(ዘ-ሐበሻ) አርበኞች ግንቦት 7 በሰሜኑ የኢትዮጵያ ግዛት በሕወሓት አገዛዝ ወታደሮች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የሕወሓት መንግስት ደህንነቶች በጎንደር የለውጥ አረአያና አንቀሳቃሽ ይሆናሉ ብለው ያሰቧቸውን ሰዎች እያፈኑ ወዳልታወቀ ስፍራ እየወሰዱ እንደሚገኙ ለዘ-ሐበሻ የመጡ መረጃዎች ጠቆሙ::
በአሁኑ ወቅት በከፍተኛ ፍራቻ ውስጥ የሚገኘው የሕወሓት አስተዳደር በተለይም በጎንደር ከተማ እንዲህ ያለውን የአፈና እርምጃ መውሰድ የጀመረው “አማራው ልቡ ከኛ ከራቀ ቆይቷል; አሁንም ግንቦት 7 እና አርበኞች ግምባርን ደብቆ ያስወርረናል” በሚል ፍራቻ እንደሆነ የደረሰን መረጃ አመልክቷል::
የዘ-ሐበሻ የጎንደር ዘጋቢዎች እንደሚሉት የሕወሓት አስተዳደር በአማራው ላይ ያለው እምነት ከመሟጠጡ የተነሳ አማራውን እስከመናቅና እስከማሸማቀቅ ደርሷል:: በአሁኑ ወቅት በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል የተነሳውን ጦርነት ተከትሎ እነዚህ የጎንደር ነዋሪዎች እየታፈኑ የት እንደደረሱ አለመታወቅ በከተማው መነጋገሪያ ሆኗል::