“የኢትዮጵያ ህግ ልዕልና ከአሜሪካ ፕሬዘዳንት ክብር በላይ ሊሆን ይገባዋል”
– በስደት ከሚገኙ የኢትዮጵያ ነጻ-ፕሬስ ጋዜጠኞች የተሰጠ መግለጫ
የኢትዮጵያ ነጻ ፕሬስ ጋዜጠኞችን “አሸባሪዎች” ብሎ በማሰር እና ከአገር እንዲሰደዱ በማድረግ የኢህአዴግ መንግስት ያላቋረጠ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን ሲፈጽም ቆይቷል። ይህን የሰብአዊ መብት መተላለፍ በመቃወም፤ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ድምጽ ለሌላቸው ድምጽ በመሆን ወገናቸን ታድገዋል። ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው ብቻ፤ “አሸባሪ” ተብለው በእስር ሲማቅቁ ከነበሩት ጋዜጠኞች እና ጦማርያን መካከል ተስፋለም ወልደየስ፣ ዘላለም ክብረት፣ አስማማው ሀ/ጊዮርጊስ፣ ርዕዮት አለሙ፣ ማህሌት ፋንታሁን እና ኤዶም ካሳዬ ተፈትተዋል።