Quantcast
Channel: Ethiopian News | ዘ-ሐበሻ | Latest News Provider | News For All
Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

“እኔ አንድ ነኝ ። ምን ልዩነት አመጣለሁ ?”አንበል –የሚሊዮኖች ድምጽ

$
0
0

11703157_853116228106646_6848258730754773891_nየታሰሩትን ማሰብ፣ ለታሰሩት መቆም ፖለቲካ ብቻ ሳይሆን ሰብዓዊነት ነው። ዜጎች በዉሸት ሲታሰሩ፣ ፍትህ አጥተው ሲጉላሉ፣ ሐሳባቸውን በነጻነት በመናገራቸው ብቻ ወንጀለኛ ወይንም ሽብርተኛ ተብለው ስታሰሩ፣ በእስር ቤት ራቁታቸውን ሆነው ሲደበደቡ፣ ወንዶች ብልታቸው ሲቀጠቀጥ ፣ ሴቶች በወንድ መርማሪዎቻቸው ፊት ጅምናስቲክ እንዲሰሩ ተደረጎ ክብራቸዉን የሚነካ ነገር ሲፈጸምባቸው፣ በፍርድ ቤት ፍትህ ማግኘት ሳይቻል ሲቀር፣ ዳኞች ከደህንነቶች “ይሄን ፍረዱ፣ ይሄን በይኑ” ተብሎ በሚሰጣቸው መመሪያ መሰረት ብይን ሲሰጡ ፣ ዝም ማለት ሐጢያት ነው ። ነዉር ነው። ለአገርና ለሕዝብ የቆሙ እስረኞች ዋጋ ሲከፍሉ፣ ለነርሱ አጋርነት አለማሳየት ርስ ወዳድነትና ደካማነት ነው።

ክፋት የሚስፋፋው ጥሩ ሰዎች ዝም ሲሉ ነው። ግፍ ሲፈጸም “ይሄ ለምን ይሆናል ? ” የሚል ድምጽ ሲበዛ ግፈኞች ግፍ ለመፈጸም ይፈሩ ነበር። ዛሬ አንድ ሲገድሉ፣ አንድ ሲያስሩ ዝም ከተባሉ። ነገ አስር ያስራሉ። ቀስ በቀስ፣ የኛ ዝምታ ፣ ክፋታቸውን እንዲፈጸ ሙ ለነርሱ ባዶ ቼክ እንደመስጠት ይሆናል። የኛ ፍርሃትና ዝምታለግፈኞች ምግብ ይሆናቸዋል። ከዚያም ለክፋታቸውን ለጭካኔያቸው ማቆሚያ አይኖራቸውም።

በመሆኑም በአገር ዉስጥና ከአገር ዉጭ የምንኖር ክፋትን፣ በደልን፣ ግፍን የምንጠላ ኢትዮጵያዊያን፣ አሁን ድምጻችንን ማሰማት አለብን፡፡ ክፉዎች ሊቆሙ የሚችሉት ጥሩዎች ሲነሱ ብቻ ነው።

የሕወሃት መንግስት በክፋትና በጭካኔ የሚታወቅ ነው። ለማዘናጊያና ለኦባማ ስጦታ እንዲሆን ስድስት እስረኞችን በመፍታት ሩህሩህ መሆኑ ለማሳየት በከንቱ ቢሞክርም፣ ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆኑት አሁንም እንደታሰሩ ናቸው። ተፈቱ የተባሉት ከተፈቱ በኋላም በማግስቱ እጅግ ብዙዎች ታፍነው ታስረዋል።

እንግዲህ ለታሰሩ አፍ ሆነን ድምጻችንን እናሰማለን። ሁሉም እስረኞች ይፈቱ የሚል የ 21 ቀን ዘመቻ ሰኞ ሐምሌ 6 ቀን ይጀመራል። የዚህ ዘመቻ አካል እንሁን። መልእክቱን እናሰራጭ። ላይክ ሼር እናደርግ። “እኔ አንድ ነኝ ። ምን ልዩነት አመጣለሁ ?” አንበል። አንድ ተብሎ ነው መቶ፣ ሺህ ፣ ሚሊዮኖች የሚደረሰው። ግድ የለም። የድርሻችንን እንወጣ። የዘመቻው አካል እንሁን።


Viewing all articles
Browse latest Browse all 15006

Trending Articles