muslim1

 

መንግስት በመጪው አርብ በኢትዮጵያ የሽብርተኞች ጥቃት ሊፈጸም ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ አድርጉ ሲል ለበርካታ ኤምባሲዎችና ቆንስላዎች የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልክት (ኬብል) ላከ!
የዩናይትድ ሰቴትስ መንግስት በመላው ዓለም የሚገኙ 22 ኤምባሲዎቹና የቆንስላ ጽ/ቤቶቹ የድንገተኛ ሽብር ጥቃት ሊፈጸምባቸው ይችላል በሚል ባወጣው የቅድመ ማስጠንቀቂያ መረጃ ኢትዮጵያ ባለመካከተቷ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባቱ ታወቀ፡፡ ዩናይትድ ስቴትስ በስለላ መረጃዎች ተመርኩዛ በተለያዩ አገራት በሚገኙ ጥቅሞቿ ላይ በአሸባሪዎች ሊፈጸም ይችላል በሚል ባወጣችው መረጃ 22 አገራት የሚገኙ የአሜሪካ ጥቅሞች ቦታ የተጠቀሰ ሲሆን፤ በእነዚህ ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ መሰል የሽብር ጥቃት ሊፈጸም እንደሚችል የሚያሳይ መረጃ ባለመገኘቱ ኢትዮጵያ ሳትካተት ቀርታለች፤ በዚህም መንግስት ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ መግባቱ ተረጋግጧል፡፡
ይህ ያልተሰበ ጥቃት ሊፈጸምባቸው ነው ተብሎ ዝርዝር ውስጥ የተካተቱ አገራት ውስጥ ያሉ የዩናይትድ ስቴትስ ጥቅሞች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ለማድረግ ሲባል እስከ መጪው ቅዳሜ ነሀሴ 4 ድረስ ዝግ እንደሚሆኑ ተነግሯል፡፡ በዚህም መሰረት የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት በአራት አፍሪካ አገራት ማለትም በማዳጋስካር፣ በብሩንዲ፣ በርዋንዳና በሞሪሺየስ የሚገኙ ኤምባሲዎች እንደሚዘጉ ገልጿል፡፡ የአንዳንዶቹ ኤምባሲዎች እና ቆንስላዎች መዘጋት እስከ ፈረንጆቹ ኦገስት ወር መጨረሻ ድረስ ሊዘልቅ እንደሚችልም መስሪያ ቤቱ አስታውቋል፡፡ ሆኖም ይህ የሽብር ስጋት አለባቸው በተባሉ አገራት ውስጥ ኢትዮጵያ መካተት አለመቻሏ በኢትዮጵያ መንግስት በኩል በበጎ ካለመታየት አልፎ ከፍተኛ ቅራኔ እና ብስጭት እንደፈጠረ የዲፕሎማቲክ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ለዚህም ምላሽ ይሆን ዘንድ የኢትዮጵያ መንግስት ትናንት በውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በኩል ያልታሰበ የሽብር የጥቃት አደጋ ሊከሰት ይችላል በሚል በአዲስ አበባ ለሚገኙና ከ30 በላይ ለሚሆኑ አገራት ማስጠንቀቂያ (ኬብል) መስጠቱ ታውቋል፡፡ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመጪው አርብ ሊፈጸም ይችላል ባለው የሽብር አደጋ አገራት የራሳቸውን የቅድመ ማስጠንቀቂያ እርምጃ እንዲወስዱ አሳስቧል፡፡ በዚህም መረጃ መሰረት መንግስት የራሱን የተቀነባበረ የሽብር ተግባር በመፈጸም ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን ለጥቃቱ ተጠያቂ ለማድረግ እቅዳ እንዳለው ታውቋል፡፡ መንግስት ለሁለት አመታት የዘለቀውና ምንም አይነት የኋይል እንቅስቃሰሴ ያልታየበትን፤ ለዚህም አለም አቀፍ ተቋማት ምስክርነት የሰጡትን የኢትዮጵያ ሙስሊሞች የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ ለመቀልበስ የተለያዩ የሽብር ውንጀላዎችን ሲሰነዝር የቆየ ቢሆንም ምንም አይነት ተቀባይነት ከአገር ውስጥም ሆነ ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ሳያገኝ ቆይቷል፡፡
