Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

የዳና ዳራማዋ ተዋናይት በእስራት ተቀጣች

$
0
0

bezawit mesfin
በተለያዩ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ድራማዎች ላይ በመተወን የምትታወቀው ተዋናይት ቤዛዊት መስፍን እና ግብረ አበሯ በእስራት መቀጣታቸውን አፍቃሬ ሕወሓት የሆነው ራድዮ ፋና ዘገበ::

በአዲስ አበባ ከተማ በኮልፌ ቀራንዮ ነዋሪ የሆኑት ተከሳሾቹ በእስራት የተቀጡት ከታዘዘላቸው ውጭ ተጨማሪ ገንዘብ ከባንክ ቤት በማውጣት ለግል ጥቅማቸው በማዋላቸው ነው።

የ22 አመቷ ተዋናይት ከግብረ አበሯ ጋር በመሆን በተሰጣቸው የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት ለፊቱ ሁለት ቁጥርን በመጨመር ያልተፈቀደላቸውን 24 ሺህ ብር ከወጋገን ባንክ ሰባራ ባቡር ቅርንጫፍ አውጥተዋል።

ተከሳሾቹ ለአቶ ዮናታን ባልቻ መኪና በማከራየት የኪራይ ስምምነት ውል ያላቸው ሲሆን፥ በውላቸው መሰረትም ሚያዚያ 8 ቀን 2005 ዓ.ም ከምሽቱ 2 ሰአት አካባቢ የ4 ሺህ ብር ቼክ ተቀብለዋል።

ግለሰቦቹ ሚያዚያ 12 ቀን 2005 ዓ.ም ላይም ከመኪና ተከራዩ አቶ ዮናታን በተቀበሉት የ4 ሺህ ብር ቼክ ላይ ከፊት ለፊቱ 2 ቁጥርን በመጨመር ተጨማሪ 20 ሺህ ብር ከባንክ ቤቱ አውጥተዋል።

በዚህም መሰረት የፌደራሉ አቃቤ ህግ ተከሳሾቹ የማይገባቸውን ብልጽግና ለማግኘት በማሰብ በፈፀሙት ወንጀል ክስ በመመስረት የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን አቅርቧል።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎትም ተከሳሾቹ የወንጀል ድርጊቱን ማስተባበል ባለመቻላቸው ጥፋተኛ ብሏቸዋል ።

ተከሳሾቹ ወንጀሉን በስምምነት በማበር የፈፀሙት በመሆኑ ቅጣቱ ከፍ ብሎ እንዲወሰን አቃቤ ህግ የቅጣት ማክበጃ አቅርቧል።

ፍርድ ቤቱም የግራ ቀኙን ክርክር ካዳመጠ በኋላ ተከሳሾቹ ያላቸውን የቅጣት ማቅለያ እንዲያቀርቡ ጠይቋል።

በዚህም 1ኛ ተከሳሽ ቤዛዊት መስፍን የዕድሜዋን ወጣትነት፣ ከዚህ ቀደም በምንም አይነት የወንጀል ድርጊት አለመሳተፏንና የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆኗን በቅጣት ማቅለያነት አቅርባለች።

2ኛ ተከሳሽ አቶ ነቢል ይማም ምንም አይነት የቅጣት ማቅለያዎችን አላቀረበም።

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 5ኛ የወንጀል ችሎትም 1ኛ ተከሳሽን በ6 ወር ቀላል እስራትና በ1 ሺህ 500 ብር እንዲሁም 2ኛ ተከሳሽን በ1 አመት ከ6 ወር እስራት እና በ3 ሺህ ብር እንዲቀጡ ወስኗል።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>