መንግስት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የምናደርገውን የመብት ማስከበር እንቅስቃሴ ከሽበርተኝነት ጋር የተቆራኘ ነው የሚለውን ውንጀላውን ለተለያዩ አገራት ለማሳመን ከፍተኛ ወጪ በማውጣት የሎቢ (ጉትጎታ) ስራ ሲሰራ የቆየ ቢሆንም ምንም አይነት ተአማኒነት ለማግኘት ካለመቻሉም በላይ የአሜሪካ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽንን የመሳሰሉ ተቋማት ሙስሊም ኢትዮጵያውያን የሚያደርጉት የተቃውሞ እንቅስቃሴ ፍጹም ሰላማዊ መሆኑን በተደጋጋሚ በሪፓርታቸው መስክረዋል፡፡ በአሜሪካ ፕሬዚዳንት ግላዊ ሹመት በሚመረጡ ግለሰቦች የሚመራው የአሜሪካ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት ኮሚሽን ከወር በፊት ባወጣው ሪፖርቱ ይህን እውነታ ከማስታወሱም በላይ የኢትዮጵያ መንግስት የሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የሃይማኖት ነጻነት እየነፈገ መሆኑን መግለጹ የሚታወስ ነው፡፡
መንግስት ይህ ተአማኒነት ያጣውን ውንጀላውን በተግባር ፈጽሞ ስጋትን ለማሳየት በታቀደው የሽብር ጥቃት የትኛው ተቋም ወይም ድርጅት ኢላማ ሊሆን እንደሚችል በውል አልታወቀም፡፡ አንደመላምቶች ገለጻ ኤምባሲዎች፣ የትራንስፖርት ሰጪ አገልግሎቶች፣ የመንግስት ተቋማት ኢላማ ሊሆኑ እንደሚችሉ የተገመተ ሲሆን በቤተክርስቲያኖችና በመስጂዶች ላይም መንግስት ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችልም ታምኗል፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት ሰላማዊ የመብት ጥያቄዎችን የጠየቁ ሙስሊም ዜጎችን በሽብር ስራ በመወንጀል እስከ አሁን በተለያዩ ወቅቶች የሰሞኑን የአርሲ ኮፈሌ ጨምሮ 30 ንጹሀን ዜጎች በመንግስት ታጣቂዎች ጥይት ተገድለዋል፡፡ በተቃራኒው ሙስሊሞች ጁምአን ቀን በመጠበቅ መንግስት ሕገ መንግስታዊ የመብት ጥያቄውን እንዲመለስ በሰላማዊ መንገድ ከመጠየቅ በዘለለ ምንም አይንት የኃይል ዝንባሌ ታይቶብን አይታወቅም፡፡
መንግስት አሁን ባሰበው ሴራ መሰረት ንጹህንን በተቀነባበረ የሽበር ድርጊት በመግደልና ደማቸውን በማፍሰስ የራሱን ፖለቲካ ጥቅም እና ሽብርን ለመከላከል በሚል ከውጪ አገራት የገንዘብ ድጋፍ ለመሰብሰብ አቅዷል፡፡ መንግስት ከዚህ ቀድም መሰል የሽብር ድርጊቶችን ራሱ በመፈጸም አሻባሪ ያላቸው ድርጅቶች ላይ ሲያሳብና ውንጀላ ሲሰነዝር እንደነበር ከአሜሪካ መንግስት ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት አፈትልከው ወጥተው የነበሩ የዊኪሊክስ መረጃዎች ለአለም ማጋለጣቸው ይታወቃል፡፡ መንግስት ከዚህ ቀደም በመጓጓዣ መኪናዎች ላይ ሆቴሎች እና መሰል ተቋማት ላይ ነበር ጥቃቶችን የሰነዘረው፡፡ መንግስት የምናደርገው ሰላማዊ ትግል በሰላማዊ መርህ ብቻ የሚመራ መሆኑን አሁንም ለመቀበል ባይፈቅድም ሰላማዊ ትግላችን በአገራችን እንደዜጋ መታየት እስክንጀምርና ሕገ መንግስታዊ መብታችን እስከሚከበር ድረስ ይቀጥላል፡፡

አላሁ አክበር!


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>